DW
የዓለም ዜና
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
Glöm inte att besöka poddens webbplats och stötta skaparen: www.dw.com
Var kan du lyssna?
Poddar i appen Replaio Radio Kommer snartPoddar kommer snart till appen. Installera nu och bli först med att uppleva ett helt nytt sätt att lyssna på poddar
Avsnitt
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 14.09.2026 11:55
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ታጣቂዎቸ አደረሱት በተባለው ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ፤ 4 ደግሞ ቆሰሉ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥቢያ በሱዳኑ የብሉ ናይል ግዛት በአል-ዳማዚን ከተማ የድሮን ጥቃት ፈፀመ ። የሁቲ አማጽያን ዛሬ የሀኒሽ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ ።
የመስከረም 03 ቀን 2019 የዓለም ዜና 13.09.2026 8:31
በየመን በሑቲዎችና የመንግሥት ኃይሎች ውጊያ 86,000 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,000 በላይ ጅቡቲ ገቡ። “በዓለም ዙሪያ የግጭቶችና ውጥረቶች ቁጥር እየጨመረ” በመሔዱ በሕዝቦች ሕይወት ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስጠነቀቁ። ሩሲያ ከዋርሶ ወደ ኪየቭ በተዘረጋ ባቡር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ፖላንድ አስታወቀች።
የመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 12.09.2026 11:48
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች። ለብሪክስ ጉባኤ ሕንድ ኒውደልሂ ከተማ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢራን ፕረዚደንትን ጨምሮ ከተለያዩ ሐገራት መሪዎች መወያየታቸውን ገለፁ።ኢራቅ ከኢራን ጋር የሚያዋሱኗት ሦስት ድንበሮች ዛሬ መዝጋቷን አስታወቀች።
የመስከረም አንድ ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 11.09.2026 10:50
በአሜሪካን በኒውዮርክ፣ በፔንታገንና በፔንሲልቬንያ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት 25 ተኛ ዓመት ዛሬ በአሜሪካን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየታሰበ ነው። ነገ ህንድ ውስጥ በሚጀመረው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራት መሪዎች ኒውዴልሂ እየገቡ ነው። የሁቲ አማጻያን ዛሬ ስልታዊ የሚባለውን ፔሪም ደሴትንና የዱባብ ከተማንም ይዘዋል
የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 10.09.2026 10:35
አ.አ፥ ከ600 እስረኞች በላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ዐሳወቀ፤ ጊምቢ፥ አልጄሪያ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋረጠች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን በቀይ ባሕር ቁልፍ የወደብ ከተማን ተቆጣጠሩ፤ ዋሽንግቶን፥ ዶናልድ ትራምፕ ፓርቲያቸው በአማካይ ዘመን ምርጫ ካሸነፈ ለእያንዳንዱ አዋቂ 5ሺህ ዶላር ሊሰጡ ቃል ገቡ
የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና 09.09.2026 12:19
-- የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸዉ የኢሕአፓ መሪዎችና ጠበቃ በዋስ እንዲፈቱ የተላለፈላቸዉ ዉሳኔ ታገደ።-ብሪታንያ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኝ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን እንድትዘጋ እስራኤል ማሳሰቧን ብሪታንያ የሚጠበቅ፣ግን አሳዛኝና ግንኙነትን የሚያበላሽ በማለት ነቀፈችዉ።-የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።
የዓለም ዜና፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 08.09.2026 12:28
አርስተ ዜና፤ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች ሞቱ። -በትግራይ ክልል የሚገኙ አማፅያን የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ሌላ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል አሉ።-በሌላ በኩል በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የወጣቶችና የታዳጊ ልጆች አፈሳ ይቁም ሲሉ በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ እናቶች ለተቃዉሞ ወጡ።
የጳጉሜ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና 07.09.2026 11:03
የትግራይ ክልል ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ገለልተኛ አይደሉም” በማለት ወነጀለ። በኢትዮጵያ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጥሪ አቀረቡ። መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ያስመዘገው የምርጫ ድል ፓርቲያቸውን ከመሠረቱ እንደነቀነቀ ተናገሩ
የጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 06.09.2026 8:03
በየመን መንግስት ኃይሎችና «በኢራን ይደገፋሉ» የሚባሉት የሑቲ ደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ትላንት አገርሽቶ እስከ ዛሬ በተካሄደ ውግያ ከሁለቱም ወገን ከ140 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ተሰማ። በምሥራቅ ጀርመን በምትገኘው የዛክሰን አንሃልት ግዛት የአካባቢ ምርጫ እየተካሄደ ነው።
የነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 05.09.2026 11:13
• በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ምስራቅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 20 ሰዎች ተገደሉ ። አስራ ስድስቱ የመንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ናቸው ። • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።
የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 04.09.2026 11:48
በኢትዮጵያ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም ወደ 38,000 ኮምፒውተሮች እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።
የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 03.09.2026 10:57
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሾመው የሱዳን ጉዳይ የምርመራ ቡድን፤ የውጭ ሐገራት ታጣቂዎች በሐገሪቱ ያለውን ግጭት እያባባሱት ነው ሲል ከሰሰ። የእስራኤል ጦር አባላት በምዕራባዊ ዮርዳኖስ የባሕር ዳርቻ 2 ፍልስጤማውያን ወጣቶችን ተኩሰው መግደላቸውን
የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና 02.09.2026 12:00
-የጀርመንና የሩሲያ ተዘዋዋሪ ግጭት ወደ ቀጥታ ዉዝግብ፣ የጥቃት ሙከራ፣ ቅጣትና የአፀፋ ቅጣት ዛቻ ንሯል።---የቻይና መሪ ሺ ጂፒንግ የዉጪ መንግሥታት በመካከለኛዉ ምሥራቅ የዉስጥ ጉዳይ ጠልቃ እንዲገቡ የአካባቢዉ መንግሥታት መፍቀድ የለባቸዉም አሉ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን አንዳቸዉ የሌላቸዉን ተቋማትና ጥቅሞች መደብደባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።
የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.09.2026 11:37
አርዕስተ ዜና የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማቸውን ማቋረጣቸው ተገለፀ ። የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ ። የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ ለያዘችው አቋም ፑቲንን አመሰገኑ። ፑቲንም ፔሽኬቭያንን ለተጋድሎአቸው አወደሱ
DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 የዓለም ዜና 31.08.2026 11:22
በአንድ ሣምንት 2,463 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት ከ6,000 በላይ ሰዎች በኢቦላ መያዛቸውን አረጋገጠ። በሱዳን የታቀደው ብሔራዊ ውይይት “የመጨረሻ ግብ በሕጋዊ ሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር” ያላት “የተባበረች፣ ሉዓላዊ እና ሰላማዊ” አገር መፍጠር ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መከረ። ሕንድ ከፓኪስታን ጋር የተፈራረመችውን የውኃ መጋራት ሥምምነት እንድታከብር በፍርድ ቤት የተላለፈባትን ውሳኔ ውድቅ አደረገች። የአሜሪካና ኢራን ጦርነት ዳግም ሲያገረሽ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።
የነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 30.08.2026 8:33
የዛምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሐገር ክህደት ወንጀል እንደተከሰሱ የሐገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በወታደሮች ተቀስቅሶ የነበረው ዓመጽ በኒጀር መንግስት ታማኝ ወታደሮችና በሐገሪቱ ያሉ የሩስያ የአፍሪካ ጓድ ጦር አባላት ድጋፍ መክሸፉን ተከትሎ ከተማዋ በዛሬው ዕለት አንጻራዊ ሰላም ማግኘቷን ተነገረ። እስራኤል በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 2 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። ቱርክ፣ ሳውዲ ዓረቢያና ፓኪስታን በጋራ የመከላከያ ስምምነት ላይ ለመምከር ነገ በኢስታምቡል እንደሚገናኙ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የነሐሴ 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና 29.08.2026 10:50
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ” ያላቸውን 32 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታወቀ። ሩሲያ ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 37 ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። ኔፓልና ቲቤት በሚዋሰኑበት ተራራማ አካባቢ በደረሰው የደራሽ ጎርፍ አደጋ መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 682 ደረሰ።
የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና 28.08.2026 13:22
በዛሬው የዓለም ዜና ፤የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለስድስት ወራት ተቋርጦ የነበረውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪል ዘጋቢዎች የሥራ ፈቃድ ማደሱን መግለፁን ፣በደቡብ ሱዳን 49 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት መግለፃቸውን፣ኤስዋቲኒ አወዛጋቢ በሆነ የሶስተኛ ሀገር ስምምነት መሰረት ሁለት ስደተኞችን ከአሜሪካ መቀበሏን፣በሟቹ የኖሮዌ ንጉስ ሀኖርድ አምስተኛ ምትክ ልጃቸው ንጉሥ ሃኮን ስምንተኛ ተብለው መሰየማቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በሩ ጨርሶ አለመዘጋቱን መግለጿን እንዲሁም በኔፓል በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ህንዳውያን የደረሱበት አለመታወቁን አካቷል።
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ 27.08.2026 12:01
አርስተ ዜና፤ -በያዝነዉ ነሐሴ ወር ብቻ ከ 60 በላይ ኢትዮጵያዉያን ፤ ከዕፅ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከሳዉዲ አረብያ የሚወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። -በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው አውዳሚ ድንገተኛ የጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ 300 በላይ ደረሰ። ከ 1300 በላይ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።-የአሜሪካው 9/11 ወይም የመስከረም 11 ዱ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ።-የበቦስኒያ የጦር ወንጀለኛ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 26.08.2026 10:22
የዛሬው የዓለም ዜና የኦባሳንጆን የሰሞኑን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፁን፣በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እና በስጋት እየተመለከቱት መሆኑን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የምዕራባዉያን ዲፕሎማቶች ማስታወቃቸውን፣የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸውን፣አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ የጣለችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምንም አይነት ግብ አያሳካም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መናገራቸውን፣የአሜሪካ የስለላ ኃላፊ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ን እንዲሁም በጀርመን አንድ የፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ሰራተኛ በወባ ህይወቱ ማለፉን አካቷል።
የነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 25.08.2026 10:37
ደቡብ ሱዳን ፤ ሁለት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ የመቀሌ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ። ኢትዮጵያ እ.ጎ.አ. በ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ሰነዷን በይፋ አቀረበች። የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች 79 ስደተኞችን ታደጉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትመልስ ነው። 1501ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ ተከበረ።
የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 24.08.2026 10:21
አርስተ ዜና፤ በጫካ የሚገኙትና የፋኖ ንቅናቄ ተራ አባል ነኝ ሲሉ የገለፁልን አቶ እስክንድር ነጋ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከበርካታ የግድያ ሙከራ ማምለጣቸዉን ተናገሩ። እስክንድር ነጋ ጽምዶ የተባለዉን ጥምረት ን የኢትዮጵያ ጠላት ብለዉታል።-ዛሬ 35 ኛ ዓመት የነጻነት ቀንዋን ዛሬ ያከበረች ዩክሬይን መዲናዋ ላይ አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃምን ጨምሮ የአዉሮጳ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።- በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለዉን ግጭት ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፤ የአሜሪካን ከኢራን ጋር ስላለው ግጭት መፍትሄ ለማግኘት ከቴህራን ጋር በአክብሮት መነጋገር እንዳለባት አጽኖት ሰጡ።
የነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 23.08.2026 8:11
• በደቡባዊ ቱኒዚያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን አፍኖ ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ። • በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ቦርጉ ግዛት ታጣቂ ጂሃዲስቶች ትክክለኛውን የእስልምና አስተምሮ አልተከተሉም ባሏቸው ምዕመናን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። • ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የሚያስፈልጋትን የ30 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮጳ ህብረት እንደምትጠብቅ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። • አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ።
የነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 22.08.2026 11:09
በዛሬው የዓለም ዜና ከአንድ ወር በላይ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁን ፣በናይጄሪያ በአክራሪ ቡድኖች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መታፈናቸው መገለፁን፣የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሃን ዋዴፉል ለጉብኝት ዛሬ ዩክሬን መግባታቸውን፣የስዊድን ፖሊስ በአሥራዎቹ ዕድሜ የምትገኝ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ መገደሏን ተከትሎ የበይነመረብ ትስስር መድረኮችን እየመረመረ መሆኑን ፣እንዲሁም በምስራቅ ስፔን በተከሰተ የሰደድ እሳት ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አካቷል።
የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 21.08.2026 12:01
አንጎት፥ መንገድ ዳር የተጠመደ ፈንጂ ባለሦስት እግር ባጃጅ አጉኖ ጉዳት አደረሰ፤ ኦባሳንጆ ከአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ የማቅረቡ ምክንያት፤ ቡኒያ፥ ኢቦላ ዳግም ከተቀሰቀሰ 100ኛ ቀኑ ተቆጠረ፤ ፓሪስ፥ «ዩክሬንን ለመደገፍ የፈቃደኞች ጥምረት» የተባለው ቡድን ሰኞ ሊሰበሰብ ነው፤ ስቶኮህልም፥ ትምህርት ቤት በደረሰ የጎራዴ ጥቃት በርካቶች ቆሰሉ
Liknande poddar
Replaio är ingen poddutgivare; programnamn, omslag och ljud tillhör sina upphovspersoner och distribueras via offentliga RSS-flöden