DW

ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle

News AM ↓ 66 avsnitt

አፍሪቃን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይታዩበታል።

Glöm inte att besöka poddens webbplats och stötta skaparen: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_fokus_afrika-13603-xml-mrss

Skapare

DW

Kategori

News

Senaste avsnittet

28 nov 2026

Var kan du lyssna?

Poddar i appen Replaio Radio Kommer snart

Poddar kommer snart till appen. Installera nu och bli först med att uppleva ett helt nytt sätt att lyssna på poddar

Ladda ned på Google Play Installera gratis Android 10 mn+ nedladdningar · betyg 4,7+ iOS snart

Avsnitt

ትኩረታቸዉን አፍሪቃ ላይ ያደረጉት የጀርመን ኩባንያዎች 28.11.2026

የዓለም ንግድ እና ነባሩ የገበያ ስርዓቶች በተናጉበት በአሁኑ ወቅት የጀርመን ኩባንያዎች ትኩረታቸዉን አፍሪቃ ላይ አድርገዋል። የጀርመን የንግድ ተቋማት ስለ አፍሪቃ ያላቸው አመለካከት አዎንታዊ ነው። አፍሪቃ የብዙ እድሎች ምድር ናት።" የጀርመን እና የአፍሪቃ ግንኙነት ለሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው።

አፍሪቃ ዉስጥ አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች ከየት መጡ? ለቁጥጥርስ ለምን አስቸጋሪ ሆኑ? 28.11.2026

ጦር መሳሪያዎቹ ሁልጊዜ አዳዲስ አይደሉም። አንዳንዶቹ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ሲዘዋወሩ የቆዩ ሲሆን፣ ከአንድ የታጠቀ ቡድን ወደ ሌላው እየተሸጋገሩ እና ብሔራዊ ድንበሮችንም እያቋረጡ ይገኛሉ። ወደ አፍሪቃ የሚገባ የአነስተኛ የጦር መሳሪያዎች ከየት መጡ? ን የሚቆጣጠረው ማነው? በአፍሪቃ የሚገኙ አነስተኛ የጦር መሳሪያዎችን የሚቆጣጠረው ማነው?

የሳውዲ አረቢያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ማሽቆልቆሉ ቀጥሏል፤ ባለፉት 12 ወራት ቢያንስ 211 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፣ የአካል ቅጣቶችም ተፈጽመዋል፣ ትችት የሚያሰሙ ወገኖች ላይ የሚወሰደው እርምጃም ተጠናክሮ ቀጥሏል። 21.11.2026

AFP እንደዘገበው በሞት ከተቀጡት 211 ሰዎች መካከል 100ዎቹ የሳዑዲ አረቢያ ዜጎች ሲሆኑ፣ የተቀሩት ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ዜጎች ናቸው። ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳሳወቀው፣ በሐምሌ ወር የሳዑዲ ባለስልጣናት ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በሞት ቀጥተዋል።

ሩሲያ ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬንን በመውረሯ ከምዕራባውያኑ ያስከተለው መቃቃር ፊቷን ወደ አፍሪካ እንድታዞር አድርጓታል። በሊቢያ ሰዎች ማዘዋወር፣ ሥልጣን እና ትርፍ ማጋበስ አንዳቸው ከሌላቸው ተሣሥረዋል። 01.11.2026

ሩሲያ ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬንን በመውረሯ ከምዕራባውያኑ ያስከተለው መቃቃር ፊቷን ወደ አፍሪካ እንድታዞር አድርጓታል። በሊቢያ ሰዎች ማዘዋወር፣ ሥልጣን እና ትርፍ ማጋበስ አንዳቸው ከሌላቸው ተሣሥረዋል። የዕለቱ የትኩረት በአፍሪካ መሰናዶ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።

ጦርነቶችና የአየር ንብረት ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ሰዎችን፣ በተለይም አፍሪቃን እየጎዳ ነው። ውጤቱም፡ ስደት፣ መፈናቀልና ረሃብ ሆንዋል። ሁለት ዘገቦች እንደሚያመለክቱት ለዓለም ማህበረሰብ እውነታዎችን እና ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባሉ። 24.10.2026

ከፍተኛ የሆነ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት ካጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር አንጻር፣ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎችን የያዙት አስር ሀገራት ዝርዝር በአብዛኛው የአፍሪቃ ሀገራትን ያካተተ ነው። ናይጄሪያ፣ ኮንጎ እና ሱዳን ግንባር ቀደም ናቸው። ደቡብ ሱዳንም ለመጀመርያ ጊዜ ተካታለች። ከህዝቧ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰብአዊ እርዳታ ጥገኛ ነዉ።

ጦርነቶችና የአየር ንብረት ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ሰዎችን፣ በተለይም አፍሪቃን እየጎዳ ነው። ውጤቱም፡ ስደት፣ መፈናቀልና ረሃብ ሆንዋል። ሁለት ዘገቦች እንደሚያመለክቱት ለዓለም ማህበረሰብ እውነታዎችን እና ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባሉ። 24.10.2026

ከፍተኛ የሆነ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት ካጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር አንጻር፣ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎችን የያዙት አስር ሀገራት ዝርዝር በአብዛኛው የአፍሪቃ ሀገራትን ያካተተ ነው። ናይጄሪያ፣ ኮንጎ እና ሱዳን ግንባር ቀደም ናቸው። ደቡብ ሱዳንም ለመጀመርያ ጊዜ ተካታለች። ከህዝቧ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰብአዊ እርዳታ ጥገኛ ነዉ።

ትኩረት በአፍሪቃ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም. 17.10.2026

ኬንያ ራይላ ኦዲንጋ የታገሉለትን ዴሞክራሲያዊ ምህዳር ማስጠበቅ ትችል ይሆን? ውጊያ ያባባሰው ሰብአዊ ቀውስ በሱዳን

ለሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የጦር መሣሪያ ለሚያቀብሉ ሀገራት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰጠው ማሳሰቢያ 19.09.2026

ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን በሱዳኑ ግጭት ላይ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ ውይይት ሊካካሄድ እንደሚችልም ዲፕሎማቶች ከወዲሁ ጠቁመዋል። ይሁንና ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ጉዳዩን የዘገበው AFP ግን በሱዳኑ ግጭት ላይ ከጉባኤው ጎን ለጎን ውይይት ሊካሄድ ይችላል ከማለት ውጭ እነማን እንደሚነጋገሩ አልገለጸም።

የየመን ሁቲ አማጽያን በግብጽ ላይ ያሳደሩት ጫና 19.09.2026

ሁቲዎች ባብ ኤል ማንዴብ የመርከቦች እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ የማቆም እቅድ እንደሌላቸው ምልክት ማሳየት የፈለጉ ይመስላል። ሆኖም በቀይ ባህር ላይ የሚጓጓዙ መርከቦች ቁጥር መቀነስ ለግብጽ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት የሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮች አንዱ በሆነው የሱዌዝ ቦይ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ዋሽንግተን የሱዳን ማዕቀብ እንዲሰፋ ጠየቀች- አፍሪካ ከኢራኑ ጦርነት ተጽዕኖ አልወጣችም 29.08.2026

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ዳርፉር ግዛት ተጥሎ የቆየው የመሳሪያ ማዕቀብ በመላው ሀገሪቱ የሚተገበር ሆኖ እንዲሻሻል ለፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ያቀረበችው ሰሞኑን ነው።

የነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት 29.08.2026
ትኩረት በአፍሪቃ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. 08.08.2026

የሱዳን ጦር ተጻራሪውን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በያዝነው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማለቂያ ድረስ ድል አደርጋለሁ ሲል ዝቷል። የሱዳን ጦር ኃይል እንደዛተው የተቀናቃኙን ኃይሎች ለማጥፋትን በተለያዩ ግንባሮች በእርምጃው እየገፋ መሆኑን የጦሩ አዛዥ ለዘጋቢዎች ተናግረዋል። ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ማሊ፤ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ይከሰት ይሆን? 01.08.2026
ዳንጎቴ በምሥራቅ አፍሪቃ ለመጀመሪያው የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ፕሮጀክት ኬንያን ለምን መረጡ? 18.07.2026

በቀን 700ሺህ በርሜል የተጣራ ነዳጅ ዘይት እንደሚያቀርብ የተነገረው ተቋሙ ኬንያን ብቻ ሳይሆን መላውን የምሥራቅ አፍሪቃ አካባቢ ይለውጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ተቋሙ በአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በምስራቅ አፍሪቃ የነዳጅ አቅርቦትን፣ ንግድን እና የኢኮኖሚ እድገትን እንደገና ሊቀርጽ ይችላልም ተብሏል።

ትኩረት በአፍሪካ የሐምሌ 04 ቀን 2018 መሰናዶ 11.07.2026

ደቡብ አፍሪቃ፤ ስደተኛ ጠል ጥቃቶችን ሸሽተዉ የወጡ አፍሪቃዉያን፤ አፍሪቃን ለድርቅ እና ለጎርፍ የሚያጋልጠዉ የኤል ኒኞ

ደቡብ አፍሪቃ፤ ስደተኛ ጠል ጥቃቶችን ሸሽተዉ የወጡ አፍሪቃዉያን 11.07.2026

በደቡብ አፍሪቃ የተከሰተዉን የመጤ ጥላቻ ጥቃት ተከትሎ ብዙዎች ህይወታቸውን እንደገና ለመገንባት እየታገሉ ቢሆንም፤ በአፍሪቃ ውስጥ ፍልሰትን የሚያባብሱ ጥልቅ የአስተዳደር እና የኢኮኖሚ ችግሮች መኖራቸዉን የሚጠቁም ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ ውጭ ዜጋ እስከሆንክ ድረስ እዚያ እንድትኖር አይፈልጉም።

ትኩረት በአፍሪቃ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 04.07.2026

የደቡብ አፍሪቃ የመጤ ጠል እንቅስቃሴ አብዛኞቹን የአፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት አስቆጥቷል። ናይጀሪያ እና ኬንያን ጨምሮ በርካቶቹ ዜጎቻቸውን ለማውጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ደክመው ያፈሩት ሀብት ለተዘረፈ ለወደመባቸውም ካሣ እንደሚጠይቁ እየገለጹ ነው። በዚህ መሀል እዚያ ያሉ ወገኖች ሰቀቀን ከፍቷል።

ትኩረት በአፍሪቃ፣ ሱዳን-አል ዑቤይድ ላይ ያጠላዉ ሥጋት፤ የጊኒ ቢሳዉ ቀዉስ 20.06.2026

ከዚሕ ዉስጥ ከ14 ሚሊዮን የሚበልጠዉ አንድም ተፈናቃይ ሁለትም ሥደተኛ ነዉ።የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) እና የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ባለሥልጣናት ባገባደድነዉ ሳምንት አጋማሽ እንዳሉት በዓለም በርካታ ሕዝብ ለረሐብ ከተጋለጠባቸዉ 13 ሐገራት ወይም ግዛቶች ግንባር ቀደሟ ሱዳን ናት።

የደቡብ አፍሪቃ የፍልሰተኞች ቀውስ፥ የፕሬዚደንቱ ዕቅድ ያጠራጥራል 13.06.2026

የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት «ሕገ ወጥ» ያላቸው ስደተኞች ላይ ቁጥጥሩን እንደሚያጠብቅ ዝቷል ። ስደተኞቹ እንዲወጡ የሚያስተባብሩ የደቡብ አፍሪቃ ሰልፈኞች ግን የአገሪቱን መንግሥት ዕቅድ የመስማት ፍላጎቱም ያላቸው አይመስሉም ።

ትኩረት በአፍሪቃ 13.06.2026
የግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ/ም የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት 16.05.2026
የሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት 02.05.2026
የሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ትኩረት በአፍሪካ 25.04.2026
ሶማሊያ ቱርክ የነዳጅ ክምችቷን እንድትጠቀም ለምን ፈቀደች? 18.04.2026

ቱርክ በሶማሊያ የባህር ዳርቻ ነዳጅ ለማውጣት ዝግጅት ላይ ነች፡። ለነዳጅ ፍለጋው ባለፈው ሳምንት የአገሪቱ ትልቅ መርከብ ካግሪ ቤይ፤ ከሞቃዲሾ የባህር ዳርቻ ደርሳለች። በጎርጎሪያኑ በ2024 ሁለቱ ሀገራት የመከላከያ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብሩ አሁን ወደ ነዳጅ ፍለጋ አድጓል።

በአፍሪቃ የኑክሌር ተቋምን ለመገንባት ሩጫ 28.03.2026

የግል የኒኩሌር ተቋም፦ ደቡብ አፍሪቃ የራሷ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አላት፣ ግብፅ በግንባታ ላይ ነች፣ ኬንያ፣ ጋና እና አንዳንድ ሌሎች አገራት እናም ቢኖረን ሲሉ ያልማሉ ። ስኬቱ ለየቅል ቢሆንም፤ የሕዝቡ ስጋት ግን ተመሳሳይ ነው ። ሙሉ ዘገባውን በድምጽ እና በጽሑፍ ከገናኛው ማግኘት ይቻላል።

Lyssna på podden ትኩረት በአፍሪቃ | Deutsche Welle i Replaio

Radio och poddar i en och samma app - gratis och utan konto. Installera redan idag och missa inte premiären

Ladda ned på Google Play

Replaio är ingen poddutgivare; programnamn, omslag och ljud tillhör sina upphovspersoner och distribueras via offentliga RSS-flöden