DW

የዓለም ዜና

News AM ↓ 242 avsnitt

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

Glöm inte att besöka poddens webbplats och stötta skaparen: www.dw.com

Skapare

DW

Kategori

News

Poddens webbplats

www.dw.com

Senaste avsnittet

28 nov 2026

Var kan du lyssna?

Poddar i appen Replaio Radio Kommer snart

Poddar kommer snart till appen. Installera nu och bli först med att uppleva ett helt nytt sätt att lyssna på poddar

Ladda ned på Google Play Installera gratis Android 10 mn+ nedladdningar · betyg 4,7+ iOS snart

Avsnitt

የህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 28.11.2026

የዛሬው የዓለም ዜና፤በትግራይ ይደረጋል የተባለው ምርጫ እና ተቃውሞው፣በመጭው የካቲት የሚካሄደው የደቡብ ሱዳን ምርጫን፣ በሳዑዲ አረቢያ የክሩዝ ሚሳኤል መትታ መጣሏን መግለጿን፣ሁቲዎች በየመን ዋና ከተማ ጥቃት መፈፀሙን፣ ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን የእስራኤልን ጥቃት ማውገዙን እንዲሁም በአፍጋኒስታን በደረሰ ፍንዳታ በርካቶች መሞታቸውን አካቷል።

የዓለም ዜና ፦ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም. 27.11.2026

አርዕስተ ዜና የአውሮፓ ምክር ቤት በኤርትራ ይፈጸማል በተባለ “ማሰቃየት ላይ ገለልተኛ ምርመራ” እንዲደረግ ጠየቀ። ዶናልድ ትራምፕ፣ቭላድሚር ፑቲን በታኅሳስ በፍሎሪዳውየቡድን -20 ጉባኤ ላይ መገኘት-አለመገኘታቸዉን አላውቅም አሉ። በቅርቡ በ16 አገሮች ረሃብ ይባባሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ድርጅቶች አስጠነቀቁ።

DW Amharic የኅዳር 17 ቀን 2019 የዓለም ዜና 26.11.2026

በትግራይ ክልል በተደረገ ጦርነት ጎረቤት አገራት ለማጽያኑ “ድሮን የሚተኩሱ ሙያተኞች” ልከው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወነጀሉ። የኤርትራ መንግሥት “የኢትዮጵያ ጠላት” ያሏቸው ኃይሎች “የማስታጠቂያ መስመር” ከመሆን እና ከእነሱም ጋር ከመተባበር እንዲያቆም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳስበዋል።

ጀርመን በኬንያ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ላይ አይኗን አሳርፋለች፣ ሳዑዲ መራሹ ኅብረት የየመን የወደብ ከተማ ሆዴይዳን መምታቱን አስታወቀ። የስደተኞች መጠለያን ለማጥቃት በማሴር የተጠረጠሩ ታዳጊ ወጣት ጀርመናውያን ታሰሩ 25.11.2026

የህዳር 16 ቀን አርዕስተ ዜና በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በባድመ አቅራቢያ ገመሃሎ ዛሬ ከባድ ውጊ ያመካሄዱን ነዋሪዎች ተናገሩ RSF ማክሰኞ ለሊት በብሉ ናይል ግዛት በፈጸመው የድሮን ጥቃት 19 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ 20 ቆሰሉ የደቡብ አፍሪቃ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረገ

የዓለም ዜና፤ ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 24.11.2026

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዉስጥ በተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ድብደባ የጦር ወንጀሎች ተፈጽመው ሊሆን ይችላል ሲል ከሰሰ፤ ምርመራ እንዲደረግም አሳሰበ። የጀርመን ፕሬዝዳንት ሽታይንማየር፣ከጋናው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ ጋር በመሆን ስድስተኛውን የጀርመን-አፍሪቃ የንግድ ጉባኤ አክራ ላይ በይፋ ከፈቱ።

DW Amharic የኅዳር 14 ቀን 2019 የዓለም ዜና 23.11.2026

ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ120 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን መንግሥት አስታወቀ። በናይጄሪያ የካምባሪ ጎሳ አባላት በፉላኒዎች ላይ በፈጸሙት የበቀል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ60 በላይ አሻቀበ። በሊቢያ በሩሲያ መርከብ ላይ ጥቃት የፈጸመችው ዩክሬን እንደሆነች የአገሪቱ ፕሬዝደንት አታወቁ።

የህርዳ 13 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 22.11.2026

ካርቱም በድሮን በተፈፀመ ጥቃት የመኖሪያ ቤቶች ላይና የተባበሩት መንግስታት ህንፃ ላይ ጉዳት ደረሰ።በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ያለ ጋራ ስምምነት ተጠናቀቀ። ከዩናይትድ ስቴትስ የተጠረዙ 25 ስደተኞች ላይቤሪያ ገቡ። ናይጄሪያ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጽ ከታዋቂ ደቡብ አፍሪቃዊ የጎልፍ ተጫዋች ሻንጣዎች ያዘች።...

የህዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 21.11.2026

የህዳር 12 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና

ኅዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ የአማርኛ ዜና 20.11.2026

የዓለም ዜና ፤ የኅዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ የአማርኛ ዜና ከዶቼ ቬለ

የዓለም ዜና፤ የዕለተ ሐሙስ ኅዳር 10 ቀን፣ 2019 ዓ.ም 19.11.2026

ባድመ፥ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ወታደራዊ ውጥረቱ አይሏል፤ ኦሞ፥ በቤሮ ወረዳ 10 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ «ሸባ ማይልስ» አገልግሎቱ ላይ ስለተከሰተው የመረጃ ብርበራ ምርመራ ጀመረ ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና የሶማሊያ አዲሱ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ፤ ሼንዤን ፥ ትራምፕ፤ ሺ እና ፑቲን የሰላም ስምምነት አወጁ

የኅዳር 9 ቀን 2019 የዓለም ዜና 18.11.2026

ኢትዮጵያና ኤርትራ በሚያዋስናቸዉ ድንበር አካባቢዎች ጦር ኃይሎቻቸዉን በብዛት እያሰፈሩ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች አስታወቁ።ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የግጭት ጉዳይ አጥኚ ተቋማትን፣የትግራይ አማፂ ያላቸዉን ህወሓትንና የትግራይ ሠላም ኃይላት ተዋጊዎችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የሁለቱ ጠላት መንግሥታት ጦር ኃይላት በተኩስ ርቀት ላይ ተፋጥጠዋል

የዓለም ዜና፦ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. 17.11.2026

የህዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በአርሲ ሽርካ ወረዳ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነቱን ወሰደ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አከባቢባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ውጊያ እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ በ2026 ዓ.ም. በሱዳን ጦርነት ከሞቱት ሰዎች ሦስት አራተኛው በድሮን ጥቃት የተገደሉ ናቸው ሲል የተመድ አስታወቀ

የዓለም ዜና፤ ኅዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም ሰኞ 16.11.2026

-በምሥራቅ ጎጃም፣ ደብረ ወርቅ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀስቀሱ ተሰማ።-ሞያሌ የጀመረዉ ከባድ መሳርያ የታገዘ ግጭት መቀጠሉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናገሩ።-አምስት የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ስደተኞችን ለመመለስ አዳዲስ ደንቦች ላይ እየሰሩ ነዉ። በሩዋንዳ ለተመላሾች ማዕከል ይገነባል ተብሏል።

የሕዳር 6 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና 15.11.2026

የዛሬው የዓለም ዜና ፤የመን ሁቲዎች ከመንግስት ጎን የተሰለፉ 600 ታጣቂዎችን መልቀቃቸውን፣ የእስራኤል ወታደሮች አንድ ጋዜጠኛውን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉበት የኤኤፍፒ መዘገቡን፣ማክሮን የፈረንሰኛ ተናጋሪ ሀገሮች ማኅበር አንድነቱን እንዲያጠናክር ማሳሰባቸውን እና ፊሊፒንስ የመጀመሪያውን የዩሮቪዥን እስያ የሙዚቃ ውድድር ማሸነፏን አካቷል።

የሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 14.11.2026

የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥና የባለ አደራ አስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የጀነራል ገብረእግዚአብሔር በየነ ልጅ ተገደለ። በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ሲጓዙ የነበሩ 3 የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በፈንጂ መንጎዳቸውን። በተለያዩ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች በተፈጠረ የግንኙነት ችግር ከ10,000 በላይ በረራዎች መሰረዛቸውን

የህዳር አራት ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 13.11.2026

አርዕስተ ዜና የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪነት የወነጀሏቸዉ 520 ያክል ኢትዮጵያዉያንን በሞት ልትቀጣ ወሰነች። ማይክሮሶፍት የሚሰጣቸዉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ከትናንት ጀምሮ መታጎሎ የዓለምን የዓምደ መረብ እንቅስቃሴ አጎለ። አውሮጶች ለዩክሬን እና ሩስያ የሰላም ንግግሮች ማንን መላክ እንዳለበቸው እየተከራከሩ ነው።

የኅዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 12.11.2026

የቡድን 7 የው/ጉ/ሚኒስትሮች በኢትዮ-ኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እንዳሳሰባቸዉ አመለከቱ። ከሞያሌ ተፈናቅለው ወደ ኬንያ የተሰደዱ እናቶች ከጥቃት ቢሸሹም ለልጆቻቸው ምግብና መጠለያ ለማግኘት ተቸግረዋል። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የአውሮፓ ሃገራት ዩክሬን ውስጥ ሰላም ወይም ጦርነት ይፈልጉ እንደሁ እንዲወስኑ ጠየቁ።

የሕዳር 2 ቀን 2019 የዓለም ዜና 11.11.2026

-በአማራ ክልል ዋግሕምራ ዞን ሰሐላ ወረዳን የመታዉ ድርቅ ከወባ ወረርሺኝ ጋር ተዳምሮ ሰዎች መሞት፣ መራባቸዉን ነዋሪዎች አስታወቁ።-የዓየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትለዉን ጉዳት ለመቀነስ የበለፀጉት ሐገራት ሁነኛ ርምጃ እንዲወስዱ የሚደረገዉ ጥሪና ጥያቄ እንደቀጠለ ነዉ።

የዓለም ዜና፤ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓም ማክሰኞ 10.11.2026

የሩስያን እና የዩክሬይንን ጦርነት ለማስቆም ፤ አቡ ዳቢ ላይ ዛሬ በሩሲያ፣ በዩክሬን እና በአሜሪካ መካከል የሰላም ድርድር እየተካሄደ ነዉ።-የቀድሞዉ የፎክስ ኒዉስ አቅራቢ የዛሬዉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር፤ በኢራን ላይ ጦርነት እንዲጀመር ግፊት በማድረግ ጨምሮ ብዙ ክስ ቀረበባቸዉ።

በርሊን ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነር የመጀመሪያዋ ሴት የጀርመን እጩ ፕሬዝዳንት ሆነው በሜርስ ተመረጡ 09.11.2026

ሮቤ-ዲዳዓ ወረዳ እንደቶ ከተማ በታጣቂዎች የተገደሉትች ቁጥር ወደ 40 ከፍ አለ። ባለፈው ቅዳሜ በግሪክዋ ደሴት ክሬታ ደቡባዊ ክፍል፣ ስደተኞችን ጭነው የነበሩ 4 ጀልባዎች ባጋጠማቸው አደጋ ቢያንስ 20 ስደተኞች ሞቱ። የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየርን ለመተካት፣ ፖለቲከኛ ኢልዘ አይግነርን በእጩነት ቀረቡ።

DW Amharic የጥቅምት 29 ቀን 2019 የዓለም ዜና 08.11.2026

በሴኔጋል አንዲት ትንሽ ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፤ የሶማሊያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዲሱ ዋና ዳኛ ኢብራሒም ሱሌይማን ቃለ-መሐላ ፈጸሙ። የፖላንድ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በካራኮቫ ስድስት ሰዎች የተገደሉበትን የጅምላ ተኩስ የሽብር ጥቃት በማለት በየነ። የእስራኤል ፕሬዝደንት ጋዲ አይዘንኮት መንግሥት እንዲመሰርቱ ኃላፊነት ሰጡ።

የጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 07.11.2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤በትግራይ ከተሞች እየተስተዋለ ያለውን የፀጥታ ችግር፤ በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ አካባቢ በምትገኝ መንደር በተፈጸመ የአየር ጥቃት 25 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን

የጥቅምት 27 ቀን 2019 የዓለም ዜና 06.11.2026

-የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ የሠላም ኃይላት ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ ከህወሓት ጋር በገጠሙት ጦርነት የማረኳቸዉ ጦር መሳሪያዎች ዛሬ ለዉጪ ዲፕሎማቶች ለዕይታ ቀረቡ።-ኬንያ ዉስጥ የምፅዓት ቀን ኑፋቄ ሰባኪ የተባለ ፓስተር ሰዎችን እያስራቡ በመግደል ወንጀል 200 ዓመታት እስራት ተፈረደበት።

የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ሐሙስ 05.11.2026

የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት የገጠሙት መወቃቀስና መወጋገዝ ወደ ፍጥጫና ዲፕሎማሲያዊ መበቃቃር እየናረ ነዉ። ሁለቱ ሃገራት አንዱ በሌላዉ ላይ ቆንስላ ዘግተዋል።-ኦሮሚያ ክልል ኪረሙ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የሰዉ ህይወት ጠፋ፤ንብረትም ወደመ።--በአፍሪቃ ቀንድ የናረው ውጥረት «በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ይረግባል» የሚል ተስፋ እንዳላች ቻይና አስታወቀች።

የዓለም ዜና፦ የዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2019 ዓ.ም 04.11.2026

ኮንሶ፥ ታጣቂዎች አራት አርሶ አደሮችን በአሰቃቂ ኹኔታ ገደሉ አንድ አገሩ፤ ዩኒሴፍ፤ ዴሞክራቶች ታሪካዊ በኾነ ድል ሁለቱንም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ተቆጣጠሩ፤ ቴሕራን፥ የፕሬዚደንት ትራምፕ እና ፓርቲኢቸው ሽንፈት ኢራኖችን በደስታ አደባባይ አትምሟል፤ ዓለም፥ ስለአሜሪካ ምርጫ ውጤት ዓለም አቀፍ አስተያየቶች

Lyssna på podden የዓለም ዜና i Replaio

Radio och poddar i en och samma app - gratis och utan konto. Installera redan idag och missa inte premiären

Ladda ned på Google Play

Replaio är ingen poddutgivare; programnamn, omslag och ljud tillhör sina upphovspersoner och distribueras via offentliga RSS-flöden