DW

ዜና መጽሔት

News AM ↓ Odcinki: 189

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

Koniecznie odwiedź stronę podcastu i wesprzyj twórcę: www.dw.com

Autor

DW

Kategoria

News

Strona podcastu

www.dw.com

Ostatni odcinek

12 lis 2026

Gdzie słuchać?

Podcasty w aplikacji Replaio Radio Już wkrótce

Podcasty trafią do aplikacji już wkrótce. Zainstaluj teraz i jako pierwszy zobacz nowe podejście do podcastów

Pobierz z Google Play Zainstaluj za darmo Android prawie 10 mln pobrań · ocena 4,7+ iOS niedługo

Odcinki

የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 25.06.2026

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?

የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 24.06.2026

በዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤ የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁን ከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።

የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 23.06.2026

የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።

የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 22.06.2026

መጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገ 20.06.2026

ምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።

DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 19.06.2026

በሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።

የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 18.06.2026

የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤ መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።

የሰኔ 10 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 17.06.2026

አሳሳቢው የጦርነት ስጋት በሰሜን ኢትዮጵያ ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ «የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ»ን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ፣ ዩናይትድ ስቴትሰና ኢራን ደረሱበት የተባለው ስምምነት አፍሪካን እንዳያዘናጋ ተንታኛች ማሳሰባቸው እንዲሁም ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች ዩክሬንን ለመደገፍ መስማማታቸው የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው

የሰኔ 9ቀን 2018 የዜና መፅሔት 16.06.2026

የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ዉድነት በደሞዝተኞች ላይ ያሳረፈዉን ጫና ችግር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በትግራይ ክልል አዲስ የወጣዉ የወታደራዊ አገልግሎት ሕግ ያስከተለዉ ተቃዉሞና ሥጋት፣ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ መታሰሯና የአፍሪቃ ሕብረት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ በተቀጣጠለዉ የዉጪ ጠል ጥቃትና ዛቻ ላይ ሊነጋገር ማቀዱን ዜና መፅሔቱ በየተራ ይተነትናል።

DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 15.06.2026

በሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተና፣ የኢራን አሜሪካ ስምምነት እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ተካተዋል።

የሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.06.2026

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጥሪ ነዋሪዎች ከአሸናፊው ፓርቲ ምን ይጠብቃሉ ? ሳዑዲ አረቢያ 4 ኢትዮጵያውያንን በሞት ቀጣች፤ 1655 ዜጎች ደግሞ በምህረት እንዲለቀቁ ተደረገ ለአሜሪካዉያን የኤቦላ ማገገምያ ማዕከል ኬንያ ዉስጥ መገንባቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረትና ደቡብ ኮሪያ፤ የሰሜን ኮሪይና ቻይና ጉባኤዎች

የሐሙስ ሰኔ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 11.06.2026

በዜና መፅሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችና እያሳወቀ እና ቅሬታዎችንም እያጣራ መሆኑን መናገሩ፣ ሰቆጣ የተጠለሉ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጻግምጅ እና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቃዮች ለረሀብ መጋለጣቸውን መግለፃቸው ፣ -ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ መቀጠሉ ፣ የኤቦላ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅኝት ስራዎች እንዲጠናከሩ መጠየቁ ፣ ዛሬ በሜክሲኮ የሚጀመረው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው ። በባህል መድረክ ለህክምና ወደ በጀርመን በመጣበት አጋጣሚ እና የስዕል እግዚቢሽን ያቀረበውን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላን እንግዳዉ አድርጓል።

የሰኔ 3 ቀን፣ 2018 የዜና መፅሔት 10.06.2026

ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት፣ ጋምቤላ ክልል ዳግም ያገረሸው የፀጥታ ስጋት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ24 የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ይፋ ማድረግ መጀመሩ፤ ለመጪው ዓመት ከ2,3 ትሪሊየን በላይ ብር የመንግሥት በጀት መታቀዱ እንዲሁም የዲጂታል ገቢ እና አዲሱ ፈተና የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።

የዜና መጽሔት፤ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 09.06.2026

የዜና መፅሔት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ፈደ,ራዊ መንግሥትና በህወሓት መካከል የናረዉን ዉጥረት ለማርገብ የአፍሪቃ ሕብረትን ሚና የሚቃኝ ቀለ ምልልስን ያስቀድማል።የትግራይ ወጣቶች በብዛት ከክክልሉ መዉጣታቸዉንና ምክንያቱን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።የትራፊክ አደጋ መደጋገምና መፍትሔዉ ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕሳችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የኤርትራና የግብፅ ወዳጅነት ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላም የሚኖረዉን በጎ መጥፎ ዉጤት በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።

የሰኞ ሰኔ አንድ ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 08.06.2026

በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ስጋት በትግራይ የየደረሰዉ የድሮን ጥቃት እና አካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ያልሰጡ በሰሜንና ደቡብ ወሎ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ነገ ሰኔ 2 ቀን የምርቻ ድምፅ ሊሰጡ መሆኑ ፤ እንዲሁም ኢሰመኮ - አርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ምዕመናን እና ቤተክርስትያን ላይ የተፈፀመ ጥቃትን በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለፁ በሚሉ ርዕሶች የተቀናበሩት በስፋት ይተነተናሉ።

የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አርብ 05.06.2026
የግንቦት 27 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄት 04.06.2026

በዜና መጽሔት በአርሲ ዞን የተገደሉ ወገኖችን በሚመለከት የመንግሥት እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ምላሽ፤በአማራ ክልል ዋግህምራ ብሔራዊ አስተዳደር የጻግብጂ ወረዳ በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል መባሉ፤ግንቦት 24 ቀን ስለተካሄደው ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት፤ ድኅረ ምርጫ በደቡብ ሕዝቦች ክልል ፤ በሰባተኛው ምርጫ የተሳተፈው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ድሬደዋ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ችግር ደርሶብኛል ማለቱ፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት IMF ለኢትዮጵያ 468 ሚሊየን ዶላር ለመልቀቅ መስማማቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።

የግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 03.06.2026

ከምርጫ ማግሥት ማን ምን አለ? የተሰጡ አስተያየቶች፤ በአርሲ የተፈጸመው ግድያ እና የቀረበው አቤቱታ፤ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የኢጋድና የኅብረት-ለምርጫ የመጀሪያ ጊዜ ዘገባ፣ የአማራ ክልል ወጣቶች ጥሪ ከምርጫው ማግስት በኋላ፤ ብርን ያዳከመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሰኞው ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ። ድህረ ምርጫ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ቃለ መጠይቅ

ልዩ ዝግጅት፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ማክሰኞ 02.06.2026

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ዛሬ በየአካባቢው የወጡ ጊዜያዊ ውጤቶችን እንዲሁም የምርጫውን ሂደት፣ የፀጥታ ችግሮችና እና ተያያዥ ክስተቶችን የሚቃኙ ዘገባዎችን ያካተተ ልዩ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትናንት የካቢኔ አባላት እና የዞን አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችንም ማጽደቁን መነሻ ያደረገ ዘገባም አለን።

በምርጫ ከሚያሸንፈው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል? 02.06.2026

ትናንት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በመጭው አመስት አመታት የሚያስተዳድራቸውን ለመምረጥ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል። ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊው አካል በቀጣይ አምስት አመታት ሀገሪቱን የማስተዳደር ሀላፊነት ይጣልበታል።ለመሆኑ ከመጭው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?

የግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.06.2026

አርዕስተ ዜና ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ዛሬ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ለሚወዳደሩ እጩዎች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በበሻሻ ከተማ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ታዬ ዐፅቀ ሥላሴ ደግሞ በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት ድምጽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በጸጥታ ምክንያት ወደ 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ” አለመከፈታቸውን ዛሬ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ ችግር መቋረጡን ተናግረዋል።

የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 29.05.2026

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጎሀፅዮን አካባቢ፤ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የጓሚዙ 12 መንገደኞች መገደላቸውን መጭው ምርጫ ከተሳታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከታዛቢዎች እና ከመራጮች አንፃር በአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በክልሉ ባለው ግጭት ሳቢያ ግድያ እና ዝርፊያ እየደረሰብን ነው ማለታቸው በደቡብ አፍሪቃ የሚታየውን የመጤ ጠል ጥቃት የሚያስቃኙ አራት ዘገባዎችን አካቷል።

DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 28.05.2026

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ማስጠንቀቂያና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምላሽ፣ የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ድባብ በአዲስ አበባ፣ ''ምርጫው፣ አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው።''የጋራ-መድረክ፣ ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣

የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 27.05.2026

የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱንን የኢድ አል አድሀን በዓል የተመለከቱ ዘገባዎች ያስቀድማል፤ የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ እና የፓርቲዎች አስተያየት፤ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል። በትግራይ ክልል “የወጣቶች የግዳጅ ምልመላ” እየተደረገ መሆኑ መገለጹ፤ በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ከህወሃት ቃል አቀባይ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል።

የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 26.05.2026

በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በአማራ 8፣ በትግራይ 38 ምርጫ ክልሎች ላይ ግንቦት 24 ምርጫ አይደረግም መባሉ፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በአማራ ክልል፤ የምርጫ ቅስቀሳቃ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫ ዘመቻ እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት ባልተጠናቀቁ የቤት ስራዎቹ ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለፀ በሚሉ ርዕሶች ስር ተጠናቅረዋል።

Słuchaj podcastu ዜና መጽሔት w Replaio

Radio i podcasty w jednej aplikacji - za darmo, bez zakładania konta. Zainstaluj już dziś i nie przegap premiery

Pobierz z Google Play

Replaio nie jest wydawcą podcastów; nazwy audycji, okładki i audio należą do ich autorów i są rozpowszechniane przez publiczne kanały RSS