DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
Koniecznie odwiedź stronę podcastu i wesprzyj twórcę: www.dw.com
Gdzie słuchać?
Podcasty w aplikacji Replaio Radio Już wkrótcePodcasty trafią do aplikacji już wkrótce. Zainstaluj teraz i jako pierwszy zobacz nowe podejście do podcastów
Odcinki
የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 03.09.2026 27:34
በዛሬው መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪቃ ህብረት የምታበረክተውን የገንዘብ አስተዋጽዖ በእጥፍ ለማሳደግ መፈለጓ ፣ ህወሃት በፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው ማለቱ፣ በኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ ላይ የአብን መግለጫ እና አንድምታው፣ የተሰኙ ዘገባዎች በትንታኔ ይደመጣሉ።
የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 02.09.2026 19:53
የዜና መጽሔት የምስራቅ ወለጋ ዞን አንጌር ጉቴ አከባቢ ግጭትና ግጭቱ ያፈናቀላቸው ሰዎች ብሶት በጃናሞራ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ መዳረጋቸው መነገሩ፣ በጋምቤላ የምርት መቀነስን ለማካካስ መስኖ እንደማራጭ መያዙ፣ጀርመን በሀገርዋ የሚገኙ የተለያዩ የሩስያ ተቋማት እንዲዘጉ መወሰኗ ላይ ያተኮሩ ቅንብሮች ይቀርባሉ።
የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.09.2026 19:29
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤን ከነሒደቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉድቅ ማድረጋቸዉ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሠላም እንዲሰፍን በተደጋጋሚ የሚደረገዉ ጥሪና ዉጤቱ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የመሬት መንሸራተት ያደረሰዉ ጉዳትና አልርጀንቲናዊዉ የእግር ኳስ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጡረታ መዉጣቱን ያስቃኘናል።
DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 31.08.2026 18:45
በባቲ ወረዳ «የኦነግ ሸኔ» ጥቃት፣ እገታና መፈናቀል ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ምሬት መዳረጉ፤ ግጭት ማስወገድ የተሳናቸው የአፍሪካ ኀብረት መዋቅሮችና የማሻሻል ሂደቶች፤ በአሜሪካ እና ካናዳ መካከል ያገረሸው የንግድ ጦርነትና የዲፕሎማሲ ውጥረት፤ አይስላንድ ለግዜው ወደ አውሮጳ ህብረት ላለመግባት ወሰነች
የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዜና መፅሄት 28.08.2026 23:39
የዛሬው የዜና መፅሄት-ዛሬ ችሎት የነበሩት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ለመጪው ሐሙስ መቀጠራቸዉ ፤, በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች የቀጠለዉ ጥቃት፤ በአፋር ክልል የክረምት ዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ የአርብቶ አደሩን ህይወት መፈተኑ፤ በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ለማኅበረሰባቸው በጎ የሰሩ ግለሰቦች ተሸለሙ የተሰኙ አምስት ርዕሶችን አካቷል።
የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና የዜና መፅሄት 26.08.2026 18:42
ከዓለም ዜና በኋላ በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የመቀሌ ጉብኝት ያመጣው አዲስ ምክረሃሳብ የለም ማለታቸው፤በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የኦባሳንጆን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው መግለፁን፣ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ሰዎች ገድለው፤ ንብረት ስለማውደማቸው እንዲሁም በአላማጣ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ከባድ የእህል እና የገንዘብ መዋጮ በግዴታ እየተጠየቅን ነው ማለታቸውን የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።
የነሐሴ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መፅሔት 25.08.2026 18:47
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የዛሬዉ የመዉሊድ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት መሪዎችን እንደገና ለመሸምገል የጀመሩትን ዲፕሎሲ የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ሥለ ዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት የተጠናቀረዉ ያሰልሳል።ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በተከፈቱ ጥቃቶችና ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛትና ጥያቄን የሚዳስስ ዘገባም አለን።
የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም መጽሔተ ዜና 21.08.2026 25:50
ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፤ ሰሜን ወሎ በፀረ ተሽከርካሪ ቦምብ ፍንዳታ አራት ሰዎች መገደላቸው፤ የመቀሌው የአየር ጥቃት ሰላባዎችና ነዋሪዎች አስተያየት በምክክሩ የጎላ መነጋገሪያ ሆኖ የቀጠለው የአዲስ አበባ ጉዳይ ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው ከፍተኛ የዶላር ጨረታ እንዲሁም በአውሮጳ አትሌቲክስ ውድድር ለጀርመን ወርቅ ያስገኘው ትውልደ ኤርትራዊው ጀርመናዊ አማናል ጴጥሮስን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤ የዕለተ ዓርብ ሳምንታዊ መሰናዶ ከወጣቶች ዓለም፤ እንዲሁም የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ እንወያይ የቅምሻ ጥንቅርም ይኖረናል።
የነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.08.2026 25:01
በዜና መጽሔት ፤ ስለአገራዊው ምክክር የነዋሪዎች አስተያየት ፣ በትግራይ ክልል እየተፈፀሙ ያሉ የድሮን ጥቃቶች ፣ የምስራቅ ወለጋው የጊዳ አያና ጥቃትና የነዋሪዎች ተቃውሞ ፣ በደቡብ ወሎ 3,500 ያህል ከአረብ ሀገራት ተመላሾች በሀገራቸው የስራ እድል ማግኘታቸውን ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አርማውን ያለ አግባብ የሚጠቀሙ እንዳሉ መግለጹን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።
የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 19.08.2026 18:04
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ የመጨረሻ ሰነድ ነገ ለተመካካሪዎች ይቀርባል ሥለመባሉ የተጠናቀረ ዘገባን ያስቀድማል።የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት አሜሪካ ዉስጥ በጊዚያዊነት እንዲኖሩ የተፈቀደላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ፍቃድን ማቋረጡን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳን ድርቅና ወረርሺኝ የሰዉና የእንስሳት ሕይወት ማጥፋታቸዉን የሚያወሳዉ ያሰልሳል።ዜና መፅሔቱ የኑሮ ዉድነት በቡሔ በዓል ላይ ያደረሰዉን ጫና የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
የነሐሴ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 18.08.2026 22:32
ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መጽሔት ጥንቅራችን ፤ ማነጋገሩን የቀጠለው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ቀዳሚዉ ዘገባችን ነዉ። በምክክር ጉባኤው ከፍተኛ መነጋገርያ የሆነዉ የአዲስ አበባ ጉዳይ፤ ሌላዉ በስፋት የምናየዉ ጉዳይ ነዉ። ወጣቶችና ሴት ተፈናቃዮች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው እና ሴተኛ አዳሪነት የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱ ፤ አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ወጣቶች የተሰማሩት መደበኛ ባልኾኑ የስራ ዘርፎች መኾኑን የዓለሙ የስራ ድርጅት ማስታወቁ፤ እንዲሁም በናይል ውሃ አጠቃቀም የግብጽ ዛቻ የሚሉ ዘገቦችንም ዜና መጽሔት የአካተተዉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸዉ።
የነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 14.08.2026 28:30
የጋዜጠኞች መብት ተማጋቹ ድርጅት ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን ጫና ማውገዙ ኢትዮጵያውያን በሚያዘወትሩት ምሥራቃዊ የፍልሰት መስመር ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 106 ስደተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች መርጃ ድርጅት መግለፁን፣ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ድርጅት የዜጎች መብት እንዲከበር የሚቀርባቸው ሃሳቦች አለመተግበሩ እንዳሳሰበው መግለፁ በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ብሔራዊ ቀውስ ሆኖ እንዲታውጅ የመብት ተሟጋቾች ማሳሰባቸውን፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የቻይና እና የአሜሪካ ኩባንያዎች ፉክክርን ያስቃኛሉ።
የሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 13.08.2026 29:22
የዜና መጽሔት፦ አፋር ክልል የተከሰተው የውኃ እጥረት ያስከተለው የእንስሳት ሞት፤ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ዝናብ መቀነሱ፤ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ ያነሱት ሥጋት እና ያደረጉት ጥሪ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተፈጸመ ግድያ እና የክልሉ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ያወጣው መግለጫ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት እና ውጥረት፤ እንዲሁም ኢትዮጵያና ሌሎችም ሃገራት ያወጣሁትን ወጭ ይክፈሉኝ ስትል ደቡብ አፍሪካ መጠየቋን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካትቷል ።
የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.08.2026 18:53
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከከሳቸዉ ተጠርጣሪዎች 30 ያክሉ የተከሰሱበትን ወንጀል አምነዉ ምሕረት እንዲደረግላቸዉ የቀረበላቸዉን ጥያቄ ዉድቅ ማድረጋቸዉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ ምሥራቅ ወለጋ ዉስጥ የተጠናከረዉ ግጭት ሰዎች መጉዳትና ማፈናቀሉ፣ ከአማራ ክልል ከዋግኽምራ የተፈናቀሉ ሰዎች ርዳታ መማፀናቸዉ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያጫረተዉን የዉጪ ምንዛሪ የሚያስተነትኑ ዘገቦች አሉት።
የነሐሴ 5 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 11.08.2026 16:29
በዜና መጽሔት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። የሕወሓት ታጣቂዎች ላይ የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት በአላማጣ፣ ለሰብአዊ መብት ሥጋት የደቀነ «የጦርነት አዝማሚያ» አለ መባሉ፤ በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ለሶማሊያ ኅይሎች ያስረከቡት የስምሪት ቀጠና የሚሉ ዘገባዎችን ነው የምናስተነትነው ።
የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 10.08.2026 18:27
የዜና መጽሔት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - እያደገ የመጣው ውጥረት፤ ከራያ አካባቢ በጦርነት ስጋት የወጣቶችና ሕጻናት በብዛት ለስደት መዳረግ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ድርቅ እና ግጭት ያጠላው ስጋት፤ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶአደሮች «የእርሻ ማዳበሪያ አልደረሰንም» ማለታቸው መገለጹ፤ የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤
የነሐሴ 1 ቀን የዜና መጽሔት 07.08.2026 24:42
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉም የማይሳተፉም ፓርቲዎች ስለ ሂደቱ የሰጡት አስተያየት፣አሳሳቢው የሙስና አሻጥር በኢትዮጵያ ፣ "በስውር የአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡ ፖለቲከኞች ለነሐሴ 11 መቀጠራቸው ፣ በጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚደረግ ጥረት እንዲሁም ጥቂቶችን ተጠቃሚ ያደረገው የድሬዳዋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በዜና መጽሔት ዝግጅታችን ትንታኔ የሚቀርብባቸው ርዕሶች ናቸው።
የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 06.08.2026 29:26
በዛሬው የዜና መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ራያና እና አላማጣ አካባቢዎች ጦርነቱ ማየሉን እና ሴቶች ለቡድን ጾታዊ ጥቃት መዳረጋቸው ፤በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት ፤ ተጎጂዎች እና የአውሮጳ የሰላም ፋውንዴሽን ጥሪ ፤የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት እና የቀጣይ ሥራዎች ላይ ለዶቼ ቬለ የተሰጠ ምላሽ፤ የዐማራ ግሎባል ፎረም የምክክር ጉባኤውን መቃወሙ፤ ሲፒጄ ለ6 ሃገራት ጋዜጠኞች ሽልማት ሲሰጥ በኢትዮጵያ የታሠሩት እንዲፈቱ መጠየቁ፤ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የ14 ሀገራት ቅንጅት በይፋ ከተገለጸው አላማ የሰፋ ትርጉም አለው መባሉ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።
የሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 05.08.2026 21:57
የዜና መጽሔት: ኢትዮጵያና ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዉኃ አዘቃቀም ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ሞቅ ቀዝቀዝ እንዳለ መቀጠሉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ከወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ሥጋት ባንዣበበት ባሁኑ ወቅት የደቡብ ወሎ ወጣቶች፣ የአቅመ-ደካሞችን ቤቶች መጠገንን ጨምሮ ለየአካባቢያቸዉ ሕዝብ 1.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት ነፃ አገልግሎት መስጠታቸዉ ተዘግቧል።ለጋምቤላ በተለይ ለኑዌር ዞን የዘንድሮዉ ክረምት የድርቅ ሥጋት አስከትሏል።ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወባ በሽታ አለቅጥ ተዛምቷል።ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሰጠችዉ የገንዘብ ድጋፍ የአፍሪቃ ሐገራትን ድንበሮች ለማካለል እየጠቀመ መሆኑ ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።
የሐምሌ 28 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 04.08.2026 21:51
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው አባል ፖለቲከኛ አበበ አካሉ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መታሠራቸውን ፓርቲው ገለፀ።የሰሜን ኢትዮጵያው የጦርነት ስጋት ቀጠናዊ ስጋት ያጭር ይሆን?የሸረሪናው ውጊያ ያሰጋው የከባድ ጦርነት መጀመሪያ ይሆን? "በቀደመው የትግራይ ጦርነት የፍትህና ተጠያቂነት ማጣት ለቀጣይ ግጭት በር ከፍቷል " አምነስቲ
የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 03.08.2026 18:12
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሞነኛው የግጭት መረጃ እና የመገናኛ ብዙኃን የይዘት አቀራረብ አንደምታ፤ በትግራይ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካቶች ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ማስገደዱ፤ በቆቦ አካባቢ ወታደራዊ ዝግጅት መጠናከሩ እንዲሁም ሕይወት የቀጠፈ የመሬት መንሸራተት አደጋ በጻድቃኔማርያም ገዳም መከሰቱን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል
የሐምሌ 24 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 31.07.2026 27:25
አንድ የጀርመን ተቋም በኢትዮጵያ ግጭት እንዳይከሰት የሰጠው ምክረ-ሐሳብ፤ ፌደራል ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ መስመር በሕገወጥ ሰዎችን የሚያሸጋግሩትን መቆጣጠሩን መግለጹ፤ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ኢላማ ያደረገው የኢንተርኔት ማጭበርበር፤ ዋግህምራ ዞን አበርገሌ እና ጻግብጂን የተቆጣጠረዉ ታጣቂ ቡድን ተዋጊዎችን እየመለመለ ነው መባሉ፣ መተከል ዞን ከጉባ-ግልገል በለስ የተበላሸው መንገድ፤ እንዲሄም ሮም ጣሊያን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ድግስን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
Podobne podcasty
Replaio nie jest wydawcą podcastów; nazwy audycji, okładki i audio należą do ich autorów i są rozpowszechniane przez publiczne kanały RSS