DW
በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle
ሳይንሳዊ እና ስነ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እና ለህብረተሰቡ ያላቸቸውን ጠቀሜታ ይመለከታል።
Autor
DW
Categoría
Web del podcast
Último episodio
8 de jul. de 2026
¿Dónde escuchar?
Podcasts en la app Replaio Radio Muy prontoLos podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts
Episodios
እየተባባሰ የመጣው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ጥቃት 04.03.2026 13:05
በኢትዮጵያ ዲጂታል ክኖሎጂ አጠቃቀም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እያደገ መጥቷል። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሳትፎ ደግሞ 17.7% ደርሷል። በዚያው ልክም ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ጨምሮ በበይነመረብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚያሳድሩ ጎጅ ባህሪያትንም እንዲስፋፋ እና በስፋት ሊሰራጩ የሚችሉባቸውን ምቹ ሁኔታም ፈጥሯል።
ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች 25.02.2026 10:50
እነዚህ መተግበሪያዎች ኢንተርኔት ፈፅሞ በሌለባቸው ወይም ደካማ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ባላቸው አካባቢዎችም ያለ ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያግዙ ናቸው። መተግበሪያዎቹ በተፈጥሮ አደጋዎች የኃይል መቆራረጥ ሲኖር፣ ኢንተርት ሆን ተብሎ በሚዘጋበት ወይም ተደራሽነት በሌለበት ቦታ የሰዎች መስተጋብር ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋሉ።
አሳሳቢው የልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም 18.02.2026 10:19
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘትን ለረጅም ጊዜ መመልከት፤ ባህሪን እና የአእምሮ ጤናን በዘላቂነት ሊጎዳ ይችላል።ጉዳቱ በተለይም እድገቱ ባልተጠናቀቀ የልጆች አእምሮ ላይ በመሆኑ ደግሞ የሚመጣው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።ይህ ያሳሰባቸው ሀገራት ልጆጆን ከዲጅታል መድረኮቹ የሚያግዱ ህጎችን እያወጡ ነው።
ብራይት ኬን፤ዓይነስውራንን በድምፅ የሚመራው ቴክኖሎጂ 04.02.2026 11:08
ብራይት ኬን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የፈጠራ ስራ ባልተስተካከሉ መንገዶች እና በተጨናነቁ ጎዳናዎች ላይ እንቅፋቶችን እና አደጋዎችን ቀድሞ ለማስጠንቀቅ ያግዛል።ይህ መሳሪያ የ«አልትራሶኒክ ሴንሰሮች»ን በመጠቀም የተገነዘበውን አደጋ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በድምጽ ያሳውቃል።በዚህም አይነስውራንን ከአደጋ ያስጠነቅቃል አቅጣጫም ይመራል።
የዲጅታል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተከታዮቻቸው ላይ ያላቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ 21.01.2026 11:52
የቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም እና የፌስቡክ ዘመን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከተዋናዮች፣ ስፖርተኞች ወይም ከፖለቲካ መሪዎች - በተለይም በወጣቶች ዘንድ የበለጠ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የሚያቀርቧቸው ይዘቶች ጠቃሚ እና በሳል ዕይታ እና አስተሳሰብ የታከለበት ካልሆነ፣ተፅዕኗቸው በሚከተሏቸው ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
የኦንላይን ግብይት ስጋቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች 14.01.2026 12:10
ማሽን ሰዎችን ተክቶ እንዲሰራ የሚያደርገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዲጅታል መንገድ ግብይቶችን ለመፈፀም አገልግሎት ላይ ይውላል። ቴክኖሎጂው የኦንላይን ግብይቶችን ምቹ እና በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አቅርቦቶችን ለማግኘት የሚያግዝ ቢሆንም፤ የግል መረጃ ደህንነት፣ ማጭበርበር ፣ የቁጥጥር ወይም የግልጽነት ችግር ስጋቶች ናቸው።
በማንጎ ተክል በሽታ ላይ የተደረገው ምርምር 17.12.2025 9:09
በአሶሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘውን የማንጎ በሽታን ለማከም የተደረገው ጥናት ለውጥ ማስገኘቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች አጋሮች ጋር ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጥናት በአሶሳ በሁለት ቦታዎች ላይ በሽታውን በማከም ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኒዎሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር አብዱልሙሲን ሀሰን አመልክተዋል፡፡ ጥናቱ አብዛኛውን የገቢ ምንጫቸው በማንጎ ምርት ላይ ያደረጉት አርሶ አደሮችን ችግር እንደሚፈታም አክለዋል፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለምን አሳሳቢ ሆነ? 26.11.2025 10:57
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሰሞኑን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።ኮሚሽነሩ እንዳሉት በተለይም ጀነሬቲቭ ኤአይ ቁጥጥር ካልተደረገበት «ራንከንስታይን ሞንስተር» እየተባለ የሚጠራውን እኩይ ወይም በተለምዶ «ጭራቅ» የምንለው አይነት ገፀባህሪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዕድል እና ፈተና በአፍሪቃ 19.11.2025 11:44
ሰውሰራሽ አስተውሎት በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው።ቴክኖሎጂው ትምህርትን ግላዊነት በማላበስ፣ በቂ አገልግሎት ለሌላቸው ተማሪዎች ተደራሽነትን በማሻሻል በአፍሪካ በትምህርት ላይ በጎ ተጽእኖ እያሳደረ ነው።ያም ሆኖ ቴክኖሎጂውፈተናዎችም አሉት።ባለሙያዎች ፈተናዎቹን ለመሻገር ቴክኖሎጂው የሚገዛበት ፖሊሲዎች ማውጣትን ይመክራሉ።
የዓይን ብርሃንን ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ቴክኖሎጂ 12.11.2025 11:19
የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተመራማሪዎች፤ የእስፒል ራስ መጠን ያላት በጣም ትንሽ ቁስ (ቺፕ) ሬቲና በሚባለው የዓይን ክፍል ውስጥ በመቅበር የዓይን ብርሃንን ለመመለስ ያስችላል የተባለ ህክምና ላይ ሙከራ አድርገዋል። በአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ፣ ኔዘርላንድ እና ጣሊያን በተደረገ ሙከራ ተስፋ ሰጪ ውጤት መገኘቱንም ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።
የኤሎን ማስክ ግሮክፒዲያ ምን የተለዬ ነገር ይዞ መጣ? 05.11.2025 13:07
ቱጃሩ ኤሎን ማስክ፤ በቅርቡ ግሮክፔዲያ ተብሎ የሚጠራ በሰውሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረተ አዲስ የበይነመረብ ኢንሳይክሎፔዲያ ይፋ አድርጓል። ግሮክፔዲያ በጎርጎሪያኑ ባለፈው ጥቅምት 27 ቀን 2025 ይፋ የተደገ ሲሆን፤በአሁኑ ጊዜ 900,000 የሚጠጉ መጣጥፎችን በውስጡ ይዟል።ለመሆኑ አዲሱ ዲጅታል መድረክ ከዊኪፒዲያ በምን ይለያል?
በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሰተኛ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት እንለይ? 29.10.2025 15:38
በሰውሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚፈጠሩ ሀሰተኛ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው።በተለይ ዲፕፌክ የሚባለው ዘዴ ሰዎች ያልተናገሩትን አስመስለው የሚናገሩ፣ያላደረጉትን ድርጊት የሚፈጽሙ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይውላል። ለመሆኑ እነዚህ ይዘቶች ከእውነተኛዎቹ እንዴት መለየት ይቻላል?
የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች 22.10.2025 11:59
ከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔው የሚጎዳ ነው ተብሏል።
የ2025 የኬሚስትሪ እና የፊዚክስ የኖቬል አሸናፊ ግኝቶች 15.10.2025 10:25
የዘንድሮው የኖቬል ሽልማት በኬሚስትሪ ዘርፍ ተፈጥሯዊ የብረት ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ምርምር ላደረጉት ሶስት ሳይንቲስቶች ተሰጥቷል።ይህ ግኝት ብክለትን ለመቀነስ፤በረሃማ በሆኑ አካባቢዎች እርጥበታማ አየርን በመጭመቅ ዝናብ እንዲኖር ለማድረግ፣ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።በፊዚክስ ዘርፍ ደግሞ የኳንተም ሜካኒካል መተላፊያ አሸናፊ ግኝት ሆኗል።
ኢትዮጵያ የኒዩክሌር ኃይል ማመንጫ ያስፈልጋታልን? 09.10.2025 11:11
የኑክሌር ኃይል ለአዳጊ ሀገራት ዕድሎችን እና ጉልህ ተግዳሮቶችን አካቶ የያዘ ነው።የኑክሌር ሃይል ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመደገፍ እና ከካርቦን ነፃ የሆነ አስተማማኝ ኃይል ለማግኘት ይረዳል ። ነገር ግን ማብላያውን ለመገንባት ከፍተኛ ወጭ ይጠይቃል። የሕግ ማዕቀፎችን ፣ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲሁም ትልቅ እና የተረጋጋ የኤሌክትሪክ መረቦችን ይፈልጋል።
የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን? 01.10.2025 9:39
ስለ ጠፈር ቴክኖሎጂ ሲነሳ ብዙ ጊዜ የሚታሰበው ስለጨረቃ እና ማርስ ጉዞ ነው። ከዚህ አኳያ ቴክኖሎጂው በድህነት እና በኋላ ቀርነት ስማቸው ተደጋግሞ ለሚነሳው የአፍሪቃ ሀገራት ቅንጦት ተደርጎ ይታያል።እውን የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን?
የአውሮፓ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ከስራ ያስተጓጎለው የሰሞኑ የሳይበር ጥቃት 24.09.2025 11:57
ካለፈው አርብ ምሽት ጀምሮ በአውሮፓ ታላላቅ አውሮፕላን ማረፊያዎች የመንገደኞችን የመግቢያ ፍተሻ የሚከውኑ የዲጅታል ስርዓቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል።በሂትሮው፣በርሊን እና ብራስልስ አየር ማረፊያዎች የደረሰው ይህ የሳይበር ጥቃት በመያዣነት ወይም በ«ራሰምዌር» የተከሰተ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቋል።
Podcasts similares
Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos