SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 1031 Folgen

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Besuch unbedingt die Website des Podcasts und unterstütze die Macher: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Kategorie

News

Podcast-Website

www.sbs.com.au

Neueste Folge

29. Okt 2026

Wo hören?

Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbar

Podcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts

Bei Google Play herunterladen Kostenlos installieren Android fast 10 Mio. Downloads · Bewertung 4,8 iOS bald

Folgen

"ግጥም ውስጤ ያለውን ስሜት የምገልፅበት፣ አንባቢን በእኔ ዓለም ውስጥ፣ ስሜቶቼ ውስጥ የምጋብዝበት መድረክ ነው" ናዲያ ሞናያ 17.04.2026

በዩኒቨርሲቲ Exeter የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናዲያ ሞናያ፤ ምርምራቸው ስለሚያተኩርበት ለውጥ የሚያሻቸው የሴቶች ጉዳዮችና የመድብለ ባሕል ፋይዳዎችን አንስተው ያናገራሉ። ከግጥም ሥራዎቻቸው በቅርቡ "I Hugged a Tree" በሚል ርዕስ ለአባታቸው ዝክረ መታሰቢያ ከፃፉት የስንኝ ቋጠሯቸው በቅንጭቡ ያስደምጣሉ።

"ከመማር ጋር ኃላፊነት አለ፤ የተማሩትን ለሌላው ማስተላለፍ የራስን ኃላፊነት መወጣት ነው። ለሕይወትም ትርጉም አለው።" ናዲያ ሞናያ 16.04.2026

ናዲያ ሞናያ - በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናቸው። ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያዊት፣ ኤርትራዊትና ጣሊያናዊት ዝንቅ ብሔራዊ ማንነትን አጣምረው ይዘዋል። ሁለት ሀገርኛና አምስት የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው። የውልደት፣ ዕድገትና የትምህርት ሕይወታቸውን ነቅሰው ያጋራሉ።

በአውስትራሊያ ጅሎንግ በሚገኝው የነዳጅ ማጣሪያ የእሳት አደጋ ተከሰት 16.04.2026

የአውስትራሊያ ከተሞች የራሳቸውን የነዳጅ ክምችት ለርመፍጠር ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል አሉ

Women’s legal services in Australia: Understanding your options - በአውስትራሊያ ለሴቶች ነጻ የህግ አገልግሎት ተቋማት አማራጮች እንዳሉ ይረዱ 15.04.2026

Workplace discrimination, gender-based violence and financial inequality—these are just some of the reasons why women need dedicated legal services. You don’t have to navigate the legal system alone. In Australia, free legal services exist to advocate for vulnerable women in ways that are safe, confidential and culturally appropriate. - ሴቶች የተለየ የህግ ባለሙያዎች እንዲያስፈልጋቸው ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ፤ በስራ ቦታ የ...

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቀውስ በጦርነት አይፈታም ፤ መፍትሄው የሰላም ውይይት ነው - አንቶኒዮ ጉተሬዝ 15.04.2026

በሱዳን ከ 21 ሚልዮን በላይ ዜጎች ለጽኑ ረሀብ እና የምግብ እጦት ተጋልጠዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ወኪል አስታወቁ

በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች መሠረታዊ አቅርቦት ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ 15.04.2026

በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ከደቡብ ሱዳን ፤ ኬንያ ፤ ኤርትራ እና ሶማሊያ የተፈናቀሉ ስደተኞች እንደሚኖሩ ተገለጠ

በሺህ የሚቆጠሩ አራናውያን አሜሪካ በሆርሙዝ የጣለችውን ገደብ በቃወም ለሰልፍ ወጡ 14.04.2026

የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የኡበር አሽከርካሪዎች ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ ዋጋ እንዲያስከፍሉ ደንብ ወጣ

"ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችንም የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመሰባሰቢያ፣ ራሳችንን የመጠየቂያ በዓል እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን" ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ 11.04.2026

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የበዓለ ትንሣኤን ትርጓሜ ያስረዳሉ። የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

"እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ አደረሳችሁ! እግዚአብሔር ሀገራችንን ኢትዮጵያንና መኖሪያችንን አውስትራሊያን ይባርክ" ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ 11.04.2026

ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ፤ በዘፀዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አገልጋይ፤ የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የ ‘እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን’ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

"የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብን ሁለቱንም ወላጆች ላጡ ተፈናቃይ ልጆች ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦ እናመሰግናለን" ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ የም/ቤት አባል 10.04.2026

ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ የኤፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በደብረ ብርሃን መጠለያ ቻይና ካምፕ ተጠላይ እናት ሩቂያ አሕመድ ስለ ተፈናቃዮች ሕይወት፣ በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አስተባባሪነት ሁለት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት ስለተደረገላቸው ሰብዓዊ እርዳታ አንስተው ይናገራሉ። ልባዊ ምስጋናቸውንም ያቀርባሉ።

ለጋሽ እጆች ከደቡብ አውስትራሊያ እስከ ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች 10.04.2026

የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ለገሰ ጋረደው፣ የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አቶ ጥላዬ ተከተልና አቶ መሐመድ በያን፤ እንደምን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ከወለጋ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ልገሳቸውን እንደቸሩ ይናገራሉ።

"የኢትዮጵያን ሙዚቃ ካልነበረበት ወደ ነበረበት ያደረስነው በ60ዎቹ ጊዜ ነው" ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ 09.04.2026

የአደራ ቃል "አውስትራሊያ ላላችሁ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከልባችሁ አታውጡ። ምንም ይሁን ምን - እንደ ሀገር የሚሆን ነገር የለም" ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ (ዳግም የቀረበ)

አንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ፤ ከሀገር ቤት እስከ አሜሪካ 09.04.2026

አንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ፤ ገጣሚና ሙዚቃ ቀማሪም ነው። ከሙዚቃ ዓለም አዘላለቁ እስከ ስደት ሕይወቱ አንስቶ ያወጋል። (ዳግም የቀረበ)

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጥቃታቸውን ለሁለት ሳምንታ ሲገቱ፤ ኢራን በበኩሏ ለሁለት ሳምንታት የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ መተላልፊያን እከፍታለሁ አለች 08.04.2026

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ አባል ፕሬዚደንት ትራምፕን ኮንግረስ ከፕሬዚደንታዊና ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥነት ስልጣናቸው እንዲያነሳቸው ጥሪ አቀረቡ

ፋና ወጊዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በ84 ዓመታቸው ከእዚህ ዓለም ተለዩ 08.04.2026

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩና ከ100 በላይ ሰዎችም ለሞት እንዲዳደረጉ ምክንያት ነው ያለውን ተጠርጣሪ ሕገ ወጥ አዘዋዋሪ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

የአውስትራሊያ የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን ተሸላሚ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ተጠርጣሪነት ለእሥር ተዳረገ 07.04.2026

በወርኃ ማርች በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በአውስትራሊያ ታሪክ ከፍተኛውን ሬኮርድ የያዘ የአዲስ ኤክትሪክ መኪና ሽያጭ ተመዘገበ

የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መካከለኛው ምሥራቅ 'ሊጋይ' እንደሚችል አሳሰቡ 06.04.2026

አውስትራሊያ ለተጨማሪ አንድ ወር የሚበቃ የነዳጅ አቅርቦት እንዳላት የፌዴራል መንግሥቱ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአንድ ወር ሲያካሒድ የቆየውን የምርጫ ምዝገባ ለሁለት ሳምንታት አራዘመ 06.04.2026

ኢትዮጵያ በቡድን 20 ማዕቀፍ ስር ከቻይና ያለባትን ዕዳ መልሶ ለማዋቀር ከቻይና መንግሥት ጋር መግባባት ላይ መድረሷ ተነገረ

የመኪና መንዳት ስልጠና ለለማጆች መጀመር ያለበት ከወላጆች፣ ወዳጆች ወይስ ባለሙያ አስልጣኞች? 05.04.2026

"አንዱ ዓላማችን ማኅበረሰቡን ማገልገል ነውና በአቅም ውስንነት የመንጃ ፈቃድ ለሌላቸው አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ነፃ የመኪና መንዳት ስልጠና እንሰጣለን" ያሉት አቶ ግዛቸው መኮንን፤ የፍቅር ለማጅ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ ማሰልጠኛቸው የምሥረታ ዓላማና የአገልግሎት ዘርፎች ይናገራሉ።

"ማኅበራዊ አንቂ መሆን አለብን፤ ሀገራችን ውስጥ ብዙ የሚሠሩ ማኅበራዊ ነገሮች አሉ" ሶስና ወጋየሁ 02.04.2026

ለወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት መሥራችና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዳይሬክተር፤ ላቋቋመችው የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት በሜልበርን- አውስትራሊያ ሚሊኒየም ሃውስ የማኅበረሰብ ማዕከል የተካሔደ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ድጋፍ።

አውስትራሊያ የሃርሙዝ ባሕረ ሰላጤ መተላለፊያን ለመክፈት ዩናይትድ ስቴትስን አግልለው በአስቸኳይ ጉባኤ ላይ ከሚታደሙ 35 ሀገራት ጋር መቀላቀሏን አስታወቀች 02.04.2026

ፕሬዚደንት ትራምፕ የኢራን ጦርነት ለፍፃሜ መቃረቡን ገለጡ

#107 Protecting Wildlife | Talking About Animals and Nature (Med) - #107 የዱር እንሰሳትን መጠበቅ | ስለ እንሰሳትና ተፈጥሮ መናገር 01.04.2026

Learn useful English for talking about animals, nature, and protecting wildlife. Practise everyday phrases for discussing threats to animals, expressing concern, and describing the environment. - ስለ እንሰሳት፣ ተፈጥሮና የዱር እንሰሳት ጥበቃ ጠቃሚ እንግሊዝኛን መናገር ይማሩ። እንሰሳት ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን አስመልክቶ መወያየትን፣ ስጋትን ማመላከትና የተፈጥሮ አካባቢን የዕለት ተዕለት አዘቦታዊ አባባሎችን መግለፅን ይለማመዱ።

ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ ዛሬ ከምሽቱ 7:00 pm የመካከለኛ ምሥራቅ ጦርነትን አስመልክተው ለመላ አውስትራሊያውያን በሬዲዮና ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ንግግር ሊያደርጉ ነው 01.04.2026

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዩናይትድ ስቴትስ፣ እሥራኤል፣ ኢራን ጦርነት ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት ጊዜያት ውስጥ ሊያከትም እንደሚችል አመላከቱ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በረራዎችን በከፊል ማስጀመሩን አስታወቀ 01.04.2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ እንዳለ ገለጠ

"የዳያስፖራ ባንክ አገልግሎት ክፍል ዓላማ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ፍላጎቶችና የባንኩን አቅርቦቶች በማያያዝ ለማገልገል ነው"አቶ ዘሪሁን ተከተል 31.03.2026

አቶ ዘሪሁን ተከተል፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ባንክ ክፍል ሥራ አስኪያጅ፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መካከል የተካሔደውን የመግባቢያ ሰነድ ፍረማ ፋይዳዎችን አንስተው ያስረዳሉ።

Höre den Podcast SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ in Replaio

Radio und Podcasts in einer App - kostenlos und ohne Anmeldung. Installiere sie noch heute und verpasse den Start nicht

Bei Google Play herunterladen

Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet