SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Besuch unbedingt die Website des Podcasts und unterstütze die Macher: www.sbs.com.au
Wo hören?
Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbarPodcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts
Folgen
የብሪስበን 2032 ኦሎምፒክ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በይፋ ይጀመራል 01.06.2026 5:06
የደቡብ አፍሪካ ቡድን በቪዛ ችግር ሳቢያ የሜክሲኮ ጉዞው ተስተጓጉሏል
"በአሜሪካን ሀገር 'ወደ ነጮቹ ነው የንሳበው ወይስ ወደ ጥቁሮቹ?' የሚል ትልቅ ጥያቄ አለ። ስንቶቹ አስበውበታል? ስንቶቹ ችላ ብለውታል?" ዶ/ር ስዩም ገብረእግዚአብሔር 31.05.2026 19:33
ዝክረ መታሰቢያ - ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር፤ የ Symphony of My Life መጽሐፍ ደራሲ፤ ከጎንደር ከተማ ከንቲባነት እስከ ስደት ሕይወት ትረካ (በሕይወት ሳሉ)።
"ሳልጠየቅ፣ ሳልፈቅድ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆነህ ተሹመሃል ተባልኩ። 'እንዴት ይሆናል?' ብዬ ጃንሆይ ዘንድ ቀረብኩ" ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር 31.05.2026 23:51
ዝክረ መታሰቢያ - ዶ/ር ስዮም ገብረእግዚአብሔር፤ የ Symphony of My Life መጽሐፍ ደራሲ፤ ግለ ታሪካቸውን ባሰፈሩበት መጽሐፋቸው በሀገረ አሜሪክ "ኢትዮጵያ PhD ለምን ያስፈልጋታል?" ተብለው 'ሀገሬ እንዴት እንዲህ ትባላለች?' ብለው ትምህርታቸውን እንደምን እንደጨረሱና 'ያለ ፈቃዴ እንደምን ነው የጎንደር ከታማ ከንቲባ ሆኜ የምሾመው?' በሚል ቁጣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት እንደቀረቡ ካወጉት (በሕይወት ሳሉ)።
#111 Water problems at home? |Talking to a plumber (Med) - #111 Water problems at home? |Talking to a plumber (Med) 28.05.2026 10:10
Learn English useful for describing plumbing problems at home. Practise everyday phrases for explaining issues, asking about cost, and arranging repairs. - የመፀዳጃ፣ መታጠቢያና ቧምቧ የመሳሰሉ ቁሳ ቁሶች ችግር ቤት ውስጥ ሲገጥም ዘርዝሮ ለማስረዳት ያስችል ዘንድ እንግሊዝኛን መማር ጠቀሜታ ይኖረዋል። እክሎችን ለማብራራት፣ ዋጋን ለመጠየቅና ጥገናን ለማመቻቸት እያንዳንዱን አባባል በየዕለቱ ይለማመዱ።
"በኢትዮጵያዊነቴ ሁሌ እኮራለሁ፤ ተሸማቅቄ አላውቅም። በአፍሪካ ቀን ስሸለም በወገኖቻችን ከፍ ያለ ድጋፍ በጣም ነው የኮራሁት። የጋራ ክብር ነው።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 27.05.2026 28:54
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የአፍሪካ ቀን የማኅበረሰብ ስኬት ሽልማት ተሸላሚ፤ የሽልማቱን ፋይዳና የማኅበሩን ማኅበረሰባዊ አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል ካሉ ስምንት የምርጫ ጣቢያዎች በስተቀር በተያዘለት የምርጫ መርሃ ግብር መሠረት እንደሚካሔድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ 27.05.2026 10:24
ኢትዮ- ቴሌኮም በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዋዕለ ንዋይ ላይ በይፋ ተመዘገበ
"ወደ አረንጓዴ ምጣኔ ሀብት መሸጋገሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም እንዲያስችላቸው ሊያግዝ ይችላል የሚል እምነት ነው ያለኝ" ዶ/ር ዮናታን ድንቁ 27.05.2026 20:08
ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ ከ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት ጋር የተሰናሰሉ ምክረ ሃሳቦችን ያጋራሉ።
" ሀጅ መሄድ እና በአረፋ ቦታ መቆም ከእስልምና እምነት ምሶሶዎች አንዱ ነው :: " ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 26.05.2026 13:19
ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር ፤ በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ እንዳሉት ፤ አረፋ አደም እና ሀዋ የተገናኙበት ቦታ ሲሆን ፤ ለሀጂ የሚጓዙ ሰዎች አረፋ የተባለው ቦታ ከጠዋት ጀምረው እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰአት ባለው ጊዜ ከዚያ በመሄድ ያሳልፋሉ ። አረፋ ሰፊ ስፍራ ሲሆን በተራራም የታጀበ ነው ። ቦታው የአእምሮ ሰላምን የሚሰጥ የሚያረጋጋ ስፍራ ነው ።
አውስትራሊያ ውስጥ የግል ተመራጭ የምክር ቤት አባላትን ያሰባሰበ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ታስቧል 25.05.2026 4:40
የኢቦላ ወረርሽኝ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ስር እየሰደደ ነው
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀጥታ አካላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈፀሙ የአፈሳና የጅምላ እሥር ድርጊቶች አሁንም አሳሳቢ ሆነው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ አመለከተ 25.05.2026 11:39
ኢትዮጵያ በዜጎቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የሚከታተል የልዑካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደምትልክ አስታወቀች
"ትልቁ የቤት ችግር አቅርቦት ነው እንጂ የፍልሰተኞች ቁጥር አይደለም፤አንደኛና ሁለተኛ ዜጎችን የመፍጠር አዝማሚያ ማኅበራዊ ትስስሮሽ ላይ ችግር ይፈጥራል" ዶ/ር ደሴ ታርቆ 22.05.2026 23:32
ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ የ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖችን አንስተው ያስረዳሉ።
"አባታችን መቼም እንደማይተካ እናውቃለን። በጣም አዝነናል። ለማኅበረሰቡ ምስጋናችን ትልቅ ነው።" ሚካኤል ብርሃኑ 21.05.2026 18:49
ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ለመጨረሻ ጊዜ ለተለዩት የማኅበረሰብ መሪ፣ ቅን አገልጋይ፣ የሶስት ልጆች አባትና መልካም ወዳጅ ዶ/ር ብርሃኑ ወልደኪዳንን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክቶ ልጃቸው ሚካኤል ብርሃኑና የቅርብ ወዳጆቻቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጣሉ። ለዶ/ር ብርሃኑ ቤተሰቦችና የማኅበረሰብ አባላት በሙሉ መፅናናትን ይመኛሉ።
የ2026 የአውስትራሊያ ፌዴራል በጀት ተጠቃሚና ተጎጂዎች እነማን ናቸው? 21.05.2026 15:24
ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ - በአደላይድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህርና ተመራማሪ፤ የ2026 የአውስትራሊያ ዓመታዊ የፌዴራል በጀት ትሩፋቶችንና እንከኖችን ነቅሰው ያመላክታሉ።
የትግራይ ክልልን ለማስተዳደር ዓላማ ያደረገ ነው የተባለለት ጊዜያዊ ምክር ቤት መመሥረቱ ተገለጠ 20.05.2026 9:03
ዳን ጎቴ ለማዳበሪያ ፋብሪካ የመደበውን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረጉን አስታወቀ
"አማርኛ እየተናገረ ትምህርት ቤት የሚገባውም፣ በትግርኛ የሚማረውም፤ በቋንቋህ ፃፍ ስትለው አይችልም። ኦሮምኛውም እንደዚሁ ነው።" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026 17:18
ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህርና "የአማርኛ ሰዋሰው" መጽሐፍ ደራሲ፤ በመጽሐፋቸው ውስጥ ስላነሷቸው የአማርኛ ሰዋሰው አወዳደቅ ሂደትና ደረጃ፣ የሆህያት አጠቃቀምና ጥቅል የቋንቋ ሥርዓተ ትምህርትን አስመልክተው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።
"ቋንቋ የሃሳብ መግለጫ፣ የሃሳብ መመሥረቻ፤ ዐልፎም ሃሳቡን የሚገልፀውን ሰው ማንነት ማሳወቂያ ነው" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026 18:16
ኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም፤ በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህር፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ባሉት "የአማርኛ ሰዋሰው" መጽሐፋቸው አማርኛ ግዕዝንና አገውኛን ተክቶ እንደምን ለቤተ መንግሥት ቋንቋነት እንደበቃ፤ የቋንቋን ውልደትና ሞት ጊዜ ፈጂነት ከሌሎች አንኳር ሃሳቦቻቸው ጋር አያይዘው ይናገራሉ።
"እኔ እንደምገምተው፤ የማናውቀው ጉዳይ ቢኖር የቋንቋን ረቂቅነት ነው" ኢመረተስ ፕ/ር ባየ ይማም 19.05.2026 14:14
በአዲስ አበባና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች የቋንቋ መምህር፤ ኢመረተስ ፕሮፌሰር ባየ ይማም፤ በቅርቡ ለሕተመት ስላበቁት "የአማርኛ ሰዋሰው" መፅሐፋቸውን ትሩፋቶች ነቅሰው ያስረዳሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት የኢቦላ ወረርሽኝን በዓለም አቀፍ አጣዳፊ ክስተትነት ፈረጀ 18.05.2026 5:30
በኩዊንስላንድ ተጨማሪ የቤት ግንባታዎች እንደሚካሔዱ የፌዴራል በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ አስታወቁ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ 10 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ጠየቀ 18.05.2026 9:57
በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች
"ሽሮና በርበሬን ወደ አውስትራሊያ ለማስገባት ሁለት ችግሮች አሉ። አንዱ እኛ ዘንድ ነው፤ ሌላው የጉምሩክ ሰዎች ጋር ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 17.05.2026 14:20
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የበርበሬና ሽሮ ወደ አውስትራሊያ የማስገባት ፈቃድን ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትና የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ዘንድ ያሉ ብዥታዎችን አንስተው ያመላክታሉ። የማኅበሩን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችና ውጥኖችንም ይገልጣሉ።
ለኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእራሳቸው የሆነ የመቃብር ሥፍራ የሚያስፈልጋቸው ስለምን ነው? 17.05.2026 20:59
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ማኅበሩ ስለምን ለኢትዮጵያውያን የሚውል የመቃብር ሥፍራ ለማግኘት ተነሳሽነት እንደወሰደ ያስረዳሉ። የማኅበረሰብ አባላትን አተያዮች ይጠይቃሉ።
ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ መከላከያን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ለመተባበር የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጠ 14.05.2026 8:53
የቻይና በኢትዮጵያ ቀጥተኛ ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ
Tips to manage financial stress | Fuel in Focus - የፋይናንስ የመንፈስ ሁከትን ሚዛን የማስጠበቂያ ፍንጮች | ትኩረት ነዳጅ ላይ 12.05.2026 5:32
Australia's petrol and diesel prices remain under pressure. The RBA’s decision to hike the cash rate this month is adding to the financial strain facing many households. We look at some free and independent support services that are available to help people manage financial stress. - የአውስትራሊያ የነዳጅና ናፍጣ ዋጋዎች ጫናዎች ሳይረግቡ አሉ። የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪም አያሌ ቤቶች ላይ ታካይ የፋይናንስ ሸምቀቆውን አጥብቋል። በፋይናንስ ጭ...
" አባቴ እግዚአብሄር ይባርክህ " - በቅርቡ በሞት የተለየው የአቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ የመጨረሻ የስንብት ቃል እና ሽኝት 11.05.2026 42:57
አቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ ባደረበት ህመም ሳቢያ ሚያዚያ 22 ቀን 2026 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ። አቶ ሰለሞን ወደ አውስትራሊያ ለመጀመሪያ የመጡት የአቶ አዲስ ታምሩ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን ፤ እናቱ ወ/ሮ ሊሊያን ኒኮላስ የአቦርጅናል ዝርያ ያላቸው ናቸው። የጸሎት እና ሽኝት ስነ ስርአቱም በደብረ ሰላም መድሃኒአለም ሜልበርን ቤተክርስቲያን ተከናውኗል። ስርአተ ቀብሩም ሰኞ ሜይ 21 ቀን 2026 በሜልበርን ተፈጽሟል። በሽኝት ስነስርአቱ ላይ በሜልበርን እና በአውስትራሊያ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል ። በስፍራው ከተገኙት መካከልም ፤ መላክ ጸሃይ ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲ...
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት በተመለከተ በአዲስ አበባ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደርን ጠርቶ አነጋገረ 11.05.2026 10:39
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተጨማሪ 9 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ
Ähnliche Podcasts
Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet