SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Besuch unbedingt die Website des Podcasts und unterstütze die Macher: www.sbs.com.au
Wo hören?
Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbarPodcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts
Folgen
በኢትዮጵያ የእሥራኤል አምባሳደር የአፍሪካ ኅብረት የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ ለመዘከር ካዘጋጀው ስብሰባ ተገድደው እንዲወጡ ተደረገ 09.04.2025 8:51
በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ሴቶችን ከማኅበራዊ ተሳትፎ እየገደበ ነው ተባለ
በጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚና የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን መካከል ማምሻውን የመጀመሪያ ዙር የምረጡኝ ዘመቻ ክርክር ይካሔዳል 08.04.2025 2:38
የግሪንስ ፓርቲ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ በተቻለ ፍጥነት የወለድ መጠን ቅነሳ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ
አውስትራሊያውያን የምርጫ ምዝገባ ቀነ ገደብ ሳያከትም ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ወይም የስምና አድራሻ ለውጦቻቸውን እንዲያስታውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ 07.04.2025 6:06
የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ከቤት ውስጥ መሥራትን ለማገድና ከ40ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን ለመቀነስ የነደፈው ፖሊሲ የተሳሳተ መሆኑን አመነ
በኢትዮጵያ ለቤት ሠራተኞች የጡረታ ክፍያ ሊጀመር ነው 07.04.2025 13:16
"ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ፤ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው" በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ
"ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ 03.04.2025 9:22
አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።
#83 Describing menopause symptoms (Med) - #83 Describing menopause symptoms (Med) 03.04.2025 16:15
Learn how to talk about menopause and its symptoms. - Learn how to talk about menopause and its symptoms.
የፌዴራል መንግሥቱ ለሶስት ሚሊየን አውስትራሊያውያን ሠራተኞች ተጨማሪ ደመወዝ ለማስገኘት እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ 02.04.2025 4:33
የተቃዋሚ ቡድን መሪው ዶናልድ ትራምፕን በታሪፍ ጭማሪ ላይ ተገዳድረው እንደሚቆሙ ገለጡ
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትን ያለ ክልሎች ፈቃድ ጣልቃ መግባት የሚያስችል የማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ 01.04.2025 11:33
በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ሥራዎች ለማጠናቀቅ 18 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለጠ
የፌዴራል መንግሥቱ በጀት ይፋ ከሆነ በኋላ የሌበር ፓርቲ የተቃዋሚ ቡድኑን እየመራ መሆኑን የሕዝብ አስተያየት ስብስብ አመለከተ 31.03.2025 7:58
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን እንዳስቆጧቸውና ለሶስተኛ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ለመቀጠል እያሰቡ መሆኑን ገለጡ
በፓስፖርት ድለላ ተሠማርተዋል የተባሉ 65 ተጠርጣሪዎች ተያዙ፤ 25ቱ ሴቶች ናቸው 30.03.2025 13:21
በባሕር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ - ኢትዮጵያውያን ሐዋላ የሚያስተላልፉበት አዲስ የክፍያ ሥርዓት ይፋ ሆነ
Why are we debating Welcome to Country? - በወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የምንሟገተው ስለምን ነው? 30.03.2025 4:29
The government's Welcome to Country spending has been heavily criticised but some believe the cultural protocol is being used as a "political football". - መንግሥት ለወደ ሀገር እንኳን ደህና መጡ የሚያወጣው ወጪ በብርቱ ተትችቷል፤ በተወሰኑቱ ዘንድም ባሕላዊው ፕሮቶኮል ለ"ፖለቲካ እግር ኳስነት" መጠቀሚያ ሆኗል የሚል አመኔታንም አሳድሯል።
" እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ " ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 30.03.2025 10:14
በአገር ቤት ምንም እንኳን የሰላም ስጋቱም ሆነ የኑሮ ውድነቱ ህብረተሰቡን ለስጋት ቢጥልም ፤ የእስልምና እምነት ተከታዪች የረመዳን ጾምን በመረዳዳት አሳልፈው ፤ የኢድ አልፈጥር በአልን በደስታ እያከበሩ ነው ፤ ሲሉ በአገር ቤት የሚገኙት እና በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ የሆኑት ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር ተናግረዋል» በአውስትራሊያ ለሚገኙት የእምነቱ ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አድርሰዋል።
"የተማረ የሰው ኃይል በበቂ ቁጥር አለማግኘትን በተግዳሮት፤ ለችግር ፈቺነት መብቃትን በስኬት እንመለከታለን" ዶ/ር አሥራት አፀደወይን 27.03.2025 43:52
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አፀደወይን "ምርጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆንና ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት መብቃት የዩኒቨርሲቲያችን ርዕይ ነው" ይላሉ። የዩኒቨርሲቲውን 70ኛ፤ የአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፋይዳና ታሪካዊ ምልከታ አንስተው ያስረዳሉ።
ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ የመንግሥታቸው በጀት አማካይ ገቢ ላላቸው አውስትራሊያውያን 2500 ዶላር ያህል እንደሚያስገኝ ሲገልጡ የተቃዋሚ ቡድኑ የግብር ቅነሳውን አልደግፍም አለ 26.03.2025 9:17
ፕሮዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደራቸው ከፍተኛ አመራር አባላት ወታደራዊ ዕቅዶችን በማኅበራዊ ሚዲያ ኧፕ መወያይትን አስመልክቶ ምልከታ እንደሚያደርጉበት አስታወቁ
በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መኪናዎች ኤርትራውያንን ሲያጓጉዙ የተገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእሥራት ተቀጡ 25.03.2025 10:28
የኢትዮጵያ የግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያስመጡ ተፈቀደላቸው
"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤታችን ወደ ቀድሞ ስሙ 'ተፈሪ መኮንን' እንዲመለስ አፅድቋል፤ ትልቅ ደስታ ላይ ነው ያለነው" ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ 24.03.2025 20:54
ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ፤ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበር ሰብሳቢ፤ የአሁኑ የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ወደ መሠረተ ስያሜው ተፈሪ መኮንን እንዲመለስ የመወሰኑን ታሪካዊ ፋይዳዎችና የትምህርት ቤቱን 100ኛ ዓመት ለማክበር እየተደረጉ ስላሉ መሰናዶዎች ይናገራሉ።
ብርቅዬዎቹ የኢትዮጵያ ቅርስ ዋሊያዎች በሕገወጥ አደን ለምግብነት እየዋሉ መሆኑና ቁጥራቸውም አሽቆልቁሎ 300 መድረሱ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጠ 23.03.2025 13:42
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠች
የደብረ ዘይት በአል ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት የሚታዩ ምልክቶችን በተራራው ስብከቱ ያስተማረበትን ለማስታወስ የሚከበር በአል። " 23.03.2025 17:49
ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ የተነበያቸው ትንቢቶች በአብዛኛው እየታዩ ናቸው፤ የትንቢቱ መፈጸሚያዎች እንዳንሆን ወደ ንሰሀ መመለስ ይኖርብናል፤ የሚሉን በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ አገልጋይ የሆኑት መጋቢ ሓዲስ ብሩክ ተስፋዬ ናቸው ።
"መሬት ከፖለቲካ ወጥቶ ለኢኮኖሚው መሆን አለበት፤ አለመታደል ሆኖ የብሔር ፖለቲካ ከመሬት ጋር ተጣብቆ ተያይዟል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 22.03.2025 17:29
ዶ/ር ዳንኤል ካሣሁን - በኦስተን ኮሌጅ የጂኦ ስፔስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ የመሬት ለአራሹ አዋጅ ግማሽ ክፍለ ዘመን መድፈን አስባብ አድርገው "የመሬት ለአራሹ አዋጅ፤ ዋዜማ፣ መባቻ፣ እና ማግሥት" በሚል ርዕስ ሰሞኑን ለሕትመት ስለአበቁት መጣጥፋቸው አንኳር ጭብጦች ያስረዳሉ።
ማኅበረሰባዊ የስንብት ቃል፤ "የዶ/ር እንግዳ ሕልፈት ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ትልቅ ጉድለት ነው" አቶ ሰለሞን ወንድሙ 21.03.2025 18:50
በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩት ዶ/ር እንግዳወርቅ ለማ ዘላለማዊ ዕረፍት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ ጥልቅ ሐዘንን አሳድሯል። የቅርብ ጓደኞቻቸውና ብቸኛ ልጃቸው ጥልቅ የሐዘን ስሜታቸውን ይገልጣሉ። የዶ/ር እንግዳወርቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ መጋቢት 13 / ማርች 22 በ Bulla Cemetery ዕኩለ ቀን ላይ ይከናወናል።
Cultural burning: using fire to protect from fire and revive Country - ባሕላዊ እሳት ልኮሳ፤ እሳትን በእሳት የመከላከል አጠቃቀምና ሀገራዊ ትድግና 20.03.2025 10:08
Did you know that Indigenous Australians have been using fire to care for the land for tens of thousands of years? Evidence show that cultural burning practices not only help reduces the intensity and frequency of wildfires but also plays a vital role in maintaining healthy ecosystems. Experts share insights on the latest evidence behind this ancient practice. - የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ለአሥር ሺህ ዓመታት ያህል ለ...
#82 Describing taste (Med) - #82 Describing taste (Med) 19.03.2025 15:36
Learn how to describe the taste of food. - Learn how to describe the taste of food.
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 'በትግራይ ክልል ለሰላም ስምምነቱና ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ስጋት የሆነው ውጥረት' በሰላም እንዲፈታ ሲል አሳሰበ 18.03.2025 12:30
ለኢትዮጵያ የሚዲያ ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ምክረ ሐሳብ ቀረበ
" 'አፊኒ' ዕርቅ ማውረጃ፣ ግጭቶችን መፍቻና ቅድመ ግጭቶችን መከላከያ የሲዳማ ባሕላዊ ዕሴት ነው" አቶ ጃጎ አገኘሁ 18.03.2025 19:01
አቶ ጃጎ አገኘሁ፤ የሲዳማ ክልል የባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፤ ሰሞኑን በቢሯቸው ተደግፎ በ21ኛው New African Film Festival ላይ ቀርቦ ስላለው "አፊኒ" ፊልም ፍቺ፣ ጭብጦችና ስኬቶች ይናገራሉ።
የዘንድሮው የአውስትራሊያ በጀት የተረፈ ፈሰስ ጉድለት እንደሚኖረው ተመለከተ 17.03.2025 6:40
የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ የግብር ቅናሽን የምርጫ አጀንዳው ለማድረግ ከውሳኔ ላይ አለመድረሱን ገለጠ
Ähnliche Podcasts
Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet