DW

ዜና መጽሔት

News AM ↓ 206 avsnitt

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።

Glöm inte att besöka poddens webbplats och stötta skaparen: www.dw.com

Skapare

DW

Kategori

News

Poddens webbplats

www.dw.com

Senaste avsnittet

27 nov 2026

Var kan du lyssna?

Poddar i appen Replaio Radio Kommer snart

Poddar kommer snart till appen. Installera nu och bli först med att uppleva ett helt nytt sätt att lyssna på poddar

Ladda ned på Google Play Installera gratis Android 10 mn+ nedladdningar · betyg 4,7+ iOS snart

Avsnitt

የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ዜና መጽሔት 29.09.2026

የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በተፈናቃዮችና በየአካባቢዉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ያደረሰዉን ጉዳትና መከራን በሁለት ዘገቦች ይቃኛል። የኦሮሚያ ክልል 21 የአስተዳደር ዞኖችን ወደ 6 ዞኖች ማጠፉን የሚቃኘዉ ዘገባ አሠልሶ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 81ኛ ጉባኤና የድርጅቱ ፋይዳ ቢሲስነት በሚተነትነዉ ያሳርጋል።

የመስከረም 18 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄት 28.09.2026

በዛሬው የዜና መፅሄት በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በተቀሰቀሰው ውጊያ ላይ የጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። የኦሮሚያ ምክር ቤት ዛሬ አዲስ ክልላዊ መንግሥት መሥርቷል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሬዝደንትነት ሲቀጥሉ ስድስት ምክትሎች ተሾመውላቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቅ የተመለከቱዘገባዎችም ተካተዋል

News Magazine 250926 - MP3-Stereo 25.09.2026

ዜና መጽሔት ከሚያስቃኘን መካከል - የባልስልጣናት እስርና ዕገዳ በትግራይ - በትግራይ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቋረጡ - ጦርነት ኤርትራንና ሱዳንን ያሳትፍ ይሆን? - ጦርነቱ የሚያስከትለዉ ሰብዓዊ ቀዉስ ምን ሊሆን ይችላል? - ኤርትራዊ ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሀቅ 25 ዓመታት በኤርትራ እስር ቤት የሚሉት ይገኙበታል።

የመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 24.09.2026

የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላይ የሚያተኩሩ ዘገባዎች ተካተዋል። -የአፋር ክልል «አሸባሪ» ባለው የህወሓት ጦር ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ማለቱ - የፀጥታው መናጋት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች -ጦርነቱ ሺዎችን ማፈናቀሉ እና የቀረበው የምግብ ድጋፍ ጥያቄ -የአውሮጳ ህብረትና ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ጥሪን ይመለከታል

የመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 23.09.2026

የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይላት እና የትግራይ አማጽያን ውጊያ፤ የትግራይ ክልል አለመረጋጋት፤ የአየር በረራው መቋረጥ፤ አፋር ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት ኃይላት እና በሕወሓት መካከል ውጊያው ቀጥሏል መባሉ፤ ቃለ መጠይቅ፤ በርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪ ላይ ደረሰ የተባለ የድሮን ጥቃት እንዲመረመር መጠየቁ

የዜና መፅሔት፤ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 22.09.2026

ትብብር ለህልውና የተባለው የታጣቂዎች ቡድን ምስረታ ላይ አስተያየቶች ፤ ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በርካታ ተጎጂዎች ጋምቤላ ውስጥ ወደሚገኘው የህክምና መስጫ መምጣታቸውን መግለፁ፤ በሶማሊያ የአፍሪካ ኀብረት ተልዕኮ የሚደረገው ድጋፍ በአንድ አመት መራዘም መጠነኛ እፎይታ እንደሚሰጥ መነገሩ

የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 21.09.2026

በዜና መጽሔት አስተያየት ሰባት ታጣቂ ኃይላት መንግሥትን ለመጣል የፈጠሩት ትብብር በራያ አካባቢ የወታደራዊ ውጥረቱ ማይልና ተፈናቃዮች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዎች የጥቃት እና እገታ ሥጋት እና በበርሊን እና በሜክለንቡርግ ፎርፖመርን ግዛቶች የተካሄደዉ ምርጫ ዉጤትና የመራኄ መንግስቱ እጣ ፈንታን ያስቃኛል።

የመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት 18.09.2026

በኢትዮጵያ ከተካሄደ 20 ዓመታትን የደፈነው የህዝብና ቤት ቆጠራ -በአማራ ክልል ዘንድሮ 4.9 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበዋል መባሉ -የኢትዮጵያዉያንና የኤርትራዉያን ስደተኞች ችግር በዩጋንዳ የናይል እና ቀይባህር ስልታዊ መድረክ ምስረታ- በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኀብረት የሁቲ አማጺያን የፈፀሙትን ጥቃት ማዉገዙ፤

የመስከረም 6 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 16.09.2026

የዜና መጽሔት እስረኞችን በምህረትና በይቅርታ የመልቀቅ ሕጋዊ ማዕቀፍን የሚያስቃኘው ዘገባ ይቀድማል ። ድርቅ በአማራ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች ያስከተለውን ጉዳት፣ኤልኒኖ ሌላው የግብርና ምርት ተግዳሮት፣ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የጉዞ አቅም ከዓለም የመጨረሻዎቹ ተርታ መመደቡ ላያ ያተኮሩ ዘገባዎችም ተሰናድተዋል

የመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መጽሔት 15.09.2026

ትግራይ ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ሌላ አካባቢ እንዲመደቡ መወሰኑና የክልሉ ተቃዉሞ። የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚኒስቴር የ2019 የትምህርት ዘመን የሬሜዲያል መርሐ ግብር።

የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 14.09.2026

በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ አዲስ ከሚመሰረተዉ መንግሥት ምን ይጠበቃል? በኮንሶ ምንድን ነው የሆነው ?በዋግህምራ በግጭትና ድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተሰደዱ ነውä፣በህንድ የተካሄደው የብሪክስ ጉባኤና የኒውዴልሂዉ መግለጫን አካቷል።

የአዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት 11.09.2026

እንቁጣጣሽ፣ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ አሮጌውን 2018 ዓ.ም.ሸኝታ አዲsune 2019 ዓ.ም ተቀበለች። በ2018 ግጭት፣ አለመረጋጋትና የኑሮ ውድነት የተፈታተናቸው ኢትዮጵያውያን በአዲሱ ዓመት ለውጥ ይናፍቃሉ። የተሻለ ሕይወት ይመኛሉ። የዶቸ ቬለ ዘጋቢዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የላኳቸው ዘገባዎች ይቀርባሉ።

የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት 10.09.2026

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ዘና መጽሔት ዘገባችን፦ -ፖለቲከኛ ክርስቲያን ታደለን እና በርካታ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በዛሬው እለት ከእስር መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐሳውቋል። ይህና -ግጭት ያጠላበት የአዲስ አመት አከባበር በአማራ ክልልና ሌሎችም ዘገባዎች አካትተናል ።

የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዜና መጽሔት 09.09.2026

በትግራይ ክልል በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መኖሩን ህወሓት መግለፁ፤ በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት የጸጥታ ችግር ያስከተለው ስጋት፤ በአላማጣ ከተማ ይፈጸማል የተባለው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ፤ የመስቃን እና ማረቆን ሰላም ለመመለስ የተደረገውን ጥረት እንዲሁም የአሜሪካ እና ኢትዮጵያን የኤኮኖሚ ጉድኝት የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል።

የዜና መጽሔት፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓም ማክሰኞ 08.09.2026
የጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 07.09.2026

የትግራይ ክልል በኦባሳንጆ የአሸማጋይነት ሚና ላይ የገለልተኝነት ጥያቄን ማንሳቱ፣ ቻይና በአባይ እና ቀይባህር ላይ የግብጽን አቋም መያዟ ለኢትዮጵያ ስጋት ነውን?የኤልኒኞ ክስተት ተፅዕኖ በሶማሌ ክልል ያሳደረዉ ስጋት፤ ፖሊስ የዋስትና መብት በተፈቀደላቸው የኢሕአፓ አመራሮች ላይ ይግባኝ ጠየቀ

የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት 04.09.2026

በራያ እና በአላማጣ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ርሃብ፣ ድርቅ እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተዳርገናል ሲሉ አማረሩ። ደብዛው የጠፋው የፎቶግራፍ ባለሙያ ፊልሞን ገብረሕይወት የት እንዳለ ይፋ እንዲደረግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ ። በእሥር ላይ ለሚገኙት የኢሕአፓ አመራሮች የዋስትና መብት መፈቀዱ፣

የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት 03.09.2026

በዛሬው መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪቃ ህብረት የምታበረክተውን የገንዘብ አስተዋጽዖ በእጥፍ ለማሳደግ መፈለጓ ፣ ህወሃት በፌደራል መንግስት ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው ማለቱ፣ በኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ ላይ የአብን መግለጫ እና አንድምታው፣ የተሰኙ ዘገባዎች በትንታኔ ይደመጣሉ።

የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዜና መፅሔት 02.09.2026

የዜና መጽሔት የምስራቅ ወለጋ ዞን አንጌር ጉቴ አከባቢ ግጭትና ግጭቱ ያፈናቀላቸው ሰዎች ብሶት በጃናሞራ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ መዳረጋቸው መነገሩ፣ በጋምቤላ የምርት መቀነስን ለማካካስ መስኖ እንደማራጭ መያዙ፣ጀርመን በሀገርዋ የሚገኙ የተለያዩ የሩስያ ተቋማት እንዲዘጉ መወሰኗ ላይ ያተኮሩ ቅንብሮች ይቀርባሉ።

የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 01.09.2026

የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤን ከነሒደቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉድቅ ማድረጋቸዉ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሠላም እንዲሰፍን በተደጋጋሚ የሚደረገዉ ጥሪና ዉጤቱ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የመሬት መንሸራተት ያደረሰዉ ጉዳትና አልርጀንቲናዊዉ የእግር ኳስ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጡረታ መዉጣቱን ያስቃኘናል።

DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 ዜና መጽሔት 31.08.2026

በባቲ ወረዳ «የኦነግ ሸኔ» ጥቃት፣ እገታና መፈናቀል ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ምሬት መዳረጉ፤ ግጭት ማስወገድ የተሳናቸው የአፍሪካ ኀብረት መዋቅሮችና የማሻሻል ሂደቶች፤ በአሜሪካ እና ካናዳ መካከል ያገረሸው የንግድ ጦርነትና የዲፕሎማሲ ውጥረት፤ አይስላንድ ለግዜው ወደ አውሮጳ ህብረት ላለመግባት ወሰነች

የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዜና መፅሄት 28.08.2026

የዛሬው የዜና መፅሄት-ዛሬ ችሎት የነበሩት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች ለመጪው ሐሙስ መቀጠራቸዉ ፤, በኦሮሚያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ምስራቃዊ ወረዳዎች የቀጠለዉ ጥቃት፤ በአፋር ክልል የክረምት ዝናብ መቅረትና የቀረጥ ጭማሪ የአርብቶ አደሩን ህይወት መፈተኑ፤ በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ለማኅበረሰባቸው በጎ የሰሩ ግለሰቦች ተሸለሙ የተሰኙ አምስት ርዕሶችን አካቷል።

የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ 27.08.2026
የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና የዜና መፅሄት 26.08.2026

ከዓለም ዜና በኋላ በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የመቀሌ ጉብኝት ያመጣው አዲስ ምክረሃሳብ የለም ማለታቸው፤በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የኦባሳንጆን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው መግለፁን፣ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ሰዎች ገድለው፤ ንብረት ስለማውደማቸው እንዲሁም በአላማጣ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ከባድ የእህል እና የገንዘብ መዋጮ በግዴታ እየተጠየቅን ነው ማለታቸውን የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።

የነሐሴ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መፅሔት 25.08.2026

የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የዛሬዉ የመዉሊድ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት መሪዎችን እንደገና ለመሸምገል የጀመሩትን ዲፕሎሲ የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ሥለ ዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት የተጠናቀረዉ ያሰልሳል።ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በተከፈቱ ጥቃቶችና ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛትና ጥያቄን የሚዳስስ ዘገባም አለን።

Lyssna på podden ዜና መጽሔት i Replaio

Radio och poddar i en och samma app - gratis och utan konto. Installera redan idag och missa inte premiären

Ladda ned på Google Play

Replaio är ingen poddutgivare; programnamn, omslag och ljud tillhör sina upphovspersoner och distribueras via offentliga RSS-flöden