SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au
Unde asculți?
Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curândPodcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor
Episoade
"ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች!"ተወዳጅ ሚዲያና የአንጋፋ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዕውቅናና ምስጋና 26.12.2024 22:48
ዕዝራ እጅጉ፤ የተወዳጅ ሚዲያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የ"ታላላቆቻንን እናክብር" የዕውቅናና ምስጋና ሽልማት ተሽላሚ ስለሆኑት 13 አንጋፋ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጉልህ ሥራዎችን በማጣቀስ የውርሰ አሻራዎቻቸውን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ፋይዳዎች ያስገነዝባል።
" እንኳን ለፈረንጆቹ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ " - ዶ/ር ግርማ ሞላ 25.12.2024 2:02
ዶ/ር ግርማ ሞላ የኢትዮጵያን እናድን ሰብሳቢ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውን የፈርንጆቹን የገና በዓል እንዲሁም የመጪውን አዲስ ዓመት እና የኢትዮጵያን ገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡
ቪክቶርያ ከ2019 በኋላ ከፍተኛ በተባለ የእሳት አደጋ ስጋት ላይ ወድቃለች ተባለ 25.12.2024 7:41
ከአውስትራሊያ ውጭ አገራቸውን በማገልገል ላይ ያሉ የጦር ኃይል አባላት የገና በዓልን አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላለፉ
ከመተሀራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ 25.12.2024 7:25
ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የአፍሪካ የቀረጥ ነፃ አገራት ዝርዝር ዳግም መመለስ አልቻለችም
"ለP2P 25ኛ ዓመት የደረስነው ትኩረታችንን ጎሣ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ላይ ሳይሆን ሳይማር ያስተማረን ሕዝባችን ላይ በማድረግ ነው" ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ 24.12.2024 19:44
ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ፤ የPeople To People Inc (P2P) የቦርድ ሊቀመንበርና ዶ/ር እናውጋው መሃሪ፤ የPeople To People Inc (P2P) መሥራችና ፕሬዚደንት፤ የP2Pን የ25 ዓመታት የሕክምና መስክ ዋነኛ አስተዋፅዖዎችና የወደፊት ውጥኖች አንስተው ይናገራሉ።
"የ P2P አነሳስ 'የሰዎች ችግር፤ በሰዎች ይፈታል' በሚል ዕሳቤ ነው" ዶ/ር እናውጋው መሃሪ 23.12.2024 14:37
ዶ/ር እናውጋው መሃሪ፤ የPeople To People Inc (P2P) መሥራችና ፕሬዚደንት፤ ዶ/ር አንተነህ ሀብቴ፤ የPeople To People Inc (P2P) የቦርድ ሊቀመንበር፤ የሩብ ክፍለ ዘመን የአገልግሎት ዓመታትን ስላስቆጠረው P2P ጅማሮና አስተዋፅዖዎች ያስረዳሉ።
አዲስ አበባ ለመኖር ውድ ከሆኑ ከተሞች መካከል ተካተተች 23.12.2024 10:57
'ሕወሓት ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው' ሲሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመላከቱ
ሶርያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ የተርኪዬ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠየቁ 23.12.2024 7:35
በቪክቶሪያ ለተከሰተው የሰደድ እሳት በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ በሚታየው የአየር ለውጥ ሳቢያ ሊባባስ እንደሚችል ተነገረ
"የኢትዮጵያ ቀን ግብዣችን ለሁሉም ነው፤ እኛ ኢትዮጵያዊነትን አንሰጥም፤ አንነፍግም" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 23.12.2024 15:43
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ዲሴምበር 28 / ጥር 20 በሜልበርን - አውስትራሊያ ተከብሮ ስለሚውለው የኢትዮጵያ ቀን ፋይዳዎች ይናገራሉ። ግብዣቸውንም በማኅበሩ ስም ያቀርባሉ።
"በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም እንኳ ኢትዮጵያ ስትጠራቸው እጅግ የሚያኮራ ድጋፍ ማድረጋቸውን እናደንቃለን" ሚ/ር ጫልቱ ሳኒ 20.12.2024 19:29
ጫልቱ ሳኒ፤ የኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው፣ የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘርፈ ብዙ የሀገር ግንባታ ሁነኛ ሚናዎችና ተጠቃሚነትን ይገልጣሉ።
"የአውስትራሊያ ከተሞችን በመጎብኘት ለከተሞቻችን የበለጠ ዕድገት፣ ውበትና ምቹነት የሚያግዙ መሠረታዊ ነገሮችን ለመቅሰም ዕድል አግኝቻለሁ" ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ 20.12.2024 20:38
ጫልቱ ሳኒ፤ የኢፌዴሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር፤ ሰሞኑን አውስትራሊያ ተገኝተው ስላካሔዱት ይፋ የሥራ ጉብኝት ዓላማና ፋይዳዎች ይናገራሉ።
"ፍቅር ዘላለማዊ እንዲሆን እንመኛለን፤ ዘላለማዊ እንዳልሆነ እያወቅን፤ የፍቅርን ጅማሬ እንጂ መጨረሻውን አናውቅም" ደራሲት ከበደች ተክለአብ 19.12.2024 15:34
ደራሲት ከበደች ተክለአብ ሰሞኑን በቀይ ባሕር ፕሬስ ለሕትመት ስላበቋቸው "የት ነው?" እና "ሱታፌ" መፅሐፍት ይዘቶች ይናገራሉ፤ ያስደምጣሉ።
"በልዩነት መሃል የሰውነትን ሰብዓዊነት መገንዘብ ትልቅ ነገር ነው፤ በጥቃቅን ነገሮች መስማማት ከቻልን በትልቁም መስማማት እንችላለን" ደራሲት ከበደች ተክለአብ 19.12.2024 18:20
ደራሲት ከበደች ተክለአብ ሰሞኑን በቀይ ባሕር አሳታሚ በኩል ለአንባብያን እነሆኝ ስላሏቸው "የት ነው?" እና "ሱታፌ" መፅሐፍት ጭብጦች ይናገራሉ። ከሥነ ግጥሞቻቸው መካከልም ነቅሰው ያስደምጣሉ።
Summer listening: Into the bush | Let's go bushwalking (Adv) 18.12.2024 13:39
Learn how to talk about bushwalking. Plus find out tips on how hikers can stay safe and have fun.
"የት ነው?" ገጣሚት፣ ደራሲትና መምህርት ከበደች ተክለአብ 18.12.2024 12:54
በሥነ ግጥም፣ ቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎች ዘርፍ ስመጥር ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆኑት ከበደች ተክለአብ፤ ዳግም ለሕትመት ስላበቁት "የት ነው?" መፅሐፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን አዲስ ስላሳተሙት "ሱታፌ" መፅሐፍ ይዘት ያስረዳሉ፤ ከግጥሞቻቸውም ጥቂቶቹን በአንደበታቸው ያስደምጣሉ።
Are gambling organisations targeting CALD communities? - የቁማር ድርጅቶች ባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ ማኅበረሰባትን ዒላማቸው አድርገዋልን? 17.12.2024 7:35
Australians lose $32 billion a year to gambling — more per person than any other nation. And it’s affecting diverse communities differently. - አውስትራሊያውያን በዓመት በቁማር 32 ቢሊየን ዶላር ያጣሉ፤ በግለሰብ ደረጃ ከማናቸው አገር በበለጠ። በተለየ ሁኔታም ዝንቅ ማኅበረሰባቱ ላይ ጉዳትን እያስከተለ ነው።
Summer listening: Into the bush | Let's go fishing! (Med) 16.12.2024 16:52
Learn how to talk about fishing. Plus, find out a bit of history on why Australians love fishing.
ጉዞ ወደ አውስትራሊያ፤ "ባለ ጋቢው" ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ 16.12.2024 21:50
ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ፤ ሜልበርን - አውስትራሊያ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 በሚካሔደው 28ኛው ዓመታዊው የእግር ኳስ ውድድርና የኢትዮጵያ ቀን ክብረ በዓል ላይ ይገኛል። የሕይወት ጉዞውን ከጠዳ እስከ አውስትራሊያ አንስቶ ያወጋል።
"በ13ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ብሔረሰቦች መካከል አርጎባ ነበር" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ 12.12.2024 28:53
ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ፤ የ"ኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፍ ደራሲ፤ በኩሽና ኩሻዊነት ዙሪያ ያሉ ብዥታዎችን ያመላክታሉ። የማረቂያ ምክረ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።
በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ ዕውቅናና ውክልና ያላቸው 76 ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ናቸው ተባለ 11.12.2024 11:01
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያውን ደብር ሰየመች
"የጥንቱ የኩሽ ሀገረ መንግሥት ከአሁኑ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር ምንም ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም" ዶ/ር ግርማ ደመቀ 10.12.2024 14:02
ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ ሰሞኑን ለሕትመት ስላበቁት "የኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፋቸው ጭብጦች ያስረዳሉ።
"ካለፈው ዓመት ዘንድሮ አንድነታችንን አጠንክረናል፤ ኢትዮጵያውያንን አነቃቅተናል" ወ/ት ገነት ማስረሻና አቶ አሕመድ ዳውድ 09.12.2024 11:10
ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና አቶ አሕመድ ዳውድ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ንብረት ኃላፊ ዘንድሮ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 ስለሚካሔደው 28ኛው የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር መሰናዶና ሂደት ይናገራሉ።
ኢሰመኮ በኦሮሚያ አካባቢ የግዳጅ ምልመላ የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ እንደሚገባ አሳሰበ 09.12.2024 14:24
አምስቱ የቦብ ማርሌይ ልጆች የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በወርኃ ግንቦት ሊካሔድ ነው
"ትንሽ ፊደል ቀመስን በሚለውም ውስጥ ኩሽና ኩሻዊነትን በተመለከተ ማደናገር አለ" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ 08.12.2024 15:15
ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ የሥነ ልሳን ተጠባቢ ናቸው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ታሪክ ዙሪያ የምርምር ግኝቶችን ያካተቱ ደርዘን የተጠጉ መፅሐፍትን ለሕትመት አብቅተዋል። ሰሞኑንም በኩሽ ዙሪያ በውዥንብር የታጨቁ ዕይታዎችን ለማጥራት በሚል ሙያዊ ኃላፊነት ዕሳቤ "ኩሽ እና ኩሻዊ" በሚል ርዕስ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ የፈጀ ጥናታዊ ሥራቸው የተካተተበትና የሁለት ዓመታት የጽሕፈት ጊዜያትን የወሰደባቸውን የአዕምሮ ጭማቂ የመጽሐፍ በረከታቸውን ለአንባብያን እነሆኝ ብለዋል። ከዶ/ር ግርማ ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ በእዚሁ አልተቋጨም። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን የኩሽ ነገድ፣ ሀገረ መንግሥትና የመፅሐፍ ቅዱስን የኩሽ አጠቃቀም አንስተው...
"ኔልሰን ማንዴላን ከአንድ ሳምንት በላይ አስታመናል፤ ከእሥር ነው የወጡት ምንም የላቸውም በሚል 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሰጥቻለሁ" የቀድሞው ፕ/ት መንግሥቱ ኃ/ማርያም 05.12.2024 14:15
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የSBS አማርኛ እንግዳ ሆነው ለሁለት ጊዜያት ቀርበዋል። በቀዳሚነት ለደቡብ ሱዳን ነፃነትና ሉዓላዊነት የኢትዮጵያን አስተዋፅፆዎች በማስረዳት፤ ዳግም "ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት ኮከብ ሆና እንደኖረችና ከልጅነት ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲያስቡ፣ ኢትዮጵያን እንደ ተስፋ ሲመለከቱ የኖሩ ሰው መሆናቸውን፤ በሂደትም የተገነዘቡትና ያዩትም ይህንኑ መሆኑን" ከእሥር እንደተፈቱ ያወጓቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ ዲሴምበር 5, 2013 የዛሬ 11 ዓመት ከእዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስመልክተው። የማንዴላን ዝክረ መታሰቢያ አስባብ አድርገን ቃለ ምልልሱን ደግመን አ...
Podcasturi asemănătoare
Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice