SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categorie

News

Site-ul podcastului

www.sbs.com.au

Cel mai nou episod

18 nov. 2026

Unde asculți?

Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curând

Podcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor

Descarcă din Google Play Instalează gratuit Android 10 mil.+ descărcări · nota 4,7+ iOS în curând

Episoade

በሜልበርን የጥምቀት በአል እንዴት አለፈ ? በካህናት ዕይታ 19.01.2025

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤እንዲሁም መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ አባተ፤ በምሥራቅ አውስትራሊያ አኅጉረ ስብከት የሜልበርን ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በካህናቱ እና ምእመናኑ የጋር ሥራ የተዋጣለት በዓል እንደነበረ ተናግረዋል ።

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ ኢትዮጵያን ከራሷ ልጆች ማን ያድናታል? 19.01.2025

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።

"እንኳን ለበአለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ።"- ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ 17.01.2025

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ ጥምቀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሀንስ እጅ መጠመቁን የምታዘክረበት በአል ነው ብለዋል ።

የጥምቀት ዋዜማ፤ የሙዚቃ ድግስ በሜልበርን 17.01.2025

አንጋፋውን ድምፃዊ ሻምበል በላይነህን ማዕከል ያደረገ፤ በሜልበርን ምርጥ ድምፃውያንና ሙዚቀኞች የታጀበ የሙዚቃ ድግስ ምሽት ስለመሰናዳቱ አስተባባሪው አቶ አበራ አያሌውና የጥበብ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

"ሕዝቤ የማያውቀውንና ከሕይወቱ ጋር ግንኙነት በሌለው የባዕዳን ሀገር ዕውቀትና ሀብት ራሴን ትልቅ አድርጌ ለማቅረብ የምሞክር ዘመናዊ ደንቆሮ አይደለሁም" ዶ/ር ይርጋ ገላው 16.01.2025

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።

"የተራቡትን ይመግብልን፣ የተበተኑትን ይሰብስብልን፣ በዓላችን የታይታ ሳይሆን የክብር በዓል ይሁንልን" መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ 15.01.2025

መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ ተስፍዬ፣ የደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ዜናዊ ቸኮል፣ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ መል አከ ሕይወት ቀሲስ ሰናይ ዜና፣ የመካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ በዓለ ጥምቀት የሚከበርበትን ዋነኛ ምክንያትና ፋይዳዎች አንስተው ይናገራሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥትና ታጣቂ ኃይሎች መካከል በየትኛውም ሥፍራ ንግግር እንዲደረግ ለመደገፍ ዝግጁነቷን ገለጠች 15.01.2025

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለስልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሾመለት

"ሰንደቁን እንደ አንድ ዋርካ ነው የምናየው፤ ሰውን በዘሩ፣ በሃይማኖቱ የማያርቅ ሰው ነው ያጣነው" አቶ መስቀሉ ደሴ 14.01.2025

አቶ ሰንደቁ ተሰማ፤ በምዕራብ አውስትራሊያ - ፐርዝ ከተማ በታክሲ አገልግሎት ሥራ ላይ ተሠማርተው ሳለ፤ በፖሊስ ገለጣ መሠረት ሆን ብሎ መንገድ አሳብሮ በመጣ መኪና በደረሰባቸው የግጭት አደጋ ከጫኗቸው ሁለት ተሳፋሪዎቻቸው ጋር በ58 ዓመታቸው ከባለቤታቸውና ሶስት ልጆቻቸው ተነጥለው ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

"በዓለ ጥምቀት በሃይማኖትም፣ በማኅበራዊም፣ እንዲሁም፤ ባሕልን አስጠብቆ ለትውልድ ለማውረስ ትልቅ ፋይዳ አለው" ቀሲስ አንተነህ ወርቁ 14.01.2025

ቀሲስ አንተነህ ወርቁ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ዲያቆን ዳዊት ይርጉ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ፤ ስለ ዘንድሮው የሲድኒ በዓለ ጥምቀትና በዓለ ጊዮርጊስ አከባበር መርሃ ግብሮችና ትሩፋቶች ይገልጣሉ።

ኢትዮጵያና ሶማሊያ አዲስ አበባና ሞቃዲሾ ላይ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ውክልና ለማድረግ ተስማሙ 12.01.2025

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደገና እንዲዋቀር ተጠየቀ

"ኤርምያስ ወንድሙ ከመሀል ሜዳ መትቶ ያስቆጠራት ግብ ዛሬ ድረስ ባልንጀሮች ሆነን እንድንቀር መንሰአኤ ናት ።" - ሻምበል በላይነህ 09.01.2025

ድምጻዊ ሻምበል በላይነህ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ኤርሚያስ ወንድሙ ሩብ ምእተ አመት ያስቆጠረው የጓደኝነታቸውን ትሩፋት አጫውተውናል ።

ሶስና ወጋየሁ፤ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሀገረ አውስትራሊያ 09.01.2025

ሶስና ወጋየሁ፤ ስርከስ ኢትዮጵያ ካፈራቸው ምርጥ ኮከቦች አንዷ ናቸው። ከሜክሲኮ አደባባይ ውልደትና ዕድገታቸው እስከ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃ ሕይወታቸው ያወጋሉ።

"የእኔ ሕልም ኢትዮጵያውያን ተስማምተው፤ በአንድነት ሀገራቸውን አሳድገው እኩልና ባለፀጋ እንዲሆኑ ነው፤ በሕይወት ዘመኔ ይኼ ሆኖ አያለሁ ብዬ አላስብም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ 09.01.2025

ያለ ዝንፈት ሁሌም ውድ ሀገሬ ብለው በጠሯት የኢትዮጵያ ዕቅፍ ውስጥ ዳግም ላይመለሱ ለዘላለሙ ያረፉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ሀገራቸውን በምጣኔ ሃብት ባለሙያነት በምክትል የፋይናንስ ሚኒስትርነት፣ በዓለም አቀፍ መድረክ በዓለም ባንክና በተባበሩት መንግሥታት፣ በፖለቲካው መስክ ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማ የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል። በሕይወት ሳሉ ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ በዝክረ መታሰቢያነት ደግመን አቅርበናል።

በዓለ ልደት በኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን ዘንድ 07.01.2025

ወ/ሮ ወጋሐተ መለስ (ከሜልበርን)፣ አቶ ጥላዬ ታረቀኝ (ከብሪስበን)፣ እና ወ/ሮ ሱዛ አበበ (ከፐርዝ)፤ እንደምን በዓለ ልደት 2017ን እንዳከበሩ ይገልጣሉ፤ የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውንም ያስተላልፋሉ።

"ይህን ታላቅ በዓል በአውስትራሊያና የተለያዩ ቦታዎች ለምታከብሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን፤ ምኞቴም ፀሎቴም የሕይወት ለውጥ እንዲሆንላችሁ ነው" ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 06.01.2025

ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ በዓለ ልደትን አስመልክተው መንፈሳዊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።

"በዓሉ የእምነት፣ የትህትና፣ የደስታና የሰላም እንደመሆኑ እግዚአብሔር የደስታ በዓል ያድርግልን፤ በመከራ ውስጥ ያሉ ወገኖችን በምሕረት እጁ ይጎብኝልን" ቀሲስ መልአከ ፀሐይ 06.01.2025

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የገና በዓልን አስመልክተው መንፈሳዊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያና ሶማሊያ አልሻባብን ለመፋለም ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቀ 05.01.2025

ሴት እንጀራ ልጁን ለ10 ዓመታት አስገድዶ ሲደፍር ቆይቶ የገደላት ግለሰብ የሞት ፍርድ ተበየነበት

"በእርግዝና ወቅት ማጤስ ለከማኅፀን ውጪ እርግዝና ያጋልጣል፤ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው እናቶች ልጆች በሁለት እጥፍ ለኦቲዝም የተጋለጡ ይሆናሉ"ዶ/ር በረከት ዱኮ 05.01.2025

ዶ/ር በረከት ዱኮ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ተመራማሪ ናቸው። በቅርቡ ከአንድ አጥኚ ቡድ ጋር በመሆን በቅድመ እርግዝናና በእርግዝና ወቅት ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች ላይ የሚከሰቱ የጤና ጠንቆችን፤ እንዲሁም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ሴቶች የሚወልዷቸው ልጆች ለኦቲዝም ተጋላጭነታቸው እጥፍ መሆኑን ስለሚያመላክተው የጥናት ግኝቶቻቸው ያስረዳሉ።

የኢትዮጵያውያን-አውስራሊያውያን የ2025 አዲስ ዓመት ተስፋና ምኞቶች 05.01.2025

ኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዮናስ ሐጎስ (ከብሪስበን)፣ ቲቲ ጥሩነህ (ከሜልበርን) እና አዱኛ ኢቲቻ (ከፐርዝ)፤ የ2024 ስንብትንና የ2025 አዲስ ዓመት ቅበላን አስመልክተው ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለገናና ጥምቀት በዓላት ተጨማሪ የሀገር ውስጥ በረራዎችን መመደቡንና የዋጋ ጭማሪም ማድረጉን አስታወቀ 01.01.2025

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሕወሓት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ከዋጋ ግሽበት ቅነሳ እስከ የግዴታ መጠባበቂያ ተቀማጭ ሂሳብ ላይ ማስወሰኑን አስታወቀ 01.01.2025

የ2025 አዲስ ዓመት ቅበላ በዓለም ዙሪያ ተካሔደ

"በሜልበርን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ፍቅር፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ ሰላማዊነትና አንድነት እረክቻለሁ" የሀገረ ጀርመን ነዋሪ አቶ ደረጀ ኃይሉ 31.12.2024

ከ28ኛው የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር ጋር ተያይዞ ዲሴምበር 28 / ታሕሳስ 19 በድምቀት ተከብሮ የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ ቀን በማስመልከት ጎብኚና ነዋሪ የማኅበረሰቡ አባላት አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።

"የስፖርት ውድድሩና የኢትዮጵያ ቀን ካሰብነው በላይ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቅቋል፤ ዓመቱን ሙሉ በልጆቻችን የሚናፈቅ እናድርገው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 30.12.2024

28ኛው የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር መጠናቀቅን አስመልክቶ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፣ የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ ስቲት ሁመራ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ወጣት ዮሃንስ እና ቢንያም ከበደ፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የ renewaustraliaforall.org አስተባባሪና ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።

ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ መካተት እስካሁን አልተረጋገጠም 29.12.2024

መንግሥት በአምስት የሲቪል ማኅበረሰብ ላይ የጣለውን ዕገዳ እንዲያነሳ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ

"28ኛውን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር ጀምረናል፤ 'የኢትዮጵያ ቀን' ን በጉጉት እየተጠባበቅን ነው" አስተባባሪዎችና ታዳሚዎች 26.12.2024

የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያዎችና ውጤቶች

Ascultă podcastul SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ în Replaio

Radio și podcasturi într-o singură aplicație - gratuit și fără înregistrare. Instaleaz-o azi și nu rata lansarea

Descarcă din Google Play

Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice