SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 1001 episodi

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: www.sbs.com.au

Autore

SBS

Categoria

News

Sito del podcast

www.sbs.com.au

Ultimo episodio

1 ott 2026

Dove ascoltare?

I podcast nell'app Replaio Radio In arrivo

I podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast

Scaricala su Google Play Installala gratis Android quasi 10 mln di download · valutazione 4,8 iOS in arrivo

Episodi

#61 Tackling a DIY project (Med) 10.05.2024

Learn how to talk about doing do-it-yourself (DIY) projects.

Navigating the implicit right to protest in Australia - አውስትራሊያ ውስጥ ስውር የተቃውሞ መብትን ማሰስ 09.05.2024

Every week, impassioned Australians take to the streets, raising their voices in protest on important issues. Protesting is not an offence, but protesters sometimes test the limits of the law with extreme and antisocial behaviour. The chance of running into trouble depends on where you’re protesting and how you behave. - በየሳምንቱ ስሜታቸው የገነፈለ አውስትራሊያውያን ጎዳናዎች ላይ ወጥተው ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንስተው ድምፆቻቸውን ያሰማሉ።...

የአስትራዜኒካ ኮቪድ-19 ክትባት ከዓለም ገበያዎች እየተሰበሰበ ነው 08.05.2024

የዘንድሮው የአውስትራሊያ በጀት የዋጋ ግሽበትን በማያባብስ መልኩ የተበጀተ መሆኑ ተመለከተ

የበዓለ ትንሣኤ አከባበር በአገረ አውስትራሊያ 08.05.2024

ወ/ሮ ሰላማዊት ታደሰ (ከፐርዝ)፣ ዘውዴ ተስፋማሪያም (ከብሪስበን) እና አቶ ወንድወሰን ሽቱ (ከሜልበርን) እንደምን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳሳለፉ ይናገራሉ። ለመላ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

"የባና ርዕይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለዓለም ገበያ ማቅረብና የኢትዮጵያን ባሕል በሉላዊ መድረክ ላይ እንዲያንፀባርቅ ማስቻል ነው" ድምፃዊትና ሥራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን 08.05.2024

የባና ሙዚቃ አሳታሚ መሥራች፣ ድምፃዊትና ዋና ሥራ አስፈፃሚት ብሌን መኮንን፤ ስለ ባና አመሠራረትና ሚና ታስረዳለች፣ ድምፃዊ ዕብነ ሐኪም እንደምን ወደ ሙዚቃ ዓለም እንደዘለቀና ስለመጪ የሙዚቃ አልበሙ "ብራና" ይናገራል።

ኢትዮጵያ በሕዋ የአምስት ዓመት የቆይታ ዕድሜ የሚኖራት ሳተላይት ለማምጠቅ ጨረታ አጠናቀቀች 07.05.2024

40 በመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል አስፈላጊ ሰነድ የሌላቸው መሆኑ ተገለጠ

የእሥራኤል ጦር የጋዛ ራፋህ መተላለፊያን ተቆጣጠረ 07.05.2024

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሱዳን ፈጣን ኃይል ሕወሓት ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር አብሮ እየወጋን ነው የሚለው ክስ መሠረተ ቢስ ነው ሲል አስተባበለ

"የአድዋ ጀግኖች ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉት ለእንጀራና ቡና አይደለም፤ የተለያየ ዘርና ሃይማኖት ላለው ሕዝብ ነፃነት ነው" ድምፃዊት ቤቲ ጂ 07.05.2024

"ሽልማት ማለት ሥራችሁን ጨርሳችኋል፤ አቁሙ ማለት አይደለም። ለኒሻን ሲሆን ደግሞ ለሀገር ገና ብዙ ትሠራላችሁ የሚል አደራም ጭምር ነው" የምትለዋ ድምፃዊት፣ የሰብዓዊ ረድዔትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ማንነት አጉሊ ድምፅ ብሩክታይት ጌታሁን "Betty G"፤ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ስለተበረከተላት የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ኒሻንና ሀገራዊ አንድነት ፋይዳዎች ትናገራለች።

የፐርዝ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት በእስልምና ስም የሚካሔዱ የአመፅ ድርጊቶችን አወገዙ 06.05.2024

የሃማስና እሥራኤል ድርድር በተስፋና ጥርጣሬ መካከል ነው

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በ1.5 ቢሊየን ዶላር ተጨማሪ የኔትዎርክ ማስፋፊያ ሊያደርግ ነው 05.05.2024

ኢትዮጵያ ውስጥ የጉበት በሽታ እየጨመረ ነው

“ የክርስቶስ ትንሳኤ ሞት የተሸነፈበት ታላቅ የምስራች የተሰበከበት ቀን ነው ። ” - መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ 05.05.2024

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አሕጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ እንዲሁም የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የፋሲካ በዓል መልዕክት፡፡

"እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ትንሣኤ የክርስቲያኖች ተስፋ የተረጋገጠበት ነው” ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 05.05.2024

ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋሉ።

"ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ 04.05.2024

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።

"ሥነ ፅሑፍ ቁራኛ ነው፤ ከፀሐፊው ጋር በፍቅርም በትንቅንቅም ተያይዘው ይዘልቃሉ፤ አይላቀቁም" ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ 04.05.2024

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉና የሥነ ግጥም በረከቶቹ ይናገራል።

"ጋዜጠኛ በንፁህ ኅሊናው ሚዛናዊ የጋዜጠኛነት ሥራን መሥራት እንጂ፤ ሙያውን የሚያራክስ ነገር መሥራት የለበትም። አሁን እንደወረርሽኝ የወረረን እሱ ነው" አበራ ለማ 04.05.2024

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ የአገረ ኢትዮጵያን የራዲዮ ስርጭት፣ የጋዜጣ ሕትመት ውጤቶችንና የባለ ሙያዎቹን የሥነ ምግባር ደረጃ መዝኖ ግለ አተያዩን ያጋራል።

አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት 03.05.2024

ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።

Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት 02.05.2024

The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለሚከናወነው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አስታወቀች 30.04.2024

ከአፍሪካ ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ መመዝገቡ ተገለጠ

“ ግላኮማን አንዴ ከተከሰተ ባለበት ማቆም እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማዳን አይቻልም ” - ዶ /ር ለምለም ታምራት 30.04.2024

ዶ /ር ለምለም ታምራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የዓይን ሐኪምና የግላኮማ ስፔሽያሊስት (ልዩ ሐኪም ) የዓይን ውስጥ ዕብጠት ግላኮማ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ዕይታችንን ሊጋርድ የሚችል በሽታ መሆኑን ያስረዳሉ።

ሰሙነ ህማማት እና ትርጓሜው - በመጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ 30.04.2024

መጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማንያን ዘንድ በተለየ ሁኔታ የሚታሰቡትን የሰሙነ ህማማት ቀናት ትርጓሜ አስረድተዋል ።

"ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓለ ትንሣኤን እንመኛለን" በሜልበርን-አውስትራሊያ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን 30.04.2024

በአገረ አውስትራሊያ-ሜልበርን ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤልና የመካነ ሰላም ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት መዘመራን፤ ቤተልሔም ትዕግስቱ፣ ፅዮን ብሩክ፣ ኤማንዳ ወንድወሰንና ኤፍራታ ሚሊዮን ሰሙነ ሕማማትን ምክን ያት በማድረግ "በጌቴ ሰማኔ" መንፋሳዊ መዝሙርን ያሰማሉ።

ዜና - በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የአውስትራሊያ ፓርላማ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረገ 29.04.2024

በአብላጫው በሴቶች ለሚሰሩ ስራዎች የ9 በመቶ የክፍያ ጭማሪ እንዲደረግ የሰራተኞች ማህበር ጠየቀ

በአዲስ አበባ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ ከ77 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚኖሩና 92 በመቶው ኤርትራውያን መሆናቸው ተገለጠ 28.04.2024

የ2016 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተወሰኑ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

የአንዛክ ቀን በመላው አውስትራሊያና በባሕር ማዶ ተከበረ 25.04.2024

የአውስትራሊያ ፌዴራል ፖሊስ ከእምነት መሪዎች ጋር መክረናል ሲል፤ በሲድኒ የእስልምና እምነት መሪዎች አሰሳውን አስመልክቶ "እንድናውቀው" እንጂ "እንድንመክርበት" አልተደረገም ይላሉ

#60 Talking about commemorating | Anzac Day (Med) 24.04.2024

Learn how to talk about commemorating Anzac Day, plus find out why it's important for all Australians.

Ascolta il podcast SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ su Replaio

Radio e podcast in un'unica app - gratis e senza registrazione. Installala oggi e non perderti il lancio

Scaricala su Google Play

Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici