SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: www.sbs.com.au
Dove ascoltare?
I podcast nell'app Replaio Radio In arrivoI podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast
Episodi
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመግታት የድርጊት እርምጃ ጥሪ ቀረበ 24.04.2024 6:40
ሕወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ነው የሚለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው አለ
በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተገለጠ 23.04.2024 6:28
ከየመን የባሕር ዳርቻ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ በነበረች አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ተሳፋሪ ከነበሩት 77 ኢትዮጵያውያን ውስጥ 5 ሕፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ የ16 ዜጎች ሕይወት አለፈ
Tackling misinformation: How to identify and combat false news - ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል 23.04.2024 12:55
In an era where information travels at the speed of light, it has become increasingly difficult to distinguish between true and false. Whether deemed false news, misinformation, or disinformation, the consequences are the same - a distortion of reality that can affect people's opinions, beliefs, and even important decisions. - መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች...
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትጥቅ ታጋዮች በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ፤ ጥበቃም እንደሚደረግላቸው ገለጠ 23.04.2024 3:24
የራያና አላማጣ ተፈናቃዮች ቁጥር እንደሚጨምር ተመለከተ
በጅሮንድ ቻልመርስ የአውስትራሊያ የወደፊት የምጣኔ ሃብት ዕድገት ትንበያን አለዝበው ገለጡ 22.04.2024 8:44
በሲድኒ ቦንዳይ ጃንክሽን የገበያ ማዕከል በስለት ተወግታ የነበረችው የዘጠኝ ዓመት ሕፃን አገግማ ከሆስፒታል ወጣች
"የጋምቤላ ችግር መታየት ያለበት የኑዌሮችና አኟኮች ተደርጎ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ሊያዋጋ የሚችል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ነው" ዶ/ር ኦፒዎ ቻም 22.04.2024 15:20
ዶ/ር ኦፒው ኦሙት ቻም፤ የቀድሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ተከስተው ስላሉት ዋነኛ ችግሮች፣ መንስዔዎችና ምክረ ሃሳቦችን አንስተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በአገራዊ ምክክር ሂደቱና በኮሚሽኑ ዕቅዶች ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ገለጠ 21.04.2024 6:49
ኢትዮጵያ የጠየቀችውን አዲስ ብድር አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር ያላት ልዩነት አልተፈታም
"በሐረሪ ሕብረተሰብ ውስጥ 40 ያህል የአለላ ስፌት ዓይነቶች መኖራቸውን ጥናቶች ያመለከታሉ" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም 20.04.2024 16:04
ወ/ሮ ዉዳድ ሳሊም፤ የጤና ባለሙያና አንቂ፤ ስለ ሐረሪ ማኅበረሰብ የአለላ ስፌት ባሕላዊ ቅርስነትና የማንነት መገለጫነት አስመልክተው ይናገራሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በረሃብና ተላላፊ በሽታ እየተፈነች እንደሆነና ከፍ ያለ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻት አሳሰበ 18.04.2024 5:09
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት 'ሕወሓት ወረራ ፈፅሞብኛል' ሲል ለፀጥታ አካላት፣ ለነዋሪዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አስታወቀ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ግጭት ውስጥ አይደለሁም አለ
የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ 18.04.2024 9:51
በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ 16.04.2024 6:35
ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች? 16.04.2024 20:21
የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
"የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የማነአብ 16.04.2024 18:52
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።
" 'የመኢሶን ሰማዕታት' መጽሐፍ ፋይዳ አንድ ተጨባጭ የሆነ የታሪክ ሰነድ ማቆየት ነው" ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ 16.04.2024 12:03
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የድርጅታቸው የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት የመዘከሪያ መጽሐፍን መሰናዶና ትሩፋቶቹን አስመልክተው ያስረዳሉ።
የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ የገበያ ማዕከል በስለት የተገደሉ ስድስት ሰዎችን በክብርና በሐዘን ለመዘከር በግማሽ ዝቅ ብሏል 15.04.2024 6:35
አውስትራሊያ ኢራን በእሥራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አወገዘች
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተካተተች 14.04.2024 5:46
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች ከሥራና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች እንዲገለሉ የሚያደርግ ምዝገባ ልትጀምር ነው
ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ባቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ ገለልተኛና ሙሉዕ ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ 11.04.2024 4:30
ዩናይትድ ስቴትስ የዊኪሊክስ መሥራቹን ጁሊያን አሳንጅ ክስ ልታነሳ እንደምትችል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አመላከቱ
#59 Talking about cooking (Med) 11.04.2024 13:31
Learn how to talk about cooking and sharing recipes.
ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ይጓዙ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ 10.04.2024 7:04
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ አውስትራሊያ ለፍልስጤም አገራዊ ዕውቅና ለመስጠት ዕሳቤ እንዳላት አመላከቱ
"ኢድ አልፈጥር! አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን፤ ደም ማፍሰሱን አላህ በኃይሉ ያስተካክልልን" ሼክ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር 10.04.2024 8:45
ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የዘንድሮውን ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የፆምና ፀሎት መንፈሳዊ ፋይዳዎችንና የሰላም ምኞታቸውን አሰናስለው ይገልጣሉ።
አውስትራሊያ ውስጥ ከ2035 አንስቶ በነዳጅና በናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዳይውሉ ጥሪ ቀረበ 09.04.2024 3:42
የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት አዲስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሾመ
ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድርድር ሊቀጥል ነው 09.04.2024 9:33
በነዳጅ የሚሠሩና ሙሉ በሙሉ በውጭ አገር ተገጣጥመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ ተጣለ
በአዲሱ የምግብና ግሮሰሪ ሥነ ምግባር ደንብ ሱፐርማርኬቶች እስከ 10 ሚሊየን ዶላርስ የሚደርስ መቀጮ ሊያገኛቸው ነው 08.04.2024 6:59
የቀድሞው የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አዛዥ በእሥራኤል የአየር ጥቃት ለተገደለችው አውስትራሊያዊት የእርዳታ ሠራተኛ ምርመራ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሰየሙ
"ኤልያስ ካለ ጎል አለ፤ አብዛኛዎቹ የመብራት ኃይል ቡድን ዋንጫዎች የኤልያስ ጁሐር ዋንጫዎች ናቸው" የፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 08.04.2024 11:49
"የኤልያስ ዋንጫ" አዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ በዘጋቢ ፊልም ቀርፀው ለሕዝብ ዕይታ ለማቅረብ ስለምን እንደወደዱና የፊልሙን ጭብጥ አሰናስለው ይናገራሉ። "የኤልያስ ዋንጫ" በሳምንቱ መጨረሻ በሜልበርን - አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ በነፃ ይቀርባል።
" የደብረ ዘይት በዓልን ስናከብር የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እያሰብን ነው ። ” መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ 07.04.2024 9:28
መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ በአውስትራሊያ የልደታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በትናንትናው እለት የተከበረውን የደብረ ዘይት በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ አደራ ብለዋል ።
Podcast simili
Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici