SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 1001 episodi

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: www.sbs.com.au

Autore

SBS

Categoria

News

Sito del podcast

www.sbs.com.au

Ultimo episodio

1 ott 2026

Dove ascoltare?

I podcast nell'app Replaio Radio In arrivo

I podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast

Scaricala su Google Play Installala gratis Android quasi 10 mln di download · valutazione 4,8 iOS in arrivo

Episodi

የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚረዱት እንደምን ነው? 15.06.2024

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ፋርማሲ - የቤት ሽያጭና ግዢ 14.06.2024

በፍሬድ ማየር ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያዋ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከመሀል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ ያለፉበትን የሕይወት ጉዞ አንስተው አውግተዋል። በውይይታችን መቋጫ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን በሲያትል ከተማ ተሰማርተው ስላሉበት የቤት ግዢና ሽያጭ (Real Estate) የንግድ መስክ ይናገራሉ።

"ሀገር ቤት ፋርማሲ ውስጥ በዝቶ የገጠመኝ የፋርማሲ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው" ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ 13.06.2024

በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ እንደምን ወደ ፋርማሲ ሙያ እንደዘለቁና በሙያው መስክ እንደተሠማሩ ያወጋሉ። የኢትዮጵያንና የአሜሪካ ፋርማሲዎች አሠራርን ነቅሰው ያስረዳሉ።

የአላማጣ የሰላም ጥሪ ችላ ሊባል እንደማይገባ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ አሳሰቡ 12.06.2024

ዩናይትድ ስቴትስ የእሥራኤል - ጋዛ ጦርነትን አስመልክቶ የሃማስን ተኩስ አቁምና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ምላሽ እያጤነች መሆኗን ገለጠች

ኢትዮጵያ የብር መግዛት አቅምን ካዳከመች የዋጋ ንረቱ እንደሚባባስ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አሳሰበ 11.06.2024

የኢትዮጵያ ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር 129.7 ሚሊየን መድረሱና በ28 ዓመታት ውስጥም በእጥፍ እንደሚያድግ ተገለጠ

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ከመሃል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ 11.06.2024

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው። ከመሀል ሜዳ ተነስተው ሀገረ አሜሪካ የዘለቁት የከፍተኛ ትምህርት ጥማታቸው ለማርካትና በላቀ ክህሎት ተጠብበው ሙያዊ አስተዋፅዖ ለማበርከት ተልመው ነው።

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከእሥር ተለቀቁ 11.06.2024

ኮልስ በቪክቶሪያ የኤቪያን ኢንፍሉዌንዛ መከሰትን ተከትሎ ከምዕራብ አውስትራሊያ በስተቀር የዕንቁላል ሽያጭ ገደብ ጣለ

"በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቻለሁ፤በሕይወት እያለሁ ይህን ክብር በማየቴ አመሰግናለሁ"ለማ ክብረት "በዝግጅቱ ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ"የሺሐረግ ግርማ 11.06.2024

ከአምስት ዓለም አቀፍ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የግብ ጠባቂ ሬኮርድ ያስመዘገበውና በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ሞሪሽየስን ለማሸነፍ እንድትበቃ ላስቻለው አንጋፋና ዝነኛው ለማ ክብረት ቅዳሜ ሰኔ 1 ቀን 2016 በሜልበርን - አውስትራሊያ የተካሔደው የዕውቅናና ምስጋና ምሽት ዝግጅት ተጠናቅቋል። ስኬቱም በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ የ"ይበልና ይቀጥል" ስሜትን አሳድሯል።

13 ሚሊየን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የግብርና ግብዓት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ 09.06.2024

ኢትዮጵያ ውስጥ በ10 ወራት ውስጥ ከመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል፤ 16 በመቶ የሚሆነው ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተገኘ መሆኑ ተገለጠ

Australia’s coffee culture explained - የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ሲገለጥ 07.06.2024

Australians are coffee-obsessed, so much so that Melbourne is often referred to as the coffee capital of the world. Getting your coffee order right is serious business, so let’s get you ordering coffee like a connoisseur. - አውስትራሊያውያን አቅላቸው ለቡና የማለለ ነው፤ ተዘውትሮም ሜልበርን የዓለም የቡና መዲና በሚል ተቀጥላ ትጠቀሳለች። ቡናዎን በውል ማዘዝም ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ልክ ቡናን በማጣጣም ክህሎት እንደተላበሰ ባለሙያ ቡናዎን እንዘዝልዎት።

ኢሰመኮ የአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማክተምን ተከትሎ ከአዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ያሉ እሥረኞች እንዲለቀቁ ጠየቀ 06.06.2024

የጁባላንድና ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ አስተዳደር ግዛቶች የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ሶማሊያን ለቅቆ እንዲወጣ የሚሹ አለመሆናቸውን ገለጡ

#63 Taking a dog to the park (Med) 05.06.2024

Learn how to talk about your dog at a dog park.

የቀድሞው የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ታሰሩ 05.06.2024

የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ድንጋጌ አሳለፈ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመሆን '60 ቢሊየን ብር ያስፈልገኛል' አለ 04.06.2024

ሕወሓትን ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሕልውና ሊያላብስ ይችላል የተባለለት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ

"ከእነ ልጆቻችን መጠለያ የለንም፤ እባካችሁ ከቻላችሁ ጋራዣችሁን ወይም ጓሯችሁን ለድንኳን መትከያ ፍቀዱልን" አቶ ጊቤ ዘለቀና ወ/ሮ መቆያ ታምራት 04.06.2024

ከአራት ሕፃናት ልጆቻቸው ጋር መጠለያ አጥ ሆነው ለጎዳና የተዳረጉት የሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን አቶ ጊቤ ዘለቀና ወ/ሮ መቆያ ታምራት፤ ከኪራይና ጥገኛ ደባልነት አልፈው ለድንኳን ነዋሪነት ተዳርገዋል። ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት የድጋፍ ተማፅኖአቸውን ያቀርባሉ።

በሚሊየን የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ከጁላይ 1 ቀን አንስቶ የደመወዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው ነው 03.06.2024

አውስትራሊያ የዩናይትድ ስቴትስን የተኩስ ማቆምና ታጋቾችን የማስለቀቅ ዕቅድ እንደምትደግፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስታወቁ

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር በኢትዮጵያ በሚካሔዱ ግጭቶች ሳቢያ በተለይ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በቂ ሕክምና እንደማያገኙ አስታወቀ 02.06.2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ300 ሚሊየን የናይጄሪያን አየር መንገድ የማቋቋም ፕሮጄክት ድርሻ ግዢ በዕግድ ሊቆይ ነው

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረት 02.06.2024

በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።

ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነት 02.06.2024

ለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።

"የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድ ግብ ጠባቂ ለማ ክብረት ወገን አለኝ እንዲል፤ላበረከተው አገልግሎት ተሰባስበን እናመስግነው"ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና አቶ ኤርሚያስ ወንድሙ 01.06.2024

"ለማ ክብረት በዓለም ላይ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሊሰኝ የሚችል፤ ቅን፣ ሰው አክባሪና የታመመን ጠያቂ ነው" የሚሉት የቀድሞው የለማ ክብረት የብሔራዊ ቡድን ባልደረባ አቶ ኤርሚያስ ወንድሙና "ለሀገራቸው ያገለገሉ የማኅበረሰብ አባላትን ዕውቅንና ከበሬታ ልንቸራቸው ይገባል" የሚሉት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ቅዳሜ ሰኔ 1 / ጁን 8 በሜልበር ስለሚካሔደው የሕይወት ዘመን አገልግሎት ልዩ የዕውቅና ፕሮግራም ያስረዳሉ፤ የግብዣ ጥሪና ምስጋናም ለማኅበረሰብ አባላት ያስተላልፋሉ።

"የዛጉዌ መንግሥት ዋነኛው የውድቀት ምንጭ የስልጣን ወራሾች ያደረሱት የእርስ በእርስ ቀውስ ነው" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 31.05.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ባበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ውስጥ ተካትተው ያሉትን የንጉሥ እስክንድር፣ አምደ ፅዮንና ናኦድ ዘመነ መንግሥታት አንስተው ይናገራሉ።

"አፄ ዘርአ ያዕቆብ 'መንግሥቴን በሃይማኖታችሁ መለያየት መክፈል አይቻልም' ብለው ደንግገው ነበር" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 31.05.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ባበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ውስጥ ተካትተው ያሉትን የንጉሥ ዘርአ ያዕቆብና ንጉሥ በዕደማርያምን ዘመነ መንግሥታት አንስተው ይናገራሉ።

የሕወሓት 14ኛ ጉባኤ - "ከለውጡ ጋር አብሮ መለወጥ ያስፈልጋል" ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 30.05.2024

የምዕራብ አውስትራሊያ የሌበር ሴናተር ከጥምር የውጭ ጉዳዮች፣ መከላከያና ንግድ ኮሚቴ አባልነታቸው ለቀቁ

"የመፅሐፉ ዋነኛ ዓላማ የታሪኩ ባለቤትና ቅርስ ወራሽ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን ጋር ማገናኘት ነው" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው 30.05.2024

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ለሕትመት ስላበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ያስረዳሉ።

የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር የሥራ ኃላፊነታቸውን እንዲለቁ ጫና እየደረሰባቸው ነው 29.05.2024

የሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ለኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ለጋሾች ምስጋና አቀረበ

Ascolta il podcast SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ su Replaio

Radio e podcast in un'unica app - gratis e senza registrazione. Installala oggi e non perderti il lancio

Scaricala su Google Play

Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici