SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: www.sbs.com.au
Dove ascoltare?
I podcast nell'app Replaio Radio In arrivoI podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast
Episodi
ሳም ሞስቲን 28ኛዋ የአውስትራሊያ ጠቅላይ እንደራሴ ሆኑ 01.07.2024 5:37
የሌበር ፓርቲ ሴናተር ፋጡማ ፔይማን ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተቃርነው የሙስሊም መሪዎችና የመብቶች ተሟጋች ቡድኖች ገልፅ ደብዳቤ አወጡ
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል በባሕር በር ዙሪያ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ውጥረት እንዳሳሰባት ገለጠች 30.06.2024 10:19
ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎች ያገኘችው የዕዳ ክፍያ እፎይታ በድጋሚ ይራዘማል ብላ እንደምትጠብቅ አመላከተች
"ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አበርካቾችንና የንግድ ማኅበረሰብ ተሳትፎን እንሻን፤ የአባልነት ጥሪም እናቀርባለን" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 30.06.2024 12:36
ዶ/ር ተስፋዪ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንትና አቶ ንብረት ዓለሙ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ስለ መጪው 2017 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዝግጅትና አስፈላጊ ማኅበረሰባዊ ተሳትፎ ይናገራሉ።
የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ለውጥ አደረገ 30.06.2024 12:55
የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ስለምንና እንደምን የማኅበሩን ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት የሥራ አገልግሎት ኃላፊነታቸውን እንዲለዋወጡ ከመግባባት ላይ እንደደረሰ ያስረዳሉ።
"ኢትዮጵያውያን በብዛት መጥተው የስዕል ኤግዚቪሽኔን ቢመለክቱልኝ ደስ ይለኛል" ሰዓሊ ኦላና ዳመና ጃንፋ 27.06.2024 11:24
አርቲስት ኦላና ዳመና ጃንፋ፤ ኢትዮጵያ ተወልዶ። የኖርዌይ ዜኘትን ተላብሶ፣ ከአውስትራሊያዊት ባለቤቱ ለልጅ አባትነት በቅቶ መኖሪያውያን ሜልበርን አውስትራሊያ ያደረገ ሰዓሊ ነው። "Too Much Drama" የሚለው የስዕል ኤግዚቪሽኑ ቅዳሜ ጁን 29 ተጋባዥ ታዳሚ እንግዶች ባሉበት የሚከፈት ሲሆን፤ ከጁላይ 2 እስከ ሴፕቴምበር 6 ድረስ በዳንዲኖንግ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ይበቃል።
Indigenous art: Connection to Country and a window to the past - የነባር ዜጎች ሥነ ስዕል፤ ሀገራዊ ቁርኝትና የትናንት መስኮትነት 27.06.2024 8:49
Embracing their oral traditions, Aboriginal and Torres Strait Islander peoples have used art as a medium to pass down their cultural stories, spiritual beliefs, and essential knowledge of the land. - ቃለ ልማዶችን ሞገስ በማላበስ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሥነ ስዕልን ባሕላዊ ወጎቻቸውን፣ መንፈሳዊ እምነቶቻቸውንና ስለ መሬታቸው ያላቸውን መሠረታዊ ዕውቀቶች የማሸጋገሪያ ተግባቦት አድርገው ተጠቅመውበታል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮሚሽን (ኢሠማኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦርድ ሰብሳቢ እንዳይሆኑ ተቃውሞ አሰማ 26.06.2024 9:32
በመቀሌ ከተማ በሴቶችና ላይ የሚፈፀሙ የእገታና ፆታዊ ጥቃቶች እንዲቆሙና ጥቃት አድራሾች ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ሴት ሰላማዊ ሰልፈኞች ጠየቁ
የዊኪሊክስ መሥራቹ ጁሊያን አሳንጅ "ነፃ ወጣ" ወደ ትውልድ ሀገሩ አውስትራሊያ ሊመለስ ነው 25.06.2024 2:49
የአውሮፓ ኅብረት በሩስያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ
እሬቻ አፍራሳ - የተራራው እሬቻ በሜልበርን ከተማ ተከበረ 25.06.2024 9:25
እሬቻ አፍራሳ - የተራራው እሬቻ በአውስትራሊያ - ሜልበርን ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ ተከበሮ ውሏል።
በእጅጉ ከፍተኛ በሆነ ሙቀት ሳቢያ ከ1 ሺህ 300 በላይ የሐጅ ተጓዥ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች 24.06.2024 8:04
በሁከት ፈጠራና ሸማቾችን በማደናገጥ የአደላይድን የገበያ ማዕከል ያዘጉ ሁለት ታዳጊ ወጣቶች ዘብጥያ ወረዱ
ኢትዮጵያ በ13 ፕሮጄክቶች መጓተት 16.6 ቢሊየን ብር ተጨማሪ ወጪ አወጣች 23.06.2024 9:26
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያን በኑሮ ውድነት ለተቸገሩ መምህራን ጊዜያዊ መጠለያ አደረገ
የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ 21.06.2024 19:23
የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።
እሬቻ አርፋሳ - የተራራው እሬቻ እሑድ በአውስትራሊያ - ሜልበርን ከተማ ሊከበር ነው 21.06.2024 7:02
እሬቻ አፍራሳ - የተራራው እሬቻ በአውስትራሊያ - ሜልበርን ከተማ እሑድ ሰኔ 16 / ጁን 23 እንደምን እንደሚከበር የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ኦቦ በንቲ ኦሊቃና አባ መልካ ዳኜ ደፈርሻ ይናገራሉ።
"ሥነ ጥበብ የቡድን ሥራ ሲሆን፤ ፖለቲካውንና የሕብረተሰብን አስተሳሰብ መምራት ይችላል" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ 21.06.2024 14:24
ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ወደ ሀገረ አውስትራሊያ ስለመጡበት መንፈሳዊ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ይናገራሉ። ምዕመናንም ሜልበርንና ሲድኒ በሚካሔዱት መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።
"የትዳር አጋሬ ባትረዳኝ ኖሮ የጥበብ ሥራዬ አይቃናም ነበር" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ 21.06.2024 13:40
ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ለምዕመናን ስላበረከቷቸው መዝሙሮች፣ ለሕትመት ያበቋቸውን መፃሕፍትና ለዕይታ ያቀረቧቸውን የቅብ ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን አንስተው ይናገራሉ። ለጥበባዊ ሕይወት ስኬታቸው የቤተሰባቸውን ሚና አንስተው ምስጋና ያቀርባሉ።
"እንደ ሀገር የተቋም ግንባታ ችግር አለብን፤ አዲስ አበባ ውስጥ ቢያንስ ተጨማሪ አራት ቲአትር ቤቶች ያስፈልጉናል" አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት 20.06.2024 17:23
አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት፤ የኢትዮጵያን ዐበይት የቲአትር ችግሮችና ዕምቅ የኪን ጥበብ ክህሎቶችን አንስተው ይናገራሉ።
ኪነ ጥበብና ዲፕሎማሲ፤ የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ 120ኛው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጥበባዊ ተሃስቦ 20.06.2024 18:26
በ1903 በዳግማዊ ምኒልክ ፊርማ መሠረቱ የፀናው የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከኮሪያ እስከ ቀዝቃዛው ጦርነት፤ ከምጣኔ ሃብትና ረድዔት ድጋፍ እስከ ሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ ርዕዮተ ዓለሞች ተፈትኖ 120ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ኪነ ጥበባዊ ትሩፋቶቹም እንደምን በመድረክ ተነስተው በኢትዮጵያውያን የጥበብ ባለሙያዎች አንደበት እንደተዘከሩ አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት ነቅሰው ይናገራሉ።
የተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን አውስትራሊያ ውስጥ የኑክሊየር ኃይል ማመንጫዎች የሚተከሉባቸውን ሰባት ሥፍራዎች ይፋ አደረጉ 19.06.2024 7:31
የመሣሪያ ዕገዳ መነሳትን አስመልክቶ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተፃራሪ መግለጫዎችን ሰጡ
Facing religious discrimination at work? These are your options - በመሥሪያ ቤትዎ የሃይማይኖት መድልዖ ገጥሞዎታል? አማራጭዎችዎን እነሆ 19.06.2024 7:54
Australia is a party to the International Covenant on Civil and Political Rights, which provides extensive protections to religious freedom. However, specific legislated protections vary across jurisdictions. If you have experienced religious discrimination at work, it is important to know your options, whether you are considering submitting a complaint or pursuing the matter in court. - አውስትራሊያ ለ...
73 መሥሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከደንብና መመሪያ ውጪ የ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግዢ መፈፀማቸው ተመለከተ 18.06.2024 12:28
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በግለሰቦች ስም የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ከ17 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡና ከእዚያም ውስጥ 9 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ለትርፍ ሰዓት ክፍያና የበዓል ስጦታ መዋሉ ተገለጠ
ፍቅርና አመፅ፤ 'ለምን ለቅቃ አትወጣም?' 'ለምን ኃላፊነትን አይወስድም? 18.06.2024 22:16
ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅ አማራጭ መፍትሔዎች ምንድን ናቸው? 18.06.2024 18:25
ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንትና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
የኢድ አል አድሃ በዓል በመላው ዓለም ተከበረ 17.06.2024 6:48
አውስትራሊያና ቻይና ልዩነቶቻቸው ላይ እየተነጋገሩ የጋራ ጥቅሞቻቸውን በትብብር እንደሚገነቡ ተመለከተ
በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊየን 336 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ መረጋገጡ ተገለጠ 17.06.2024 8:09
የኢትዮ - ቴሌኮምን ድርሻ ለውጭ ኩባንያዎች የመሸጥ ሂደት በጊዜያዊነት ተገታ
እናቶቻቸው ላይ ጥቃት ሲፈፀም የማወዱ ኢትዮጵያውያን ወንዶች፤ ፍቅረኞቻቸውና ሚስቶቻቸው ላይ ጥቃቶችን አድራሽ የሚሆኑት ስለምን ነው? 16.06.2024 13:05
ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
Podcast simili
Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici