fr

DW

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

N'hésitez pas à visiter le site du podcast et à soutenir son créateur : www.dw.com

Auteur

DW

Catégorie

News

Site du podcast

www.dw.com

Dernier épisode

12 nov. 2026

Où écouter ?

Les podcasts dans l'appli Replaio Radio Bientôt disponible

Les podcasts arrivent très bientôt dans l'appli. Installe-la dès maintenant et découvre en avant-première une toute nouvelle façon de vivre les podcasts

Télécharger sur Google Play Installe-la gratuitement Android près de 10 M de téléchargements · note de 4,7+ iOS bientôt

Épisodes

የነሐሴ 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና 29.08.2026

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ” ያላቸውን 32 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታወቀ። ሩሲያ ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 37 ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። ኔፓልና ቲቤት በሚዋሰኑበት ተራራማ አካባቢ በደረሰው የደራሽ ጎርፍ አደጋ መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 682 ደረሰ።

የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና 28.08.2026

በዛሬው የዓለም ዜና ፤የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለስድስት ወራት ተቋርጦ የነበረውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪል ዘጋቢዎች የሥራ ፈቃድ ማደሱን መግለፁን ፣በደቡብ ሱዳን 49 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት መግለፃቸውን፣ኤስዋቲኒ አወዛጋቢ በሆነ የሶስተኛ ሀገር ስምምነት መሰረት ሁለት ስደተኞችን ከአሜሪካ መቀበሏን፣በሟቹ የኖሮዌ ንጉስ ሀኖርድ አምስተኛ ምትክ ልጃቸው ንጉሥ ሃኮን ስምንተኛ ተብለው መሰየማቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በሩ ጨርሶ አለመዘጋቱን መግለጿን እንዲሁም በኔፓል በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ህንዳውያን የደረሱበት አለመታወቁን አካቷል።

የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ 27.08.2026

አርስተ ዜና፤ -በያዝነዉ ነሐሴ ወር ብቻ ከ 60 በላይ ኢትዮጵያዉያን ፤ ከዕፅ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከሳዉዲ አረብያ የሚወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። -በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው አውዳሚ ድንገተኛ የጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ 300 በላይ ደረሰ። ከ 1300 በላይ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።-የአሜሪካው 9/11 ወይም የመስከረም 11 ዱ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ።-የበቦስኒያ የጦር ወንጀለኛ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 26.08.2026

የዛሬው የዓለም ዜና የኦባሳንጆን የሰሞኑን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፁን፣በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እና በስጋት እየተመለከቱት መሆኑን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የምዕራባዉያን ዲፕሎማቶች ማስታወቃቸውን፣የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸውን፣አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ የጣለችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምንም አይነት ግብ አያሳካም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መናገራቸውን፣የአሜሪካ የስለላ ኃላፊ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ን እንዲሁም በጀርመን አንድ የፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ሰራተኛ በወባ ህይወቱ ማለፉን አካቷል።

የነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 25.08.2026

ደቡብ ሱዳን ፤ ሁለት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ የመቀሌ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ። ኢትዮጵያ እ.ጎ.አ. በ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ሰነዷን በይፋ አቀረበች። የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች 79 ስደተኞችን ታደጉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትመልስ ነው። 1501ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ ተከበረ።

የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 24.08.2026

አርስተ ዜና፤ በጫካ የሚገኙትና የፋኖ ንቅናቄ ተራ አባል ነኝ ሲሉ የገለፁልን አቶ እስክንድር ነጋ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከበርካታ የግድያ ሙከራ ማምለጣቸዉን ተናገሩ። እስክንድር ነጋ ጽምዶ የተባለዉን ጥምረት ን የኢትዮጵያ ጠላት ብለዉታል።-ዛሬ 35 ኛ ዓመት የነጻነት ቀንዋን ዛሬ ያከበረች ዩክሬይን መዲናዋ ላይ አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃምን ጨምሮ የአዉሮጳ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።- በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለዉን ግጭት ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ፤ የአሜሪካን ከኢራን ጋር ስላለው ግጭት መፍትሄ ለማግኘት ከቴህራን ጋር በአክብሮት መነጋገር እንዳለባት አጽኖት ሰጡ።

የነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 23.08.2026

• በደቡባዊ ቱኒዚያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን አፍኖ ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ። • በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ቦርጉ ግዛት ታጣቂ ጂሃዲስቶች ትክክለኛውን የእስልምና አስተምሮ አልተከተሉም ባሏቸው ምዕመናን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። • ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የሚያስፈልጋትን የ30 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮጳ ህብረት እንደምትጠብቅ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። • አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ።

የነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 22.08.2026

በዛሬው የዓለም ዜና ከአንድ ወር በላይ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁን ፣በናይጄሪያ በአክራሪ ቡድኖች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መታፈናቸው መገለፁን፣የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሃን ዋዴፉል ለጉብኝት ዛሬ ዩክሬን መግባታቸውን፣የስዊድን ፖሊስ በአሥራዎቹ ዕድሜ የምትገኝ ልጅ ትምህርት ቤት ውስጥ መገደሏን ተከትሎ የበይነመረብ ትስስር መድረኮችን እየመረመረ መሆኑን ፣እንዲሁም በምስራቅ ስፔን በተከሰተ የሰደድ እሳት ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን አካቷል።

የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 21.08.2026

አንጎት፥ መንገድ ዳር የተጠመደ ፈንጂ ባለሦስት እግር ባጃጅ አጉኖ ጉዳት አደረሰ፤ ኦባሳንጆ ከአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ የማቅረቡ ምክንያት፤ ቡኒያ፥ ኢቦላ ዳግም ከተቀሰቀሰ 100ኛ ቀኑ ተቆጠረ፤ ፓሪስ፥ «ዩክሬንን ለመደገፍ የፈቃደኞች ጥምረት» የተባለው ቡድን ሰኞ ሊሰበሰብ ነው፤ ስቶኮህልም፥ ትምህርት ቤት በደረሰ የጎራዴ ጥቃት በርካቶች ቆሰሉ

የነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 20.08.2026

ዛሬ ከቀትር በፊት መቀሌ ከተማ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 13 ሰዎች መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች አመለከቱ። ጥቃቱ የደረሰው በሲቪሎች መኖሪያ አካባቢ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የ4 ዓመት እስር ፍርድ አጸና። ኬንያ ውስጥ በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ አብራሪውን ጨምሮ 7 ሰዎች ሞቱ። ስድስቱ ሀገር ጎብኚዎች ናቸው። ዶሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው M 23 የተሰኘው ታጣቂ ቡድን የኢቦላ ተሐዋሲ መዛመትን ለመቆጣጠር አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ደነገገ።

የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 19.08.2026

የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በስምንት አጀንዳዎች ላይ የመከሩባቸው ምክረ ሀሳቦች የተጠናቀረበት የመጨረሻ ሠነድ ነገ ለ 4 ሺህ ጉባኤተኞች እንደሚቀርብ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። በጎርጎሮሳዊው 2025 ዓ.ም. በዓለም ዙሪያ 350 የእርዳታ ሠራተኞች መገደላቸውን ያሳወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግድያዎች ተቀባይነት የሌላቸው ሲል ኮነነ የጀርመን አፍሪቃ ፋውንዴሽን የ35 ዓመቷን ወጣ ኬንያዊት ዋዊራ ንጂሩን ለዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት መረጠ። ንጂሩ የተመረጡት በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ኬንያውያን ተማሪዎች ምገባ በማደራጀታቸው ነው።

የነሐሴ 12 ቀን 2018 የዓለም ዜና 18.08.2026

-የኢትዮጵያ የፈደራል መንግስት ጦር መቀሌ አጠገብ የሚገኝ ሥፍራን ዛሬ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል በማለት ህወሓት ወቀሰ።ህወሓት በድብደባዉ ሥለደረሰዉ ጉዳት አልገለፀም።አንድ የዓይን ምስክር ግን ቢያንስ አንድ ታጣቂ መገደሉንና ሌሎች ሁለት መቁሰላቸዉን አስታዉቀዋል።---የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያዉያን የተሰጠዉ አሜሪካ የመኖርና የመሥራት ጊዚያዊ ፈቃድ እንዲሰረዝ ወሰነ።--የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረግም፣ ሊደረግ የታቀደም ድርድር የለም አሉ።የኢራን ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ዩናይትድ ስቴትስ የገባችዉን ግዴታ ካላከበረች ሥልታዊዉ ወሽመጥ አይከፈትም።

የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ሰኞ 17.08.2026

አርስተ ዜና --የሞሮኮ የጸጥታ ኃይሎች ድንበር አቋርጠዉ የስፔን ራስ-ገዝ ወደ ሆነችዉ ሴዑታ በየብስ እና በባህር አቋርጠዉ ለመግባት የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በቁጥጥር አዋሉ።-የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ኅልውና፣ ባለቤትነት እና የራስ-አስተዳደር መብት ዙሪያ "የክህደት ተግባር" ታይቷል ሲል እርምት ጠየቀ። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ባወጣዉ መግለጫ፤ የአብንን "ድምዳሜ የማይጋራው መሆኑን" ገልጿል።-የኢራን ጦር አንድ የአሜሪካ ወታደርን ለያዘ ወይም ለገደለ ሰው 30,000 ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታወቀ።

DW Amharic የነሐሴ 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና 16.08.2026

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልል “የፖለቲካ መሪዎች የሕዝቡን ድምጽ እንዲሰሙ፣ ሰዎችን እየጎዱ ያሉ ችግሮችን የጋራ መግባባት በመፍጠር ለመፍታት እንዲሞክሩ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ አቀረበ። የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሱዳን ሊካሔድ ለታቀደው ብሔራዊ ውይይት ተሳታፊዎች “ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊና የጸጥታ ዋስትና” ለመስጠት ቃል ገቡ። ለሊቱን በሩሲያና በዩክሬን በተፈጸሙ ኃይለኛ የድሮንና የሚሳይል ጥቃቶች በሁለቱም ሀገራት 12 ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 15.08.2026

የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው የቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሃት ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ “ በመንግስት የፀጥታ አባላት ተፈጸመ “ የተባለውን ግድያ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አወገዘ ፡፡ በኢትዮጵያ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች አሁንም "ከባድ" የሚባሉ ሥጋቶች መቀጠላቸውን የአውሮፓ ሕብረት ይፋ ባደረገው ኢትዮጵያን የተመለከተ የ2025 የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ገጽታ ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ይፋ ተደረገ።

የነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 14.08.2026

• ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒ ጄ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ጋዜጠኞች የሽብር ወንጀል ፈጽመናል ብለው አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚደረግባቸውን ግፊት አወገዘ። • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በብሄራዊ ጦሩ ላይ መጠነ ሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት መክፈቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። • ዩጋንዳ በሶማሊያ የሚገኘውን የሰላም አስከባሪ ኃይሏን እዚያው እንደምታቆይ አስታወቀች። • የኢቦላ ወረርሽኝ ኮንጎ ውስጥ ተዋህሲው እስካሁን ባልደረሰበት ግዛት ውስጥ ተከሰተ • ፈረንሳይ የእስራኤል ሰፋሪዎች በኃይል በተያዘችው የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የሚፈጽሙትን ጥቃት በይፋ አወገዘች።

የሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 13.08.2026

አ.አ፥ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ ሥጋት እንዳላቸው ገለጡ፣ አፋር፥ ብርቱ ድርቅ ባስከተለው የውኃ እጥረት የተነሳ የቤት እንስሳት እየሞቱ ነው፣ ሞቃዲሹ፥ ሶማሊያ ውስጥ ብርቱ የረሐብ አደጋ አንዣብቧል፣ ኪየቭ፥ ዩክሬን በጦርነቱ የሚሞቱ ሰላማዊ ሰዎች በከፍተኛ ኹኔታ ጨምሯል፣ ሞስኮ፥ ዩክሬን እና ሩስያ ድንበር ዘልቀው በድሮን እየተደባደቡ ነው፣ ቦጎታ፥ በኮሎምቢያ የደረሰው ብርቱ ርእደ መሬት የነፍስ አድን ፍለጋ የመጨረሻ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው

የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 12.08.2026

የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ወስደው እንዲፈርሙና ከእሥር እንዲፈቱ ጥያቄ እንደቀረበላቸው የገለፁ 30 የሽብር ተከሳሾች አንፈርምም ማለታቸው ተነገረ። በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከፃግምና አበርገሌ ወረዳዎች ተፈናቅለው ሰቆጣ ከተማ የተጠጉ ወገኖች ለከፋ የምግብ እና የመጠለያ እጥረት ተዳርገናል እያሉ ነው። የአስተዳደር ዞኑ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ አዲስ ለመጡት ካልሆነ ድጋፍ እየተደረገ ነው ይላል። ደቡብ አፍሪቃ ዜጎቻቸውን ወደ የሃገራቸው የመለሰችላቸው የሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት ወጪውን እንዲከፍሏት መጠየቋ ተሰማ።

የነሐሴ 5 ቀን 2018 የዓለም ዜና 11.08.2026

-የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር አላማጣ ከተማ አጠገብ ትምሕርት ቤት ዉስጥ የሰፈረ የትግራይ ተዋጊ ኃይልን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱን የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት አስታወቁ፤ አወገዙም።በጥቃቱ ተዋጊዎችም ሰላማዊ ሰዎችም መሞት መቁሰላቸዉ ተነግሯል።---በሱዳን መከላከያ ጦር የሚመራዉ የሐገሪቱ መንግሥት «ከኢትዮጵያ የተሻገሩ» ያላቸዉ የፈጥኖ ደራሽ ኃይላት አንዲት የድንበር ከተማ ማጥቃታቸዉን አስታወቀ።- የሆርሙዝ ወሽመጥን የወደፊት አጠቃቀም በተመለከተ ኢራንና ኦማን የሚያደርጉት ድርድር የመግባባት ፍንጭ ማሳየቱን ቀጠር አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የስማ በለዉ ድርድርም መዛዛት መወነጃጀሉም እንደቀጠለ ነዉ።

የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 10.08.2026

የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና -በምሥራቃዊ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በግንቦት የመጀመሪያ ሣምንት ከመታወጁ ሦስት ወራት ገደማ አስቀድሞ እንደነበር የዓለም የጤና ድርጅት ዛሬ አስታወቀ። -ዩክሬን በሩስያ ላይ በጣለችው የድሮን ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ 13 ሰዎች መገደላቸውን 39 ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። -ኮሎምብያና ጎረቤቶቿን የላቲን አሜሪካ ሀገራት በመታው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የርዕደ መሬት ንዝረት እስከ ኢኳዶር፣ ፓናማ እና ቬንዙዌላ ድረስ ተሰምቷል።

የነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 09.08.2026

• የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስቱ እና የክልል መሪዎች እውነተኛ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ጥሪ አቀረቡ ። • በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማፂያን በሳውዲ አረቢያ የቀይ ባሕር ዳርቻ በሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በድሮን ጥቃት ማድረሳቸውን አስታወቁ። • የሮማ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሱዳናዉያን የሰብአዊ ርዳታ የሚያልፍባቸው መስመሮች በአስቸኳይ እንዲከፈቱ ጥሪ አቀረቡ። • አሜሪካ ኦሬገን እያስተናገደች ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጡ።

የነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 08.08.2026

የዛሬው የዓለም ዜና በአለታ ወንዶ ከተማ በመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ከ178,000 በላይ ስደተኞች ከደቡብ አፍሪቃ መልቀቃቸውን፣ኢራን እና ኦማን ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል ማለታቸውን፣ኢራን በኤምሬትስ መርከብ ላይ ጥቃት ፈፀመች መባሉን፣በጀርመን ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ድሮኖች መታየታቸውን ፣እንዲሁምየአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት በሴውታ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ላይ ከትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር መምከሩን አካቷል።

የነሐሴ 1 ቀን 2018 የዓለም ዜና 07.08.2026

-የኢትዮጵያ መንግሥት ሐገርና ሕዝብ ጎድተዋል፣ ገንዘብ አጭበርብረዋል፣ በሙስና ተዘፍቀዋል ያላቸዉን ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ማሰሩን አስታወቀ።----የዩጋንዳ ጦር የጋዛን ሠላም ለማስከበር ይሰፍራል ለተባለዉ ዓለም አቀፍ ሠራዊት ወታደሮች እንዲያዋጣ የሐገሪቱ ምክር ቤት ወሰነ።የጋዛን ሠላም ያስከብራል የተባለዉ ዓለም አቀፍ ሠራዊት የሚሰፍርበት ጊዜ በዉል እይታወቅም።--ሳዑዲ አረቢያ፣ ቱርክና ፓኪስታን የጦር ቃል ኪዳን ሥምምነት ተፈራረሙ።የሶስቱ ሐገራት መሪዎች ዛሬ መካ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተፈራረሙት ሥምምነት መሠረት አንዱ ሐገር ከተጠቃ ሶስቱም እንደተጠቁ ይቆጠራል።

የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 06.08.2026

የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ። ከራያ አለማጣና አካባቢው በጦርነት ስጋት ከተፈናቀሉ ሴቶች መካከል በርካቶቹ ለአሰቃቂ የቡድን ጾታዊ ጥቃት፣ ለአካል ጉዳትና ለሕክምና እጦት ችግር መዳረጋቸውን አስታወቁ። የህክምና ባለሞያ ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑት ሴቶች ከለላ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ ስታንዳርድ ባለቤት Jakenn Publishing Plc እንዳስታወቀዉ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር በመንግሥት የሥለላ ኃይላት ከመታገቱ በተጨማሪ ተደብድቧል፤ ተንገላትቷል፤ ታስሯልም።

የሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 05.08.2026

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች የተከሰተው የዝናብ እጥረት የተለያዩ ሰብሎችና አትክልቶችን ለጉዳት መዳረጉን ነዋሪዎች እና የዞኑ አስተዳደር ለዶቼቬለ ተናገሩ። በዴሞክራቲክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ግዛት የተቀሰቀሰው የኢቦላ ተሐዋሲ ስርጭት መባባሱ ተገለጸ። የሟቾች ቁጥር ከ1,700 በልጧል። በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን በአንድ ተጨማሪ የሳዑዲ አረብያ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸመቸው ተዘገበ። ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭና አካባቢው ላይ በሚሳኤል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች ተገደሉ፤ ከ40 በላይም ቆሰሉ።

Écoute le podcast የዓለም ዜና sur Replaio

La radio et les podcasts dans une seule appli - gratuite, sans inscription. Installe-la dès aujourd'hui et ne rate pas le lancement

Télécharger sur Google Play

Replaio n'est pas éditeur de podcasts ; les noms des émissions, les visuels et l'audio appartiennent à leurs auteurs et sont diffusés via des flux RSS publics