SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Besuch unbedingt die Website des Podcasts und unterstütze die Macher: www.sbs.com.au
Wo hören?
Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbarPodcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts
Folgen
የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ 18.04.2024 9:51
በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ 16.04.2024 6:35
ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች? 16.04.2024 20:21
የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
"የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የማነአብ 16.04.2024 18:52
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።
" 'የመኢሶን ሰማዕታት' መጽሐፍ ፋይዳ አንድ ተጨባጭ የሆነ የታሪክ ሰነድ ማቆየት ነው" ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ 16.04.2024 12:03
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የድርጅታቸው የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት የመዘከሪያ መጽሐፍን መሰናዶና ትሩፋቶቹን አስመልክተው ያስረዳሉ።
የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ የገበያ ማዕከል በስለት የተገደሉ ስድስት ሰዎችን በክብርና በሐዘን ለመዘከር በግማሽ ዝቅ ብሏል 15.04.2024 6:35
አውስትራሊያ ኢራን በእሥራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አወገዘች
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተካተተች 14.04.2024 5:46
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች ከሥራና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች እንዲገለሉ የሚያደርግ ምዝገባ ልትጀምር ነው
ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ባቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ ገለልተኛና ሙሉዕ ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ 11.04.2024 4:30
ዩናይትድ ስቴትስ የዊኪሊክስ መሥራቹን ጁሊያን አሳንጅ ክስ ልታነሳ እንደምትችል ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አመላከቱ
#59 Talking about cooking (Med) 11.04.2024 13:31
Learn how to talk about cooking and sharing recipes.
ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ይጓዙ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ 10.04.2024 7:04
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ አውስትራሊያ ለፍልስጤም አገራዊ ዕውቅና ለመስጠት ዕሳቤ እንዳላት አመላከቱ
"ኢድ አልፈጥር! አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን፤ ደም ማፍሰሱን አላህ በኃይሉ ያስተካክልልን" ሼክ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር 10.04.2024 8:45
ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የዘንድሮውን ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የፆምና ፀሎት መንፈሳዊ ፋይዳዎችንና የሰላም ምኞታቸውን አሰናስለው ይገልጣሉ።
አውስትራሊያ ውስጥ ከ2035 አንስቶ በነዳጅና በናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዳይውሉ ጥሪ ቀረበ 09.04.2024 3:42
የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት አዲስ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሾመ
ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድርድር ሊቀጥል ነው 09.04.2024 9:33
በነዳጅ የሚሠሩና ሙሉ በሙሉ በውጭ አገር ተገጣጥመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ ተጣለ
በአዲሱ የምግብና ግሮሰሪ ሥነ ምግባር ደንብ ሱፐርማርኬቶች እስከ 10 ሚሊየን ዶላርስ የሚደርስ መቀጮ ሊያገኛቸው ነው 08.04.2024 6:59
የቀድሞው የአውስትራሊያ መከላከያ ኃይል አዛዥ በእሥራኤል የአየር ጥቃት ለተገደለችው አውስትራሊያዊት የእርዳታ ሠራተኛ ምርመራ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሰየሙ
"ኤልያስ ካለ ጎል አለ፤ አብዛኛዎቹ የመብራት ኃይል ቡድን ዋንጫዎች የኤልያስ ጁሐር ዋንጫዎች ናቸው" የፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 08.04.2024 11:49
"የኤልያስ ዋንጫ" አዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ በዘጋቢ ፊልም ቀርፀው ለሕዝብ ዕይታ ለማቅረብ ስለምን እንደወደዱና የፊልሙን ጭብጥ አሰናስለው ይናገራሉ። "የኤልያስ ዋንጫ" በሳምንቱ መጨረሻ በሜልበርን - አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ በነፃ ይቀርባል።
" የደብረ ዘይት በዓልን ስናከብር የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እያሰብን ነው ። ” መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ 07.04.2024 9:28
መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ በአውስትራሊያ የልደታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በትናንትናው እለት የተከበረውን የደብረ ዘይት በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ አደራ ብለዋል ።
በነባር ዜጎች መካከል ያለ ባሕላዊ ዝንቅነትን የመረዳት ጠቀሜታ 07.04.2024 7:28
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ከሆኑት የአቦሪጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ተሳትፎ በማድረግ ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመገንባት ካሹ በመካከላቸው ያሉ ባሕላዊ ዝንቅነቶችን መረዳት ግድ ይላል።
#58 How to say 'no' at work (Adv) 07.04.2024 15:19
Learn how to professionally and politely decline additional workload.
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ የአውስትራሊያዊቷን እርዳታ ሠራተኛ ሞት ተከትሎ የእሥራኤል መንግሥት ኃላፊነት እንዲወስድ ጠየቁ 03.04.2024 4:20
*** ሰማንታ ሞስቲን በአውስትራሊያ የንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ እንደራሴ ሆነው ተሾሙ
" የ29ኛው ኩዊል የጋዜጠኛነት ልህቀት ሽልማት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውያንም ጭምር ነው ። "- የኩዊል ሽልማት አሸናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ 02.04.2024 16:27
“ ይህ ታሪክ እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አይደለም ፤ ሲያነቡትም ሆነ ሲጽፉት ስሜትን የሚፈታተን ስለሆነ አጠናቅቆ ለማውጣት ስድስት ወራትን ፈጅቷል ። ” ሩቺካ ታልወር
“ ጋዜጠኝነት ለእኔ ሕዝብን እና አገርን በቀናነት ማገልገል ነው ። ” የኩዊል ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ 02.04.2024 20:59
“ በሽልማቱ ላይ ከተገኙት ሰዎች መካከል የኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ዝርያ ካላቸው የተገኘሁት እኔ ብቻ ነበርኩ ።ይህ የታሪክ አጋጣሚም የሽልማቱን ዋጋ በተለየ ሁኔታ ላቅ ብሎ እንዲታይ አድርጎታል ። ” ለሜልበርን ፕሬስ ክለብ በመድብለባሕል ጉዳዮችና ሚዲያ ዘርፍ በአውስትራሊያ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ሙያ የላቀ ደረጃ ያለውን 29ኛውን የኩዊል የጋዜጠኛንት ልህቀት ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ “ SBS ታሪኬን ሲያወጣ ከስደተኝነት ባሻገር ለአውስትራሊያ ማኅበረሰብ የማበረክተው እንዳለ እድርጎ አጉልቶ በማሳየቱ በበርካቶች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል ። ” ቤተልሔም ጥበቡ
የረመዳን ጾም እና የሴቶች ድርሻ 02.04.2024 16:00
ወይዘሮ ነጁም አብደላ የረመዳን ጾም ወቅት በመስጠት በረከትን የምንቀበልበት ቅዱስ ወር ነው ይላሉ። ወ/ሮ ነጁም የሜልበርን ነዋሪ እና የአራት ልጆች እናት ናቸው ፤ ምንም እንኳን ልጆቻቸውን ለብቻቸው ቢያሳድጉም ውጤታም ልጆችን ለማውጣት እና እርሳቸውም ያለሙትን የከፍተኛ ትምህርት ግብ ለማጠናቀቅ ብቸኝነታቸው እንዳላገዳቸው ነግረውናል ።
በአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውኃ እየተሟጠጠ ነው ተባለ 01.04.2024 6:45
*** በቀይ ባህር በተፈጠረው የጸጥታ ሁከት ሳቢያ የገቢ እና ወጪ ንግድ ላይ ችግር መፈጠሩ ተገለጠ
በኩዊንስላንድ የዝናቡ መጠን እንደቀነሰ ቢነገርም ፤ ውኃው እስኪደርቅ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገለጸ 01.04.2024 6:40
*** የአርስናል የሴቶች ቡድን ቼልሲን አንድ ለባዶ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆነ
በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ምዕመናን መገደላቸው ተመለከተ 28.03.2024 3:18
የአውስትራሊያ ጦር አዛዥ ይቅርታ ጠየቁ
Ähnliche Podcasts
Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet