SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au
Unde asculți?
Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curândPodcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor
Episoade
Embracing the wisdom of traditional Indigenous medicine - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ጥበብ ሞገስ ማላበስ 27.08.2024 8:31
Understanding and respecting Indigenous knowledge of medicine may be the key to providing more holistic and culturally sensitive care in today's healthcare setting. - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ዕውቀት መረዳትና ከበሬታንም መቸር፤ ጥንቃቄ የተመላበት ክብካቤን ለሚሻው ሁሉን አቀፍ የዘመናዊው ጤና ክብካቤ አወቃቀር ቁልፍ ሊሆን ይችላል።
"በ'ውጫሌ ውል' ተውኔት መክፈቻና መዝጊያ ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ፈንቅሎ የወጣ የጋለ ሀገራዊ ስሜት ነበር" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 27.08.2024 16:48
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ውልደትና ዕድገቱን፣ የቀለም ትምህርትና የትወና ጅማሮውን ነቅሶ ግለ ታሪኩን በከፊል አውግቷል። ወደ ቀጣዩ ግለታሪክ ትረካው ያመራው እንደምን ከአንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር ለመድረክ እንደበቃ በማንሳት ነው።
የአውስትራሊያ ሠራተኞች ከመደበኛ ሥራ ሰዓት ውጪ የስልክ ጥሪዎችንና ኢሚሎችን ያለመመለስ መብት ግብር ላይ ዋለ 26.08.2024 14:40
የአውስትራሊያ የአውሮፕላን ተጓዦች ተጨማሪ መብቶችን ሊያገኙ ነው
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይፋ ተደረገ 26.08.2024 14:40
የቻይናው አሊባባ በይነ መረብ የሸቀጦች ጅምላ መገበያያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የንግድ ሥራውን ለመጀመር ስንዱ መሆኑን አስታወቀ
ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና፤ ከወላይታ እስከ አውስትራሊያ 22.08.2024 15:36
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና ከስመ ገነን የተውኔት ተጠባቢዎች አንዱና ተጠቃሽ ነው። በሀገረ አውስትራሊያ ከቤተሰቡ፤ በሀገረ ኢትዮጵያ ከትወና ጋር ተዋድዶና ተዛንቆ አለ።
Why is sex and sexuality education taught in Australian schools? - SBS Examines: አውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የወሲብና ወሲባዊነት ትምህርት የሚሰጠው ስለምን ነው? 22.08.2024 5:11
Sex ed in schools is controversial, but experts say it's vital for young people to learn about their bodies, identities, and healthy relationships. Why are some parents concerned? - የትምህርት ቤቶች ወሲባዊ ትምህርት አወዛጋቢ ነው፤ ይሁንና ጠበብት የወጣቶች ስለ አካሎቻቸው፣ ማንነቶቻቸውና ጤናማ ግንኙነት መማር ወሳኝ እንደሁ ይናገራሉ። የተወሰኑ ወላጆች ስጋት ያደረባቸው ስለምን ነው?
በኢትዮጵያ ከ120 ሺህ በላይ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሚገኙና 1400ዎቹ ሕፃናት መሆናቸው ተመለከተ 21.08.2024 7:42
በሀገር ውስጥ ከተለያዩ ተቋማት ከሚመረቁ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች 42 ፐርሰንቱ ሥራ እንደማያገኙ ተገለጠ
"የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያው የሚያስከትለው የዋጋ ግሽበት ሀብትን ከፍተኛ ገቢ ላላቸው በተለይም ለነጋዴዎች ያሸጋግራል፤ ይህም በቅርብ ጊዜ የሚታይ ውጤት ነው" ዶ/ር ወርቁ አበራ 19.08.2024 23:12
ዶ/ር ወርቁ አበራ፤ በዶውሰን ኮሌጅ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰርና የምጣኔ ሃብት ዲፓርትመንት ሊቀመንበር በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግሥት ግብር ላይ የዋለው "ውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ" ፖሊስን አስመልክተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሀገራዊ ምክክር ተወካዮች ሰንደቅ ዓላማን አካትቶ እስከ መገንጠል የሚፈቅደው የፌዴራል ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ምክረ ሃሳብ አቀረቡ 18.08.2024 13:23
በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረመድኅን የተመራው የሕወሓት ጉባኤ የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የማዕከላዊ አባላትን ማግለልና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ሰብሳቢነት እየተካሔደ ያለው ሌላኛው "ሕወሓትን መታደግ" ጉባኤ በሕወሓት መካከል ተከስቶ ያለውን ልዩነት አስፍቶ ቀጥሏል።
#68 Discussing the news (Med) 14.08.2024 16:39
Learn how to talk about news that makes us feel scared or hopeful.
የሕወሓት ጉባኤ አወዛጋቢነቱ ቀጥሏል 14.08.2024 9:55
የኢትዮጵያና ሶማሊያ ውይይይት በአንካራ ተካሔደ
የአውስትራሊያ ኦሎምፒክ ቡድን ሲድኒ ላይ የሞቀ አቀባበል ተደረገለት 14.08.2024 7:03
የዝንጀሮ ፈንጣጣ አፍሪካን አስግቷል
"ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን 13.08.2024 17:37
እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።
"የዳያስፖራ ሰዎች ብዙ ማድረግ ስንችል ያለንን አጋጣሚና ሁኔታ መጠቀም ባለመቻላችን እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ ውስን ናቸው" ደራሲ አዳሙ ተፈራ 13.08.2024 7:50
ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ ሰሞኑን ለሕትመት ስለበቃው "ዳያስፖራው" መፅሐፋቸው አንኳር ጭብጦችና ፋይዳዎች ይናገራሉ።
"እሥራኤል ቃሎችን አትሰማም" የአውስትራሊያ ፌዴራል ሚኒስትር እሥራኤል ላይ ጠንካራ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳሰቡ 12.08.2024 6:39
የፓሪስ ኦሎምፒክ ተፈፀመ፤ ሎስ አንጀለስ የ2028 ኦሎምፒክ ተራን ተረከበች
"የዳያስፖራው መፅሐፍ ተልዕኮ በተለያዩ ምክንያቶች ለሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በሚሔዱባቸው ሀገራት ስለሚገጥማቸው ሁኔታ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው"ደራሲ አዳሙ ተፈራ 12.08.2024 12:59
ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ ሰሞኑን ለሕትመት ስለበቃው "ዳያስፖራው" መፅሐፋቸው አንኳር ጭብጦችና ፋይዳዎች ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ አቡ ሴራ በዓመት ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ ሊገነባ ነው 11.08.2024 13:20
ሕወሓት በምርጫ ቦርድ በልዩ ሁኔታ የተሰጠውን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እንደማይቀበል አስታወቀ፤ በሌላም በኩል ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት የሰጠው የምዝገባ ማረጋገጫ በተጭበረበረ ማስረጃ የተመሠረተ በመሆኑ ምርመራ እንዲካሔድበት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንትና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ
"እመቤቴ ማርያም" የንስሐ ዝማሬ በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዘማሪያን 08.08.2024 8:39
ዘማሪያን፤ ቤተልሔም ዘገየ ተፈራ፣ ሲካር ያሬድ፣ ደሊና ካሳሁን ላይችሉህ፣ አፎምያ ብስራት ታዬ፣ ቤቴል ጌታቸው ለገሰ፣ ኑኅሚን ወንድወሰን ክብረት፣ በጸሎት አስማረ ይታይህ፣ ማርያማዊት ጌታቸው ለገሰ፣ ማርያማዊት ገብረሕይወት ተፈሪ፣ ኤድና ብስራት ታዬ እና አርሴማ ተስፋዬ።
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ ቲም ዎልዝን በዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት መረጡ 07.08.2024 7:54
የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ በመካከለኛ ምሥራቅ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲከናወን ዳግም ጥሪ አቀረቡ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብይታቸው በዶላር ለሚካሔድ ዓለም አቀፍ በረራዎች የተለየ ለውጥ አለማድረጉን አስታወቀ 06.08.2024 9:13
ኢትዮጵያ ለ2017 ከተመደበው 971.2 ቢሊየን ብር በጀት ላይ ተጨማሪ ከ500 ቢሊየን ብር በላይ አክላ ልታፀድቅ ዝግጅት መደረጉ ተገለጠ
What is genocide? - SBS Examines: ዘር ማጥፋት ምንድነው? 06.08.2024 6:20
'Genocide' is a powerful term — it's been called the "crime of crimes". When does large-scale violence become genocide, and why is it so difficult to prove and punish? - 'ዘር ማጥፋት' እጀግ ብርቱ ቃል ነው፤ "የወንጀሎች ወንጀል" ተብሏልም። የመጠነ ሰፊ አመፅ ክስተት የዘር ማጥፋት ድርጊት ሆኖ ሲገኝ እውን መሆኑን ለማረጋገጥና ቅጣትን ለመጣል በእጅጉ አዋኪ የሚሆነው ስለምን ነው?
የአውስትራሊያ የሽብር ስጋት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ወደ 'ሊከሰት ይችላል' ከፍ አለ 05.08.2024 10:13
ከ40 ፐርሰንት በላይ ወጣት አውስትራሊያውያንና ከአራት አንድ ጎልማሶች ለብቸኝነት የተዳረጉ መሆኑ ተመለከተ
የአምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሥነ ሕዝብና ጤና ቆጠራ መጀመሩ ተገለጠ 04.08.2024 10:55
በአንድ ቀን ውስጥ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 542 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ
"ብር እየወደቀና የዋጋ ንረት እየበዛ የሚያስቸግር ከሆነ፤ዋጋውን ለመቆጣጠር ያለችን ትንሽ ቁልፍ የወለድ መጠን መጨመር ነው፤ያ ደግሞ ምርታማነትን ይጎዳል" ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024 21:55
ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግብር ላይ መዋሉን ስላስታወቀው "የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ" ፖሊሲ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች፣ የሚያስከትላቸውን መዘዞችና ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊቀሰሙ የሚገቡ ልምዶችን ነቅሰው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።
"የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ ትልቁ ችግር ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችንም ማናጋት መቻሉ ነው፤በጀትን ጨምሮ ከታክስ፣ እስከ ወለድ መጠን ድረስ"ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024 16:30
"ሚዲያ/ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መንግሥት ገንዘቡን ጣለ የሚለው ትክክል አይደለም። መንግሥት ገንዘቡን አይደለም የጣለው፤ ይደግፈው የነበረውን ብር ነው መደገፍ የተወው። በነፃ ገበያ እንዲወሰን ነው ያደረገው፤ ይህ ፖሊሲ ነው ብር እንዲወድቅ ያደረገው፤ ሁለቱን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል" የሚሉት ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ፖሊሲ ያስረዳሉ።
Podcasturi asemănătoare
Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice