SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categorie

News

Site-ul podcastului

www.sbs.com.au

Cel mai nou episod

18 nov. 2026

Unde asculți?

Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curând

Podcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor

Descarcă din Google Play Instalează gratuit Android 10 mil.+ descărcări · nota 4,7+ iOS în curând

Episoade

ዝክረ መታሰቢያ፤ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ገጣሚ ዜናነህ መኮንን 11.11.2024

"የኩላሊት ሕመም እንደያዘኝ ከማወቄ በፊት፤ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ የራሴ ስቱዲዮ እንዲኖረኝ ሃሳብ ነበረኝ" ያለን ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ገጣሚ ዜናነህ መኮንን በገጠመው የኩላሊት ሕመም ሳቢያ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተሰናብቷል። በሕይወት ሳለ ከ SBS አማርኛ ጋር ኢትዮጵያውያን ወገኖች ለሕመሙ መፈወሻ የችሮታ ጥሪ ያቀረበበትንና ስለ ሙያ ሕይወቱ በአንደበቱ የገለጠበትን ቃለ ምልልስ ዳግም አቅርበናል።

"በምንሔድበት ሁሉ ኢትዮጵያዊነታችንን አጉልተን የምንገልጥበት፤የይድነቃቸው ተሰማን ስም የምናስተዋውቅበት ተሞክሮዎች እንዲኖሩን ጥረቶችን እያደረግን ነው" አቶ ኢዮብ እሱባለው 11.11.2024

አቶ ኢዮብ እሱባለው፤ የይድነቃቸው ተሰማ ማኅበራዊ እግር ኳስ ክለብ የስልጠና ክፍል ኃላፊ፤ ከኦክቶበር 25-27 የይድነቃቸው ተሰማን ቡድን አካትቶ 313 ቡድኖችና ከ4000 በላይ ታዳጊ ወጣቶች ተሳትፈው የእግር ኳስ ግጥሚያ ስለተካሔድበት የሸፐርተን ዋንጫ 2024 ሂደትና ውጤት ይናገራሉ።

ኢትዮጵያ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ከሆኑባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል በሁለተኛነት ተጠቀሰች 10.11.2024

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ አርጌ በተባለች አነስተኛ ከተማ ሰሞኑን በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከ60 በላይ እንደቆሰሉ ተመለከተ

"ኢትዮጵያ ውስጥ የፅንስ ማቋረጥ/ማስወረድ ሕግ አንዳለ የሚያውቁ ዜጎች 55 ፐርሰንት ያህል ብቻ ናቸው፤ የግንዛቤ ክፍተት አለ" ዶ/ር ግዛቸው ተሰማ 10.11.2024

ዶ/ር ግዛቸው ተሰማ፤ በከርቲን ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ፅንስን የማቋረጥ / የማስወረድ አፋላሚ አስባብ ከሆኑት ከሕግ፣ ሃይማኖት፣ ሕክምና፣ ፖለቲካና ሥነ ምግባር አኳያ ነቅሰው ያስረዳሉ።

"ኢትዮጵያዊነት የደም፣ የባሕልና የቋንቋ ልውውጥ ውጤት ነው" ዶ/ር አውግቸው አማረ 07.11.2024

ዶ/ር አውግቸው አማረ አጎናፍር፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ናቸው። በ Journal of Afroasiatic Languages, History and Culture (JAAL) ላይ "በኢትዮጵያ የሕዝብና ባሕል ትስስር የጦር ሠራዊቱን ሚና የሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች (ከ14ኛው እስከ 16ኛው መካከለኛ ክፍለ ዘመን)" በሚል ርዕስ መጣጥፋቸውን ለሕትመት አብቅተዋል። በዘመኑ 'የጨዋ ሠራዊት' ተብሎ ይጠራ ስለነበረው የጦር አደረጃጀት ታሪክና የብሔራዊ ማንነት ግንባታ አስተዋፆ ታሪካዊ ዋቤ ነቅሰው ያመላክታሉ።

"የጨዋ ሠራዊት በተሠማራበት ሁሉ ቀልጦ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በማስጠበቅ ቀጣይ አድርጓል" ዶ/ር አውግቸው አማረ 06.11.2024

ዶ/ር አውግቸው አማረ አጎናፍር፤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ናቸው። በ Journal of Afroasiatic Languages, History and Culture (JAAL) ላይ "በኢትዮጵያ የሕዝብና ባሕል ትስስር የጦር ሠራዊቱን ሚና የሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች (ከ14ኛው እስከ 16ኛው መካከለኛ ክፍለ ዘመን)" በሚል ርዕስ መጣጥፋቸውን ለሕትመት አብቅተዋል። በዘመኑ 'የጨዋ ሠራዊት' ተብሎ ይጠራ ስለነበረው የጦር አደረጃጀት ታሪክና የብሔራዊ ማንነት ግንባታ አስተዋፆ ታሪካዊ ዋቤ ነቅሰው ያመላክታሉ።

#74 Talking about your pet peeves (Med) 06.11.2024

Learn how to talk about things that annoy you.

ዩናይትድ ስቴትስ በአማራ ክልል እየተባባሰ ያለው ግጭት አሳሳቢ ነው አለች 05.11.2024

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ከ700 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ብድር ፈቀደች

"የአንድ ሀገር የመሬት ፖሊሲ መቀረጽ ያለበት የመንግሥት ስልጣንን መገደብና የአርሶ አደሮችን መብትና ነፃነት ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ነው" ዶ/ር ብራይትማን ገ/ሚካኤል 05.11.2024

ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል ጋንታ፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመሬት አስተዳዳር ተቋም የሕግ መምህርና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መብቶች ክፍል ዳይሬክተር ናቸው። በቅርቡ "Federalism and Land Rights in the Context of Post-1991 Ethiopia" በሚል ርዕስ በ Journal of Development Societies ላይ ለሕትመት ያበቁትን ጥናታዊ መጣጥፋቸውን አስመልክተው ያስረዳሉ።

"መሬትን በብሔር ከተረዳነው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ዜጋ ከተወለደበት ሥፍራና ከብሔሩ ውጪ መሬት የማግኘት ዕድሉ ጠባብ ነው" ዶ/ር ብራይትማን ገ/ሚካኤል 05.11.2024

ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል ጋንታ፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመሬት አስተዳዳር ተቋም የሕግ መምህርና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መብቶች ክፍል ዳይሬክተር ናቸው። በቅርቡ "Federalism and Land Rights in the Context of Post-1991 Ethiopia" በሚል ርዕስ በ Journal of Development Societies ላይ ለሕትመት ያበቁትን ጥናታዊ መጣጥፋቸውን አስመልክተው ያስረዳሉ።

"አሁን ላለንበት የፖለቲካ ቀውስ የመሬት ባለቤት ሕገ መንግሥቱ ላይ የሠፈረውን ብሔርን መሠረት ያደረገ አረዳድ ስላለ ነው" - ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል 05.11.2024

ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል ጋንታ፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመሬት አስተዳዳር ተቋም የሕግ መምህርና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መብቶች ክፍል ዳይሬክተር ናቸው። በቅርቡ "Federalism and Land Rights in the Context of Post-1991 Ethiopia" በሚል ርዕስ በ Journal of Development Societies ላይ ለሕትመት ያበቁትን ጥናታዊ መጣጥፋቸውን አስመልክተው ያስረዳሉ።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ቢያንስ ሶስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ 03.11.2024

የዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አስነሳ

ስምንት የአውስትራሊያ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ሊባኖስ ውስጥ በእሥራኤል በተወነጨፈ ሮኬት ቀላል የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው 30.10.2024

ቪክቶሪያ የኪራይ ቤት ሕጎችን አጠበቀች

"አንድ አገር እየኖሩ በቋንቋ አለመግባባት አገሪቱ ፀንታ ለመኖር ያላትን ዕድል ያመነምነዋል፤ ብሔራዊ ቋንቋ ያስፈልጋል" ፕ/ር አዴኖ አዲስ 29.10.2024

በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የሕዝባዊና ሕገ መንግሥታዊ ሕግ ፕሮፌሰር አዴኖ አዲስ "አገራችን ብዙ ቋንቋዎች አሏት፤ መራራቂያ እንጂ መቀራረቢያ አላደረግናቸውም" ይላሉ። በቅርቡ "The Making of Strangers: Reflections on Ethiopian Constitution" በሚል ርዕስ በ "Journal of Developing Societies" መጽሔት ላይ ለሕትመት ስላበቁት መጣጥፋቸው ይዘት ያስረዳሉ።

"ብሔር ተብሎ መዋቀርና የመገንጠል መብት ባይኖር ኖሮ፤ የወሰን ሽኩቻው እንደዚህ አይብስም ነበር" ፕ/ር አዴኖ አዲስ 29.10.2024

በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የሕዝባዊና ሕገ መንግሥታዊ ሕግ ፕሮፌሰር አዴኖ አዲስ "የብሔር ማንነት እየጠነከረ የሔደው በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን፣ በሃይማኖትም፤ በብዙኅን መገናኛም ነው" ይላሉ። በቅርቡ "The Making of Strangers: Reflections on Ethiopian Constitution" በሚል ርዕስ በ "Journal of Developing Societies" መጽሔት ላይ ለሕትመት ስላበቁት መጣጥፋቸው ይዘት ያስረዳሉ።

"የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አፈፃፀሙ ብቻ ሳይሆን አወቃቀሩ አገሪቱ አሁን ላለችበት ችግር ትልቅ አስተዋፅዖ አለው" ፕ/ር አዴኖ አዲስ 29.10.2024

በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የሕዝባዊና ሕገ መንግሥታዊ ሕግ ፕሮፌሰር አዴኖ አዲስ "ሕገ መንግሥት ማለት ሕዝብን የሚያስተሳስር ዜጎች ዕጣ ፈንታችን አንድ ነው ብለው ተያይዘው የሚጓዙበት ጎዳና፣ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመመሥረት የሚያስችል ዘርፍ ነው፤ የአንድነት መኖሪያና ተስፋ መግለጫ ሰነድ ነው" ይላሉ። በቅርቡ "The Making of Strangers: Reflections on Ethiopian Constitution" በሚል ርዕስ በ "Journal of Developing Societies" መጽሔት ላይ ለሕትመት ስላበቁት መጣጥፋቸው ይዘት ያስረዳሉ።

Is democracy on the decline in Australia? - የአውስትራሊያ ዲሞክራሲ እያሽቆለቆለ ነውን? 29.10.2024

Home Affairs Minister Clare O’Neil has labelled democracy our most precious national asset. But some people say it’s at risk. - የቀድሞዋ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች (የወቅቱ የቤቶች) ሚኒስትር ክሌር ኦኒል ዲሞክራሲን በብርቅ ብሔራዊ ቅርስነት መስለውታል። የተወሰኑ ወገኖች በፊናቸው ለአደጋ ተጋልጦ ያለ ስለመሆኑ ይናገራሉ።

#73 When public transport goes wrong (Med) 28.10.2024

Learn how to communicate when using public transport, particularly when there are disruptions.

ዴቪድ ክሪሳፉሊ የኩዊንስላንድ 41ኛው ፕሪሚየር ሆነው ቃለ መሐላ ፈፀሙ 28.10.2024

የዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ብርቱ መዘዞችን የሚያስከትል እንደሁ ካማላ ሃሪስ አመላከቱ

የኤርትራ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3.7 ሚሊየን ዶላር እንዲከፍለው ጠየቀ፤ በሀገር ውስጥ ፍርድ ቤትም ክስ መሠረተ 27.10.2024

በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 127 የአሳት፣ ጎርፍና ሌሎች አደጋዎች መከሰታቸው ተገለጠ

ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ዝግጁነቷን አስታወቀች 22.10.2024

በአማራ ክልል የወባ በሽታ ከምንጊዜውም በላይ መስፋፋቱና ከ600 ሺህ በላይ በበሽታው መጠቃታቸው ተገለጠ

Rumours, Racism and the Referendum - አሉባልታ፣ ዘረኝነትና ሕዝበ ውሳኔ 22.10.2024

Misinformation and disinformation were rife during the referendum. The effects are still being felt a year on. - የተሳሳተ መረጃና አሳሳች መረጃ በሕዝብ ውሳኔ ወቅት ስር ሰደው የተሰራጩ ነበሩ። አንድ ዓመት አስቆጥሮም የጉዳት ስሜቱ አለ።

የኩዊንስላንድ የምርጫ ዘመቻ ብርቱ ፉክክርና እሰጥ አገባ እያሳየ ነው 21.10.2024

ዩናይትድ ስቴትስ በምስጢር የተያዘ የእሥራኤል ኢራንን የማጥቃት ዕቅድ እንደምን ሾልኮ አደባባይ እንደዋለ ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች

" 'ማንኛውም ዜጋ መራብ የለበትም' የሚለው መብት እየተጠበቀ አይደለም፤ ቀውሱ ሰፍቶ እየቀጠለ ነው" ዶ/ር ሚሊዮን በላይ 21.10.2024

ዶ/ር ሚሊዮን በላይ፤ Alliance for Food Sovereignty for Africa ዋና አስተባባሪ፤ ከ45 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 200 ወጣቶች አዲስ አበባ ስለታደሙበት የአፍሪካ ምግብ ሉዓላዊነት፣ የሰላም ጉዳይ፣ ግብርና፣ የምግብ ኢንተርፕሬነርሺፕና መሰል ጉዳዮች ላይ ስለመከረው የ "1000 ወጣቶች ጉባኤ" ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያ ከ86 ሚሊየን በላይ በድህነት ውስጥ የሚገኝ ሕዝብ በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሥፍራ መያዟን ተመድ አመለከተ 20.10.2024

ኢትዮ - ቴሌኮም ያስጀመረው የ30 ቢሊየን ወይም 10 በመቶ ድርሻ አክሲዮን ሽያጭ በኢትዮጵያ ብርና ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተፈቀደ መሆኑ ተነገረ

Ascultă podcastul SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ în Replaio

Radio și podcasturi într-o singură aplicație - gratuit și fără înregistrare. Instaleaz-o azi și nu rata lansarea

Descarcă din Google Play

Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice