SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categorie

News

Site-ul podcastului

www.sbs.com.au

Cel mai nou episod

12 nov. 2026

Unde asculți?

Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curând

Podcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor

Descarcă din Google Play Instalează gratuit Android aproape 10 mil. descărcări · nota 4,7+ iOS în curând

Episoade

የውይይት መድረክ፤ የአውስትራሊያ ሚና ለሰሜን ኢትዮጵያና ኢትዮ-ኤርትራ ግጭትና ውጥረት ቅነሳ 16.10.2026

ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የአውስትራሊያ መንግሥት ለኢትዮጵያና ኤርትራውያን አውስትራሊያውያን፤ ዐልፎም ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በማሳደር ረገድ ለሰላም መስፈን እንደምን የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ያላቸውን ግለ አመለካከቶች ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast

የውይይት መድረክ፤ የኢትዮ-ኤርትራ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የወደብ አጠቃቀም 15.10.2026

ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የኢትዮጵያና ኤርትራን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማስከበርን በተመለከተ አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ። #sbsaudiopodcast

የውይይት መድረክ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያ - ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ጫና 15.10.2026

ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው ጦርነት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከርረው ያሉት ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ውጥረቶች በሀገረ አውስትራሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፤ ትውልደ - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደራቸውና ሊያሳድሯቸው ስለሚችሉት ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast

በርካታ አውስትራሊያውያን መንግሥት በቤት ኪራይ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ላይ ጣልቃ ቢገባ እንደሚሹ ገለጡ 14.10.2026

በራፕ ኮከቡ ቱፓክ ሻኩር ግድያ የተከሰሰው ግለሰብ የ40 ዓመት እሥራት ተበየነበት #sbsaudiopodcast

የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳይኖረው ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለጠ 14.10.2026

በኢትዮጵያ በዓመት 600 ቶን ወርቅ የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ተመረቀ #sbsaudiopodcast

ሕጎች እንዴት ነው የሚቀረፁት፤ እርስዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩትስ እንደምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር 12.10.2026

ሕጎች አውስትራሊያ ውስጥ የሚቀረፁት እንደምን ነው? በዉራንጄሪው አረጋዊ አጎት ዴቭ ዋንዲን አማካይነት የቢራራንግ እንዲሁም ያራ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ወንዝ ታሪክ ይቅሰሙ፤ እንደምን ፅንሰ ሃሳብ ለረቂቅ ድንጋጌነት እንደበቃ፤ በቪክቶሪያ ፓርላማ ይሁንታን እንዳገኘና ንጉሣዊ ፅድቅ ተችሮት ለሕግነት እንደበቃ። አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራ...

"የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026

ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast

"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026

ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast

ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ 10.10.2026

ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏ...

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏል 09.10.2026

ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛቷ በአስቸኳይ እንዲወጡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመለከተች #sbsaudiopodcast

"ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 06.10.2026

ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ። #sbsaudiopodcast

ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል 06.10.2026

ዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ። #sbsaudiopodcast

Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደምትተገብር 05.10.2026

After receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ...

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር 05.10.2026

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች #sbsaudiopodcast

የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው 05.10.2026

አውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች #sbsaudiopodcast

የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል 04.10.2026

በርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል። #sbsaudiopodcast

#119 Talking about hay fever (Med) - #119 Talking about hay fever (Med) 01.10.2026

Learn English useful for talking about hay fever. Practise everyday phrases for describing symptoms, talking about medicine, and responding kindly when someone has hay fever. - ስለ ሄይ ፊቨር (hay fever) ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩን ይጠቀሙ። የሕመም ምልክቶችን ገላጭ ስለሆኑ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎች፣ ስለ መድኃኒትና በሄይ ፊቨር የታመመን ሰው በትሁት አንደበት ማናገርን ይለማመዱ። Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz...

የአውስትራሊያ መንግሥት ቬይትናም ውስጥ አንድ ለእሥር የተዳረገ ዜጋውን እንዲያስፈታ ግፊት እየተደረገበት ነው 30.09.2026

የአውስትራሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪ ለመንግሥት የምጣኔ ሀብት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ እንዲያካሂድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሁ አመላከተ #sbsaudiopodcast

"ኢሬቻ ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት እንጂ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም፤ መልካም የኢሬቻ በዓል" አቶ አብደታ ሆማ 30.09.2026

አቶ አብደታ ሆማ፤ የቪክቶሪያ ኢሬቻ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ሜልበርን አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን መከበር እንደጀመረና ዘንድሮም እንደምን ተከብሮ እንደዋለ ይናገራሉ። #sbsaudiopodcast

" 'ኢሬቻ ከጨለማ አውጥተኸን ለብርሃን ስላደረስከን እናመሰግናለን' የሚባልበት ቀን ነው" ወ/ሮ ይፍቱ ሚደቅሳ 29.09.2026

የኢሬቻ በዓል 2026 በሜልበርን Wilson Botanic Park እሑድ መስከረም 17 / ሴፕቴምበር 27 በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ተከብሮ ውሏል። ከታዳሚ የማኅበረሰብ አባላት እስከ አባ መልካ የበዓሉን አከባበር አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast

Who really runs Australia, and where you fit in | How Australia Works - በእርግጥ አውስትራሊያን የሚያስተዳድረው ማን ነው? የእርስዎ ሥፍራስ የት ነው? | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር 28.09.2026

Do you know who can help you with a business permit, a rental problem or family support? Through the stories of Fedele, Carol and Abeer, learn how Australia’s three levels of government work. Find out what local, state or territory, and federal governments are responsible for and where to turn for help. - የንግድ ፈቃድ ለማግኘት፣ የቤት ኪራይ ችግርዎን ለመፍታት ወይም የቤተሰብ ድጋፍ ለማግኘት ማን ሊያግዝዎ እንደሚችል ያውቃሉን? ከፌደል፣ ካሮልና አቢር...

You are already inside the system | How Australia Works - ከወዲሁ ሥርዓተ ስሪቱ ውስጥ ተካትተዋል | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር 28.09.2026

How do Australia’s governments, laws and public services affect your everyday life? Through real stories, this introduction to the series shows you where to start when you need information and support, and how to question a decision. - የአውስትራሊያ መንግሥታት፣ ሕጎችና ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደምን የእርስዎ የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተፅዕኖ አንዳላቸው? እውነተኛ ታሪኮችን ተመርኩዞ፤ ይህ መንደርደሪያ መረጃንና ድጋፍን ሲሹ፤ ሲልም በውሳኔ ላይ ጥያቄን ለማንሳት ከተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹ ው...

የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረትና የውጭ ሀገር መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ስጋቶቻቸውን ገለጡ 28.09.2026

በ 660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የኢትዮ - ጂቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጠ #sbsaudiopodcast

የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የበጀት ጉድለት ከተገመተው ያነሰ ሆኗል 28.09.2026

አምስት ግለሰቦች ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ላይ ለጥቃት በተጠቀመችበት አንድ የእንግሊዝ አየር ኃይል ጦር ሠፈር አካባቢ በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ #sbsaudiopodcast

" እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ " - መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ 27.09.2026

መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ በሜልበርን የደብረሰላም መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ የዘንድሮውን በአል አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። #sbsaudiopodcast

Ascultă podcastul SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ în Replaio

Radio și podcasturi într-o singură aplicație - gratuit și fără înregistrare. Instaleaz-o azi și nu rata lansarea

Descarcă din Google Play

Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice