SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Vizitează neapărat site-ul podcastului și susține-i creatorul: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categorie

News

Site-ul podcastului

www.sbs.com.au

Cel mai nou episod

18 nov. 2026

Unde asculți?

Podcasturi în aplicație Replaio Radio În curând

Podcasturile ajung în curând în aplicație. Instaleaz-o acum și fii primul care descoperă o abordare complet nouă a podcasturilor

Descarcă din Google Play Instalează gratuit Android 10 mil.+ descărcări · nota 4,7+ iOS în curând

Episoade

"የኢኮኖሚ ዕድገት ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ያደርጋል፤ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት የሚያስገኘውን ጥቅም እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም 12.09.2025

ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ለሕትመት ስላበቁት መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ይናገራሉ።

2018 - አዲስ ዓመት፣ አውደ ዓመት፣ ዕንቁጣጣሽ 11.09.2025

የ"ክብረ በዓላት፤ ሃይማኖትና ባሕል" መፅሐፍ ደራሲ መላኩ ጌታቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘመን ቅመራና ባሕላዊ አከባበር ያስረዳል።

"አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 10.09.2025

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

" አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋበት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ" - ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ 10.09.2025

ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋብት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

" አዲሱ አመት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን "- ሼህ አብዱራህማን 10.09.2025

ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ አዲሱ የ2018 አመተ ምህረት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

"ዕንቁጣጣሽ ወዳጅነትና ክብር በተመላበት መልኩ ሁሉንም የማሰባሰቢያ ጊዜ ነው፤የእናንተ ስኬት የአውስትራሊያ ስኬት ነው፤መልካም አዲስ ዓመት!" የተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ 10.09.2025

የአውስትራሊያ ፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ፤ ለኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት።

"ኢትዮጵያዊነት ልዩ ኩራታችን ነው፤ ይህን አዲስ ዓመት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለልጆቿ የሰላም፣ የጤናና የሕዳሴ ያድርግልን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ 09.09.2025

"አንድ ስንሆን፤ ሳንለያይ ብዙ መስራት እንደምንችል ይህ [ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ] ትልቅ ምሳሌ ነው። እግዚአብሔርም የግርማዊ ጃንሆይን ሕልም ተሠርቶ ስላሳየን ስሙ ምስጉን ይሁን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ

የአባቶች ቀን አከባበር በሀገረ አውስትራሊያ 08.09.2025

አቶ ጉግሳ አሊጋዝ "ለኢትዮጵያውያን ሁሌም የአባቶች ቀን ነው። እኛ ጥሩ አባቶች ነን። ልጆቼን እጅግ በጣም ነው የምወዳቸው፤ በእዚህ ምድር ላይ በጣም ያስደሰተኝ ነገር ቢኖር ከልጆቼ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ነው " ሲሉ፤ አቶ ኃይለማርያም ኃይለየሱስ በበኩላቸው "እግዚአብሔር በልጆች ባርኮኛል፤ ልጆቼን በፍቅር ነው ያሳደግኳቸው። የወላጅ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ ብዬ አስባለሁ። ልጆቼም ለእኔ ትልቅ ፍቅርና አክብሮት አላቸው፤ የአባቶችን ቀን በጣም ደስ ብሎኝ ነው ያከበርኩት" ይላሉ።

"አዲሱን ዓመት ስናከብር በአንድነቷ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ጠንክራችሁ የምትቀጥሉበት ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" አምባሳደር አንዋር ሙክታር 08.09.2025

አኑዋር ሙክታር፤ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ አምባሳደር፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 233 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አስታወቀ 08.09.2025

በሰሜን ጎንደር ዞን ድርቅ ስጋት ማስከተሉ ተመለከተ

የቀን መቁጠሪያችን የማንነታችንን መገለጫ እሴቶቻችን አንዱ ነው ፤ ይህንንም ቤ/ክ ብቻ ሳትሆን መላው ኢትዮጵያውያን የማስጠብቅ ሀላፊነት አለብን 07.09.2025

ከኢትዮጵያውያን ማንንት መገለጫ አንዱ ልዩ የሆነ የቀን መቁጠሪያችን ነው ። ምንጩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ቢሆንም አገልግሎቱ ግን ለመላው ኢትዮጵያውያን ነው በዚህም ልንኮራ ይገባናል፤ የሚሉን መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት የሜልበርን ምእራፈ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያ አስተዳዳሪ እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ቀሲስ ቴዎድሮስ በሜልበርን ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው።

የጳጉሚት ወር በአትዮጵያውያን የቀን መቁጠሪያ የአመቱን ትርፍ ቀናት ሸክፋ የያዘች ልዩ ወር ናት ። 06.09.2025

መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት የሜልበርን ምእራፈ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያ አስተዳዳሪ ፤ እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ቀሲስ ቴዎድሮስ በሜልበርን ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የጳጉሜ ወር ትርጓሜን ፤ ሀይማኖታዊ እና አገራዊ ጠቀሜታን አስረድተውናል

#94 Talking about autism (Med) - #94 Talking about autism (Med) 05.09.2025

Learn how to talk about Autism Spectrum Disorder respectfully. Understand common autism symptoms and use simple language to describe autism in everyday conversations. - Learn how to talk about Autism Spectrum Disorder respectfully. Understand common autism symptoms and use simple language to describe autism in everyday conversations.

"ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መጪው ዘመን ከትናንት የተሻለ፣ ሀገራችን ገናናነቷ ጎልቶ የሚወጣበትና አብረን የምንቆምበት እንዲሆን እመኛለሁ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 04.09.2025

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

"ለመላ ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመት! አብረን እናሳልፍ፤ አንድ ጎረቤት አንድ ጓደኛ ይዛችሁ ኑ፤ በባሕላችሁ ተደሰቱ!" የአዲስ ዓመት ቅበላ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት 03.09.2025

አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የመድረክ መሪ፤ በሜልበር ፉትስክሬይ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6 / ጳጉሜን 1 በሚካሔደው የአዲስ ዓመት ቅበላ ልዩ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲገኙ ይጋብዛሉ።

"የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ፉትስክሬይ ላይ ማድረጋችን፤ የሕዝባችን ሱቆችና ንግዶች ብዛቱና የመገናኛ ቦታው ፉትስክሬይ ስለሆነ ነው" ዳይሬክተር ካሪም ደጋል 03.09.2025

አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የመድረክ መሪ፤ በሜልበር ፉትስክሬይ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 6 / ጳጉሜን 1 ስለሚካሔደው የአዲስ ዓመት ቅበላ ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ 46 በመቶ የሚሆነውንና የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጠ 02.09.2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራ ማኅበረሰብ 50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አዘጋጅቻለሁ አለ

የፀረ ፍልስተኞች የተቃውሞ ሰልፍ ውግዘት ደረሰበት 01.09.2025

የትራምፕ አስተዳደር ፍልስጥኤማውያንን የቤት ኪራይ ገንዘብ ሰጥቶ ከጋዛ ለማስወጣት መወጠኑ ተጠቆመ

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 4 ቀን ይመረቃል ተባለ 01.09.2025

የቦይንግ ኩባንያ አዲሱ የአውሮፕላኑ ሞዴል በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ፍተሻ ይደረግለታል አለ

ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር 30.08.2025

ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።

"ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር 30.08.2025

"የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን ከእሥር እንዳስለቀቀው ነቅሶ ያወጋል።

ዓለም አቀፍ በረራዎች ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመቀሌ፣ ባሕርዳርና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሊጀመር ነው 27.08.2025

የግዕዝ ቋንቋ ከመጪው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በአማራ ክልል ከሶስተኛ ክፍል በመጀመር እንደሚሰጥ ተገለጠ

"የአሸንዳ በዓል ሃይማኖታዊም ባሕላዊም ነው፤ ክብርና ልጅነታችንን ያስታውሳል፤ የሴቶች በዓል በመሆኑ የነፃነታችን በዓል ነው" ነርስ ሰላማዊት ደሞዝ 27.08.2025

በተለይ የሴቶች ልዩ በዓል የሆነው ሀገር በቀሉ የአሸንዳ ክብረ በዓል በሜልበርን አውስትራሊያ ቅዳሜ ነሐሴ 17 / ኦገስት 23 በትግራይ ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ በሐሴት ተመልቶ፤ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በቪክቶሪያ የትግራይ ሴቶች ማኅበር አመራር አባላትና የበዓሉ ተሳታፊዎች የአሸንዳ በዓል ስሜቶቻቸውን ገልጠዋል፤ ለመላ ኢትዮጵያውያንም የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢ-ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ነው፤ 32 በመቶ የሚሆነው የማኅበረሰብ ክፍልም ሱስ ውስጥ ይገኛል 25.08.2025

የውጭ ዜጎች በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ለሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት በእጥፍ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ

"ትዝታ ትናንትን በምልስት በማውሳት ዛሬ ላይ ሕይወት ዘርተን የምናቆየው ነው፤ ለፊልሜ መጠሪያ ያደረግኩትም ቃለ መልዕክቱ ለልብና ለነፍስ ስለሆነ ነው"አራማዝት ካላይጂያን 22.08.2025

የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ። አርመናውያን በአጼዎቹ ዮሐንስ አራተኛ፣ ዳግማዊ ምኒልክና ቀዳማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥታት ውስጥ ከአድዋ ጦርነት ጣሊያንን መመከቻ መሣሪያ አበርካችነት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ግንባታዎችና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ መስኮች ያበረከቷቸውን ሁነኛ አስተዋፅዖዎች ያነሳሉ። ትዝታ ነሐሴ 25 /ኦገስት 31 በሜልበርን Lido Cinemas ለሕዝብ ይቀርባል።

Ascultă podcastul SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ în Replaio

Radio și podcasturi într-o singură aplicație - gratuit și fără înregistrare. Instaleaz-o azi și nu rata lansarea

Descarcă din Google Play

Replaio nu este editorul podcasturilor; numele emisiunilor, coperțile și materialul audio aparțin autorilor lor și sunt distribuite prin fluxuri RSS publice