DW

ከኤኮኖሚው ዓለም

Business AM ↓ 100 episodes

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።

Author

DW

Category

Business

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የኢትዮጵያ መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የተመለከቱ አሐዞች የገበያውን እውነታ ምን ያክል ያሳያሉ? 18.06.2025

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በግንቦት ወር የዋጋ ግሽበት 14.4% ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እንቁላል፣ አትክልት፣ ሥጋ እና ስኳርን መሰል ግብዓቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። የዋጋ ግሽበት 34.5% ከደረሰበት ከ2014 ወዲህ በከፍተኛ መጠን ቢቀንስም የኑሮ ውድነት አሁንም ሸማቾችን በኃይል እየተፈታተነ ይገኛል።

ከኢትዮጵያ የ2018 አጠቃላይ በጀት 24 በመቶ ገደማ ለዕዳ ክፍያ ተመደበ 11.06.2025

ከ2018 የኢትዮጵያ 1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት 463 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ ተመድቧል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት “የተሟላ” የሚሉት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ያተኮረው በጀት ለአዳዲስ ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልመደበም። በቀጣዩ ዓመት 1.2 ትሪሊዮን ብር ገቢ ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ አዳዲስ የታክስ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ እንደሚያውል መንግሥት አስታውቋል።

የዶናልድ ትራምፕ ታክስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ሐዋላ ወደ ኢ-መደበኛው ገበያ ሊገፋ ይችላል 04.06.2025

በአሜሪካ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ሰዎች ሐዋላ ሲልኩ 3.5 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ የሕግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ የሴኔቱን ይኹንታ እየጠበቀ ነው። ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአሜሪካ ሐዋላ በሚቀበሉ በርካታ ሃገራት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለውጥ ለገበሬዎች ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? 28.05.2025

ከ60,000 በላይ የልማት ሠራተኞች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት መሠረታዊ ለውጥ የሚያደርግበት ምዕራፍ ላይ ነው። አገልግሎቱ እስከ ቀበሌ የተዘረጋ መዋቅር ቢኖረውም ውጤታማ አይደለም። መንግሥት ተቆጣጥሮት የቆየውን አገልግሎት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የግሉን ዘርፍ ጨምሮ ለሌሎች ተዋንያን አሳልፎ ለመስጠት ቆርጧል።

የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በሥራ ላይ ከሚገኙ ባንኮች አንዱን መግዛት ይፈልጋል 21.05.2025

የኬንያው ኬሲቢ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ “ቅርንጫፍ ለመክፈት ወይም አዲስ ለማቋቋም” ሳይሆን በሥራ ላይ ከሚገኙት አንዱን መግዛት ይፈልጋል። በታኅሳስ 2018 ገደማ የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። መጪዎቹ ወራት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በርከት ያሉ ለውጦች የሚያይበት ይመስላል።

አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ቀነሱ 14.05.2025

አሜሪካ እና ቻይና አንዳቸው በሌላቸው ሸቀጦች ላይ የጣሉትን ታሪፍ ከዛሬ ጀምሮ ለ90 ቀናት በከፍተኛ መጠን ቀንሰዋል። ሁለቱ የንግድ ከባድ ሚዛን ተፋላሚዎች ታሪፍ የቀነሱት ከጥቂት ቀናት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው በተስማሙት መሠረት ነው። በሥምምነቱ መሠረት የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ አሜሪካ ገበያ በሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ላይ የጣለውን ታሪፍ ከ145 በመቶ ወደ 30 በመቶ ይቀንሳል። ቻይና በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለችው ታሪፍ በአንጻሩ ከ125 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ይላል። ዶናልድ ትራምፕ በታሪፍ የጀመሩት የንግድ ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያቀዛቅዝ አስግቶ ነበር።

የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች የሚሰበስቡት ግብር በሚያዝያ ወር “ከትሪሊዮን ብር ይሻገራል” 07.05.2025

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እስከ ሚያዝያ 2017 ድረስ ባሉት ዘጠኝ ወራት ፌድራል መንግሥት እና ክልሎች ከታክስ የሰበሰቡት ገቢ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ ፌድራል መንግሥት 720 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። የታክስ ገቢ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር በ279 ቢሊዮን ብር ቢልቅም ወይዘሮ ዓይናለም በቂ ነው የሚል ዕምነት የላቸውም። በ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት 1.5 ትሪሊዮን ብር በግብር መልክ የመሰብሰብ ዕቅድ አለው። ከዚህ ውስጥ የፌድራል መንግሥት 900 ቢሊዮን ብር፤ የክልል መንግሥታት በአንጻሩ 600 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚመሩ ሹማምንት በዋሽንግተን ምን አሉ? 30.04.2025

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የጸደይ ጉባኤ በዋሽንግተን ሲካሔድ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መንግሥታቸው ተግባራዊ ስለሚያደርገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ውጤቶቹ ማብራሪያ ሲሰጡ ሰንብተዋል። ኢትዮጵያ የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ እየጠበቀች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ አማራጭ የገንዘብ ምንጭ እያፈላለገች ነው።

የትራምፕ ታሪፍ የዓለምን ኢኮኖሚ ዕድገት እንዳቀዛቀዘ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ አሳየ 23.04.2025

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለዓለም ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች በጥር የሰጠውን የዕድገት ትንበያ የዶናልድ ትራምፕ ታሪፍ ባስከተለው ውጥረት ምክንያት ከልሷል። ተቋሙ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ6.6% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርጓል። ትንበያው የኢትዮጵያ መንግሥት በ2017 ከሚጠብቀው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በ1.8 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።

የኢትዮጵያውያን መከራ በደቡብ አፍሪካ የፍልሰት ጉዞ 02.04.2025
የኢትዮጵያ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለዕዳ ሽግሽግ ድርድር እንዲዘጋጁ ገንዘብ ሚኒስቴር አሳሰበ 26.03.2025

ገንዘብ ሚኒስቴር “ዋና ዋና” ላላቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአበዳሪ መንግሥታት ጋር ለሚደረግ የመግባቢያ ሥምምነት ድርድር እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የገንዘብ ሚኒቴር ተቋማቱ እንዲዘጋጁ ያሳሰበው ኢትዮጵያ አበዳሪዎቿን ከሚወክለው ኮሚቴ ጋር የ8.4 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ዕዳ ለማሸጋሸግ “በመርኅ ደረጃ” ሥምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ነው። ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የተደረሰው ሥምምነት በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2028 ባሉት ዓመታት ለኢትዮጵያ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የዕዳ ክፍያ እፎይታ ይሰጣል።

ለኢትዮጵያ ከዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ምን አለ? 19.03.2025

የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት በቡድን ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር የተደራደሩበት አምስተኛ ስብሰባ ዛሬ በጄኔቫ ተካሒዷል። ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ሒደት ለማጠናቀቅ ወደ ጄኔቫ የተመለሰችው “በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጥያቄ” በሚነሳበት ወቅት ነው። ባለፉት ዓመታት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት ብሔራዊ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ እና ተገዳዳሪዎቻቸውን ለመቅጣት የድርጅቱን ሕግጋት እየጣሱ መሔዳቸውን ባለሙያዎች ታዝበዋል።

የአፍሪካ መንግሥታት የናጠጡ ባለጠጎችን የሐብት ግብር ማስከፈል አለባቸው? 12.03.2025

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ብርቱ የኢኮኖሚ ፈተናዎች እየገጠሟቸው ነው። መንግሥታት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች እና ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ለመገንባት የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ለማግኘት ሲቸገሩ የአፍሪካ ሀገራት በየጊዜው እየጨመረ በሚሔድ የዕዳ ጫና እየቃተቱ ነው። ላለፉት በርካታ ዓመታት የአፍሪካ መንግሥታት በአማካይ ለጤና አገልግሎት ከመደቡት የበለጠ ለዕዳ ክፍያ ወጪ አድርገዋል። በአኅጉሪቱ የናጠጡ ባለጠጎች ቁጥር ሲጨምር የሐብት ግብር ማስከፈል እንዲጀመር የሚደረጉ ጥሪዎችም ከፍ ብለው መሰማት ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዞረ 05.03.2025

ለዓመታት ለመንግሥት “ርካሽ” ብድር ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረታዊ የወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ተግባራዊ ሲያደርግ ፊቱን ወደ ገበያ ተመን አዙሯል። ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ከውጪ ምንዛሪ ግኝት ጋር በተያያዘ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ደንበኞቹ የሚያቀርባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች በመተው ለወጪ ንግድ በሚሰጠው ብድር የሚያስከፍለውን ወለድ አሳድጓል። በማሻሻያው የግብርና ብድር ወለድ በመጠኑ ሲቀንስ የኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ቤቶች በነበረበት ቀጥሏል። ንግድ ባንክ ከአርብ ጀምሮ ለቤት መግዣ በ14 በመቶ ለተሽከርካሪ በ15 በመቶ ወለድ ያበድራል።

የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤቶች የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትን ሪፖርት ለምን ተቃወሙ? 19.02.2025

ኢትዮጵያ የገጠማት የዕዳ ጫና የመክፈያ ጊዜ በማራዘም የሚፈታ የአጭር ጊዜ የገንዘብ እጥረት ወይስ የተለቃችውን ብድር ለመቀነስ የሚያስገድድ የመክፈል ችግር? ጉዳዩ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማስፋፋት እና ስኳር ፋብሪካዎች ለመገንባት ሲነሳ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያበደሩ የግል ኢንቨስተሮችን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት እያወዛገበ ነው።

ኢትዮጵያ የመረጠችው የሊብራል ኢኮኖሚ ሥርዓት ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ከባቢ አለ? 12.02.2025

ኢትዮጵያ በታሪኳ ከየትኛውም ጊዜ በላይ አሁን የበለጠ ወደ ሊብራል የኢኮኖሚ ሥርዓት ማዘንበሏን ባለሙያዎች ይስማማሉ። ሊብራል የኤኮኖሚ ሥርዓት ግለሰቦች ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት በነጻ እንዲገበያዩ የሚፈቅድ ነው። ሊብራል ኤኮኖሚ በኢትዮጵያ ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል የፖለቲካ ሥርዓት እና ጠንካራ የግል ዘርፍ አለ?

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪፍን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ሥልት የዓለም የንግድ ሥርዓትን አስግቷል 05.02.2025

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸዉን የንግድ ጉድለት ለማሟላት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም ታሪፍን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙ ነው። አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ከካናዳ በምትሸምታቸው ሸቀጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል ትራምፕ ያስተላለፉት ውሳኔ ለ30 ቀናት እንዲቆም ተደርጓል። በቻይና ላይ የተጣለው ታሪፍ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን የፕሬዝደንት ሺ ዢፒንግ መንግሥት በአጸፋው በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ተመሣሣይ እርምጃ ወስዷል። ቻይና ጉዳዩን ወደ የዓለም የንግድ ድርጅት እንደምትወስድ ዝታለች። የዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ የታሪፍ ውጥረት የፈጠሩ ሀገራት አደብ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? 29.01.2025

ባለፉት አምስት አመታት አሜሪካ ለኢትዮጵያ 7.6 ቢሊዮን ዶላር ሰጥታለች። ባለፈው ዓመት ብቻ ግጭት፣ ድርቅ እና የምግብ ዋስትና እጦት ለገጠማቸው ኢትዮጵያውያን የሕይወት አድን ርዳታ ለማቅረብ አሜሪካ 676 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች። ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የምትሰጠው ርዳታ ለ90 ቀናት እንዲቆም ያሳለፉት ውሳኔ ካሁኑ ተጽዕኖ አሳድሯል። ትራምፕ በጎርጎሮሳዊው 2020 በታላቁ የኅዳሴ ግድብ መዘዝ የሚነታረኩትን ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ለማደራደር ሞክረው ሲከሽፍባቸው አዲስ አበባን ያስቆጣ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ስለ ኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ምን አሉ? 22.01.2025

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ለዜጎች ፈታኝ ቢሆንም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ ነው የሚል እምነት አላቸው። ዓለም ባንክ ያለፈው ዓመት የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቱ ምጣኔ ሐብት ዕድገት ጥቅም እንደሚኖረው አስታውቋል። የማሻሻያውን አፈጻጸም የገመገመው አይኤምኤፍ 248 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት ለቋል።

በኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል? 15.01.2025

ኢትዮጵያውያን በቤት እና በመሬት ግብር የሚከፍሉበት የንብረት ታክስ በተቃዋሚዎች ኃይለኛ ትችት ቢገጥመውም በአራት ተቃውሞ እና በአስር ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽጸድቋል። ተቃዋሚዎች አዲሱ ታክስ በሸማቾች ላይ ጫና እንደሚፈጠር አስጠንቅቀዋል። መንግሥት “ፍትኃዊ የሀብት ክፍፍል የሚያሰፍን” ያለው የንብረት ታክስ በክልሎች ይሰበሰባል። ለመሆኑ በንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል? የማይከፍሉትስ እነ ማን ናቸው?

ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ማመንጫዎች እና መሠረተ-ልማቶች ግንባታ 14 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል 08.01.2025

ኢትዮጵያ ከናፍጣ ከሚመነጭ ብርሀን ከተዋወቀች ከ127 ዓመታት ገደማ በኋላም በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቀበሌዎች አሁንም ጭለማ ውስጥ ናቸው። ኃይል የማስፋፋት ኃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኪሳራ ተጭኖታል። ሀገሪቱ እየጨመረ የሚሔደውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ የኃይል ማመንጫዎች፣ ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለመገንባት 14 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያስፈልጋታል።

የዝንጅብል አምራቾች የገጠማቸው የገበያ ተግዳሮት 01.01.2025
የኢትዮጵያ የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ጥያቄ ተነሳበት 25.12.2024

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (IDA) ያጸደቁት የኢትዮጵያ የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በዓለም ባንክ ባለሙያዎች ጥያቄ ተነስቶበታል። እስከ 2023 የኢትዮጵያ የውጪ ዕዳ 33.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የ3 ቢሊዮን ዩሮ የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

የውጪ ባንኮች ከሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ መፈቀድ 18.12.2024
የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ ምን ይዞ መጣ? 11.12.2024

የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታን አጣምሮ የያዘው አዋጅ “ብዙ የሚያሻሙ” ነገሮች ቢኖሩትም ባለሙያዎች “ገበያውን ቅርጽ ያስይዘዋል” ብለው ይጠብቃሉ። አዋጁ ያለ ደንበኛው ፈቃድ “ቢያንስ 80% ያልተጠናቀቀ ቤት” ማስተላለፍ ይከለክላል። በዘርፉ የሚደረገው ግብይት በባንክ ወይም በኤሌክሮኒክ የክፍያ ዘዴ ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

Listen to the ከኤኮኖሚው ዓለም podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.