DW
ከኤኮኖሚው ዓለም
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የግል ባንኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይውጣ ለተባለበት የወርቅ ግብይት ዝግጁ ናቸው? 08.07.2026 12:21
ባለፈው ዓመት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የወርቅ የወጪ ንግድ ዘንድሮ 5.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በብቸኝነት ከተቆጣጠረው ገበያ እንዲወጣ አይኤምኤፍ ግፊት እያደረገ ነው። የግል ባንኮች የወርቅ ግብይትን ለማካሔድ የሚያስችል የባለሙያ፣ የጥሬ ገንዘብ እና የመሠረተ-ልማት እጥረት አለባቸው።
የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው? 01.07.2026 11:17
ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።
“የኢትዮጵያ ዕዳ አሁን ዘላቂ ነው” የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ 24.06.2026 11:25
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ የዕዳ ጫና “ዘላቂ” ወደሚባልነት ደረጃ ዝቅ እንዳለ ተናግረዋል። ዶክተር ኢዮብ የዕዳ ጫናው መቃለሉን የገለጹት ለአከፋፈል ሽግሽግ የሚካሔደው ድርድር ሳይጠናቀቅ ነው። በድርድሩ የሚፈጸሙ የሁለትዮሽ ሥምምነቶች ሲተገበሩ ኢትዮጵያ የሁለት ዓመት ዕዳ በአንድ በጀት ዓመት ልትከፍል እንደምትችል የገንዘብ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አሕመድ ሽዴ ከፍተኛ አማካሪ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በ2019 ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ተብሎ ይጠበቃል 17.06.2026 9:29
የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊያደርግ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። መንግሥት በዓመቱ በኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከነዳጅ 235.6 ቢሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ ይፈልጋል። ለሚቀጥለው ዓመት የተዘጋጀው በጀት ለነዳጅ ድጎማ 20 ቢሊዮን ብር መታቀዱን አሳይቷል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ከፈቀደው ብድር 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ ሊለቅ ነው 10.06.2026 10:36
አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ያሳደረውን ተጽዕኖ ኢትዮጵያ እንድትቋቋም አይኤምኤፍ (IMF) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከፈቀደው ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ እንዲለቀቅ ታቅዷል። ገንዘቡ የተራዘመ ብድር አቅርቦት መርሐ-ግብር አምስተኛ ግምገማ ሲጸድቅ ከሚለቀቀው 468 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።
የሥራ እጥነት እና የመፍትሄ እርምጃዎች በኢትዮጵያ 03.06.2026 8:59
ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዲግሪ ይዘው ሥራ ማግኘት ቸግሯቸዋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ምህንድስና የተመረቀችው ወጣት ሥራ ሲጠፋ "ይኸን ሁሉ አመት ባላቃጠልኩ" ለማለት በቅታለች።
ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች? 20.05.2026 9:58
ታላቁን የህዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተከታታይ ያስመረቀችው ኢትዮጵያ ለኬንያ የምትሸጠውን ኤሌክትሪክ ለማሳደግ እያጤነች ትገኛለች። አራት ተማሪ ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በኩራዝ የሚያጠኑትን እናት ጨምሮ 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ግን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ቀን ይናፍቃሉ።
ባይናንስ ከአርብ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረግ ግብይት ያቆማል 13.05.2026 12:30
በዓለም ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የሆነው ባይናንስ ከመጪው አርብ ጀምሮ በብር የሚደረጉ ግብይቶች እንደሚያቆም አስታውቋል። ባይናንስ በዘረጋው የመገበያያ መድረክ ከኢትዮጵያ የሚሳተፉት ክሪፕቶከረንሲ “አዋጭ ኢንቨስትመንት” እንደሆነ የሚያምኑ ወጣቶች ናቸው። መሰል ግብይቶች ግን ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 250% ጨመረ 06.05.2026 10:59
የኢትዮጵያ መንግሥት የ2018 የመጀመሪያ መንፈቅ የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ 126.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሰነድ አሳይቷል። የወለድ ክፍያው በስድስት ወራት ለዕዳ ከተመደበው በጀት 64.6% ድርሻ አለው። ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት አኳያ ሲነጻጸር ግን ከ250 በመቶ በላይ ጨምሯል። በ2017 የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለሀገር ውስጥ ወለድ መንግሥት 36 ቢሊዮን ብር ከፍሎ ነበር።
የአውሮፓ ኅብረት የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 559 ሚሊዮን ዩሮ ለማቅረብ ቃል ገባ 22.04.2026 10:28
የአውሮፓ ኅብረት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ያቋረጠውን የበጀት ድጋፍ ወደ 140 ሚሊዮን ዩሮ ከፍ አድርጎ እንደሚጀምር አስታውቋል። ለዲጂታል ኢኮኖሚ 150 ሚሊዮን ዩሮ፤ ኤሌክትሪክ ለማስፋፋት፣ ፋይበር ኦፕቲክ ለመዘርጋትና የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ለመጠገን 269 ሚሊዮን ዩሮ ያቀርባል። የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ 130 ሚሊዮን ዩሮ ለዘመን ባንክ እና ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማበደር ሥምምነት ተፈራርሟል።
በአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ሲስፋፉ በኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ እንደሚቀንስ ጥናት አሳየ 15.04.2026 11:20
የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ለአረቢካ ቡና በጣም ምቹ የሆነውን አካባቢ አሁን ከሚገኝበት 38% በመቶ በምዕተ-ዓመቱ አጋማሽ ወደ 49% ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል አንድ ጥናት አሳይቷል። በሮቦ ባንክ ጥናት መሠረት የዓለም ሙቀት ሲጨምር በኢትዮጵያ ደጋማ አካቢዎችን ቡና አምራች ሊያደርጋቸው ቢችልም ኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ ተጎጂ ናቸው። ደጋማ አካባቢዎች ሞቃታማ እየሆኑ ሲሔዱ በቡና አመቺነታቸው ቢጨምርም የዝቅተኛ ወይም ቆላማ አካባቢዎች በአንጻሩ ይቀንሳል።
የኢትዮጵያ መንግሥት “ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ” የሚከላከል ደንብ እንዲያወጣ እና የግብር እፎይታ እንዲሰጥ ተጠየቀ 08.04.2026 10:58
አምስት ሊትር ዘይት በአሶሳ፣ ደሴ እና መቐለ ከተሞች ከ2,200 እስከ 2,500 ብር እየተሸጠ ነው። የመንግሥት መዋቅሮች የዋጋ ጭማሪዎችን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ሸማቾች መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት “ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎችን በግልጽ የሚከለክል እና የሚያስቀጣ ልዩ መመሪያ” መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያወጣ ጥሪ አቅርቧል።
የኢራን ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል” 01.04.2026 11:59
በኢትዮጵያ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት በአማካይ በቀን ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ቀንሷል። ሀገሪቱ የኢራን ጦርነት ሲቀሰቀስ የገዛችውን 180,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ማስገባት አልቻለችም። በወር ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ለመደጎም መገደዱን የገለጸው መንግሥት ዜጎች “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክሯል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ የኢራን ጦርነት ያስከተለውን የነዳጅ ቀውስ ለመቋቋም ኢትዮጵያውያን “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክረዋል።
በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ ዘይት እጥረትና ድብቅ ገበያ 25.03.2026 10:06
ነዳጅ ከማደያዎች ውጪ በሊትር ደሴ 350 ብር፣ ኮምቦልቻ 500 ብር ዳባት 900 ብር መሸጡን አሽከርካሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በጎንደር እና ባሕር ዳር በነዳጅ ማደያዎች ለወረፋ ከ2,000 እስከ 10,000 ብር ይከፈላል። በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት እና የዋጋ ለውጥ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ምርቶች መሸጫ ላይ ጭማሪ አስከትሏል።
የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የቡና ሲቀንስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብርቱ ፈተና ከፊቱ ተጋርጦበታል 18.03.2026 8:22
በታኅሳስ፣ ጥር እና የካቲት ወራት በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ነጠላ አሀዝ ሆኖ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት የነዳጅ ዋጋ ሲያሻቅብ ሊባባስ ይችላል። የነዳጅ ዋጋ የናረው ሀገሪቱ በቡና ንግድ በዓለም አቀፍ ገበያ የተጋረጠባትን ፈተና ለመሻገር በምትሞክርበት ወቅት መሆኑ በባለሥልጣናቱ ዘንድ ሌላ ሥጋት የፈጠረ ጉዳይ ነው።
የነዳጅ ዋጋ “አስፈሪ በሆነ መልኩ” ሲንር ኢትዮጵያ “የቁጠባ እርምጃዎች” ልትከተል ነው 11.03.2026 10:41
አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት የነዳጅ ዋጋ ሲንር የኢትዮጵያ መንግሥት ለቤንዚን እና ለነጭ ናፍጣ በሊትር የሚያደርገው ድጎማ በ44 ብር ገደማ እንደጨመረ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። ከነዳጅ በተጨማሪ የማዳበሪያ ዋጋ በዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሊፈታተን ይችላል። ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት የ50 ኪሎግራም የዩሪያ ከረጢት በኢትዮጵያ ከ12 እስከ 15 ዶላር ይሸጥ ነበር። በዓለም አቀፍ ገበያ የ30% የዋጋ ጭማሪ ሲከሰት በኢትዮጵያ ያለው የችርቻሮ ዋጋ ከ16 እስከ 20 ዶላር ከፍ ይላል ተብሎ እንደሚገመት የቢዝነስ ደቨሎፕመንት ባለሙያው ኢዶሳ ታመነ ይናገራሉ።
እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አደረገ 04.03.2026 11:53
በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን ጦርነት ከመግጠማቸው በፊት ከነበረው ዋጋ 12% ገደማ ጨምሮ 82 ዶላር አካባቢ ደርሷል። በቀጠር እና ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ነዳጅ ማምረቻዎች፤ በሖርሙዝ ወሽመጥ የሚቀዝፉ መርከቦች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በሖርሙዝ የመርከቦች ምልልስ በ80% ቀንሷል፤ ወደ 3,200 የሚሆኑ መርከቦች ሥራ ፈተዋል
ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል 25.02.2026 9:30
ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የባንክና ቴሌኮም አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ስልቶች የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኝ ተቋም ባልደረባ ባለፈው ወር ከደመወዛቸው 0.5% መቆረጡን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎች እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት የሚሰጡት ርዳታ በመቀነሱ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንደሚያስፈልግ ቢስማሙም መዋጮው ጫና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሲያንዣብብ የትግራይ ክልል ነዋሪዎችና ኢኮኖሚ ካሁኑ ዳፋው ተጭኗቸዋል 18.02.2026 11:08
በኢትዮጵያ ሌላ ጦርነት ሲያዣብብ በትግራይ ክልል የነዳጅ ምርቶች፣ ጤፍ እና ዘይትን ጨምሮ የምግብ ግብዓቶች በአንድ ሣምንት የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። በክልሉ ከኤቲኤም ገንዘብ ማግኘት አይቻልም። ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ የሚያደርጉትን የገንዘብ መጠን ገድበዋል። በክልሉ በተፈጠረ ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ለንግድ እና አገልግሎቶች ክፍያ የሚፈጸመው በሞባይል የገንዘብ ማዘዋወሪያዎች ሆኗል።
“ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የላቭግራስ ኢትዮጵያ መሥራች ዮናስ አድማሱ 11.02.2026 17:47
የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት (BII) ለላቭግራስ ኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ኩባንያው በሱሉልታ በሚገኘው ፋብሪካ ከጤፍ ፓስታ እና ኩኪሶችን ጨምሮ የተለያዩ ምግቦች እያመረተ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብ ነው። ላቭግራስ ብድሩን ያገኘው “ማኅበረሰቡ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የሚል ግልጽ ዓላማ ስላለው እንደሆነ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ዮናስ አድማሱ ይናገራሉ። ዮናስ ኩባንያውን ከመመሥረታቸው በፊት በቢኤንፒ ፓሪባ፣ ጄፔ ሞርጋን እና ክሬዲት ስዊዝ ባንኮች ሠርተዋል።
የግል አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ሊከሱ እንደሚችሉ ቢገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአከፋፈል ሽግሽግ ይጠብቃሉ 04.02.2026 10:03
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ዕዳ ለማሸጋሸግ በሚደረገው ጥረት “በሁለት ዓመት ይከፈል የነበረው ዕዳ እንደየአበዳሪው ሁኔታ እስከ 15 ዓመት እንዲራዘም ሥምምነት” መፈጸሙን ተናግረዋል። የግል አበዳሪዎች ግን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት ሥምምነት ውድቅ ከሆነ በኋላ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል። ገንዘብ ሚኒስቴር እና የግል አበዳሪዎች በመርኅ ደረጃ ያደረጉት ሥምምነት ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ እንዲከፍል በማስገደድ አስፈላጊ የመንግሥት አገልግሎቶችን አደጋ ላይ ይጥላል” የሚሉት የዴብት ጀስቲስ ዋና ዳይሬክተር ሐይዲ ቻው ውድቅ መደረጉን ደግፈዋል።
በጨረታ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ያከፋፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በካፒታል ገበያ በኩል የባንኮች የውጭ ምንዛሪ መገበያያ ሥራ አስጀመረ 28.01.2026 11:28
በጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር ያከፋፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) በኩል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገበያዩበት ሥርዓት አስጀምሯል። ባንኮች በመጫረቻ ዋጋ የጠየቁት 592.3 ሚሊዮን ዶላር ከቀረበው በላይ ነበር። ከ31 ባንኮች ለ25ቱ የተከፋፈለው ዶላር መጠን ከፍተኛ ቢሆንም በምንዛሪ ተመን ላይ ትልቅ ለውጥ አላመጣም።
ከኤኮኖሚዉ ዓለም፣ የግዙፉ አዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታና ፈተናዎቹ 14.01.2026 11:47
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደሚሉት በ3 ሺህ 900 ሄክታር ቦታ ላይ የሚያርፈው አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ሲጠናቀቅ 110 ሚሊየን ደንበኞችን በዓመት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል
ጀርመን ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ድጋፍ ለጸጥታ ጉዳዮች ትኩረት እየሰጠች ነው? 17.12.2025 6:55
ኢትዮጵያ እና ጀርመን ባለፈው ሣምንት 100 ሚሊዮን ዩሮ ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ለሦስት ዓመታት የሚዘልቅ “የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነት” ተፈራርመዋል። በሥምምነቱ ጀርመን ለኢትዮጵያ 206 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.