Digafie Debalke

የሰላም መድረክ ኢትዮጵያ/ PEACE TALK ETHIOPIA ስራችን ስላም ነው፡፡ / We Work for Peace

Business AM ↓ 51 episodes

የፕሮግራማችን ዋነኛ ትኩረት በዘላቂ አገራዊ ሰላም ግንባታ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ዕርቅ ላይ ሲሆን ወደዚያም ሊያደርሱ የሚችሉ መንገዶችን በማፈላለግና በመጠቆም አስተዋፅዖ ለማድረግ እንጥራለን።የተሟላ ሰላም አለ ማለት የሚቻለው ጦርነት ወይም ውጊያ ስለሌለ ሳይሆን በአንፃሩ የፓለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ማህበራዊና የሌሎች መሰረታዊ መብቶች መከበር ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ነው።ፕሮግራማችን ፍትሀዊ ሰላም በኢትዮጵያ ይረጋገጥ ዘንድ ቀናና አቀራራቢ ራዕይ ያላቸውን ሁሉ እየጋበዘ ያወያያል። ዝግጅታችን የማንኛውንም ቡድን ወይም የፓለቲካ አጀንዳ የማያስተናግድ ፣ተቀራርቦ መነጋገርን የሚያበረታታና ፤የጥላቻንና የመከፋፈል ወሬዎችንና ፕሮፓጋንዳዎችን እንደማያስተናግድ ከወዲሁ በትህትና እናሳሰባለን። ተልዕኮአችን ሰላም ብቻ ነው።

Author

Digafie Debalke

Category

Business

Latest episode

Sep 24, 2023

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

Conversation With Dr. Ashok Swain Canada - India Diplomatic Tensions, and the Tripartite Talks on the Grand Ethiopian Renaissance Dam 24.09.2023

Canada - India Diplomatic Tensions and Talks on the Grand Ethiopian Renaissance Dam

ፍትህ የለሽ "ሰላም" በኢትዮጵያ 08.05.2023

ህግና የህግ የበላይነት የሚሉት ጽንሰ ሃሳቦች በሃሳብም ሆነ በተግባር የአንድ አገር መንግስት መሰረት መሆናቸው ከጥንታዊው የሃሙራቢ ህግ ጀምሮ በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡ ህግና ሰርአት በሁሉም የማህበረሰብ እርከኖች ማለትም ከመንግስት እስከ ግለሰብ ድረስ በተጻፉና ባልተጻፉ ህጎች መተዳደራቸው ስርአተ አልበኝነትን ግለሰባዊና ቡድናዊ የበቀል እርምጃዎችንና ሁከትን ከመገደብ ባሻገር አገር በደንብና በስርአት ትመራ ዘንድ የተቀረጸ ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ ከዚህ የህግ ማእቀፍ ውጪ በግልም በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብና በአገር ደረጃ ለመሄድ መሞከር አደገኛ ብቻ ሳይሆን መመረጥ የሌለበት የጥፋት መንገድ ነው፡፡ ፍትሃዊ ህግና የህግ የበላይነት...

የሰላም ግንባታን መሰረታዊ ህጎችና ምሰሶዎች ሳያከብሩ ዘላቂ ሰላም እናሰፍናለን ማለት ከቅዥት የዘለለ ትርጉም አይኖረውም፡፡ 24.04.2023

በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀው የዘላቂ ሰላም መታጣት ዋነኛ ምንጩ አገራዊ ፖለቲካውን ላለፉት ሃምሳ አመታት የመሩት ቡድኖች ለሰው ልጆች ህይወት ክብርና ዋጋ የማይሰጡና ህዝቡን ለስልጣን እርካባቸው መወጣጫ እንደ ጭዳ እያቀረቡ መቀጠልን መምረጣቸው ነው፡፡ውዱና ክቡሩን የሰው ልጆች ህይወት እንደ ማገዶ እንጨት በየአውድማው እየጋዩ እነርሱ የፖለቲካ መንበረ ስልጣኑንና ጨምድዶ ከመያዝና የኢኮኖሚ ጥቅማ ትቅሙን ከማጋበስ በስተቀር ለህዝብ መከራና ስቃይ አንዳችም ቁብ የማይሰጣቸው በደም አድገው በደም የጎለበቱ በህዝብ እልቂት የሚያላግጡና አልፈውም በማን አለብኝነት በወገን አስከሬን ላይ የሚደግሱ በመሆናቸው ነው፡፡ ስልጣንና ከስልጣን ጋር ተ...

EPRP 22.04.2023

EPRP

Toxic Polarization : The Politics of "Us" versus "Them" and Its Deadly Effect in Ethiopia 02.04.2023

Toxic Polarization : The Politics of "Us" versus "Them" and Its Deadly Effect in Ethiopia . Conversation with Dr. Senait Senay

የኢትዮጵያን የተወሳሰቡ ችግሮችና ፈተናዎች ለመወጣት ምን አይነት ተገባራዊ ስራዎች ያስፈልጋሉ? ውይይት ከዶክተር ብስራት ለሜሳ ጋር 23.03.2023

የኢትዮጵያን የተወሳሰቡ ችግሮችና ፈተናዎች ለመወጣት ምን አይነት ተገባራዊ ስራዎች ያስፈልጋሉ?

አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ምን ይመስላል? ምን አይነት መሻሻሎችስ ያስፈልጉታል? ለምን?   21.03.2023

አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ምን ይመስላል?ምን አይነት መሻሻሎችስ ያስፈልጉታል? ለምን?     በተቋማት ደረጃም ሆነ ከተቋማት ውጪ የሚደረጉ ትምህርት ነክ የሆኑ ስራዎች በአገር የዕውቀት የስልጣኔ የልማትና እድገትጉዞ ላይ ጉሉህና ወሳኝ ተጽእኖ እንደሚኖራቸው በሚገባ ይታወቃል፡፡ በአገራችን በኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የዘመናዊነት ምሰሶውንና መሰረቱን ያገኘው የኢትዮጵያ የትምህርትስርዓት ከ1966 እኢአ በኃላ የመጡት የፖለቲካ ስርዓቶች የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካ ፍላጎታቸውና አጀንዳቸው ጋር የሚጣጣም መስመር ለማስያዝና ይህንንም ለማስፈጸም በተለያዩ ደረጃዎች ባሉ የትምህርት ተቋማት ው...

የኢትዮጵያ አገራዊ ፖለቲካ ምስቅልቅልና የፈጠረው ስጋት መፍትሄው ምን ይሆን? ይህ "የባሰው መጣ" አገራዊ የፖለቲካ አባዜ ምን ቢደረግ ነው የሚያበቃው? 20.03.2023

“ለውጥ” የሚለው ቃል በቃል ደረጃ ሲገመገምና ሲመዘን ካለፈው ወይንም ከነበረው የተለየ የተለወጠ ማለት ነው፡፡ “ለውጥ” በቃል ደረጃ መልካምም ክፉም ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ “ለውጥ” ከሚለው ቃል በፊት ግን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ የሚሉት ቃላት ከታከሉበት ትርጉሙ ወደ ዝርዝርና ሊመዘኑ ሊመተሩና ሊለኩ ወደ ሚችሉ እውነታዎች ይሄዳል፡፡ በተጨማሪም የእነኚህ ቃላት “ለውጥ” ከሚለው ቃል በፊት መታከል የተሻለ የተሻሻለ ካለፈው ያልከፋ ወደ ሚል ተስፋን መሰረት ወዳደረገ አረዳድ ይወስዳል፡፡ ለውጥና አብዮት የሚሉት ቃላት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቋንቋ ውስጥ ከገቡ እነሆ ወደ ሃምሳ አመታት ተቆጥረዋል፡፡እነኚህን ቃላት እንደ ሸቀጥ...

የፕሮግራም ማስታወቂያ / አሁን ያለው አገራዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ዕውነታ በምን መልኩ መደራጀትንና መስራትን ይጠይቃል? ወቅቱ በሚጠይቀው መልኩ መደራጀትና መስራት ካልተቻለስ ምን ሊያስከትል ይችላል? 13.03.2023

የዲሞክራሲ ስርዓትን ገንብተው አሁን ካሉበት የዳበረና ተጠያቂነትን የስርዓቱ አካል ያደረጉ አገራት ልምድ የሚያመላክተው  የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት በእጅጉ ውስብስብና አስቸጋሪ እንደሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ለስርዓቱ ግንባታ ከፍላጎት በዘለለ በርካታ ሂደቶች ክንዋኔዎችና መርሆዎች እንደሚያስፈልጉ ነው፡፡ በንድፈ ሃሳባዊ ግልጽነት በአደረጃጀት ብቃት ብልጭ ድርግም የሚል ሳይሆነ ለረዥም ርቀት ጉዞ መዘጋጀትና ይህንን ጉዞም በስነ ምግባር ጥንካሬ መደገፍና ማጽናት ለስኬቱ ግዙፍ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አቋራጭና በፍጥነት የሚያደርስ ጎዳና የለውም፡፡ብቸኛው መንገድ ውጣ ውረዶቹንን ተቋቁሞ መሰናክሎቹን ተሻገሮ...

ለውጡ ያጋጠመው ችግር ምን ይሆን? ይህን ግዙፍና በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ግዙፍ ተስፋ የተጣለበትን ለውጥ ማዳንና ሲነሳ ወደ አጫረው ህዝባዊና አገራዊ ስሜት እንደገና ማምጣት ይቻል ይሆን? ለውጡ ምን አይነት እርምቶች ያስፈልጉታል?ይህ ካልተደረገስ የሚያስከትለው አደጋና መዘዝ ምን ሊሆን ይችላል? 06.03.2023

በኢትዮጵያ ከሃምሳ አመታት በላይ የዘለቀውና በዲሞክራሲያዊ መሰረት ላይ የቆመ ፍትሃዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት የመገንባት ምኞትና ውጥን በውስጥና በውጭ ኃይሎች ርዕዮተ አለማዊና ጅኦ ፖለቲካዊ ፍላጎት ሴራና ቅንጅት በተከታታይ እየከሸፈ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት የተወሳሰበና እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች፡፡በ1966 የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በጥቂት የጦር መኮንኖች ተጠልፎ ለአስራ ሰባት አመታት በአስከፊ የመከራ ፖለቲካና የላሸቀ ኢኮኖሚያዊ ስርአት ውስጥ አገራችን ለመጓዝ ተገዳለች፡፡የኢትዮጵያ አገራዊ ችግር ከመደብ ቅራኔዎች የመነጨ ነው በሚል ማርክሳዊ ሌኒናዊ ትንታኔ ላይ የተመሰረተው ይህ የምስራቁን ርዕዮተ ዓለማዊ ፖለቲካ...

የፕሮግራም ማስታወቅያ፡ ከመጠን በላይ አደገኛ እየሆነ የመጣው የማንነት ፖለቲካ አገሪቱን ሙሽ አዙር ውስጥ እንደ ገባ ጥይት እያጦዛት ነው፡፡ 02.03.2023

በኢትዮጵያ ከሃምሳ አመታት በላይ የዘለቀው በዲሞክራሲያዊ መሰረት ላይ የቆመ ፍትሃዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት የመገንባት ምኞትና ውጥን በውስጥና በውጭ ኃይሎች ርዕዮተ አለማዊና ጅኦፖለቲካዊ ፍላጎትና ሴራ ቅንጅት በተከታታይ እየከሸፈ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት  ምእራፍ ላይ ደርሳለች፡፡ በመጀመሪያ በ1966 የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በጥቂት የጦር መኮንኖች ተጠልፎ ለአስራ ሰባት አመታት አስከፊ በሆነ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ስርአት ውስጥ አገሪቱ አልፋለች፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ችግር ከመደብ ቅራኔዎች የመነጨ ነው  በሚል ማርክሳዊ ሌኒናዊ ትንታኔ ላይ የተመሰረተው ይህ የምስራቁን ርእዮተ ዓለማዊ ፖለቲካ መሰረት ያደረገው...

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት አመታት :: ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከአራት አመት በፊት ከነበሩበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበራዊና የፀጥታ ሁኔታ አኳያ ዛሬ ሁኔታዎች ተሻሽለዋል ወይንስ እየከፉ ነው የመጡት? ውይይት ከአቶ ዮሃንስ በርሄና ከአቶ ሰለሞን ስዩም ጋር 25.02.2023

የዛሬ አራት አመት ገደማ ግዙፍ አገራዊ የተስፋንና የአንድነትን መልዕከት ይዘው ወደ ብሄራዊ የፖለቲካ መድረክ ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አጋሮቻቸው የጀመሩት የለውጥ ሂደት አሁን ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል? ያለፉት አራት አመታት ሂደትን መለስ ብለን ስንቃኝ ምንድን ነው የምናገኘው? ጦርነት የጅምላ ግድያዎችና የተለያዩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች በተስተዋሉባቸው በእነኚህ አራት አመታት ምን ስኬቶችስ ተመዝግበዋል? በአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከአራት አመት በፊት ከነበሩበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበራዊና የፀጥታ ሁኔታ አኳያ ተነስተን ያለፉት አራት አመታት ስንመዝን ሁኔታዎች ተሻሻሉ ወይንስ እየተባባሱና እየ...

አሁን የደረስንበት ፈታኝ ጊዜም ሊቃውንቶቻችንንና አበዎቻችንን ለዘልአለም ካሸለቡበት ዕረፍት ሳይቀር ቀስቀሰን ምን እናድረግ? ምን እንሁን? ምንስ ትመክሩናላችሁ? እንዴትስ ትገስፁናላችሁ? እንላለን፡፡ 17.02.2023

የቋንቋ አቅም ብርታቱ የልሳን ሁሉ ጉልበቱ የዕምባን ጎርፍ የዋይታንና የሲቃን ግዝፈት የሃዘንን መጠነ ድባብ መግለፅና መሳል ሲያቅታቸው ከሰማያዊው ኃይል እርዳታንና ፅናትን ከመማፅን ባሻገር ወደ ሊቃውንቶቻችንናወደ የጥበብ  ድምጻቸው እንሮጣለን፡፡ እነርሱ እንዲያረጋጉን ለእንባችን ምክን ት ለዋይታችን ቃላት እንዲፈጥሩልን እንጠይቃቸዋለን፡፡ አሁን የደረስንበት ፈታኝ ጊዜም ሊቃውንቶቻችንንና አበዎቻችንን ለዘልአለም ካሸለቡበት ዕረፍት ሳይቀር ቀስቀሰን ምን እናድረግ? ምን እንሁን? ምንስ ትመክሩናላችሁ? እንዴትስ  ትገስፁናላችሁ? እንላለን፡፡

የዛሬ አራት አመት ገደማ ግዙፍ አገራዊ የተስፋንና የአንድነትን መልዕከት ይዘው ወደ ብሄራዊ የፖለቲካ መድረክ ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አጋሮቻቸው የጀመሩት የለውጥ ሂደት አሁን ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል? ያለፉት አራት አመታት ሂደትን መለስ ብለን ስንቃኝ ምንድን ነው የምናገኘው? 17.02.2023

የዛሬ አራት አመት ገደማ ግዙፍ አገራዊ የተስፋንና የአንድነትን መልዕከት ይዘው ወደ ብሄራዊ የፖለቲካ መድረክ ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አጋሮቻቸው የጀመሩት የለውጥ ሂደት አሁን ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል? ያለፉት አራት አመታት ሂደትን መለስ ብለን ስንቃኝ ምንድን ነው የምናገኘው? ጦርነት የጅምላ ግድያዎችና የተለያዩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች በተስተዋሉባቸው በ እነኚህ አራት አመታት ምን ስኬቶች ተመዝግበዋል? በአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከአራት አመት በፊት ከነበሩበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበራዊና የፀጥታ ሁኔታ አኳያ ተነስተን ያለፉት አራት አመታት ስንመዝን ሁኔታዎች ተሻሻሉ ወይንስ እየተባባሱና እየ...

ተደራራቢ የአገር ቁስልና መዘዙ፡፡ የዚህ በየጊዜው ሳይታከመ እየተነባበረ የመጣው ስነ ልቦናዊና ስነ መንፈሳዊ ቁስል በአገር ላይ ያስከተላቸው መዘዞች እንዴት ይታያሉ? እንዲሽሩስ ምንድን ነው መደረግ ያለበት? ቆይታ ከሰብለ ኃይሉ ጋር፡፡ 15.02.2023

ከሰው ሰራሽም ሆነ ከተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ጋር በተያያዘ በአለማችን በሰው ልጆች ላይ በየጊዜው የሚደርሱ የህይወት መጥፋት የአካል መጉደልና የንብረት መውደሞች በርካቶች ናቸው፡፡ እነኒህ አብዛኛዎቹ በአይን የሚታዩና የሚዳሰሱ ጉዳቶች ሲሆኑ በአይን የማይታዩ የማይዳሰሱ ጉዳቶችም በከፍተኛ ደረጃ የሰው ልጅን ለህመም ይዳርጋሉ፡፡ ይህም የስነ የአዕምሮና የስነ ልቦና ጉዳት ነው፡፡  ለምሳሌ ከ1989 - 2015 ባሉት አመታት ውስጥ 1.45 ቢልዮን ሰዎች ለጦርነት ጉዳት የተጋለጡ ሲሆን ከእ ነኚህ ውስጥ 354 ሚሊዮን የሚሆኑት በስነ ልቦና ህመም ወይንም ቁስል እንደተጠቁ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በአገራችን ደግሞ ባላፉት ሰላሳ አመታት...

Did the government of Ethiopia abdicate its responsibilities? 10.02.2023

Did the government of Ethiopia abdicate its responsibilities? 

አሁን የደረስንበት ፈታኝ ጊዜም ሊቃውንቶቻችንንና አበዎቻችንን ለዘልአለም ካሸለቡበት ዕረፍት ሳይቀር ቀስቀሰን ምን እናድረግ? ምን እንሁን? ምንስ ትመክሩናላችሁ? እንዴትስ ትገስፁናላችሁ? እንላለን፡፡ 08.02.2023

የቋንቋ አቅም ብርታቱ የልሳን ሁሉ ጉልበቱ የዕምባን ጎርፍ የዋይታንና የሲቃን ግዝፈት የሃዘንን መጠነ ድባብ መግለፅና መሳል ሲያቅታቸው ከሰማያዊው ኃይል እርዳታንና ፅናትን ከመማፅን ባሻገር ወደ ሊቃውንቶቻችንናወደ የጥበብ  ድምጻቸው እንሮጣለን፡፡ እነርሱ እንዲያረጋጉን ለእንባችን ምክን ት ለዋይታችን ቃላት እንዲፈጥሩልን እንጠይቃቸዋለን፡፡ አሁን የደረስንበት ፈታኝ ጊዜም ሊቃውንቶቻችንንና አበዎቻችንን ለዘልአለም ካሸለቡበት ዕረፍት ሳይቀር ቀስቀሰን ምን እናድረግ? ምን እንሁን? ምንስ ትመክሩናላችሁ? እንዴትስ  ትገስፁናላችሁ? እንላለን፡፡

Can we Sacrifice Justice for Security? 03.01.2023

Today on the first episode of the year 2023 we will ponder around the question of justice and peace. Specifically, we will discuss or attempt to answer the question: Can we sacrifice justice for security? In any post conflict society, the issue of justice in its various forms is the key question that follows once the guns are silent. As such peace and justice become inseparable. Death, physical an...

Post Pretoria and Nairobi: What has been accomplished? What remains to be done? 19.12.2022

Post Pretoria and Nairobi: What has been accomplished? What remains to be done?

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስትና ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ 06.12.2022

ይድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ መንግስትና ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከሁሉ በፊት የአክብሮት ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡ የረዥም ዘመን የባህል የወግ የሃይማኖትና የነፃነት ታሪክ ያላት አገራችን ኢትዮጵያ በእዚህ የረዥም ዘመን ታሪኳ በርካታ ትውልዶችን የፈትኑ መሰናክሎችን ተሻግራለች፡፡ ውጣ ውረዶችንም አልፋለች፡፡ ይህም በመሆኑ ትውልድ ከትውልድ እየትቀባበለ ይህችን ውድና ታሪካዊት አገር ለእኛ አስረክቦናል፡፡ ከዚህ ተነስተን የኛን የታሪክና የትውልድ ኃላፊነት ስንቃኝ ይህች እልፍ አዕላፍ ልጆችዋ መስዋ ዕትነት የከፈሉላትን አገር አንድነትዋን አፅንተን ዕድገትዋንና ልማትዋን አረጋግጠን ሰላማዊት ከራስዋ የታረቀችና ከጎረቤቶችዋ ጋር የተስማማች ኢትዮ...

Ethiopia and the Horn of Africa in a Changing World 14.10.2022

In recent years post World War II and Post-Soviet World War order has been rattled by several new developments. The rise of new economic and military power and the weakening of the old and most recently the war between NATO Ukraine on one side and Russia on the other brought significant security and military implication on our world. Including the possibility of nuclear war. One of the strategic a...

እኔ ይቅር ባልኩኝ 07.09.2022

እኔ ይቅር ባልኩኝ

Peaceful Demonstration or Organized Violence? TPLF Supporters Street Violence in European Cities 06.09.2022

Freedom of speech and assembly are fundamental values of a democratic society. As such they are guaranteed and protected by law. Citizens have the full right to express their dissatisfaction, defend and demand their rights from their governments in a peaceful manner; to petition their governments and present their grievances. At the same time, however, the same law that guarantees peaceful assembl...

Is the Peace Talk Dead? 30.08.2022

Is the Peace Talk Dead? 

Will the Ethiopian Government Have a Partner in Peace? 01.08.2022

War is a real time tragedy with real life consequences. Those unarmed and unprotected men, women, children, along with the frail and the elderly caught in the middle, endure most of the suffering. There is nothing good about war, even in the name of self-defense. The very nature of war, whether waged in the name of “liberation,” “freedom,” or authoritarian desire for domination, only causes pain a...

Listen to the የሰላም መድረክ ኢትዮጵያ/ PEACE TALK ETHIOPIA ስራችን ስላም ነው፡፡ / We Work for Peace podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.