DW

ከኤኮኖሚው ዓለም

Business AM ↓ 100 episodes

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።

Author

DW

Category

Business

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Jul 8, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

በኢትዮጵያ ምርጫ ሲቃረብ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እያደላ ነው 10.12.2025

የኢትዮጵያ ሰባተኛ ምርጫ በመካሔድ ላይ የሚገኙ ግጭቶች፣ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና የተቃዋሚዎች መዳከም አጥሎበታል። ገዥው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ስኬት የሚቆጥራቸውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አጉልቶ ለማቅረብ ሲጥር ይታያል። የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እና የድሕነት መጨመርን የመሳሰሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ክርክር ሊደረግባቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው።

የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች “እባካችሁ በተሰጣችሁ ፈቃዶች ላይ አትተኙባቸው” 03.12.2025
የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሔደ 26.11.2025

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ኩባንያዎችን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከልማት ድርጅቶች የሚያገናኘው የቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሒዷል። መርሐ-ግብሩ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች የተጋበዙበት ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አምስት ተጨማሪ ኩባንያዎች እያቋቋመ ነው 19.11.2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመማሪያ መጻሕፍት አታሚ ድርጅት እና የወጣቶች የኢንቨስትመንት ባንክ ጨምሮ በዚህ ዓመት አምስት ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም አሳውቋል። ከሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነቶች የተፈራረመው ተቋም ከ2011 ጀምሮ የስኳር ፋብሪካዎች ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ጥረት አቋርጧል።

በሰኔ ይጠናቀቃል የተባለው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ወጪ ስንት ነው? 12.11.2025

በ2.5 ቢሊዮን ብር የመነሻ ዋጋ ተጀመረው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በጀት 20.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን የፌድራል ሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሰነድ አሳይቷል። ለግንባታው በ2018 በጀት ውስጥ ከ4.9 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቧል። መንግሥት 13 ዓመታት የተጓተተው ግንባታ በስምንት ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ክልሎች እና ከተሞች የማዘጋጃ ቤት ቦንድ ቢያወጡ ማን ያበድራቸዋል? 05.11.2025

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሰነድ የክልል መንግሥታት እና የከተማ መስተዳድሮች ቦንድ በማውጣት ከገበያው የሚበደሩበት ሥርዓት የመዘርጋት ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ ሰጥቷል። የማዘጋጃ ቤት ወይም የከተማ አስተዳደር ቦንዶች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ የሚያስፈልግ ገንዘብ ለመበደር የሚያገለግሉ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ክልል በቁልፍ የልማት ዘርፎች ረገድ ያለባቸውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ቦንድ በማውጣት ከገበያው የመበደር ፍላጎት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ያደረገው አንድ ጥናት አሳይቷል።

የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት “ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም”? 29.10.2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከ23 ቢሊዮን ዶላር እንደማይበልጥ ተናግረዋል። የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በአንጻሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተበደሩትን ጨምሮ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ 31.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ያሳያል።

የዶላር ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ሣምንት ብቻ ከአምስት ብር በላይ ጨመረ 22.10.2025

ባለፈው አንድ ሣምንት ንግድ ባንክ ዶላር የሚገዛበት እና የሚሸጥበት ተመን አምስት ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ከፍ ብሏል። የብሔራዊ ባንክ አመልካች ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን በአንጻሩ 150 ብር ከ90 ሳንቲም ደርሷል። ብር በውጭ ምንዛሪ ገበያው መዳከሙን ሲቀጥል ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ለመውሰድ በድጋሚ ዝቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስር የውጪ ምንዛሪ ጨረታዎች ምን አሳኩ? 15.10.2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ባካሔዳቸው ጨረታዎች ከ690 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለባንኮች አከፋፍሏል። ጨረታዎቹ በትይዩ ገበያ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የውጪ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት ቢችሉም ዋንኛ ዓላማቸውን ያሳኩ አይመስልም። በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች የምንዛሪ ተመን ሲጨምር ልዩነታቸው አልጠበበም።

የኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክት እንደ ቀደሙት ሙከራዎች ያሰጋል? 08.10.2025

የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌ ክልል ያስጀመረውን የነዳጅ ልማት ፕሮጀክት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አንድ አንጃ ተቃውሟል። ኦብነግ ፕሮጀክቱ “ምክክር” እንዳልተደረገበት እና ሕዝቡ “ፈቃዱን እንዳልሰጠ” ተችቷል። ከዚህ ቀደም በነዳጅ ፍለጋ ወቅት ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያስታውሱ ተመራማሪዎች አዲሱ ፕሮጀክት “ጥንቃቄ” እንደሚሻ ይመክራሉ።

ኢትዮጵያ ለቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ ከቦንድ ባለቤቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት ውጤት እየጠበቀች ነው 01.10.2025

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በፊት ከግል ባለወረቶች አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶች እና የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ፓሪስ ዉስጥ ውይይት ጀምረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከግል አበዳሪዎቹ ጋር የሚደረገውን ድርድር ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተራዘመ የብድር አቅርቦት አራተኛ ግምገማ በፊት የማጠናቀቅ ዕቅድ አለው።

የፖለቲካ ኢኮኖሚስቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ የቤት ሥራዎች ምንድናቸው? 24.09.2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 11ኛ ገዥ እዮብ ተካልኝ የፖለቲካ ኢኮኖሚስት ናቸው። ከገንዘብ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት በሱዳን ጎዳና ወደሚገኘው አዲሱ ቢሯቸው ሲዛወሩ ብሔራዊ ባንክ በርካታ ሥራዎች ጀምሮ ይጠብቃቸዋል። ሹመታቸው አነጋጋሪ የመሆኑን ያህል እዮብ በብሔራዊ ባንክ ገዥነታቸው የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎችም በዐይነ ቁራኛ የሚታዩ ይሆናሉ።

ዘምዘም ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን አምስት ቢሊዮን ብር ለማድረስ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ አክሲዮኖች እየሸጠ ነው 17.09.2025

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ የሆነው ዘምዘም ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን አምስት ቢሊዮን ብር ለማድረስ አክሲዮኖች ለዲያስፖራ እየሸጠ ነው። ባንኩ እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ ሁለት ቢሊዮን ብር ገደማ ማሰባሰብ ይኖርበታል። የሸሪአ መርህ የሚከተሉ ባንኮች፣ አጠቃላይ ሐብታቸው፣ ተቀማጭ እና የደንበኞቻቸው ቁጥር ቢጨምርም በተጠበቀው ልክ ለማደግ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች አሉ

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማሳደግ ወይስ ለጎረቤት ሀገራት መሸጥ? የቱ ይቀድማል? 10.09.2025

ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሚያመነጨው ኃይል መሸመት ይፈልጋሉ። ህዳሴ ኃይል ማመንጨት ከጀመረ ወዲህ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ወደ 54% ከፍ ቢልም የዓለም ባንክ በሐምሌ ይፋ ያደረገው ሰነድ በኢትዮጵያ በገጠር እና የከተማ ዳርቻዎች የሚኖሩ ወደ 71 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኙ አሳይቷል።

“ሰላም ከሌለ ልማት የለም። ልማት ከሌለ ሰላም የለም” የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሲዲ ዑል ታ 03.09.2025

ናይጄሪያዊውን አኪንዉሚ አዴሲና የተኩት የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝደንት ሲዲ ዑል ታ ባለፈው ሰኞ በይፋ ሥራቸውን ጀምረዋል። አዲሱ ፕሬዝደንት የፋይናንስ ሚኒስትሮች እና የብሔራዊ ባንክ ገዥዎችን በሚያካትተው የአፍሪካ ልማት ባንክ አስተዳደር ቦርድ የተመረጡት ግንቦት 21 ቀን 2017 በተካሔደ ምርጫ ነው። የሞሪታኒያው ሰው የሚመሩት አኅጉራዊ ባንክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚያስገነባው አቡሴራ አውሮፕላን ማረፊያ 8 ቢሊዮን ዶላር ብድር የማፈላለግ ኃላፊነት ወስዷል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሥራ ለመፍጠር ሲያነክስ “ስደት እንደ አማራጭ ሳይሆን እንደ ብቸኛ መፍትሔ እየተቆጠረ ነው” 27.08.2025

ኢትዮጵያውያን የተሻለ የሥራ እና የገቢ አማራጭ ፍለጋ ወደ አረብ ሀገራት፣ ደቡብ አፍሪካ እና በሰሐራ በኩል ወደ አውሮፓ ሲጓዙ ለሞት፣ ስቃይ እና እንግልት ይዳረጋሉ። ዜናውን የሰሙ አለፍ ሲልም ሰቆቃውን የሚያውቁ ከመሰደድ አልተቆጠቡም። ተማራማሪዎች በኢትዮጵያ “ስደት እንደ አማራጭ ሳይሆን እንደ ብቸኛ መፍትሔ እየተቆጠረ” መምጣቱን ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት በ160 ቢሊዮን ብር ደመወዝ ሊያሻሽል መሆኑን ሲያሳውቅ ሠራተኞች የዋጋ ጭማሪ አስግቷቸዋል 20.08.2025

የመንግሥት ሠራተኞች ከመስከረም 2018 ጀምሮ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ጭማሪ እጃቸው ከመግባቱ በፊት የሸቀጦች ዋጋ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ በመሳሰሉት ላይ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል። የደመወዝ ጭማሪው 160 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ተሿሚዎች፣ ተመራጮች፣ የመከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ጨምሮ ለሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች የሚደረግ ነው። ደመወዝ ይጨመራል ሲባል “ያልተገባ” የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል ያመኑት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትራምፕ 10% ታሪፍ ላይ ከአሜሪካ እንዲደራደር ባለሙያዎች መከሩ 13.08.2025

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የጣለው 10% ታሪፍ ከነሐሴ 01 ቀን 2017 ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል። የኢትዮጵያ ሸቀጦች ወደ አሜሪካ ሲገቡ የሚከፈለው ቀረጥ “ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ” ይሆናል የሚሉ ባለሙያዎች መንግሥት ከዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እንዲደራደር መክረዋል። ይሁናን ዝቅተኛው ቀረጥ 50% ታሪፍ የተጣለባት የሕንድ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን እንዲያማትሩ አድርጓል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ በትይዩ የውጪ ምንዛሪ ገበያ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ እንደሚወረስ አስጠነቀቁ 06.08.2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከአሜሪካ እና ከዱባይ የሚዘወሩትን ጨምሮ በውጪ ምንዛሪ ትይዩ ገበያ ላይ ዘመቻ ጀምሯል። ባንኩ ከፍተኛ ልዩነት የሚታይባቸው ይፋዊ እና ትይዩ ተመኖች ተዋህደው ወጥ የውጪ ምንዛሪ ገበያ እንዲፈጠር ይፈልጋል። ነጋዴዎችን ጨምሮ ኢ-መደበኛውን ገበያ ለሚጠቀሙ ገንዘባቸው ሊወረስ እንደሚችል የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ አስጠንቅቀዋል።

የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ በዓመቱ ምን አሳካ? 30.07.2025

የኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ካደረገ ወዲህ የሸቀጦች የወጪ ንግድ እና ሐዋላን ጨምሮ ሀገሪቱ 32 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በለውጡ ብር ዶላርን ከመሳሰሉ የመገበያያ ገንዘቦች ያለው የምንዛሪ ተመን እየተዳከመ ሲሔድ እንደ ነዳጅ ያሉ ሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ የሸማቾችን አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።

የመንግሥት የቀጣዩ ዓመት የፋይናንስ ዘርፍ ትኩረት ምን ላይ ነው? 23.07.2025
ኢትዮጵያ ተስፋ የጣለችበት የካፒታል ገበያ ፍሬ መቼ ይታያል? 16.07.2025

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በደረሰበት ምዕራፍ መንግሥት እና የዘርፉ ተዋንያን ከፍ ያለ ተስፋ ሰንቀዋል። ገበያው የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች፣ የወጋገን እና የገዳ ባንኮችን አክሲዮኖች መዝግቦ ለሁለተኛ ገበያ አቅርቧል። ባለሙያዎች “ፈጣን ግብይት” እስኪፈጠር መታገስ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። ነገር ግን “ቀስ በቀስ እያደገ ካልመጣ ሊሞት ይችላል” የሚል ሥጋትም አለ።

ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፊቷን ከያዮ እና ድሬዳዋ ወደ ጎዴ አዞረች 09.07.2025

ሜቴክ በያዮ የጀመረው የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን በቢሊዮን ብሮች አክስሮ ገበሬ አስለቅሶ ቆሟል። በሞሮኮ ኩባንያ በድሬዳዋ ሊገነባ የታቀደው ከወረቀት አልዘለለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በሶማሌ ክልል በምትገኘው ጎዴ ከተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስፋውን በናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ ላይ አሳርፏል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጀት መፈተሽ እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናገሩ 02.07.2025

የኢትዮጵያ መንግሥት ለ2018 ለትምህርት 114.7 ቢሊዮን ብር መድቧል። በትምህርት ሚኒስቴር ሥር ለሚገኙ 47 ዩኒቨርሲቲዎች ለመደበኛ እና ካፒታል ወጪ በጠቅላላ የተመደበው 106 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው። ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የማስተማሪያ ሆስፒታሎች የበጀት ጉዳይ ግን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆኗል።

የብር ምንዛሪ ተመን እየላሸቀ ሲሔድ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ድጎማ አስቀረ-ከዚያስ? 25.06.2025

የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዳጅ ግብይት ያደርግ የነበረውን “ጥቅል ድጎማ” ከግንቦት ወር ጀምሮ አቁሟል። እርምጃው ኢትዮጵያውያን ቤንዚን እና ናፍጣን የመሳሰሉ የነዳጅ ውጤቶች ሲገዙ የዓለም ገበያ ዋጋን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው። የድጎማ መቅረት ለመንግሥት ወጪ ፋታ የሚሰጥ ቢሆንም በገበያው ወደ ሸማቾች የሚተላለፍ ጫና ሊያስከትል ይችላል።

Listen to the ከኤኮኖሚው ዓለም podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.