DW

ከኤኮኖሚው ዓለም

Business AM ↓ 116 episodes

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።

Be sure to visit the podcast's website and support the creator: www.dw.com

Author

DW

Category

Business

Podcast website

www.dw.com

Latest episode

Nov 11, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 10M+ downloads · 4.7+ rating iOS soon

Episodes

የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ምርት ወደ 24 ትሪሊዮን ብር ሲከለስ የታክስ ነገር በዐይነ ቁራኛ የሚታይ ሆኗል 11.11.2026

በ2018 መንግሥት የሚሰበስበው ታክስ ከአገር ውስጥ ምርት (GDP) ያለው ምጣኔ ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የ2017 ኢኮኖሚ በወረቀት ላይ ተከልሶ 24 ትሪሊዮን ብር ሲተመን ምጣኔው ከ5% በታች ወርዷል። ይኸ በመንግሥት ዘንድ “ሕብረተሰቡ በቂ የሆነ ታክስ እየከፈለ አይደለም” የሚል ዕምነት እንዳያሳድር የሚያሰጋ ነው

የብሔራዊ ባንክ የወርቅ ግዢ በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበትን እያባባሰ ነው? 04.11.2026

የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ እንደተመዘገበ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። ዳቦ፣ እንጀራ እና አትክልት ከ10 በመቶ በላይ፤ ሥጋ እና እንቁላል በአንጻሩ ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። የዋጋ ግሽበቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራትም ወደ ነጠላ አሐዝ ይወርዳል ተብሎ አይጠበቅም።

ሞያሌ፦ የይገባኛል ውዝግብ ከሚቀሰቅሰው ግጭት ያልተላቀቀች የኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ከተማ 28.10.2026

የኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ መሸጋገሪያ የሆነችው ሞያሌ ዳግም በግጭት ስትናጥ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሰዎች ተሰደዋል። ሞያሌ የሰዎች፣ የአደንዛዥ እጽ እና የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች የሚያዘወትሯት ኹነኛ የገበያ ማዕከል ነች። የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡባት ከተማ የግጭት ሰለባ ስትሆን የአሁኑ የመጀመሪያ አይደለም።

ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ “ለመገምገም ጊዜው ገና” እንደሆነ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ገለጸ 21.10.2026

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ “የጸጥታ ውጥረት መጨመር” እና ግጭት በሚደረግባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ “ማኅበሰረቦች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ” እንደሚያሳስበው አስታወቀ። የግጭቱ “ስፋትና የሚቆይበት ጊዜ” ስለማይታወቅ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ “ለመገምገም ጊዜው ገና” እንደሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለዶቸ ቬለ ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርቅ የተደመረበትን የጦርነት ጫና መሸከም ይችላል? 14.10.2026

ከ2019 የኢትዮጵያ 2.4 ትሪሊዮን ብር በጀት ውስጥ 96.3 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለመከላከያ ተመደበ ነው። ይሁንና ጦርነት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ገንዘብ በመንግሥት ወጪ እና የበጀት ጉድለት ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል። በምንዛሪ ሥርዓት ለውጥ እየተዳከመ የሔደው ብር ጭምር እና የዋጋ ግሽበት ድርቅ በተደመረበት የጦርነት ዳፋ መፈተናቸው አይቀርም።

በትግራይ የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ 30.09.2026

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትግራይ ክልል ቅርንጫፎች የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕግድ “ትልቅ ጥሰት ነው” የሚል አቋም እንዳላቸው የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል። እርምጃው በትግራይ እና ከክልሉ ውጪ የሚገኙ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ አድርጓል። ይህ የዕለት ተዕለት ወጪዎችን ለመሸፈን ችግር ፈጥሯል።

አፍሪካ በከርሰ ምድሯ ከሚገኙ ውድ ማዕድናት እንዴት መጠቀም ትችላለች? 23.09.2026

ከዓለም ወሳኝ ማዕድናት 30 በመቶው በአፍሪካ ያለ ነው። አህጉሪቱ ጥሬ ወይም በከፊል የተነጠሩ ማዕድናት ለዓለም አቅራቢ ሆና ቆይታለች። የተመድ ዋና ጸሀፊ “የአፍሪካ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለይም ወሳኝ ማዕድናትን ዝም ብሎ ወደ ውጭ አገር ከመላክ ይልቅ በአገር ውስጥ እሴት እና ጥሩ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ማረጋገጥ አለብን” ብለዋል።

የአውሮፓ ባንኮች የወርቅ ክምችታቸውን ከዩናይትድ ስቴትስ የሚያወጡት ለምንድነው? 16.09.2026

ኔዘርላንድስ እና ፈረንሳይ በዩናይት ስቴትስ የነበራቸውን የወርቅ ክምችት አውጥተዋል። ለውሳኔያቸው ገፊ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚነሳ የተዓማኒነት ጥያቄ ነው። ይሁንና ቀውስ ቢፈጠር ጥቅም ላይ ለማዋል ክምችቱን ወደ ባለቤቱ ጠጋ አድርጎ ማስቀመጥ ሌላው ጠቃሚ ምክንያት እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በግጭቶች በምትናጠው ኢትዮጵያ አሜሪካ የመዋዕለ-ንዋይ ዕድሎችን እያስቀደመች ነው? 09.09.2026

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ የኢትዮጵያ ጉብኝት የንግድና የመዋዕለ-ንዋይ ዕድሎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ጋርሺያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስና የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ቢወያዩም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ስለመገናኘታቸው በይፋ የተባለ ነገር የለም።

የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት ቁጥሮች በባለሙያዎች ሲፈተሹ 02.09.2026

ኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ግሽበቱ 15.3 በመቶ መድረሱን በቅርቡ ይፋ የሆነው የሀገሪቱ ስታትስቲክስ አገልሎት መረጃ ያመለክታል። መረጃው እንደሚያመለክተው በተለይ የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ ያሳየው በዋናነት በምግብ እና አልክሆል ያልሆኑ መጠጦች ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ለጨረታ ያቀረበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር እና የኢኮኖሚው ፍላጎት አንድምታ 26.08.2026
የኢራኑ ጦርነት በዩኤኢ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ 19.08.2026
የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ከዶላር አኳያ በዓመት 15 በመቶ ተዳክሟል 05.08.2026

የኢትዮጵያ ብር ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን 15 በመቶ ተዳክሟል። በሐምሌ 2016 ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ወርቅና ቡናን የመሳሰሉ ሸቀጦችን የወጪ ንግድ እንዳበረታታ ቢታመንም ሸማቾችን በኃይል የጎዳ ነው። ከዚያ ባሻገር በመደበኛ እና ትይዩ የውጭ ምንዛሪ ገበያዎች መካከል ያለው የተመን ልዩነት አሁንም በሚጠበቀው ልክ አልጠበበም።

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ኩባንያዎች በካፒታል ገበያ እንዲመዘግቡ ግፊት እያደረጉ ነው 29.07.2026

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ከጀመረ ከ18 ወራት በኋላ ባለሥልጣናቱ ኩባንያዎች ድርሻዎቻቸውን እንዲያስመዘገቡ እየጎተጎቱ ነው። እስካሁን ስድስት ኩባንያዎች ድርሻዎቻቸውን በሁለተኛው ገበያ ያስመዘገቡ ሲሆን አምስቱ የግል ባንኮች ናቸው።

የባሕረ ሰላጤው ሃገራት አፍሪካ ውስጥ በቢሊዮን ዶላሮች መዋዕለ-ንዋይ የሚያፈሱት ለምንድነው? 22.07.2026

ሀብታሞቹ የባሕረ ሰላጤው ሃገራት በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት መዋዕለ ንዋይ በአፍሪካ በማፍሰስ ላይ ናቸው። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችና ሳዑዲ አረቢያን የመሳሰሉት ሃገራት የአፍሪካን ገበያ ሲያማትሩ ማሳካት የሚፈልጓቸው አላማዎች ግን የተለያዩ ናቸው። የዶይቸ ቬለው ኬርስተን ክኒፕ ያጠናቀረው ዘገባ ለባሕረ ሰላጤው ሃገራት መዋዕለ-ንዋይ መስፋፋት ገፊው ምክንያት ምንድነው? የአፍሪካ ሃገራትስ ምን ይጠቀማሉ? የሚለውን ይፈትሻል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር የተወሰነው ለማምረቻ ዘርፍ እንዲመደብ የሚያስገድድ ሕግ እንዳያወጣ ተመከረ 15.07.2026

የኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር የተወሰነውን ለማምረቻ ዘርፍ እንዲመድቡ የሚያስገድድ ሕግ ለማውጣት የያዘው ዕቅድ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ተቃውሞ ገጥሞታል። በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር ገደብ መነሳቱ ግን ባንኮች ለአምራቹ ዘርፍ የተሻለ ብድር እንዲሰጡ ዕድል እንደሚፈጥር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ተናግረዋል። ባለፈው ሰኞ ይፋ በተደረገው ውሳኔ በ24 በመቶ ተገድቦ የነበረው የባንኮች ብድር ዕድገት ሙሉ በሙሉ የተነሳ ሲሆን የብሔራዊ ባንክ የወለድ ተመን ወደ 16% ከፍ ብሏል።

የግል ባንኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይውጣ ለተባለበት የወርቅ ግብይት ዝግጁ ናቸው? 08.07.2026

ባለፈው ዓመት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የወርቅ የወጪ ንግድ ዘንድሮ 5.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በብቸኝነት ከተቆጣጠረው ገበያ እንዲወጣ አይኤምኤፍ ግፊት እያደረገ ነው። የግል ባንኮች የወርቅ ግብይትን ለማካሔድ የሚያስችል የባለሙያ፣ የጥሬ ገንዘብ እና የመሠረተ-ልማት እጥረት አለባቸው።

የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው? 01.07.2026

ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።

“የኢትዮጵያ ዕዳ አሁን ዘላቂ ነው” የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ 24.06.2026

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ የዕዳ ጫና “ዘላቂ” ወደሚባልነት ደረጃ ዝቅ እንዳለ ተናግረዋል። ዶክተር ኢዮብ የዕዳ ጫናው መቃለሉን የገለጹት ለአከፋፈል ሽግሽግ የሚካሔደው ድርድር ሳይጠናቀቅ ነው። በድርድሩ የሚፈጸሙ የሁለትዮሽ ሥምምነቶች ሲተገበሩ ኢትዮጵያ የሁለት ዓመት ዕዳ በአንድ በጀት ዓመት ልትከፍል እንደምትችል የገንዘብ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አሕመድ ሽዴ ከፍተኛ አማካሪ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በ2019 ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ተብሎ ይጠበቃል 17.06.2026

የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊያደርግ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። መንግሥት በዓመቱ በኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከነዳጅ 235.6 ቢሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ ይፈልጋል። ለሚቀጥለው ዓመት የተዘጋጀው በጀት ለነዳጅ ድጎማ 20 ቢሊዮን ብር መታቀዱን አሳይቷል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ከፈቀደው ብድር 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ ሊለቅ ነው 10.06.2026

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ያሳደረውን ተጽዕኖ ኢትዮጵያ እንድትቋቋም አይኤምኤፍ (IMF) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከፈቀደው ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ እንዲለቀቅ ታቅዷል። ገንዘቡ የተራዘመ ብድር አቅርቦት መርሐ-ግብር አምስተኛ ግምገማ ሲጸድቅ ከሚለቀቀው 468 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።

የሥራ እጥነት እና የመፍትሄ እርምጃዎች በኢትዮጵያ 03.06.2026

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዲግሪ ይዘው ሥራ ማግኘት ቸግሯቸዋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ምህንድስና የተመረቀችው ወጣት ሥራ ሲጠፋ "ይኸን ሁሉ አመት ባላቃጠልኩ" ለማለት በቅታለች።

ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች? 20.05.2026

ታላቁን የህዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተከታታይ ያስመረቀችው ኢትዮጵያ ለኬንያ የምትሸጠውን ኤሌክትሪክ ለማሳደግ እያጤነች ትገኛለች። አራት ተማሪ ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በኩራዝ የሚያጠኑትን እናት ጨምሮ 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ግን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ቀን ይናፍቃሉ።

ባይናንስ ከአርብ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረግ ግብይት ያቆማል 13.05.2026

በዓለም ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የሆነው ባይናንስ ከመጪው አርብ ጀምሮ በብር የሚደረጉ ግብይቶች እንደሚያቆም አስታውቋል። ባይናንስ በዘረጋው የመገበያያ መድረክ ከኢትዮጵያ የሚሳተፉት ክሪፕቶከረንሲ “አዋጭ ኢንቨስትመንት” እንደሆነ የሚያምኑ ወጣቶች ናቸው። መሰል ግብይቶች ግን ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 250% ጨመረ 06.05.2026

የኢትዮጵያ መንግሥት የ2018 የመጀመሪያ መንፈቅ የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ 126.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሰነድ አሳይቷል። የወለድ ክፍያው በስድስት ወራት ለዕዳ ከተመደበው በጀት 64.6% ድርሻ አለው። ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት አኳያ ሲነጻጸር ግን ከ250 በመቶ በላይ ጨምሯል። በ2017 የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለሀገር ውስጥ ወለድ መንግሥት 36 ቢሊዮን ብር ከፍሎ ነበር።

Listen to the ከኤኮኖሚው ዓለም podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.