DW
ከኤኮኖሚው ዓለም
በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ምን ያሳያል? 04.12.2024 9:57
በ2017 የመጀመሪያ መንፈቅ የወጪ ንግድ በ81% ማደጉን የብሔራ ባንክ ሪፖርት ያሳያል። የንግድ ሚዛን ጉድለት እየቀነሰ በመሔዱ የሀገሪቱ የክፍያ ሚዛን ተሻሽሎ ትርፍ 573 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ይጠቁማል። የሐምሌው የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥዓት ለውጥ በዶላር የክፍያ ግዴታ በነበረባቸው ባንኮች ላይ ስላደረሰው ኪሳራ ግን ምንም አላለለም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደረሰኝ ቁጥጥር ለምን ከመርካቶ ተቃውሞ ገጠመው? 20.11.2024 8:45
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመርካቶ አስመጪዎች፣ አከፋፋዮች እና ቸርቻሪዎች ደረሰኝ መቁረጣቸውን ለማረጋገጥ የጀመረው ቁጥጥር ከገበያው ተዋናዮች ተቃውሞ ገጥሞታል። ቁጥጥሩ ከተጀመረ በኋላ ባለፉት ሣምንታት በመርካቶ የንግድ መደብሮች ተዘግተው ነበር። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 የመጀመሪያ መንፈቅ የሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ በ12 ቢሊዮን ብር ከፍ ቢልም ከዕቅዱ በ10 ቢሊዮን ብር ገደማ ዝቅ ያለ ነው።
የጀርመን ጥምር መንግሥት ሲፈርስ ሀገሪቱ የተጣለባት የብድር ገደብ ሚና ምንድነው? 13.11.2024 9:58
ጀርመን በምትመራበት መሠረታዊ ሕግ ከአጠቃላይ ዓመታዊ የምርት መጠን (GDP) ከ0.35 በመቶ በላይ እንዳትበደር ገደብ ተጥሎባታል። የሀገሪቱ ኤኮኖሚን ለማነቃቃት ገደቡ እንዲነሳ በሚሹት መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ እና አይሆንም የሚል አቋም በነበራቸው በቀድሞው የፋይናንስ ሚኒስትር ክርስቲያን ሊንድነር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የጀርመን ጥምር መንግሥት ፈርሷል።
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ በኢትዮጵያውያን ትከሻ ላይ ተጫነ? 06.11.2024 11:05
ገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን 845.3 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ ከነወለዱ ለመክፈል ተረክቧል። መንግሥት ንግድ ባንክን ለመታደግ በተከተለው አካሔድ ትምህርት እና ጤና የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለመሥራት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለዕዳ ክፍያ ሊያውል አሊያም ገቢውን ለማሳደግ ተጨማሪ ግብር ሊያስከፍል እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ኢትዮጵያውያን የአፍሪካ ኮምት ተሳታፊዎች በጀርመን በቀሰሙት ልምድ ሀገራቸውን ለመጥቀም ተስፋ ሰንቀዋል 30.10.2024 11:30
አራት ኢትዮጵያውያን አፍሪካ ኮምት በተባለው እና በጎርጎሮሳዊው ከ2023 እስከ 2025 በሚዘልቀው መርሐ-ግብር በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ይኸ መርሐ-ግብር አፍሪካውያን ወጣት ባለሙያዎችን ከሥመ -ጥር የጀርመን ኩባንያዎች የሚያገናኝ ነው። ገነት አታክልት እና ጌቱ ታደለ በሁለት ግዙፍ የጀርመን ኩባንያዎች ውስጥ ለስምንት ወራት እየሰሩ ሲማቁ ቆይተዋል።
በኢትዮ-ቴሌኮም መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ ልብ መባል ያለባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? 23.10.2024 10:33
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮ-ቴሌኮምን መደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ከጀመረ በኋላ የኩባንያውን ያለፈ ዓመት ገቢ እና ትርፍ በማስላት “ያዋጣል” ወይስ “አያዋጣም” የሚሉ ትንታኔዎች በማኅበራዊ ድረ-ገጾች እና በመገናኛ ብዙኃን እየታዩ ነው። መንግሥት ከመደበኛ አክሲዮኖች ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር (255 ሚሊዮን ዶላር) የማግኘት ዕቅድ ያለው ሲሆን ወደፊት የኢትዮ-ቴሌኮም 45 በመቶ ድርሻ ለውጪ ባለወረቶች ይሸጣል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ ልብ መባል ያለባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? ባለሙያዎችስ ምን ይመክራሉ?
የኢትዮጵያ ባንኮች የውጪ ምንዛሪ መሸጫ እና መግዣ ተመን ልዩነት ወደ 2% ቢያጠቡም የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን አላሳወቁም 16.10.2024 10:05
የኢትዮጵያ ባንኮች በውጪ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ተመኖቻቸው መካከል ያለውን ልዩነት የብሔራዊ ባንክን የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ ወደ 2 በመቶ ዝቅ አድርገዋል። እርምጃው የባንኮች የዶላር የመሸጫ ተመን ከ6 እስከ 10 ብር እንዲቀንስ አድርጎታል። ይሁንና ባንኮቹ በተቆጣጣሪው በታዘዙት መሠረት ለደንበኞቻቸው ከውጪ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች ሲያቀርቡ የሚጠይቁትን ክፍያ እና ኮሚሽን ይፋ አላደረጉም።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞች ከሚጠበቀው የደመወዝ ጭማሪ ለምን ተስፋ አጡ? 25.09.2024 13:48
መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በ91.4 ቢሊዮን ብር ባቀደው የደመወዝ ጭማሪ ደስተኞች አልሆኑም። የመንግሥት “ለኑሮ ውድነት መደጎሚያ የደመወዝ ማሻሻያ” የመከላከያ ሠራዊት እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ ለ2.4 ሚሊዮን ሠራተኞች የሚደረግ ነው። ዕቅዱ ከተተገበረ ዝቅተኛ ተከፋይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በ332% ከፍ ይላል። ገንዘብ ሚኒስቴር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን “ተጠንቶ እና ተደግፎ የቀረበው እና በማክሮ ኤኮኖሚ ኮሚቴ የታየው የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ” መቅረቡን በማኅበራዊ ድረ ገጾች የተሰራጨው ሰነድ ይጠቁማል።
የኬንያ እና የጀርመን የስደት እና የሰለጠኑ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ሥምምነት 18.09.2024 10:36
የሰለጠኑ ኬንያውያን ሠራተኞች በጀርመን መሥራት እና መኖር የሚችሉበት ሥምምነት ባለፈው ሣምንት በበርሊን ከተማ ተፈርሟል። ሥምምነቱ በጀርመን የመኖር ፈቃድ የሌላቸው ኬንያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ነው። ኬንያ ለወጣቶቿ አመርቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን 82 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕዳዋን ለመክፈል የከበዳት ሀገር ሆናለች።
ሐዋላን ወደ መደበኛው ሥርዓት ለመመለስ ያቀደው የኢትዮጵያ የ100 ቢሊዮን ብር ዕቅድ ይሳካል? 11.09.2024 10:16
ባንኮች ሐዋላ ለሚላክላቸው ደንበኞች እስከ 17 በመቶ የሚደርስ የአዲስ ዓመት ስጦታ ቃል ገብተዋል። የአንዳንዶቹ ባንኮች ስጦታ ከመደበኛው የዶላር ምንዛሪ ሲደመር በተለምዶ ጥቁር ከሚባለው የጎንዮሽ ገበያ የሚያቀራርባቸው ነው። የኢትዮጵያ 31 ባንኮች ሐዋላ ለሚልኩ የ100 ቢሊዮን ብድር ማዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ይፋ አድርገዋል
አበዳሪን ከተበዳሪ ያገናኘው የቻይና አፍሪካ ዘጠነኛ የትብብር ፎረም 04.09.2024 12:20
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ መሪዎች የሚሳተፉበት ዘጠነኛው የቻይና አፍሪካ ፎረም ዛሬ በቤጂንግ ተጀምሯል። ቻይና ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ዋና አበዳሪ ሆናለች። አንጎላ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ናይጄሪያ ከቻይና በቢሊዮኖች ዶላሮች በመበደር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናቸው።
አምስት ፋብሪካዎች በ2016 ያመረቱት ስኳር ከኢትዮጵያ ፍላጎት 10% ገደማ ብቻ ነው 28.08.2024 11:06
ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫ፣ ከሰም እና ጣና በለስ ፋብሪካዎች በ2016 ያመረቱት 124,097 ቶን ስኳር እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዐስታውቋል። ይኸ የሚሸፍነው 10% የኢትዮጵያን የስኳር ዓመታዊ ፍላጎት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ኸርነስት ኤንድ ያንግ በተባለ አማካሪ ኩባንያ ያሠራው የገበያ ጥናት የሀገሪቱ የስኳር ፍላጎት በጎርጎሮሳዊው 2020/2021 መጨረሻ 1.2 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያሳያል። መንግሥት እስከ ጥር ስምንት ስኳር ፋብሪካዎችን በመሸጥ የፈሰሳባቸውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር መመለስ እና የግል መዋዕለ-ንዋይ ወደ ዘርፉ ለመሳብ አቅዷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ታክስ ሳይጨምር ከዘርፉ የሚሰበስበውን ገቢ 4 በመቶ ማሳደግ ይችላል? 21.08.2024 10:25
ኢትዮጵያ ከታክስ የምትሰበስበው ገቢ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) 4 በመቶ ለመጨመር መንግሥት ታቅዷል። ለ2017 በጸደቀው በጀት መንግሥት ከታክስ 502 ቢሊዮን ብር ሊሰበስብ ተዘጋጅቶ ነበር። በጀቱ ሲሻሻል በዕቅዱ መሠረት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በአንድ በመቶ ጨምሮ ወደ 850 ቢሊዮን ብር ገደማ ከፍ ብሎ እንደሚከለስ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ ታሪፍን ቢያንስ በየሦስት ወሩ በ10 በመቶ ሊጨምር ነው 14.08.2024 10:11
የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ በየሦስት ወሩ ቢያንስ በ10% ለመጨመር ተዘጋጅቷል። ጭማሪው መንግሥት ከዓለም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እና ብድር ባገኘበት ሥምምነት የተካተተ ነው። በሥራ ላይ ያለው ተመን ዕዳ ክፍያን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ የሚሸፍነው 18% ብቻ ነው
ዶላር ፍለጋ፦ የኢትዮጵያ ባንኮች እና የጥቁር ገበያው ፉክክር እስከ የት ይጓዛል? 07.08.2024 10:10
ኢትዮጵያ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት መከተል ከጀመረች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ ባካሔደው ጨረታ አንድ ዶላር በ107 ብር ከ90 ሣንቲም ተሸጧል። ተመኑ ትላንት በባንኮች ከነበረው አማካኝ ምንዛሪ በ4 ብር ገደማ ከፍ ያለ ነው። ባንኮች በምንዛሪ ተመን ሲሽቀዳደሙ በተለምዶ ጥቁር እየተባለ የሚጠራው የትይዩ ገበያ ተዋንያን አድፍጠው ይታዘባሉ። በአዲሱ በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት የዋጋ ግሽበት በጥር ከ30 እስከ 35 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሰነድ ያሳያል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የኢትዮጵያ የተራዘመ የብድር አቅርቦት የፖሊሲ አላባዎች የሚሳኩ ናቸው? 31.07.2024 13:21
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ያጸደቀው የተራዘመ የብድር አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ያሉበትን ሥር የሰደዱ ችግሮች ለመቅረፍ የተወጠኑ አምስት የፖሊሲ አላባዎች አሉት። የገቢ እና የወጪ ንግድ ሚዛን ጉድለትን ለማረቅ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገኝበታል። የተራዘመ የብድር አቅርቦት የተሰኘውን መርሐ-ግብር ለማስፈጸም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። ዓለም ባንክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ ሰጥቷል።
ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን አይነት ኤኮኖሚያዊ እንድምታ ይኖረዋል? 24.07.2024 12:09
ጆ ባይደን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ሲያገልሉ ዴሞክራቶች የመነቃቃት አዝማሚያ አሳይተዋል። በንግድ ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች በአንጻሩ ካማላ ሐሪስ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ በኤኮኖሚው ረገድ ምን ለውጥ እንደሚኖር እርግጠኞች አይደሉም። በርካታ ኩባንያዎች ግብር ለመቀነስ ቃል የገቡት ዶናልድ ትራምፕ እንዲመረጡ ይደግፋሉ።
የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የመገበያያ ገንዘብ ልውውጥ ሥምምነት እንዴት ያለ ነው? 17.07.2024 10:08
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ 817 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የመገበያያ ገንዘብ ልውውጥ ሥምምነት ተፈራርመዋል። ባንኮቹ ሥምምነቱ “በሁለቱ ሀገራት መካከል የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ይደግፋል” ብለዋል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ኻሊድ ሞሐመድ ባላማ ናቸው። ባንኮቹ በድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ብር እና ድርሐም የበለጠ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እንዲሁም የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ሥርዓቶችን ለማስተሳሰር የመግባቢያ ሥምምነቶች ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች አማካኝ ገቢ ለመሠረታዊ ፍላጎቶች ከሚያስፈልገው የመኖሪያ ደመወዝ በ2000 ብር ያነሰ ነው 03.07.2024 10:29
በኢትዮጵያ አማካኝ ወርሀዊ ደመወዝ 3000 ብር እንደሆነ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ይፋ አድርጓል። ይኸ ለመሠረታዊ ፍላጎቶች ከሚያስፈልገው መኖሪያ ደመወዝ (Living Wage) እጅግ ያነሰ ነው። ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤቶቿ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ካልደነገጉ የመጨረሻዎቹ የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ናት።
የብሔራዊ ባንክን ካፒታል ከ500 ሚሊዮን ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚያሳድግ የአዋጅ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል 26.06.2024 10:36
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተከፈለ ካፒታል ከ500 ሚሊዮን ብር ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚያሳድግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። በረቂቅ አዋጁ “የዋጋ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የገንዘብ ፖሊሲን ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ” የብሔራዊ ባንክ ዋና ዓላማ ነው። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደው የብድር መጠን፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ወለድ የሚወስኑ ድንጋጌዎች ተካተውበታል።
ለብድር አሰጣጥ ጠበቅ ያሉ መመሪያዎች ያወጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስከ ዛሬ የት ነበር? 19.06.2024 9:59
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመንግሥት ባንኮች እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንደ “ተዛማጅ ወገኖች” እንደሚቆጠሩ ወስኗል። የባንኩ መመሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተቋማቱ የሚሰጠውን የብድር መጠን እንዲገድብ የሚያስገድድ ነው። እስከ ጎርጎሮሳዊው 2022/23 ብቻ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች 777.8 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለባቸው።
የኢትዮጵያ የበጀት ጉድለት በ2017 ከአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት መጠን 2.1% ድርሻ ይኖረዋል 12.06.2024 10:50
በ2017 የኢትዮጵያ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ ሀገራዊ የምርት መጠን 2.1% ድርሻ እንደሚኖረው አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። መንግሥት ለሚቀጥለው ዓመት ያዘጋጀው 971 ቢሊዮን ብር በጀት 358.5 ቢሊዮን ብር ጉድለት ይገጥመዋል። ከ2017 በጀት 139.3 ቢሊዮን ብር ለዕዳ ክፍያ የታቀደ ነው። መንግሥት ኤኮኖሚው በ8.4% ያድጋል ብሎ ይጠብቃል። ኢትዮጵያ የምትከተለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት በ2017 እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዋል።
ደቡብ ኮሪያ እና አፍሪካ አንዳቸው ከሌላው የሚፈልጉት ምንድነው? 05.06.2024 8:35
በመጀመሪያው የኮሪያ አፍሪካ ጉባኤ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የኬንያን ጨምሮ 25 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል። ከደቡብ ኮሪያ የወጪ እና ገቢ ንግድ አፍሪካ ያላት ድርሻ ከ2% ያነሰ ነው። የአፍሪካ መሪዎች ደቡብ ኮሪያ ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ ዕድገት እንድታቋድሳቸው ይፈልጋሉ። ደቡብ ኮሪያ በአንጻሩ በአፍሪካ ማዕድናት ላይ አይኗን ጥላለች።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.