SBS

አውስትራሊያ ስትገለጥ

Society AM ↓ 144 episodes

ሕይወትዎን አውስትራሊያ ውስጥ ሲመሰርቱ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች። ስለ ጤና፣ መኖሪያ ቤት፣ ሥራ፣ ቪዛዎችና ዜኘት፣ የአውስትራሊያ ሕጎችና ሌላም በአማርኛ ያድምጡ።

Author

SBS

Category

Society

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Jun 9, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የሠፈራ መምሪያ፤ የመሸጋገሪያ ቪዛ ዓይነቶች 29.10.2021

አንድ ሰው አውስትራሊያ ውስጥ ሆኖ የቪዛ ማመልከቻ ሲያቀርብ፤ ማመልከቻው ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ አገሪቱ ውስጥ ሕጋዊ ሆኖ እንዲቆይ የመሸጋገሪያ ቪዛ ይሰጠዋል። የመሸጋገሪያ ቪዛ ዓይነቶች ዘርፈ ብዙ ናቸው። አሰጣጣቸውም እንደ አመልካቹ ሁኔታ ይወሰናል።

የላቀ ውጤት ያላቸው ተማሪዎችን ስለሚቀበሉ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት የሚገባ 07.06.2021

የላቀ የትምህርት ውጤት ላላቸው ልጆች የተሻለ ትምህርት ቤት መሻት የአያሌ ወላጆች ፍላጎት ነው። ብርቱ ፉክክርና ውጤት ተኮር ከሆኑት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በላቀ ውጤት የሚዘለቀባቸውና ትኩረትንም የሚሹት የምርጥ ተማሪዎች መማሪያ የሆኑ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ኑዛዜ ፅፎ የማስቀመጥ ጠቀሜታ 31.05.2021

በርካታ አውስትራሊያውያን ለኑዛዜ ጠቀሜታ ያላቸው ግምት አነስተኛ መሆኑን የምርምር ግኝቶች ያመለክታሉ። የመስኩ ተጠባቢዎችም ያለ ዕድሜ፣ የማኅበራዊ ምጣኔ ደረጃና ብሔራዊ ማንነት ልዩነቶች፤ ዜጎች ለቅርብ ቤተሰባቸው ኑዛዜ የማስፈርን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተው ዕቅዳቸው ውስጥ እንዲያስገቡ ይመክራሉ።

በቅጡ የማይታወቁና አውስትራሊያ ውስጥ ሁሉም ሾፌር ልብ ሊላቸው የሚገቡ የመንገድ ሕጎች 17.05.2021

ታዝማኒያ ውስጥ መኪና እየነዱ በሞባይል ስልክዎ የGPS አቅጣጫ ጠቋሚ አፕስ መጠቀም ወይም እጅዎን መስኮት ላይ አሳርፈው ማሽከርከር ሕገ ወጥ መሆኑን ያውቃሉ? የአውስትራሊያ መንገዶች ላይ ሳያውቁ ሕግ ጥሰው አንዳይገኙ ለሎች እምብዛም ልብ የማይባሉ የመንገድ ሕጎችን እናጋራዎታለን።

የቪዛዎን ቀነ ገደብ ማሳለፍና መዘዞቹ 16.04.2021

አውስትራሊያ ውስጥ ሆነው የቪዛዎ ቀነ ገደብ ቢያልፍ ምን ይገጥምዎታል? ምንስ ሊያደርጉ ይችላሉ?

ከአውስትራሊያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተመረቁ በኋላ እንደምን የሥራ ቪዛ ማግኘት ይችላሉ? 25.03.2021

አውስትራሊያን የዓለም አቀፍ ተማሪዎች መዳረሻ ለማድረግ የሞሪሰን መንግሥት የቪዛ መመዘኛዎቹን ለባሕር ማዶ ተማሪዎች አላልቷል። ይህንንም ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ጊዜያዊ የምሩቃን ቪዛቸውን ተጠቅመው የሥራ ልምድ በማግኘት ለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኛነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

በደን ቃጠሎ ወቅት ቤተሰብዎንና ንብረትዎን ከአደጋ ለማዳን እንደምን ዕቅድ ሊነድፉ ይችላሉ? 23.12.2020

ቤተሰብዎንና ቤትዎን ከእሳት አደጋ ተጋላጭነት መታደግ ማለት ቀድመው ስንዱ መሆን ማለት ነው። የመስኩ ጠበብትም ለደን ቃጠሎዎች ተጋላጭ የሆኑ ቀዬዎች የሚኖሩ ሰዎች የድንገተኛ አደጋ ዕቅድ እንዲኖራቸው ምክረ ሃሳብ የሚለግሱት ለዚህ ነው።

በእርጥብ በጋ ወቅት ከጎርፍ ለመዳን እንደምን መሰናዶ ማድረግ ይቻልዎታል? 22.12.2020

የአውስትራሊያ ምሥራቃዊ ክፍለ አገራት ከአማካይ የዝናብ መጠን በተጨማሪ እርጥብ በጋን ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረጉ ነው። የመስኩ ጠበብቶችም ሰዎች ጎርፍ ሊከስትባቸው በሚችሉ አካባቢዎች ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እያስጠነቀቁ ነው።

ጥንቃቄ በዓሣ ጠመዳ፣ ጎርፍና ዋና ወቅት 20.12.2020

በበጋ ወራት በአውስትራሊያ የባሕር ዳርቻዎች፣ ወንዞችና ወራጅ ውኃዎች ለመዝናናት ተስማሚ ጊዜ ነው። ሆኖም ራሳቸውን ከውኃ ደህንነት ደንቦች ጋር ላላዋደዱ መጤዎች ሕይወታቸው ተጋላጭም ነው።

በበጋ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን እንደምን ማወቅና መረጃዎችንም ማግኘት ይችላሉ? 18.12.2020

አውስትራሊያ በጋ ሲመጣ ዘና የምትልበት ወቅት ነው፤ ሆኖም ደህንነትን ጠብቆ መቆየት ጠቃሚ ነው። የድንገተኛ አደጋ ማስጠንቀቂያ አሠራሮችና ማንቂያዎች ደህንነትዎን እንዲጠብቁና ግንዛቤ እንዲጨብጡ ያግዝዎታል።

ዋና ለመልመድ ጊዜው መቼም አይረፍድም 13.12.2020

በአብዛኛው መጤዎችና ጎብኚዎች አውስትራሊያ ውኃዎች ውስጥ ለመስጠም አደጋ ተጋላጭ ናቸው። በየዓመቱ ውኃ ውስጥ ሰጥመው ሕይወታቸው ከሚያጡት ውስጥ ግማሽ ያህሉ የአውስትራሊያ ነዋሪ ያልሆኑቱ ናቸው።

Silent killers: Heatwaves and skin damage in the Australian summer - ድምፅ አልባ ገዳዮች፤ የሙቀት ወላፈንና የቆዳ ጥቃት በአውስትራሊያ በጋ 10.12.2020

Australia has just experienced its hottest November on record. While La Niña is expected to bring a wetter summer season, the Bureau of Meteorology, also predicts that heatwaves will last over a prolonged period. Experts warn to take extra precaution indoors and outdoors to prevent sun and heat-related health problems. - አውስትራሊያን በወርኃ ኖቬምበር የጋለ ሙቀት ጎብኝቷታል። የመስኩ ጠበብት በቤት ውስጥም ሆነ በውጪ ከፀሐይና ከሙቀት ጋር በ...

በጎ ፈቃደኛ የእሳት አደጋ ተከላካይ መሆን እንደምን ይችላሉ? 04.12.2020

የእሳት አደጋ ተከላካዮች በየዕለቱ በርካታ አደጋዎች ይደቀኑባቸዋል። በግል ሕይወታቸውም ይህ ነው የማይባል መስተጓጎሎች ይገጥሟቸዋል። አውስትራሊያ ቤቶችና ማኅበረሰባትን በመከላከል ረገድ የበጎ ፈቃደኛ እሳት አደጋ ተከላካዮች ላይ ከፍ ባለ መልኩ ታመዝናለች።

የሠፈራ መምሪያ - ለሥራ ቃለ መጠይቅ እንደምን ሊዘጋጁ ይገባል 18.09.2020

አውስትራሊያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ፈልጎ ለማግኘት ወይም ሌላ አዲስ ሥራ ለመፈለግ ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል። የሥራ ፈላጊ ማመልከቻዎ ተመራጭ ሆኖ ለቃለ መጠይቅ ሲጠሩ በቅድሚያ ደስታን ይፈጥራል፤ ጥቂት ቆይቶም ጭንቀትን ሊያሳድር ይችላል።በሥራ ቃለ ምልልስ ወቅት መልካም ውጤት ለማግኘት የሚያሻዎ በቂ ዝግጅት ማድረግና ምን ሊገጥምዎት እንደሚችል ግንዛቤ ሊኖርዎት ይገባል።

የሠፈራ መምሪያ - ብቸኝነትን በአዲስ አገር መወጣት 05.09.2020

የቋንቋ ችሎታ ማነስ፣ የባሕል ልዩነቶች ፣ ከቤተሰብና ጓደኞች መነጠል ለበርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ለብቸኝነት መዳረግ በዋነኛ አስባብነት ይጠቀሳሉ።

አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን ለፍቺ መብቃት ይቻላል? 06.08.2020

በአውስትራሊያ የቤተሰብ ጥናቶች ኢንስቲትዩት የምርምር ግኝት መሰረት በአብዛኛው ለፍቺ የሚዳረጉት ዕድሜያቸው በ20ዎች ግማሽና መጨረሻ፤ እንዲሁም በ40ዎቹ ማጠናቀቂያ ግድም ናቸው።ለፍቺ ሲዳረጉም በአማካይ ለዘጠኝ ዓመታት ወይም ከዚያ ላነሱ ጊዜያት በትዳር የቆዩ ናቸው።

የሠፈራ መምሪያ - ወሲባዊ ትንኮሳና የእርስዎ መብቶች በሥራ ቦታ 31.10.2019

የአውስትራሊያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባሰባሰበው የሠራተኞች አተያይ መሠረት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከሶስት ሠራተኞች አንዳቸው ወሲባዊ ትንኮሳ ገጥሟቸዋል። ወሲባዊ ትንኮሳ በእርስዎ ወይም ሌላ በሚያውቁት ሰው ላይ ደርሶ ከሆነ ዕርዳታ የማግኛ መንገዶች አሉ።

አፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ላልሆኑቱ አረጋውያን በቂ የሰብዓዊና ባሕላዊ ክብካቤ ግልጋሎቶች አሉን? 28.10.2019

ከሶስት አንድ አውስትራሊያውያን እንግሊዝኛ ተናጋሪ ያልሆኑ አገራት የተወለዱ ናቸው። የአረጋውያን ክብካቤ ግልጋሎት ሰጪዎች ባሕላዊ ዝንቅነት ላላቸው የደሜንሽያ ተጠቂዎችና ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለተመለሱት ተጠዋሪዎች ሰብዓዊና ባሕላዊ ግልጋሎቶችን ለመስጠት ምን ያህል ስንዱ ናቸው?

የሠፈራ መምሪያ - ከመስጠም ራስን መታደግ እንደምን ይቻላል? 16.10.2019

ሌላ ወባቂ በጋ በመቃረቡ፤ ኃላፊዎች ዋናተኞች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳስባሉ። ውኃ ውስጥ ሰጥመው ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ወዲህ በአሥር ፐርሰንት አሻቅቧል።

Listen to the አውስትራሊያ ስትገለጥ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.