SBS
የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ
ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
"ተግዳሮት ፊታችን ሲጋረጥ፣ መልካም ዕድልንም ይዞ እንደሚመጣ ማመን፤ ተስፋ አለመቁረጥና ራስን ለአዲስ ነገር ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል" በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ 12.02.2026 12:37
በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከውልደትና ዕድገት፣ የትምህርትና ሥራ፣ የተግዳሮትና ስኬት የሠፈራ ሕይወታቸውን የዳሰሱበትን የግለ ሕይወት ትረካ በምልሰታዊ ምልከታ ይቋጫሉ። የወደፊት ትልማቸውንም ያጋራሉ።
በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ትምህርት፣ ሥራና የአውስትራሊያ ክብር ሽልማት 12.02.2026 22:27
በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ በሀገረ አውስትራሊያ ከመንፈሳዊ የአገልግሎት ተልዕኳቸው ጎን ለጎን ስላካሔዷቸው የትምህርትና የሥራ ዓለም ሕይወታቸው ነቅሰው ያወጋሉ።
በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከነገሌ ቦረና እስከ አውስትራሊያ 10.02.2026 20:39
በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከውልደት ቀዬአቸው ነገሌ ቦረና እስከ ሁለተኛ ሀገራቸው አውስትራሊያ የተጓዙበትን የመንፈሳዊና ዓለማዊ ግለ ሕይወት ታሪካቸውን ያጋራሉ።
ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር 30.08.2025 22:38
ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።
"ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር 30.08.2025 13:18
"የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን ከእሥር እንዳስለቀቀው ነቅሶ ያወጋል።
"ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴ 03.04.2025 9:22
አንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።
"የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁ 29.01.2025 21:53
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።
ሶስና ወጋየሁ፤ ከአውስትራሊያ ጥገኝነት ጥየቃ ለክብር ሽልማት መብቃት 21.01.2025 14:15
የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ እንደምን በሀገረ አውስትራሊያ ከጥገኝነት ጥየቃ ለከፍተኛ የክብር ሽልማት እንደበቁ ያወጋሉ።
ሶስና ወጋየሁ፤ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሀገረ አውስትራሊያ 09.01.2025 18:30
ሶስና ወጋየሁ፤ ስርከስ ኢትዮጵያ ካፈራቸው ምርጥ ኮከቦች አንዷ ናቸው። ከሜክሲኮ አደባባይ ውልደትና ዕድገታቸው እስከ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃ ሕይወታቸው ያወጋሉ።
" 'ሞቷል' የሚባለው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር እንደተነሳ የምናሳየው የምንሠራቸውን ነገሮች በማሳየትና ተጠያቂም በመሆን ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 29.09.2024 12:29
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ የበጎ ፈቃደኛ አገልጋይነትን ፋይዳዎች በማመላከት ጥሪዎችን ያቀርባሉ።
"በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን የምንል ከሆነ፤ የግል የፖለቲካ አቋማችንና ሃይማኖታችንን ሳናንፀባርቅ ወደ አንድነት እንምጣ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 29.09.2024 14:09
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለማኅበረሰብ አገልጋይነት ገፊና ሳቢ የሆኗቸውን አስባቦች፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን ያወጉት 'ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ' ግለ ታሪካቸው ተከታይ አድርገው ይናገራሉ።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ 24.09.2024 16:21
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው የወቅቱ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ናቸው። ከውልደት ሥፍራቸው ጎንደር ከተማ እንደምን ለሀገረ አውስትራሊያ እንደበቁ ግለ ታሪካቸውን አጣቅሰው ያወጋሉ።
"መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 09.09.2024 16:56
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።
ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም 08.09.2024 25:35
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል።
"ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 03.09.2024 12:54
ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።
"በ'ውጫሌ ውል' ተውኔት መክፈቻና መዝጊያ ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ፈንቅሎ የወጣ የጋለ ሀገራዊ ስሜት ነበር" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና 27.08.2024 16:48
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ውልደትና ዕድገቱን፣ የቀለም ትምህርትና የትወና ጅማሮውን ነቅሶ ግለ ታሪኩን በከፊል አውግቷል። ወደ ቀጣዩ ግለታሪክ ትረካው ያመራው እንደምን ከአንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር ለመድረክ እንደበቃ በማንሳት ነው።
ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና፤ ከወላይታ እስከ አውስትራሊያ 22.08.2024 15:36
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና ከስመ ገነን የተውኔት ተጠባቢዎች አንዱና ተጠቃሽ ነው። በሀገረ አውስትራሊያ ከቤተሰቡ፤ በሀገረ ኢትዮጵያ ከትወና ጋር ተዋድዶና ተዛንቆ አለ።
"ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን 13.08.2024 17:37
እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።
"ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ 28.07.2024 15:07
ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።
የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ 21.06.2024 19:23
የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።
"የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረት 02.06.2024 14:21
በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።
ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነት 02.06.2024 15:28
ለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።
"በእኔ በኩል ቀጣዩ ሕይወቴ አውስትራሊያ ይሁን ኢትዮጵያ አላውቅም" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 26.05.2024 17:40
በአንድ የጀርመን ባለስልጣን "ሰርከስ ኢትዮጵያ ጀርመን ውስጥ ኮካ ኮላ የሚታወቀውን ያህል በልጆች ዘንድ ይታወቃል" የተባለለት ድርጅት ዳይሬክተር የነበረው ዐቢይ አየለ፤ ስለ ጥገኝነት ጥየቃ ውጣ ውረዶችና የአውስትራሊያ ሕይወት ጉዞ ጅማሮው ይናገራል።
"ከ30 የሰርከስ ኢትዮጵያ አባላት ውስጥ 15ታችን አውስትራሊያ ጥገኝነት ጠይቀን ቀረን" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ 26.05.2024 14:24
የቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ስለ ትውልድና ዕድገቱ፣ የቀለም ትምህርትና የጥበብ ዕውቀት ቀሰማውን ከሰርከስ ኢትዮጵያ መቀላቀሉ ጋር አሰናስሎ አንስቷል። በሀገረ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃው ውሳኔውን አስከትሎ ያወጋል።
ዐቢይ አየለ፤ ከአዋሬ እስከ አውስትራሊያ 21.05.2024 13:52
የቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ ከጥበብ ሙያ ጅማሮው ተነስቶ፤ የስደት ጉዞውን አጣቅሶ እስከ አውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.