SBS

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

Society AM ↓ 44 episodes

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።

Author

SBS

Category

Society

Podcast website

www.sbs.com.au

Latest episode

Feb 12, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

መለስ ሳህሌ፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ 14.05.2024

የቀድሞው የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና አዘጋጅ መለስ ሳህሌ፤ ስለ ድሬዳዋ ትውልድና ዕድገቱ፣ የጂቡቲ ስደት ፈተናዎቹና የአውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።

ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ 06.02.2024

ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ እንደምን ከአገረ ኢትዮጵያ በጃፓን ዞረው ለአውስትራሊያ ምድር እንደበቁ፤ የትምህርት፣ የሥራ፣ የቤተሰብ፣ ማኅበረሰባዊና መንፈሳዊ ሕይወት ትስስሮሻቸውን አንስተው ያወጋሉ።

"ሕይወት የጣለችብኝን ውጣ ውረድ ተወጥቻለሁ፤ ተስፋ ብቆርጥ ኖሮ አልኖርም ነበር፤ አሁን በሁለት እግሬ ቆሜያለሁ" ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም 22.10.2023

ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በአዲስ አበባ አራዳ የዕድገት፣ በሱዳን የስደትና በአውስትራሊያ የሠፈራ ከፊል ሕይወቷን አጣቅሳ በቀዳሚ ሁለት ከፍለ ዝግጅቶች አውግታለች። የመደምደሚያ ግለ ታሪኳ የሚቋጨው በምስጋና ጀምሮ በወደፊት ትልሞቿ ነው።

ብዕሊ አድሃኖም፤ ከላጤ እናትነት እስከ ምሕንድስና 22.10.2023

ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት በለጋ የወጣትነት ዘመን ከአዲስ አበባ - አራዳ ተንስታ፤ የሱዳንን አዋኪ የስደት ሕይወት ገፍታና ለአቅመ ሔዋን ሳትደርስ የመጀመሪያ ልጇን አገረ አውስትራሊያ ውስጥ ለመገላገል እንደምን እንደበቃች አውግታለች። በቀጣዩ ትረካዋ የአውስትራሊያ የሠፈራ ኑሮን ተቋቁማ እንደምን ለምሕንድስና ባለሙያነት እንደበቃች አንኳር የሕይወት ጉዞ ተግዳሮቶችና ስኬቶቿን በመንቀስ ታነሳለች።

ብዕሊ አድሃኖም፤ ከአራዳ እስከ አውስትራሊያ 19.10.2023

"ልቤን ተከትዬ ጥፋት ሠራሁ" የምትለዋ ብዕሊ አድሃኖም ግለ ታሪክ መነሻ ከአዲስ አበባ ዕምብርት አራዳ ነው። አውስትራሊያን ሁለተኛ አገሯ ለማድረግ የበቃችው በለጋ ዕድሜዋ ፈታኙን የስደት ሕይወትን በአገረ ሱዳን ተቋቁማ ነው።

ስጦታው በፍቃዱ፤ ከቤተ እምነት እስከ ማረሚያ ቤት በጎ አድራጎት 17.10.2023

ደራሲ ስጦታው በፍቃዱ በአፍላ ዕድሜያቸው ወደ አውስትራሊያ የዘለቁት ነፃ የሃይማኖት ትምህርት ዕድል አግኝተው ነው። አዘላለቃቸው ግና ያለ ቪዛ ነበር።

ስጦታው በፍቃዱ፤ ከማይጨው እስከ አውስትራሊያ 17.10.2023

"ከማይጨው እስከ ሲድኒ" ግለ ታሪክነቱ የደራሲ ስጦታው በፍቃዱ ቢሆንም፤ የተነሳሽነት ግፊትና ዕሳቤዎቹ የፈለቁት ግና ከአንድ የእምነት ተጋሪ ወዳጃቸውና ከሴት ልጃቸው ሊዲያ ነው።

"የትም አገር ልኑር ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊነት ከደም የሚወጣ አይደለም" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" የማነ 28.09.2023

ድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ የማነ፤ የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ ከቀበሌ ተንስቶ የምሽት ክለብ መድረኮች ላይ አላከተመም። ከቶውንም በጦር ትምህርት ቤት ሁርሶ፣ በስደት ሞቃዲሾ፣ በዳግም ሠፈራ ኒውዝላንድና አውስትራሊያ የጥበብ ሙያው እስትንፋስ ሆኖ ዛሬም ድረስ አለ።

"ፍቅር ፍርንባዬ ድረስ ነበር የያዘኝ፤ ማሰብና መናገር እስኪያቅተኝ ድረስ" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" 25.09.2023

"የማትፈታህ ሚስት ሙዚቃ ነች" የሚለውና በቀዳሚ ክፍለ ግለ ሕይወት ትረካው ከውልደት እስከ ምሽት ክለብ ጅማሮው ያወጋው ድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ"፤ ትረካውን የምሽት ክለቡ ከቸረው የጥበብና የፍቅር ሕይወት እስከ ለጥቆ አገር ሲፈር እማኝ አስከ ሆነባትና ዝናን እስካተረፈባት የሶማሊያ ስደት አሻግሮ ያጋራል።

ለድቁና ታስቦ ለሙዚቃ መድረክ የበቃው ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" 24.09.2023

ድምፃዊ ኤልያስ የማነብርሃን ዳምጤ በቅፅል መጠሪያ ስሙ "ኪዊ" ተብሎ ይጠራል። ኒውዚላንድ በአንድ ወቅት ጥላ ከለላው ነበረችና የአገረ ኒውዚላንድ መለያ ቅፅል ስምን ይጋራል። ኤልያስ ለመድረክ የበቃው ድምፁን በሙሉቀን መለሰ ዘፈኖች አሟሽቶ፤ በጥላሁን ገሠሠ ቅላፄ ቃኝቶ ነው።

"ከሕክምና ወደ ምክር ቤት አባልነት ለመሸጋገር አስቤያለሁ" ሰላም ፈለቀ ተገኝ 25.08.2022

ሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ቀደም ባለው የግለ - ሕይወት ትረካዋ እንደምን ከዕድገት ቀዬዋ በቅሎ ቤት ተነስታ ከወላጆቿና ታናሽ ወንድሟ ጋር ለስደት እንደተዳረገችና ወደ አውስትራሊያ ከእነ ቤተሰቧ እንደዘለቀች አውግታለች። ቀጣይ ትረካዋ የአውስትራሊያ ምክር ቤት አባል የመሆን ትልሟ ዙሪያ ነው።

የእኔ ታሪክ፤ "አገርን ለመለወጥ፤ እኛ መለወጥ አለብን" - ሰላም ፈለቀ 22.08.2022

ሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ውልደቷ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ዕድገቷ በቅሎ ቤት ነው። ትውልድ አገሯን ኢትዮጵያን ለቅቃ ለስደት ሕይወት የበቃችው 10 የልደት ሻማዎችን እንኳ 'እፍ' ብላ ሳታጠፋ ነው።

ሰናይትና ኤልቪስ 21.07.2022

ኤልቪስ ፕሪስሊ በትወናው ማለፊያ ተዋናይ፤ በዘፈኖቹ "King of Rock and Roll" ተብሎ ተሞካሽቷል። የጥበብ ሥራዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት ሆነውታል። ለሙዚቃ አፍቃሪዎቹም ዋጋ የማይተመንባቸው የውብ ጊዜያት ውድ ትዝታዎች ሆነው አሉ። የጥበብ ባልደረቦቹም "Elvis" በሚል መጠሪያ የሙዚቃ ሥራዎቹንንና ግለ ሕይወቱን ነቅሰው በፊልም ሞገስ አላብሰውታል። ተዋናይት ሰናይት መብራህቱም በትወናው ዓለም የኤልቪስን ዘመን ከኤልቪስ ጋር በአጃቢ ድምፃዊነት የታሪክ ታዳሚ አድርጋናለች።

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ 18.07.2022

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ከውልደት ቀዬዋ ተንስታ፣ የካርቱም የስደት ሕይወቷን አጣቅሳ፣ የአውስትራሊያ የሠፈራና ምዕራባዊ የሥነ ጥበብ ሕይወት ጅማሮዋን አውግታለች። በቀጣይነትም እንደ ፅጌረዳ አበባ ውበትና እሾህን በተላበሰው የጥበብ ሕይወት ጉዞዋ ውስጥ የተፈተነችባቸውን ተግዳሮቶችና በሐሴት የተመላችባቸውን ስኬቶች ታነሳለች።

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከአገር ቤት እስከ አውስትራሊያ 17.07.2022

ሰናይት መብራህቱ፤ የሥነ ጥበብ ሕይወት ሕልሟ ከአገር ቤት ውዝዋዜና እንጉርጉሮ እስከ ኤልቪስ ፕሪስሊ የፊልም ትወና የዘለቀ ነው። ከውልደት እስከ ስደት ያለ የሕይወት ጉዞዋን አሰናስላ ታወጋለች።

የኔ ታሪክ፤ ጋዜጠኛ ማርታ ፀጋው - ከኮልፌ ወደ አውስትራሊያ 20.01.2020

ጋዜጠኛ ማርታ ፀጋው ምንዳ - ትውልድና ዕድገቷ ኮልፌ - አዲስ አበባ ነው።በጢያራ የአፍሪካን አየር ሰንጥቃ ከአገረ ኢትዮጵያ ወደ አውስትራሊያ ከዘለቀች ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ አስቆጥራለች።

የኔ ታሪክ፤ከያዮ እስከ አውስትራሊያ - ዶ/ር ሸሪፍ ሰዒድ 22.12.2019

ዶ/ር ሸሪፍ ሰዒድ፤ የአውስትራሊያን ምድር ረግጠው፤ ዓለም አቀፍ ደረጃን ከጠበቀ ዩኒቨርሲቲዋ የPhD ካባ ከመደረባቸው ዓመታት ርቆ መነሻቸው የቀድሞዋ ኢሉባቦር የአሁኗ ኢሉ አባቦር ናት። ዕትብታቸው የተቀበረው ያዮ ቀዬ ውስጥ ነው።

የኔ ታሪክ፤ "ባልሰልጠነ ዘመን የሰለጠነ ሃሳብ ሰጥተውን ያለፉ አባቶቻችን ዕዳ አለብን" ሰብለወርቅ ታደሰ 04.11.2019

የዛሬ “የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ” እንግዳችን ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ናቸው። የግለ-ታሪክ ትረካቸው መነሻ የትውልድ ሠፈራቸው የሆነችው ቤልኤይር ናት። የኢትዮጵያ መዲና ከሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ነው የምትገኘው።

አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሰው አገርም ብንሆን ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን እንመኝ።” - አሰፋ በቀለ - የእኔ ታሪክ፤ “ሰው አገርም ብንሆን ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን እንመኝ።” - አሰፋ በቀለ 25.10.2019

አቶ አሰፋ በቀለ ቤተሰባቸውን ጨምሮ ነዋሪነታቸው በሲድኒ - አውስትራሊያ ነው። አጭር ግለ-ታሪካቸውን ከትውልድ ቀዬአቸው ድሬ-ወሊሶ ጋር አጣቅሰው፤ የአገረ ግሪክ ቆይታና የአውስትራሊያ ሠፈራቸውን አያይዘው ያወጋሉ። - አቶ አሰፋ በቀለ ቤተሰባቸውን ጨምሮ ነዋሪነታቸው በሲድኒ - አውስትራሊያ ነው። አጭር ግለ-ታሪካቸውን ከትውልድ ቀዬአቸው ድሬ-ወሊሶ ጋር አጣቅሰው፤ የአገረ ግሪክ ቆይታና የአውስትራሊያ ሠፈራቸውን አያይዘው ያወጋሉ።

Listen to the የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.