Konso News

Konso News

News TI ↓ 341 episodes

It presents daily news digests about Konso people and its administration, politics, social issues, culture, and development efforts.

Author

Konso News

Category

News

Podcast website

podcasters.spotify.com

Latest episode

Sep 1, 2023

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

219 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 10.02.2022

የዕለተ ሐሙስ የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ መለጋና ዱጋያ ቀበሌ ላይ ጥቃት በፈጸሙ የሽብር ቡድን አባላት ላይ በጸጥታ ኃይሎች እርምጃ እየተወሰደ ነው 2. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሒደት ፖለቲካዊ ይዘት እየተላበሰ መምጣቱ ተገለጸ

218 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 08.02.2022

የዕለተ ማክሰኞ የካቲት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ከአንድ ሳምንት በላይ በኮልሜና ገዋዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ቀጥሎ ለነበረው ግጭት መፍትሔ የሚያበጅ ውይይት ትላንት በገዋዳ ከተማ ላይ መደረጉ ተገለጸ 2. የፍርድ ቤት ዳኛን ያሠሩ የካራት ከተማ አስተዳደር የጸጥታ አመራሮች ጉዳያቸው በኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳይታይ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ 3. ግሎባል ቴሌቭዥን ኔትወርክ ኦፍ አፍሪካ ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ አድርጎ በ15 ሀገራት ዘጋቢዎችን ይዞ ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ

217 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 07.02.2022

የዕለተ ሰኞ ጥር 30 ቀን2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በከና ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤትና በደል በደረሰባቸው መምህራን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ክስ ማምራቱ ተገለጸ 2. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕወሓት አመራሮች ክስ ለምን እንደተቋረጠ ለፓርላማ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ 3. በሰዓተ እስከ 160 ኪሎ ሜትር የምትጓዝ በራሪ ታክሲ በቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ቀርባለች ተባለ

216 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 04.02.2022

የዕለተ ዓርብ ጥር 27 ቀን2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የፍርድ ቤት ዳኛን ያሠሩ የካራት ከተማ አስተዳደር የጸጥታ አመራሮች ጉዳያቸው በኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳይታይ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸው ተገለጸ 2. የሰገን ዙሪያ ወረዳ ምክር ቤት የወረዳውን የጸጥታ ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ከአገር ሽማግሌዎች ጋር የቀበሌ ነዋሪዎችን ማወየት መጀመሩ ተገለጸ 3. የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በአንድ ቀን ብቻ 29 ቢሊየን ዶላር ማጣቱ ተገለፀ

215 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 03.02.2022

የዕለተ ሐሙስ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ከመንፈቅ በፊት የፍርድ ቤት ዳኛን ያሠሩ ባለሥልጣናትና የፖሊስ መኮንኖች በነገው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው የክስ መቃወሚያቸውን እንደሚያቀርቡ ተገለጸ 2. ኮንሶ ዞን በተሳተፈት የደቡብ ክልል ስፖርት ሻምፒዮና 31 መዳሊያዎችን ማግኘቱ ተገለጸ 3. የመንግሥት ተቋማት ለሕዝብ የሚያቀርቡት መረጃ ትክክለኛነት የሚረጋገጥበት አስገዳጅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ

214 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 01.02.2022

የዕለተ ማክሰኞ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ በካራት ከተማ በሚገኘው የሜትሮሎጂ ጣቢያ ላይ እየተፈጸመ ነው ተባለ 2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ የማክስ አውሮፕላኖችን ዳግም ማብረር ይጀምራል 3. ኬንያ አየር መንገድ ከአሁን በኋላ ዝንጀሮዎችን ወደ አሜሪካ አላጓጉዝም አለ

213 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 31.01.2022

የዕለተ ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በከና ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ 2. በራሪዋ መኪና የበረራ ደህንነት ማረጋገጫ ተሰጣት 3. በኬንያ በህዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ በቦምብ በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

212 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 28.01.2022

የዕለተ ዓርብ ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ በኮልሜና በገዋዳ መካከል ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች የግጭት አዝማሚያዎች እየታዩ መሆኑ ተገለጸ

211 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 27.01.2022

የዕለተ ሐሙስ ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ላለፉት 6 ወራት የነበረው የጤና አገልግሎት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ 2. ዞን አቀፍ የተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በነገው ዕለት በሰገን ዙሪያ ወረዳ ሊካሄድ ነው 3. ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከተጠቆሙ 632 ሰዎች መካከል 42ቱን መለየቱን ፓርላማው አስታወቀ 4. በእነ አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ ተከሰው የነበሩ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሠራተኞች ዋስትና ተፈቀደላቸው

210 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 25.01.2022

የዕለተ ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የሰገን ዙሪያ ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት በአካባቢው ዘላቂ መረጋጋት እንዲኖር የሚረዱ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው አለ 2. የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ግብዓት የሚሆን ጥናት መሰነዱን አስታወቀ 3. የግብፅ እና አልጀሪያ መሪዎች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰማ

209 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 24.01.2022

የዕለተ ሰኞ ጥር 16 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ምሁራን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ላለፉት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት በመገምገም ላይ መሆናቸው ተገለጸ 2. በወሩ መጀመሪያ ከኮልሜ አካባቢዎች በታጣቂዎች የተዘረፉ ከብቶች አለመመለሳቸው ተገለጸ 3. የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የቀረበውን የምርመራ ጥያቄ አሁን ሊመለከት እንደማይችል አስታወቀ

208 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ልዩ ዘገባ || Konso News | Konso News Media Special News 22.01.2022

የዕለተ ቅዳሜ ጥር 14 ቀን2014 ዓ.ም. ልዩ ዜና፡ የደቡብ ክልል መንግሥት አመታዊ የተቀናጀ የግብርና ተፋሰስ ልማት ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በኮንሶ መዲና እየተከናወነ ነው

207 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 20.01.2022

የዕለተ ሐሙስ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ከ3 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥምቀት በዓል በድምቀት መከበሩ ተገለጸ 2. አዲስ አበባ ውስጥ ግለሰቦች ከቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የተከራዩአቸው መጋዘኖች በቃጠሎ ወደመ 3. በላይቤሪያ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረ መገፋፋት የ29 ሰዎች ህይወት አለፈ

206 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 18.01.2022

የዕለተ ማክሰኞ ጥር 10 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን መዲና ካራት ከተማ በነገው ዕለት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል የዋዜማው ከተራ በድምቀት በመከናወን ላይ መሆኑ ተገለጸ 2. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የጥምቀት በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢትዮጵያ የምትፈልገው ፍቅር፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ አይደለም” አሉ 3. ቻይና ከ72 ዓመት በኋላ ዝቅተኛውን የወሊድ ምጣኔ አስመዘገበች

205 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 11.01.2022

የዕለተ ማክሰኞ ጥር 03 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮልሜና በገዋዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በታጣቂዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎችን  ተከትሎ ዛሬም ውጥረት መኖሩ ተገለጸ 2. በሁለቱ ህዝቦች መካከል በየጊዜው የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለማስቆም ከአሌ ልዩ ወረዳ አመራር ጋር ምክክር ማድረጉን የኮንሶ ዞን አስተዳደር አስታወቀ 3. ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ በታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ተጠየቀ 4. በአሜሪካ አንድ ግለሰብ የአሳማ ልብ ተገጠመለት

204 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 10.01.2022

የዕለተ ሰኞ ጥር 02 ቀን2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ኮልሜና በአሌ ልዩ ወረዳ ቀርቀርቴ አካባቢዎች በታጣቂዎች በሚደረጉ ትንኮሳዎች ሰላም መደፍረሱ እንደቀጠለ ነው ተባለ 2. ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ጋር ተወያዩ 3. ጃፓን ባቡርም አውቶቡስም መሆን የሚችል ሁለገብ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ መሥራቷን ይፋ አደረገች

203 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 06.01.2022

የዕለተ ሐሙስ ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በአገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ ጉዳዮች ላይ ሲመክር የነበረው ስብሰባ በዛሬው ዕለትም በዞን ሲቪል ሠራተኞች ደረጃ መከናወኑ ተገለጸ 2. ዓለም አቀፍ የሚል መጠሪያ ያላቸው ትምህርት ቤቶች ስያሜቸውን በአስቸኳይ እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ 3. ኢዜማ ከመንግሥት መዋቅር ጋር ትይዩ የሆነ የካቢኔ መዋቅር መሠረተ (በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዘና)

202 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 04.01.2022

የዕለተ ማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የካራት ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የተፈራረምነውን ውል አፈረሰ ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች አማረሩ 2. አዲስ የቅድመ ታሪክ ሥፍራ ኮንሶ ዞን ውስጥ በሚገኝ  ሸለቆ መገኘቱ ተገለጸ 3. ዝርፊያ መበራከቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ ሞተር ሳይክሎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ መጫን አይችሉም ተባለ

201 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 03.01.2022

የዕለተ ሰኞ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በአገራዊ፣ ክላላዊና ዞናዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር የምክክር ጉባኤ በካራት ከተማ እየተካሄደ ነው 2. በአግባቡ በተደረገ ጥናትና የህዝብ ይሁንታ ላይ ያልተመሠረተ አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ለግጭትና ለህዝብ መፈናቀል ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ አመለከተ 3. ከአሁን ቀደም የተሰጡ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ጥቆማዎች ተቀባይነት የላቸውም ተባለ

200 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 31.12.2021

የዕለተ ዓርብ ታህሣሥ 22 ቀን2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ከ 5ሺህ ለሚበልጡ የቀንድ ከብቶች ክትባት መሰጠቱ ተገለጸ 2. በመጪው እሑድ ስፖርታዊ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የካራት ዙሪያ ወረዳ አስታወቀ 3. በአፋር ክልል 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ መንግሥት አስታወቀ 4. በሱዳን በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ አራት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተሰማ

199 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 30.12.2021

የዕለተ ሀሙስ ታህሣሥ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የካራት ከተማ የውሃና የመብራት ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ 2. የኮንሶ ልማት ማህበር የጎበዝ ተማሪዎች የልዕቀት ማዕከል ለመገንባት ቦታ መረከቡን አስታወቀ 3. ከዚህ በፊት በግጭት ምክንያት ወድሞ የነበረው የፉጩጫ ጤና ኬላ ታድሶ በነገው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ

198 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 28.12.2021

የዕለተ ማክሰኞ ታህሣሥ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሥርቶ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ላለፉት 4 አመታት በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳና በዲራሼ ልዩ ወረዳ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የቆየውን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚገመግም መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው 2. የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ማካሄዱ ተገለጸ 3. ኢዜማ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ምልመላና ጥቆማ ሥልጣን ለፕሬዚዳንት እንዲሰጥ ጠየቀ

197 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 27.12.2021

የዕለተ ሰኞ ታህሣሥ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ኮልሜና በአሌ ልዩ ወረዳ ገዋዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በዘላቂነት ለመፍታት አቅጣጫ የተቀመጠበት ልዩ ስብሰባ መካሄዱ ተገለጸ 2. በአገራችን የሰሜኑ ክፍል በተከሰተው ጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የ5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ 3. በጸረ-አፓርታይድ ትግል የሚታወቁት የደቡብ አፍሪካው ዴዝሞንድ ቱቱ በ90 አመታቸው አረፉ

196 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 13.12.2021

የዕለተ ሰኞ ታህሣሥ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የህወሃት የሽብር ቡድን በሴቶችና ህጻናት ላይ ያደረሰውን ግፍ የሚያወግዝ ሰልፍ በኮንሶ ዞን ከተማ ካራት ተካሄደ 2. ኢሰመኮ በአማራና በአፋር ክልሎች የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር ከተመድ ጋር እየመከረ መሆኑን አስታወቀ 3. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያለአግባብ የተጠቀሙ 4 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተከሰሱ

195 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 10.12.2021

የዕለተ ዓርብ ታህሣሥ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮልሜና በገዋዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም የደቡብ ክልል የኮማንድ ፖስትና የጸጥታ አመራር በተገኙበት ውይይት መደረጉ ተገለጸ 2. የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ወሰነ 3. የሩሲያን ድንበር ሊያቋርጡ የነበሩ የኔቶ ጦር አውፕላኖች በሩሲያ ተጠልፈው መመለሳቸው ተገለጸ

Listen to the Konso News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.