Konso News

Konso News

News TI ↓ 341 episodes

It presents daily news digests about Konso people and its administration, politics, social issues, culture, and development efforts.

Author

Konso News

Category

News

Podcast website

podcasters.spotify.com

Latest episode

Sep 1, 2023

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

294 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 17.08.2022

የዕለተ ዕሮብ ነሐሴ 11  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ጉባኤው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን አወገዘ 2. አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ 3. የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ራይላ ኦዲንጋ በምርጫ ውጤት ላይያላቸውን ቅሬታ ወደ ፍርድ ቤት “እወስዳለሁ” አሉ

293 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 15.08.2022

የዕለተ ሐሙስ ሰኞ ነሐሴ 9  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የወላይታ ዞን አስተዳደር በኮንሶ ዞን በድርቅ ምክንያት ለረሃብ ለተጋለጡ ወገኖች የ100 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ አደረገ 2. የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ከሌሎች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ጋር በክልል እንዲዋቀር የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ውድቅ ያደረገበትን ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቀረበ 3. በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ ራይላ ኦዲንጋን አሸነፉ 4. በሱዳን በተከሰተ ጎርፍ በትንሹ 52 ሰዎች ህይወታቸውን አጡ

292 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 11.08.2022

የዕለተ ሐሙስ ሐሙስ ነሐሴ 5  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ከታሪክ በላይ በሚያስከፍሉ አገልግሎት ሰጪዎች መማረራቸው ተገለጸ 2. የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ'ክላስተር' ክልል አደረጃጀትን ውድቅ አደረገ 3. የህዳሴ ግድበ 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ 4. ኬንያውያን የፕሬዝዳንት ምርጫውን ውጤት እየተጠባበቁ ነው

291 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 08.08.2022

የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 2  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የጋሞ ልማት ማህበር በኮንሶ ዞን በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 597 ኩንታል ድንችና የተለያዩ የምግብ እህሎች ድጋፍ አደረገ 2. በደራሼ ልዩ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ 11 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ 3. የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከደመወዝ ጭማሪና ከዕርከን ዕድገት ጋር በተያያዘ መንግሥትን አስጠነቀቁ 4. ተጠባቂው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል

290 || ከእኛው ለእኛው የውይይት መርሃ ግብር || የኮንሶ ዞን ወቅታዊ ሁኔታና የዞን አስተዳደሩ አካሄድ 07.08.2022

ይህ ከእኛው ለእኛው የተሰኘው የውይይት ፕሮግራም ነው።  የዛሬው የውይይት መርሃ ግብር በኮንሶ ዞን የተከሰተውን የድርቅና ረሃብ ሁኔታ፣ ለድርቅና ረሃቡ የተሰጠው ምላሽ እና የኮንሶ ዞን አስተዳደር ያልተገባ አካሄድ የተመለከተ ነው።  አቅራቢ፡ - ያቬሎ ናታዬ  የውይይት ተሳታፊዎች፡ - አስቻለው ኮራ፣ ደጉ ገንፌ (ቄስ)፣ ካፍትሌ ቶራይቶ፣ መምህር ኩሌ ኩርሻ፣ ባሥሬ ባልቻ፣ ወ/ዊ ምትኩ ሐልጌቴ፣ አማሮ አርሳባ፣ ታምራት ጨንፋ፣ ጋይቦ ጋጋብሼ

289 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 04.08.2022

የዕለተ ሐሙስ ሐምሌ 28  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲሱን የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ 2. የኮንሶ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ወጣቶችን ለማነቃቃት ሲያከናውን የነበረውን መርሃ ግብር ማጠቃለሉ ተገለጸ 3. በጉጂ ዞን በተከሰተው ድርቅ ሰዎች በረሃብ ሕይወታቸው እያለፈ ነው ተባለ 4. ኢትዮጵያ የ“አንድትቻይና” ፖሊሲን እደግፋለሁ አለች

288 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 03.08.2022

የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 27  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ የተከሰተው ድርቅ ያስከተለውን የረሃብ አደጋ ለመቀልበስ በሚደረገው ጥረት የኮንሶ ልማት ማህበር 2ኛ ዙር የዕርዳታ ማሰባሰብ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ 2. የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በህዳሴው ግድብና በኢትዮጵያ ወቅቃዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ተወያዩ 3. ህወሓት፤ በትግራይ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ለሚሰማሩ አካላት የደህንነት ዋስትና እሰጣለሁ አለ 4. የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ “ቻይናን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ” ሲሉ አስጠነቀቁ

287 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 01.08.2022

የዕለተ ሰኞ ሐምሌ 25  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ልማት ማህበር በኮንሶ ዞን ለተከሰተው ድርቅና ረሃብ ማስታገሻ የሚሆን የመጀመሪያ ዙር 224 ኩንታል የምግብ እህል ለግብርና መምሪያ ማስረከቡን አስታወቀ 2. ኮንሶ ዞንን ጨምሮ በደቡብ ክልል የሚገኙ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች በሁለት የተለያዩ ክልሎች ለመደራጀት በምክር ቤቶቻቸው ውሳኔዎችን አሳለፉ 3. በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ29 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተገለጸ 4. አሜሪካን ጨምሮ አምስት ሀገራት የባህር ላይ ጦርነት ልምምድ ጀመሩ

286 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 28.07.2022

የዕለተ ሐሙስ ሐምሌ 21  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞንና አጎራባች ወረዳዎች የተከሰተውን የረሃብ አደጋ ለመቀልበስ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል የቀረበ የእህል ዕርዳታ ባይኖርም በአካባቢ ተወላጆች በኩል የሚደረገው ጥረት አሁንም እንደ ቀጠለ ነው 2. አትሌት ደራርቱ ቱሉ “የትግራይ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ” መንግስት መንገድ እንዲከፍት ጠየቀች 3. መንግስት ከህወሃት ጋር በየትኛውም ጊዜና ቦታ ለመወያየት መዘጋጀቱን ገለጸ 4. የፌዴራል መንግሥት በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ በይፋ እንዲያሳውቅ ኢሰመኮ ጠየቀ

285 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 27.07.2022

የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 20  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች የመምሪያዎችን የ2014 ሪፖርትና የ2015 ዓ.ም ዕቅዶች መመልከት መጀመራቸው ተገለጸ 2. ድንበር ጥሰው የገቡ ከ209 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ 3. በአለመግባባት ውስጥ ያሉት የአሜሪካ እና የቻይና መሪዎች ንግግር ሊጀምሩ ነው

284 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 25.07.2022

የዕለተ ሰኞ ሐምሌ 18  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን እና በቦረና ዞን አመራር መካከል የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ 2. ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪኳ ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገቧ ተገለፀ 3. ነዳያንና አበል የተከፈላቸውን ሠራተኞች በማስፈረም ጠቅላላ ጉባዔ አድርጓል የተባለው ኢነፓ ታገደ 4. የግብጽ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አፈጻጸም ለህዝብ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍለት ጠየቀ

283 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 22.07.2022

የዕለተ ዓርብ ሐምሌ 15  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ “በኮንሶ ዞን ድርቅ እንጂ ረሃብ አልተከሰተም” ማለታቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው 2. የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2015 ዓ.ም 46.3 ቢሊየን ብር በጀት በአጸደቀ 3. ድሮፓዲ ሙርሙ 15ኛዋ የሕንድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

282 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 20.07.2022

የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 13  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው የድጋፍ ርብርብ እንደቀጠለ ነው 2. አምባሳደር ስለሺ በቀለ፤ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በድርድርና በአጎአ ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ 3. ደቡብ አውሮፓን እያነደደ ያለው ሰደድ እሳትና ሙቀት በፍጥነት አተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ

281 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 18.07.2022

የዕለተ ሰኞ ሐምሌ 11  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የደቡብ ክልል ሴቶችና ህጻናት ቢሮ በኮንሶ ዞን በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የ1.5 ሚሊዮን ግምት ያለው ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ 2. የትራፊክ ቅጣት ሕጎች ክለሳ እየተደረገ ነው ተባለ 3. በሶማሊያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተገለበጠ 4. በሱዳን ብሉናይል ግዛት በተፈጠረ ግጭት ከ65 በላይ ሰዎች ተገደሉ

280 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 14.07.2022

የዕለተ ሐሙስ ሐምሌ 7  ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን መንግሥት በዞኑ ከሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር ምክክር ማድረጉን አስታወቀ 2. ከህወሓት ጋር የሚደረገው ድርድር በአፍሪካ ህብረት ስር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለጸ 3. በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የፈረንሳይ ስለላ ተቋም ኃላፊ ስልጣናቸውን ለቀቁ

279 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 13.07.2022

የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን መንግሥት መንግሥት ዕውቅና ባልሰጣቸው አካውንቶች ለህዝብ የሚሰበሰብ ድጋፍ እንደማይቀበል አስታወቀ 2. የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ 3. ስሪላንካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

278 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 11.07.2022

የዕለተ ሰኞ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የተከሰተው ድርቅ ያስከተለውን የምግብ እህል እጥረት ለመቅረብ በምሁራንና በልማት ማህበር በኩል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው 2. የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር የቡርጂ ልዩ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰዱ ተገለጸ 3. የዓለም ህዝብ ቁጥር ከአራት ወራት በኋላ 8 ቢሊዮን ይደርሳል ተባለ 4. ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሁሉም የዩክሬን ዜጎች የሩሲያ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው አወጁ

277 || ከእኛው ለእኛው የውይይት መርሃ ግብር || በኮንሶ ዞን የተከሰተው ድርቅ፣ የኑሮ ውድነትና የኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች የምርመራ ስብሰባ 10.07.2022

ይህ ከእኛው ለእኛው የተሰኘው የውይይት ፕሮግራም ነው።  በዛሬው የዉይይት መርሃ ግብር፣ የበኮንሶ ዞን የተከሰተው ድርቅ፣ ጣራ የነካው የኑሮ ውድነት ኅብረሰተሰቡ ላይ እየፈጠረው ያለው ጫናና ኢሰመኮ በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ያካሄደው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚመረምረውን ህዝባዊ ስብሰባ ዙርያ መወያያት ይሆናል።

276 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 06.07.2022

የዕለተ ረቡዕ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን መሥሪያ ቤት፣ ሀሰተኛ መረጃን የሚያሠራጩ ኃይላትን ለህግ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ 2. በቄለም ወለጋ ንፁኃን ዜጎች ተጨፈጨፉ 3. የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ ይፋ ተደረገ 4. የኔቶ አባላት ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን እንዲቀላቀሉ የሚያስችለውን ፕሮቶኮል ፈረሙ

275 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 01.07.2022

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ከ190 ሺህ በላይ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ 2. በዲራሼ ልዩ ወረዳ ሀይበና ቀበሌ ውስጥ በመሸጉ ታጣቂዎች ላይ በጸጥታ አካላት በተወሰደ እርምጃ ቢያንስ 5ቱ መገደላቸው ተገለጸ 3. ቻይና የፌደራል መንግስትና ህወሃትን ማደራደር እንደምትፈልግ ገለጸች

274 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 29.06.2022

የዕለተ ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ አርዕስተ ዜናውን በማስቀደም የዕለተ ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎችን አሰማለሁ። 1. በኮንሶ ዞን ለሰው ሀብት ልማትና ሥራ አመራር ኃላፊዎች ሥልጠና መሰጠቱ ተገለጸ 2. የደቡብ ብሔር ብሔርሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ከመጪው ሰኔ 30 በኋላ ሊታወቅ እንደሚችል ተገለጸ 3. የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ 4. ብልፅግና ፓርቲ ሸኔን ከማጥፋት ውጪ አማራጭ እንደሌለ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታወቀ

273 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 27.06.2022

የዕለተ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. 38 ሺህ ወጣቶችን ለክረምት የበጎ አድራጎት ሥራ ሊያሠርማራ መሆኑን የኮንሶ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ 2. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምዕራብ ወለጋና በጋምቤላ ግድያ ላይ ማጣራት እንዲካሄድ አዘዘ 3. በ”ጎበዝ አለቃ” የተማረረችው ናይጄሪያ ለዜጎቿ የጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ ነው 4. ጃፓን 37 ሚሊየን ዜጎቿ መብራት እንዲያጠፉ አሳሰበች

272 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 22.06.2022

የዕለተ ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የካራት ከተማ ማዘጋ ቤት ለ6ኛ ዙር በጨረታ ለሽያጭ ያቀረበው “የከተማ መሬት ሊዝ ጨርታ ሰነድ” ውጤት እስከ አሁን ድረስ አለመገለጽ እንዳሳሰባቸው የጨረታው ተሳታፊዎች ገለጹ 2. በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በጽንፈኞች በተደጋጋሚ በተፈጸሙና አውዳሚ ጥቃቶች ዋና ተጠርጣሪዎች አንዱ የነበረው  አቶ ለሚታ ደይጋኔ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ 3. ጠ/ሚ ዐቢይ በንጹሃን ግድያ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የአብን የምክር ቤት አባላት ጠየቁ 4. በአፍጋኒስታን በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ ደረሰ

271 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 20.06.2022

የዕለተ ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የደም ባንክ ለማቋቋም ጥሪ ቀረበ 2. በኮንሶ ዞን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 2 ትምህርት ቤቶች ተመረቁ 3. ጠ/ሚ ዐቢይ “የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት አንታገስም” አሉ 4. በፈረንሳይ በተደረገ የህግ አውጪዎች ምርጫ፣ የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ 245 የፓርላማ መቀመጫዎችን አጣ

270 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 17.06.2022

የዕለተ ዓርብ ሰኔ 10 ቀን2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. አባቱን የ24 ሺህ ብር ደሞዝተኛ ያደረገው የፋይናንስ ሠራተኛ በ9 ዓመት እሥራት እንዲቀጣ ተወሰነበት 2. በኮሎኔል ፈጠኔ ሲሳይ የሚመራው የዲራሼ ልዩ ወረዳ ወታደራዊ መንግስት በደቡብ ክልል ልዩ ሀይልና በፌደራል ፖሊስ ተተካ 3. የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዳቸውን ኢሰመኮ ገለጸ 4. የአፍሪካ ህብረት፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰዱትን እርምጃ አደነቀ

Listen to the Konso News podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.