Konso News
Konso News
It presents daily news digests about Konso people and its administration, politics, social issues, culture, and development efforts.
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
319 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 12.12.2022 12:40
የዕለተ ሰኞ ታህሣሥ 03 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ መካከል የዕርቀ ሰላም ኮንፍረንስ ተካሄደ 2. የብልፅግና ፓርቲተወካይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ ጠራ 3. አሜሪካ የቀዝቃዛው የዓለም ጦርነትን ስህተት በአፍሪካ እንደማትደግም አስታወቀች
318 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 08.12.2022 11:57
የዕለተ ሐሙስ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው 2. በኦሮሚያ ክልል ግጭቶችና ጥቃቶች የሚከሰቱባቸው ቦታዎች መጨመራቸውን ኢሰመኮ ገለጸ 3. ወንድ ልጅን መጸነስ የሚያስችለው የዋይ ክሮሞዞም በመጥፋት ላይ መሆኑን ሳይንቲስቶች ተናገሩ
317 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 05.12.2022 13:31
የዕለተ ስኞ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ የተሰኘ ድርጅት በካራት ከተማ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ 2. በኮንሶና በዲራሼ ህዝቦች መካከል የተከሰተውን አለመግባባት ለመፍታት የሰላም ኮንፍረስን ተካሄደ 3. በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው 4. ኢንዶኔዥያ ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነትን በወንጀልነት የሚቀጣ ህግ ልታጸድቅ ነው
316 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 01.12.2022 14:33
የዕለተ ሐሙስ ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ሥራ ላላገኙ ወጣቶች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ 2. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጻሕፍትን ለማሳተም 29 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ 3. መንግስት "የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዕቅድ በተመለከተ ምክክር እየተደረገ ነው” አለ 4. ናይጀሪያ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትእንዳይሰጡ አገደች
315 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 24.11.2022 13:03
የዕለተ ሐሙስ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በአምቡላንስ ከባድ የጦር መሣሪያ ሲያዘዋዉሩ የተያዙ ግለሰቦች በእሥራት ተቀጡ 2. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት፤ በመጪው ቅዳሜ ሊያከብር ነው 3. በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት የተካተተበት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
314 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 23.11.2022 11:05
የዕለተ ረቡዕ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ለአሽከርካሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና መሰጠቱ ተገለጸ 2. በታጠቁ ኃይሎች በኩሱሜ ብሔረሰብ ላይ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰ ነው 3. በስምምነቱ አተገባበር ጉዳይ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ 4. ቱርክ በከባድ ርዕደ መሬት ተናጠች
313 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 21.11.2022 8:16
የዕለተ ሰኞ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ልማት ማህበር ከጂ አይ ዚ ባገኘው ድጋፍ በአማሮ ልዩ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መሥራቱን አስታወቀ 2. በኮንሶ ዞን የመብራት ችግር በባንኮች ላይ የንብረት ውድመትና ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ ተገለጸ 3. የግብጽ እና ቱርክ መሪዎች ከአስርት አመታት ውጥረት በኋላ በዓለም ዋንጫ ተጨባበጡ
312 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 17.11.2022 13:22
የዕለተ ሐሙስ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ 2. ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሌብነትከኢትዮጵያ የጸጥታ ሥጋቶች እኩል እንቅፋት መሆኑን ገለጹ 3. ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ ጀመረች 4. የዓለም ህዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን መድረሱ ተገለጸ
311 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 16.11.2022 17:03
የዕለተ ረቡዕ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ልማት ማህበር ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ግንባታ ለማከናወን እያቀደ መሆኑን አስታወቀ 2. በኮንሶ ዞን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው 3. ሀገር መከላከያ በትግራይ ክልል ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ 4. በአንድ ወቅት ከኦባማ ጋር የደነሱት አዛውንት ሴት በ113 አመታቸው አረፉ 5. የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱ ተገለጸ
310 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 14.11.2022 10:10
የዕለተ ሰኞ ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን ቀደም ሲል ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮችና ድርቅ ምክንያት ከተጎዱ ወገኖች 84 በመቶ ያህሉ እርዳታ ማግኘታቸውን የዞኑ መንግሥት አስታወቀ 2. በመጭበርበሩ ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ነገ ይወጣል ተባለ 3. የሃይማኖት ተቋማት የሚመሩበት የፖሊሲና አዋጅ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ
309 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ልዩ (ሰበር) አንኳር ዜና || Konso News | Konso News Special (Breaking) News 02.11.2022 6:35
የዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ላለፉት 10 ቀናት ሲደረግ የነበረው ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ
308 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 19.09.2022 11:48
የዕለተ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በሐዋሳ የሚኖሩ የኮንሶ ተወላጆች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 18 ኩንታል የበቆሎ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ 2. በኮንሶ ዞን የመጀመሪያው የአካል ጉዳተኞች ማበልጸጊያ ማህበር መቋቋሙ ተገለጸ 3. አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ከዛሬ ጀምሮ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ 4. የብሪታኒያ ንግስት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ የቀብር በዛሬው ዕለት በልዩ ክብር ተከናወነ
307 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 15.09.2022 9:53
የዕለተ ሐሙስ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ 2. “አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው 3. የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተገለፀ 4. የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው ተባለ
306 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 14.09.2022 11:08
የዕለተ ረቡዕ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. “ኮንሶን እናስተዋውቅ” በሚል መሪ ሐሳብ በዘመን መለወጫ ቀን የተዘጋጀው የቁንጅናና ባህልን የማስተዋወቅ ውድድር በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ 2. በብልፅግና ጉባዔ፣ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ መሰየሙ ትክክል እንዳልነበር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ 3. ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈፀሙ
305 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 12.09.2022 16:40
የዕለተ ሰኞ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. ሄስ ትራቭል ኢትዮጵያ በኮንሶ ዞን በ180 ሚሊዮን ብር የእንቨስትመንት ተቋማት እየገነባ ነው ተባለ 2. ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ 3. የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ 4. ኤምባሲዎች በግቢያቸው ስብሰባ ከማድረጋቸው በፊት ለመንግሥት እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላለፈ
304 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 08.09.2022 15:20
የዕለተ ሐሙስ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ መከረ 2. ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ከለከለ 3. ሩሲያ፤ በቁጥጥሯ ስር ባሉ የዩክሬን ግዛቶች በመጪው ህዳር ወር “ህዝበ ውሳኔ” ልታካሂድ ነው 4. አፕል ኩባንያ በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳታላይት አማካይነት መልዕት የሚልክ አይፎን 14 የተሰኘን ይፋ አደረገ
303 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 07.09.2022 11:28
የዕለተ ረቡዕ ጳጉሜ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን የሰው ሀብት ልማት ምጣኔ ለመጨመር የሚረዳ የመረጃ ቋት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው 2. ‹‹ኢትዮጵያን የመበተን ዕቅድ በዚህኛው የጦርነት ምዕራፍ ይቋጫል›› ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ 3. ቻይና በትንፋሽ የሚወሰድ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ይፋ አደረገች
302 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 05.09.2022 17:33
የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. በካራት ከተማ ሲካሄድ የነበረው የኮንሶ የምሁራን የምክክር ጉባኤ ተጠናቀቀ 2. መንግሥት ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ 3. የኬንያ ፍ/ቤት የዊሊያም ሩቶ አሸናፊነትን አፀና 4. ሊዝ ትረስ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ
301 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 01.09.2022 12:43
የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. ሲጠበቅ የነበረው የኮንሶ ምሁራን አመታዊ የምክክር ጉባኤ ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገለጸ 2. በኮንሶ በኩል ወደ አርባምንጭ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 11 ኩንታል የቡና ምርት በቁጥጥር ሥር ዋለ 3. በኢትዮጵያ አየር ክልል ከተመታው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የየትኛውንም ሀገር ስም አልተጠቀሰም ሲል በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ 4. ከ20 ሺህ በላይ በሆኑ ንቦች የተነደፈው አሜሪካዊ ከሳምንት በኋላ ነፍስ ዘራ 5. ፖላንድ ጀርመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላደረሰችባት ጉዳት ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች
300 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 29.08.2022 12:49
የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡ 1. የመብራት ኅያል ካራት ቅርጫፍ ጽ/ቤትና የካራት ማዘጋጃ ቤት ውዝግብ በውይይት መፈታቱ ተገለጸ 2. በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር ለምስክር ትፈለጋላችሁ የተባሉ አርብቶ አደሮች በእሥርና እንግልት መዳረጋቸው ተገለጸ 3. ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ 4. ሰሜን ኮሮያ ጠላትን ለማሳሳት በሚል ስምንት ተመሳሳይ ቤተ መንግስቶችን ገነባች
299 || ከእኛው ለእኛው የውይይት መርሃ ግብር || መጪው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ 27.08.2022 2:30:30
በዛሬው ውይይት፡ 1) 2013 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የተደረገው የመጀመሪያው የኮንሶ ምሁራን የምክክር ጉባኤ ምን ምን አዎንታዊ ውጤቶችን አስገኘ? 2) በአምናው የምክክር መድረክ የተቀመጡ ተግባራት ምን ምን ናቸው? የትኞቹስ ተሳኩ? የትኞቹስ አልተሳኩም? 3) ከነሐሴ 26 እስከ 28፣ 2014 ዓ.ም ሊካሄድ ባለው 2ኛው የኮንሶ ምሁራን ምክክር ላይ ምን ምን ሐሳቦችን እንጠብቅ?? የሚሉና ሌሎችም ሐሳቦች በውይይቱ ተንሸራሽረዋል።
298 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 25.08.2022 16:52
የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. በኮንሶ ዞን 62 በኩፍኝ የተጠቁ ሰዎች መመዝገባቸውንና በሽታው ወረርሽን መሆኑን የዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ 2. የኮንሶ ዞን ምሁራን የምክክር መድረክ ከነሐሴ 26-28 እንደሚሆን ተገለጸ 3. የካራት ከተማ አስተዳደር ለዘመን መለወጫ በዓል ለከተማው ነዋሪዎች የሚሆን የአስቤዛ ባዛር ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ 4. ኢትዮጵያ ከአጎአ እድል በመታገዷ ምክንያት ከሀገር የተሰደደ ኩባንያ አለመኖሩ ተገለጸ 5. ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት 20 በመቶ ግዛቷን ማጣቷ ተገለጸ
297 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 24.08.2022 10:31
የዕለተ ዕሮብ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን መንግሥት የሚከተለው አካሄድ በመጪው የምሁራን ስብሰባ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖረው የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ተገለጸ 2. የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ኃይል የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላንን መቶ መጣሉን አስታወቀ 3. የተመድ ዋና ፀሃፊአንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም በአስቸኳይ ወደነበረበት እንዲመለስ አሳሰቡ
296 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 22.08.2022 12:00
የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት በ5ኛ መደበኛ ስብሰባው ወቅታዊው የድርቅ ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጉ ተገለጸ 2. መንግሥት ከሕወሓት ጋር የፖለቲካ ውይይት በማድረግ ቀሪ ጉዳዮችን በብሔራዊ ምክክሩ እንዲፈቱ እፈልጋለሁ አለ 3. ሶማሊያ የሽብር ጥቃትን ቀድመው ያልተከላከሉ የሥራ ኃላፊዎችን እንደምትጠይቅ ገለጸች
295 ኮንሶ ዜና | የየኮንሶ ዜና ሚዲያ ዕለታዊ አንኳር ዜናዎች || Konso News | Konso News Media Daily News Digest 18.08.2022 12:15
የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. አንኳር ዜናዎች፡ 1. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት በዛሬው ውሎው የተለያዩ ልማት ነክና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ መምከሩ ተገለጸ 2. የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ለ2015 ዓ.ም 700 ሚልዮን ብር ገደማ በጀት በማጽደቅ ማምሻውን ስብሰባውን አጠናቀቀ 3. በኢትዮጵያ 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ም/ቤት ወሰነ
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.