ECFC in Finland
Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland
This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.
Author
ECFC in Finland
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 5, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
245 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 7 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 13.11.2022 39:27
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት ክፍል 7፡ የጌታ መንገድ ለመከተል የሚረዱ እርምጃዎች - ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ራስን ማስገዛት በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡- የጌታን መንገድ በመከተል ሂደት የመንፈስ ቅዱስ ሚናዎች፡ - መንፈስ ቅዱስ የጌታን ፈቃድ ያስተምራል፣ ያሳስባል! መንፈስ ቅዱስ እውነትን ከውሸት እንድንለይ ይረዳናል። መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳዊ ሥራ ኃይልን ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ ምሪትን ይሰጣል። መንፈስ ቅዱስ በጸሎት ጊዜ አጋዥ ነው። በዚህ ክፍል የተዳሰሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 8፡12-17/ ዮሐ. 3፡5-6/ ኤፌ. 1፡13/ ዮሐ. 14፡1...
244 || እግዚአብሔር ለምን ጠራን? || በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) 06.11.2022 1:04:58
"እግዚአብሔር ለምን ጠራን?" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ራዕ. 5፡9-14/ 1 ጢሞ. 1፡5/ ዘጸ. 4፡10-17/ ሉቃ. 1፡55
243 || ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 30.10.2022 1:02:53
"ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል" በሚል ርዕስ የጌታን ራት አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ - ዘጸ. 1 2፥1-51/ ሉቃ. 22፡7-20/ 1 ቆሮ. 5፡6-8/ ሮሜ 3፡23-26/ ሮሜ 5፡8-9/ ዕብ. 9፡14/ 1 ዮሐ. 1፡7/ ሉቃ. 22፡19/ ዕብ. 1፡1-3/ ዮሐ. 3፡16
242 || ተስፋ አንቆርጥም! || በፍርዱ መሰረት(ቄስ) 23.10.2022 36:13
242_ተስፋ አንቆርጥም በፍርዱ መሰረት(ቄስ) (በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ )2ቆሮ1:8 (… ተስፋ እንዳንቆርጥ ፣ቁጥር:13 … አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ ቁጥር 18 የሚታየው የጊዜው ነውና የማይታየው ግን የዘላለም ነው። )2ቆሮ4፡1-18 (እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ) ፊሊ 3...
241 || ታናሽ መንጋ || በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 16.10.2022 47:31
241_ ታናሽ መንጋ በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።ሉቃስ 12:31-32 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። ኤፌ 2:19 ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል ተዘልሎም ይቀመጣል፥ ማንም አያስፈራውምም።ኤር 46:27
240 || እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማነው? || በዘገዬ መኮንን (ወንጌላዊ) 09.10.2022 36:34
240_እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማነው? በዘገዬ መኮንን (ወንጌላዊ) ዋና መነሻ ሃሳብ የመጽሃፍ ቅዱስ ምእራፍ ዘፍ 20:1-18 በሙሉ እግዚአብሔርን መፍራት የምንማረው:የምናሳድገው እና የምንለማመደው ነው:: እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል። መዝ 25:12 በጥሞና ሊሰሙት የሚገባ::
239 || በአንደበታችን ሃይል ይህንን ዘመን እንለፍ! || በወንድም በእምነት ካሳ 02.10.2022 50:14
239_በአንደበታችን ሃይል ይህንን ዘመን እንለፍ በእምነት ካሳ(ወንድም) ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፤... ምሳሌ 13:2 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው፣መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው። ሮሜ 10፡ 17 የእ/ርን ቃ እናውጅ ንግግር ወደ ሃሳብ ፤ሃሳብም ወደ ተግባር ያድጋልና፤.. ዮሐ 1:12 ዮሐ 3:16 ዮሐ 3:18 ሉቃ 10:19 ሮሜ 3:24 ሮሜ 8:1 &nb...
238 || እግዚአብሄር ያላለውን የሚል የሚፈጽምስ ማነው? || እህት ለምለም ጌታቸው (ሲ/ር) 25.09.2022 48:07
እግዚአብሄር ያላለውን የሚል :የሚፈጽምስ ማነው (ሲ/ር ለምለም ጌታቸው) ሰቆ 3:25-37 ... ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው? ዘፍ 38 :1-11...ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፦ ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና። ትዕማርም ሄዳ በአባትዋ ቤት ተቀመጠች። 1ሳሙ 16:1-13 ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው መዝ 27:10 አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
237 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 6 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 18.09.2022 1:05:51
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት ክፍል 6፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ በመበተን መሰብሰብ በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡- 1) ልግስናና ዘላለማዊ ፋይዳው 2) ልግስናና እውነተኛ ኃይማኖት 3) 7 የልግስና መሠረታዊ ምክንያቶች በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ መዝ. 112፡9/ ማቴ. 25፡34-36/ ያዕ. 2፡27/ 2 ቆሮ. 9፡6-12/ ማቴ. 19፡21/ 2 ቆሮ. 8፡1-5/
236 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 5 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 11.09.2022 58:21
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት ክፍል 5፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ በክፉ ፈንታ መልካምን መመለስ በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡- 1) ክፉን በመልካም ስለመመለስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? 2) በክፉ ፈንታ መልካምን ስለመመለስ የጌታ ምሳሌነት 3) ክፉን በክፉ መመለስ የማይገባን ስለምንድን ነው? በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ሮሜ 12፡17-21 (ምሳሌ 25፡21-22)/ 1 ተሰ. 5፡15/ ሉቃ. 22፡63-65/ ሉቃ. 23፡34/ ማቴ. 5፡44 (ኢሳ. 53፡12)/ ማቴ. 5፡44-45ሀ/ 1 ጴጥ. 3፡9/ ኤፌ. 4፡31-32
235 || የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መልዕክት በኮንቱላ ኅብረት በነበረው የአንድነትና የይቅርታ ጊዜ 04.09.2022 19:26
በዚህ ጊዜ፡ ወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያንን ወክሎ አጠቃላይ መልዕክት አስተላልፎ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ በዕለቱ የነበሩት ሽማግሌዎች ወንድም ያቬሎ ናታዬና ወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) በተሰጣቸው ጊዜ በራሳቸው አጭር መልዕክት አስተላልፈው ይቅርታ ጠይቀዋል።
234 || የጌታ ራት || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 28.08.2022 1:03:16
"የጌታ ራት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። ጌታ በሰጠን የመታሰቢያ ሥርዓት ውስጥ እንድናስተውል የሚፈለጉ 3 ነጥቦች። 1) መታሰቢያ መሆኑን እንድናስብ፡ ሉቃ. 22፡ 17-19፣ 1 ቆሮ. 11፡24-25፣ 2) አዲስ ኪዳን መሆኑን እንድናስብ፡ ማቴ. 26፡28፣ ማር. 14፡24፣ ሉቃ. 22፡20፣ ሮሜ 3፡25፣ 1 ጴጥ. 1፡18-19፣ ራዕ. 12፡11 3) ስለመዋደድ፣ ስለአንድነትና ስለፍቅር እንድናስብ፡ ዮሐ. 13፡ 1-38 የጌታ ራት መውሰድ የማይገባው ማን ነው? 1 ቆሮ. 11፡27
233 || የእግዚአብሔር በግ ማን ነው? || በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 21.08.2022 1:01:18
"የእግዚአብሔር በግ ማን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 4፡7-26፣ ማቴ. 16፡24-26፣ ሮሜ 12፡19-20፣ ሉቃ. 9፡57፣ ማቴ. 5፡11-12፣ 43-45
232 || በግ እንድንሆን እግዚአብሔር የጠራን ለምንድን ነው? || በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 14.08.2022 59:17
እግዚአብሔርን በግ እንድንሆን የጠራን ለምንድን ነው? በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ መዝ. 23፡1-6፣ 2 ቆሮ. 2፡14-17፣ 1ቆሮ. 3፡18-20
231 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 8 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 07.08.2022 1:22:39
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 8ተኛውና የመጨረሻው ክፍል። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡14-22 ይህ ክፍል ለሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል። በክፍሉ ውስጥ የተመለከቱ 7 ነጥቦች፡ 1) መግቢያ ስለ ሎዶቂያ ከተማ 2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡14) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዮሐ. 1፡1-3፣ ምሳሌ 8፡22-31 3) የነቀፋ ቃል (3፡15,16) 4) የተግሳጽ ቃል (3፡17) 5) የምክር ቃል (3፡18) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢሳ.9፡6 6) የማበረታቻ መ...
230 || የወንጌል ሥርጭት ገጠመኝ || በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ 30.07.2022 7:11
ቅዳሜ፣ ጁላይ 30 ቀን 2022 ዓ.ም በነበረው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ የሽብሽር ፕሮግራም ላይ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ አጭር የገጠመኝ ጽሐፍ።
229 || ፋሬስ || በእህት ሙሉ ወልደሚካኤል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል 30.07.2022 18:55
ቅዳሜ፣ ጁላይ 30 ቀን 2022 ዓ.ም በነበረው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ የሽብሽር ፕሮግራም ላይ በእህት ሙሉ ወልደ ሚካኤል የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ዘፍ. 38
228 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 7 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 24.07.2022 55:37
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 7ተኛው ክፍል። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡7-13 ይህ ክፍል ለፊላዴልፊያ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል። በክፍሉ ውስጥ የተመለከቱ 6 ነጥቦች፡ 1) መግቢያ ስለ ፊላዴልፊያ ከተማ 2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡7) 3) የምሥጋና መልዕክት (3፡8) 4) ጌታ ሊያደርገው ያለው ዕቅድ (3፡9) 5) ስለጌታ ጥበቃ የተሰጠ መልዕክት (3፡10) 6) እስከ መጨረሻ ስለመጽናት የቀረበ ምክር (3፡11) 7) ድል ለመንሳት የቀረበ የጥሪ መልዕክት (3፡12-13)
227 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 4 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 17.07.2022 58:53
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት ክፍል 4፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ነፍስን በመተው ለዘላለም ህይወት መጠበቅ በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡- 1) ጌታ ስለሞቱ ዓላማ ከተናገረበት ክፍል 3 ነጥቦችን እንመልከት የዘርና የተክል ህይወት በሞት ድልድይነት ተገናኝቷል የእኛና የጌታ ህይወት በሞት ድልድይነት ተገናኝቷል የህይወታችን ዘላለማዊ ዋስትና ለዓለማዊ ህይወት ባለን ጥላቻ ይወሰናል 2) ጠላትን በመውደድ ረገድ የጌታ ምሳሌነት 3) ህይወትን በመተው የመጠበቅ ቁልፍ በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ዮሐ. 12፡23-28/ ማቴ. 16፡24-27/ ዕብ. 12፡1-4/ ዮሐ. 10፡1...
226 || የጌታን መንገድ መከተል || ክፍል 3 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 10.07.2022 1:02:22
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት ክፍል 3፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ጠላትን መውደድ በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡- 1) ጠላት ምንድን ነው? 2) ጠላትን በመውደድ የጌታ ምሳሌነት 3) ጠላትን የመውደድ 5 ምክንያቶች 4) የካሪ ቡም ታሪክ - ጠላትን ይቅር ብሎ ስለመደድ በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ሉቃ. 23፡13-25፣ 32-34/ ማቴ. 27፡24-25/ ማቴ. 5፡43-48/ ዘሌ. 19፡18/ ሮሜ 12፡21/
225 || ኢየሱስ ማን ነው? || በወንድም በእምነት ካሳ 03.07.2022 41:35
"ኢየሱስ ማን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም በእምነት ካሳ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ቆላ. 1፡13-18/ ዮሐ. 8፡58/ ማቴ. 1፡21-24/
224 የዕርቅ መርሃ ግብር - በሁለቱ ቤተ ክርስቲያኖች መሪዎች መካከል 26.06.2022 34:10
በኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል የተደረገ ልዩና እግዚአብሔር የከበረበት የዕርቅ መርሃ ግብር። “እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።” መዝሙር 126:1-3
223 || ከተኩላዎች ተጠበቁ || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 26.06.2022 44:02
"ከተኩላዎች ተጠበቁ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፣ ማቴ. 10፡16/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40/ ዮሐ. 10፡1-12/
222 || እግዚአብሔር እረኛዬ ነው || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) 19.06.2022 1:13:27
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ መዝ. 100፡2-3/ መዝ. 23፡1-6/ ማቴ. 11፡28/ ኢሳ. 53፡6 / ኢሳ. 40፡11/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40
221 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 6 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን 12.06.2022 47:33
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 6ተኛው ክፍል። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡1-6 ይህ ክፍል ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል። መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለሰርዴስ መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን። 1) መግቢያ ስለ ሰርዴስ ከተማ 2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡1) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ራዕ. 4፡7 3) የተግሳጽ/የነቀፋ መልዕክት (3፡2) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1ሳሙ. 17፡2፣ ማቴ. 25፡1 4) የም...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.