ECFC in Finland
Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland
This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.
Author
ECFC in Finland
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 5, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
122_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 2 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 06.09.2020 1:01:04
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 2: ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሰው ምንነት ዕይታ ሀ) ሰው በትክክል ምንድን ነው? ለ) የሰው ማንነት ክፍሎች የሰው መንፈስ የሰው ነፍስ የሰው ሥጋ/ቁሳዊ አካል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ተሰ. 5:23/ዕብ. 4:12/ኢዮብ 32:8/ሉቃ. 9:56/ማር. 14:34/ሉቃ. 23:46/ሐዋ. 7:59/መክ. 12:7/ፊል. 3:20-21
121_ሰው ምንድን ነው? || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 30.08.2020 56:35
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7 በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:- ርዕስ: ሰው ምንድን ነው? ክፍል 1: ዓለም ለሰው ያላት ዕይታ 1) የማቴሪያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ 2) የአይዲያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ 3) ክርስቲያናዊ የሰው ምንነት ዕይታ
120_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 2 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ 26.08.2020 1:46:36
ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: - ርዕስ: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ 1) መግቢያ 2) በልጆች ጉዳይ ወላጆች ላይ መሥራት የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶች 3) በልጆችና ወላጆች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮች 4) ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጤንነት ለመጠበቅ የሚረዱ ነገሮች
119_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 1 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ 25.08.2020 2:18:35
ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: - ርዕስ: ባልና ሚስት እርስ በርስ ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ 1) የትምህርቱ ዓላማዎች 2) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ ሁለንተናዊ አሉታዊ ተጽዕኖዎች 3) የጤናማ ግንኙነት ወይም ትዳር (መኖር/አለመኖር) መለኪያ መስፈርቶች 4) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ የታወቁ ምክንያቶች 5) የትዳርና የቤተሰብ ግንኙነትን ጤንነት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች
118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 23.08.2020 36:21
118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 10. በጊዜውም ያለጊዜውም ቢመችም ባይመችም ተዘጋጅቶ መኖር 2 ጢሞ4:2 11. እስከ መጨረሻው መጽናት ማቲ 10:22 እንድንፀና የሚረዱን 4 ነገሮች 1 . የእግዚአብሄር ቃል በመታዘዝ ማቲ 7:26 እና 1 ዜና 28:5-7 2. ፀሎት 1ጴጥ 5:10 3. የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ሐዋ 1:8 4. ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች ሉቃ 22:32
117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ 16.08.2020 37:44
117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ እንድንጸናባቸው ከታዘዝንባቸው 6 ነገሮች የመጀመሪያዎቹ 4ቱ በ 2ቆሮ 12: 9 እና ምዕ 8:1 ጀምሮ ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ 6.በጸጋ መጽናት 7.በፍቅር መጽናት 8.በአገልግሎት መጽናት 9.በወንጌል እውነት መጽናት
116_ፅና ወይም ፅኑ በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/ 09.08.2020 40:55
116_ፅና ወይም ፅኑ በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/ ፅና ወይም ፅኑ በኢያሱ 1:6 እና በዘዳ 31:7 ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት መፅናት በግል: በቤተሰብ: በሕብረት መፅናት ለአማኞች የተሰጠ ትእዛዝ ነው:: ሀ.በመፅናት ምሳሌ የሆኑን : ሐና: ዳዊት: አሳ ለ.እንድንፀናባቸው የታዘዝንባቸው ነገሮች 1. በተስፋ መጽናት 2. በእምነት መጽናት &...
115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን || ክፍል 2 || ያቬሎ ናታዬ 02.08.2020 59:16
115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን /ክፍል 2 / ያቬሎ ናታዬ የንግግሮቻችን 7 መመዘኛዎች 1- እያንዳንዱን ሰው ታሳቢ ማድረግ አለበት : 2-አውዳዊ ስልትን የተከተለ መሆን አለበት 3-እውቀትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት 4-ትክክለኛ መልእክት የያዘ መሆኑን መረጋገጥ አለበት 5-ሁልጊዜ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት 6-ንግግራችን የተቀመመ መሆን መረጋገጥ አለበት 7-ጸጋን የተሞላ መሆን አለበት በጠብ ሳይሆን በጥበብ ለመመላለስ ንግግራችን እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል:: ቆላ 4:5-6 በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል መልእክት ላይ የተመሰረተ
114_ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10 በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 26.07.2020 46:57
114_ ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10 ባለው ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት /በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።ራዕ 5:9-10 1. ጥቅልሉ መጽሐፍ ራዕ 5: 1-3 2. ከሽማግሌዎች አንዱ ራዕ 5: 4-7 3. ለበጉ ክብር የምስጋና ዝማሬ ራዕ 5: 8-10
113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ 19.07.2020 57:51
113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን ተከታታይ ትምህርት :: በወንድም ያቬሎ ናታዬ ዘመኑን እየዋጃችሁ: በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ :: "ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመላለሱ እንደሚገባ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ :በጨው እንደ ተቀመመ :በጸጋ ይሁን"::ቆላ 4:5 ክፍል 1 1:1 ዘመኑ ምን አይነት መልክ አለው? የሚዋጅ ዘመን በኤፌ 5:15 እና 2ኛ ጢሞ3:1-5 ላይ የተመሰረተ ቃል:: 1)ዘመኑ የሚዋጅ ነው 2) ዘመኑ ክፉ ነው 3)ዘመኑን ዋጁ 1-2 ዘመኑን የምንዋጀው እንዴት ነው? በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ:: ቆላ 4:5 1)ዘመኑን መልክ በመ...
112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/ 12.07.2020 1:04:39
112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/ 1/ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: እግዚአብሔር ስሙን ከፍ ለማድረግ ይዋጋል:: ዘጸ 15:1-3 እግዚእብሔር ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለህዝቡ ብቻውን ተዋግቶ : ድል ሲነሳ ስላዩ: ሙሴና የእስራኤል ህዝብ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" አሉት:: 2/ እግዚእብሔር የራሱን ህዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት ለመታደግ 2ዜና 20: 14-15 3/ እግዚእብሔር ህዝቡን ወደ አሰበለት ስፍራ ለማስገባት:: ዘጸ 14: 14-23
111_እግዚአብሄር መሐሪ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን 05.07.2020 50:39
111_እግዚአብሄር መሐሪ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን የእግዚአብሄር መሐሪነት የገባው እግዚአብሄር የሚምር የሚራራ መሆኑንን የተረዳው አብርሃም ስለሌሎች ያደረገውን ጸሎት እና ልመና ላይ የተመሰረተ ቃል ነው:: እኛም የእግዚአብሄር ምህረት እንደገበው ሰው እግዚአብሄር ለብዙዎች ምህረትን እንዲያደርግ አጥብቀን እንጸልይ ዘንድ ያስፈልገናል::
110_የፈርሃ እግዚአብሔር በረከቶች 28.06.2020 56:19
"የፈርሃ እግዚአብሔር በረከቶች" በሚል ር ዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መል ዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: መዝ. 25:12-14/ሚል. 3:16-18
109_ጥበብን አግኝ - ክፍል 3 21.06.2020 45:48
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል:: ክፍል 3: ጥበብን እንዴት ማግኘት ይቻላል? 1. ቃሉን በመጠበቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ኤር. 8:8-12/2ጢሞ. 3:14-17/ምሳሌ 2:1-11 2. በጸሎት እግዚአብሔርን በመጠየቅ ያዕ. 1:1-5/ሉቃ. 21:14-15/1ዜና 22:12/2ዜና 1:10
108_ጥበብን አግኝ ክፍል 2 14.06.2020 50:18
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ምሳሌ 24:3፣ 1:7፣ 19:23፣ 2:5/ መዝ. 19:19/ሐዋ. 6:3
107_ጥበብን አግኝ - ክፍል 1 07.06.2020 42:39
"ጥበብን አግኝ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ምሳሌ 4:7-8/ ኤፌ. 5:15 / 1ቆሮ. 1:18-21/ ያዕ. 3:17
106_ጊዜን ማስተዋል! 31.05.2020 45:52
"ጊዜን ማስተዋል/ማወቅ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ዜና 12:32/ኤፌ. 5:15-17/1 ነገ. 15:1-32 /2 ነገ. 21:9/2 ዜና 34:1-7
105_የእግዚአብሔር ክብር መንገድ 24.05.2020 50:43
"የእግዚአብሔር ክብር መንገድ" በሚል ርዕስ በማቴ. 17:1-8 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በፓስተር ፋሲል በለጠ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ: ማቴ. 17:1-8 አራት ነጥቦች ስለ እግዚአብሔር ክብር 1) እግዚአብሔር ክብሩን የሚገልጠው በድንገት ነው 2) ሰውን ወደ ክብሩ የሚያስገባው እግዚአብሔር ራሱ ነው 3) የእግዚአብሔር ክብር ጫፍ/መደምደሚያ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው 4) የእግዚአብሔር ክብር ለሰው የሚገለጥ/ማየት የሚቻልና የማይቻል ደረጃዎች አሉት የእግዚአብሔርን የክብር መንገድ ለመጓዝ የሰው ድርሻ 1) ኢየሱስን መከተል 2) ኢየሱስን ማየት 3) ኢየሱስን መስማት
104_ንስሐ፣ ተስፋና ተሃድሶ! 17.05.2020 47:51
"ንስሐ፣ ተስፋና ተሃድሶ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ትዕግሥት ቸርነት የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል: ዕዝራ 10:1-10
103_ጌታን በተግባር መከተል ክፍል 3 10.05.2020 1:02:31
"ጌታን በተግባር መከተል" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበው የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጨረሻው ክፍል::
102_ጌታን በተግባር መከተል ክፍል 2 03.05.2020 53:16
"ጌታን በተግባር መከተል" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል:: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ዮሐ. 13:1-17/ማቴ. 5:43-48
101_ጌታን በተግባር መከተል ክፍል 1 26.04.2020 46:23
"ጌታን በተግባር መከተል" በሚል በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል::
100_መስቀሉ ትምክህታችን ነው! 19.04.2020 50:08
"መስቀሉ ትምክህታችን ነው!" በሚል ር ዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
099_ኢየሱስ ሰላማችን ነው! 12.04.2020 45:45
በፋሲካ ፕሮግራም ላይ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
098_የኢየሱስ ሞት ምን አመጣልን? ክፍል 2 12.04.2020 49:50
በፋሲካ ልዩ ፕሮግራም ላይ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ክፍል 2::
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.