SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Visita il sito del podcast e sostieni chi lo crea: www.sbs.com.au
Dove ascoltare?
I podcast nell'app Replaio Radio In arrivoI podcast stanno per arrivare nell'app. Installala ora e scopri per primo un modo tutto nuovo di vivere i podcast
Episodi
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብይታቸው በዶላር ለሚካሔድ ዓለም አቀፍ በረራዎች የተለየ ለውጥ አለማድረጉን አስታወቀ 06.08.2024 9:13
ኢትዮጵያ ለ2017 ከተመደበው 971.2 ቢሊየን ብር በጀት ላይ ተጨማሪ ከ500 ቢሊየን ብር በላይ አክላ ልታፀድቅ ዝግጅት መደረጉ ተገለጠ
What is genocide? - SBS Examines: ዘር ማጥፋት ምንድነው? 06.08.2024 6:20
'Genocide' is a powerful term — it's been called the "crime of crimes". When does large-scale violence become genocide, and why is it so difficult to prove and punish? - 'ዘር ማጥፋት' እጀግ ብርቱ ቃል ነው፤ "የወንጀሎች ወንጀል" ተብሏልም። የመጠነ ሰፊ አመፅ ክስተት የዘር ማጥፋት ድርጊት ሆኖ ሲገኝ እውን መሆኑን ለማረጋገጥና ቅጣትን ለመጣል በእጅጉ አዋኪ የሚሆነው ስለምን ነው?
የአውስትራሊያ የሽብር ስጋት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ወደ 'ሊከሰት ይችላል' ከፍ አለ 05.08.2024 10:13
ከ40 ፐርሰንት በላይ ወጣት አውስትራሊያውያንና ከአራት አንድ ጎልማሶች ለብቸኝነት የተዳረጉ መሆኑ ተመለከተ
የአምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሥነ ሕዝብና ጤና ቆጠራ መጀመሩ ተገለጠ 04.08.2024 10:55
በአንድ ቀን ውስጥ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 542 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ
"ብር እየወደቀና የዋጋ ንረት እየበዛ የሚያስቸግር ከሆነ፤ዋጋውን ለመቆጣጠር ያለችን ትንሽ ቁልፍ የወለድ መጠን መጨመር ነው፤ያ ደግሞ ምርታማነትን ይጎዳል" ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024 21:55
ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግብር ላይ መዋሉን ስላስታወቀው "የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ" ፖሊሲ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች፣ የሚያስከትላቸውን መዘዞችና ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊቀሰሙ የሚገቡ ልምዶችን ነቅሰው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።
"የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ ትልቁ ችግር ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችንም ማናጋት መቻሉ ነው፤በጀትን ጨምሮ ከታክስ፣ እስከ ወለድ መጠን ድረስ"ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ 04.08.2024 16:30
"ሚዲያ/ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መንግሥት ገንዘቡን ጣለ የሚለው ትክክል አይደለም። መንግሥት ገንዘቡን አይደለም የጣለው፤ ይደግፈው የነበረውን ብር ነው መደገፍ የተወው። በነፃ ገበያ እንዲወሰን ነው ያደረገው፤ ይህ ፖሊሲ ነው ብር እንዲወድቅ ያደረገው፤ ሁለቱን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል" የሚሉት ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ፖሊሲ ያስረዳሉ።
"በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማን ሐዘን ጥልቅ ነው፤የእርዳታ ፕሮግራም አዘጋጅተናል"አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ 02.08.2024 8:51
በምዕራብ አውስትራሊያ የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት ተጎጂዎች ጊዜያዊ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፤ አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ፤ በፐርዝ ከተማ ለእሑድ ሐምሌ 28 ስለተዘጋጀው ልዩ የእርዳታ ፕሮግራም ያስረዳሉ።
"ከ2011 ጀምሮ ኢትዮጵያ በአማካይ ከባሕር ማዶ ኢትዮጵያውያን ታገኝ የነበረው 4 ቢሊየን ዶላር በእዚህ የበጀት ዓመት 6.5 ቢሊየን ደርሷል" አቶ በላይነህ አቅናው 02.08.2024 18:00
አቶ በላይነህ አቅናው፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ አገልግሎቱ ለባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለሚያበረክታቸው አስተዋፅዖዎች ያስረዳሉ።
#67 Complaining about kids (Med) 31.07.2024 16:02
Learn how to talk about your kids when they are a bit challenging.
የሃማስ ፖለቲካ መሪ ኢራን ውስጥ ተገደሉ 31.07.2024 7:02
በሬክስ አየር መንገድ ከበረራ መገታትና ለኪሳራ መዳረግ ሳቢያ 850 ያህል ሠራተኞች ሥራቸውን እንደሚያጡ ተመለከተ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የፓሪስ ኦሎምፒክ ሃይማኖት ነክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ትዕይንት አወገዘች 30.07.2024 7:39
87 በመቶ የሚሆኑ የግል ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸው ተገለጠ
"በግሌ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተነሳ ይህችን የምንወዳትን ሀገር የሚረከብልን ወጣት አናገኝ ይሆናል የሚል ስጋት ውስጥ ነው ያለሁት" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ 30.07.2024 20:50
ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ የይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ የአዕምሮ ሕመምና አደንዛዥ ዕፅ ሱስ ምን ያህል ስር እንደሰደደ፣ የመንግሥት፣ የሕዝብ፣ የሃይማኖት መሪዎችና የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን የትድግና ድርሻ ያነሳሉ። ለእገዛቸውም ጥሪና ምስጋና ያቀርባሉ።
በባሕር ዳር ከተማ ሰዓት ዕላፊ ተጣለ 29.07.2024 9:10
የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ
የአያሌ ኢትዮጵያውንን ዕንባ ያስፈሰሰው የጎፋ ዞን የሕይወት ጥፋት ከዓለም መሪዎች የጥልቅ ሐዘን መግለጫዎች እየጎረፉለት ነው 28.07.2024 9:29
የዋቻሞ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ
"ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ 28.07.2024 15:07
ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።
"በጎፋ ዞን ከደረሰው ችግር ስፋትና ብዛት አንፃር ያሉ ድጋፎች በቂ ስላልሆኑ በሁሉም በኩል ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንጠይቃለን" አቶ ካሳሁን አባይነህ 27.07.2024 7:34
አቶ ካሳሁን አባይነህ ሓጎስ፤ የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ፤ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የደረሱትን የሕይወት ጥፋቶች፣ የአስከሬን ፍለጋ ሂደቶች፣ የሚያሹ አስቸኳይና ዘላቂ ልገሳዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራ በረራዎቹን እንዲያቋርጥ ከኤርትራ ሲቪል አቬይሽን እንደተነገረው አስታወቀ 25.07.2024 3:36
የአውስትራሊያ የወሊድ ቁጥር ከ2006 ወዲህ ከፍተኛ በተባለ ሬኮርድ መጠን ቀነሰ
በመሬት ናዳ ሕይወታቸው ያለፈ የደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን ነዋሪዎች ቁጥር ከ229 በላይ መድረሱ ተገለጠ 24.07.2024 9:42
የኒውዚላንድ ኦሎምፒክ ቡድን ካናዳ የድሮን ስለላ አካሂዳብኛለች ሲል ክስ አቀረበ
በደቡብ ኢትዮጵያ በደረሰ የመሬት ናዳ ሳቢያ ከ100 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ 23.07.2024 3:11
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ፤ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለ2024 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን የዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት መጠነ ሰፊ ድጋፍ እንዳገኙ ተመለከተ
"በዓለም አቀፍ ተቋም ግፊት የኢትዮጵያን የጥሬ ብር ምንዛሪ ግብይት አቅም መቀነስ አንገትን የመታነቅ ያህል ነው" ኢንጂነር አያሌው አስፋው 23.07.2024 11:25
ኢንጂነር አያሌው አስፋው፤ ሉላዊ የገንዘብ ዝውውርን፣ ከአሜሪካን ዶላር ውጭ ዓለም አቀፍ ግብይት የማድረግ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።
"የሳይበር ጥቃትን ዜሮ ማድረግ አይቻልም፤ ያንንም ማድረግ የቻለ ሀገር የለም" ኢንጂነር አያሌው አስፋው 23.07.2024 15:46
ኢንጂነር አያሌው አስፋው፤ የሳይበር ጥቃቶች በግለሰቦች፣ ተቋማትና መንግሥታት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖዎች፤ የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርን አንስተው ያመላክታሉ።
በአዲስ አበባ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ8 ሺህ በላይ ጥንዶች ፍቺ መፈፀማቸው ተገለጠ 22.07.2024 10:23
ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኑ ተመለከተ
ጆ ባይደን ከዕጩ ፕሬዚደንትነታትቸው ለቀቁ፤ በፕሬዚደንታዊ ስልጣናቸው ፀንተው እንደሚቆዩ አስታወቁ 21.07.2024 7:27
የሪፑብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ካማላ ሃሪስ ዕጩ ፕሬዚደንት ሆነው ከቀረቡ በቀላሉ ድል እንደሚነሷቸው ገለጡ
Is immigration worsening the housing crisis? - SBS Examines: ኢሚግሬሽን የቤት ቀውስን ያባብሳል? 21.07.2024 4:03
Australia's facing a worsening housing crisis. At the same time, the number of overseas migrant arrivals is at its highest ever since records began. Is increased migration driving up housing and rental prices? - አውስትራሊያ የቤት እጥረት ቀውስ ተጋርጦባት አለ። በሌላም በኩል የባሕር ማዶ ፍልሰተኞች ቁጥር ሬኮርድ መመዝገብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቶውንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። የፍልሰተኞች ቁጥር መናር የቤት ግዢ / ግንባታና የኪራይ ዋጋዎች እንዲያሻቅቡ ያደርጋል?
"የግብፁ መንፈሳዊ ጉዞ የሚካሔደው ከጥቅምት 28 ቀን 2017 እስከ ኅዳር 10 ቀን 2017 ነው" ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ 18.07.2024 12:56
ዶ/ር ተፈሪ በላይነ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ወደ ግብፅ ስለሚደረገው የመንፈሳዊ ጉዞ ፕሮግራም ሂደት ይናገራሉ።
Podcast simili
Replaio non è un editore di podcast; i nomi dei programmi, le copertine e l'audio appartengono ai rispettivi autori e vengono distribuiti tramite feed RSS pubblici