DW

ስፖርት | Deutsche Welle

Games AM ↓ 70 episodios

ት እንቅስቃሴ የሚታይበት ዝግጅት ነው።

No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: www.dw.com?maca=amh-podcast_amh_sportmagazin-13629-xml-mrss

Autor

DW

Categoría

Games

Último episodio

12 de oct. de 2026

¿Dónde escuchar?

Podcasts en la app Replaio Radio Muy pronto

Los podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts

Descárgala en Google Play Instálala gratis Android casi 10 M de descargas · valoración de 4,8 iOS muy pronto

Episodios

የጥቅምት 2 ቀን 2019 የስፖርት ዘገባ 12.10.2026

በአሜሪካ ቺካጎ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሽናፊ ሆናለች።የ2019ኝ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳና ከሜዳ ውጭ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።የሳምንቱ መጨረሻ የጀርመን ቡንደስሊጋ ጨዋታዎች እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች በርካታ ግቦችን፣ አስገራሚ ውጤቶችን እና ከፍተኛ ትኩሳትን የፈጠሩ ጨዋታዎችን አስተናግደዋል።

የጥቅምት 2 ቀን 2019 የስፖርት ዘገባ 12.10.2026

የጥቅምት 2 ቀን 2019 የስፖርት ዘገባ

የመስከረም 25 ቀን 2019 የስፖርት መሰናዶ 05.10.2026

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2019 የእግር ኳስ ውድድር ዘመን በተያዘው ሳምንት ይጀመራል። ቡንደስ ሊጋን ጨምሮ ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሊጎችም አርብ እና ቅዳሜ ወደ ውድድር ይመለሳሉ። ሐና ደምሴ ያዘጋጀችው የዛሬው የስፖርት መሰናዶ እነዚህን ጨምሮ አትሊቲክስ እና ሜዳ ቴኒስን የተመለተኩ ዘገባዎች አካቷል።

የመስከረም 18 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ሳምንታዊ የስፖርት ጥንቅር 28.09.2026

በዛሬ የስፖርት መሰናዶዋችን ነገ ከሴኔጋል ጋር ያለውን ጨዋታ ስለሚያስተናግደው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይዞታ እና ስለጨዋታው ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። አትሌቲክስ እንዲሁም የኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዘገባዎችንም አካትተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።

የመስከረም 11 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 21.09.2026

ማንቸስተር ሲቲ በድል ጎዳና መገስገሱን ቀጥሏል ። ሊቨርፑል ትእግስቱ የማታ ማታ ፍሬ አፍርቷል ። የብራይተን አስደማሚ ጀብድ የአርሰናልን ግስጋሴ ከመግታትም አልፎ ደጋፊዎቹን ክው አድርጓል ። በኮፐንሀገን የዓለም የጎዳና ላይ አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ፉክክር 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች ።

የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት 14.09.2026
የጳጉሜ 02 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 07.09.2026

ሦስተኛ ተከታታይ ጨዋታውን በድል ያጠናቀቀው አርሰናል ትናንት በድንቅ ኹኔታ የተፋለመው ቸልሲን ድል አድርጓል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ አስደናቂ ድል ስላስመዘገቡበት የቤልጂየሙ ዋንዳ ዳያመንድ ሊግ የአትሌቲክስ ፉክክር እና ሌሎች ስፖርታዊ መረጃዎችን አካትተናል ። ሙሉ ዘገባው በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይገኛል።

የነሐሴ 25 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 31.08.2026

በዛሬ የስፖርት መሰናዶዋችን ፕሬዚደንቱን እና ዋና ጸሐፊውን ስላፋጠጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውዝግብ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። እግር ኳስ እና የሜዳ ቴኒስን የሚመለከቱ ሌሎች ዘገባዎችንም አካትተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 31.08.2026
አማናል ጴጥሮስ፦ ከስደት እስከ የአውሮጳ ባለድል 21.08.2026

ገና አዳጊ ወጣት ሳለ ነበር ትውልደ ኤርትራዊው ጀርመናዊ የማራቶን ባለድል አማናል ጴጥሮስ ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እናት እና እህቱ እዛው ሲቀሩ ወደ ጀርመን የተሰደደው ። ዛሬ ቁጥር አንድ የጀርመን አትሌት ለመኾን በቅቷል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው መከታተል ይቻላል ።

የነሐሴ 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 17.08.2026

ክሪስቲያኖ ሮናልዶም እንደ ዋነኛ ተፎካካሪው ሊዮኔል ሜሲ በቅርቡ ጫማ እንደሚሰቅል ይፋ አድርጓል። ትውልደ ኤርትራዊው የማራቶን ሯጭ ለጀመርን የወርቅ ሜዳሊያ ስላስገኘበት የአውሮጳ አትሌቲክስ የፍጻሜ ፉክክር ሰፋ ያለ ዘገባ ይኖረናል ። እግር ኳስ እና የሜዳ ቴኒስን የሚመለከቱ ሌሎች ዘገባዎችንም አካትተናል ። ሙሉ ዘገባው በማገናኛው በኩል ይገኛል።

የነሐሴ 11 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 17.08.2026
የነሐሴ 4 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 10.08.2026

የዓለም እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ላይ ተቃውሞው በርትቷል፥ ለሥልጣናቸው ያሰጋ ይኾን? ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የኦሬጋኑ አትሌቲክስ ፉክክ ውጤቱ እንዴት ይገመገማል? ቃለ መጠይቅ አድረገናል፥ ተጨማሪ ዘገባም ይኖረናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 03.08.2026
የሐምሌ 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 03.08.2026

በዓለም እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ፉክክር ላይ ተካፋይ የሚኾኑት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለውጤት መጠበቃቸው፤ የፊፋ ውድድሮችን በከፊል ለግል ባለሐብቶች ለመሸጥ አቅርቦት የነበረው ሐሳብ በፊፋው ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ላይ ያጫረው ብርቱ ተቃውሞ የስፖርት ዘገባ ዋና ትኩረት ናቸው ።

የሐምሌ 20 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 27.07.2026

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ዬርገን ክሎፕ ማን ናቸው? ከሳቸውስ መላ ጀርመን ምን ይጠብቃል? ዝርዝር ይኖረናል ። ስለ ዓለም ዋንጫ የፊፋው ፕሬዚዳንት ብርቱ ትችት ጨምሮ ዝርዝር ዘገባ አካትተናል ። የፎርሙላ አንድ ሽቅድምድምን የተመለከተና ሌሎች ዘገባዎችንም እናስደምጣችኋለን ። ሙሉ ዘገባው በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይገኛል።

የሐምሌ 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 20.07.2026

አርጀንቲናዎች በመጨረሻው ግጥሚያ ግብግብ ፈጥረው የመንደር ጨዋታ ያስመሰሉት የዓለም ዋንጫ በፌራን ቶሬዝ ብቸኛ ግብ በስፔን አሸናፊነት ተጠናቅቋል ። ፈረንሣዊው ኪሊያን እምባፔ ቡድኑ የሦስተኛ ደረጃውን በእንግሊዝ ቢነጠቅም የወርቅ ጫማውን ግን አስጠብቋል ። ሜሲ አንብቶ ከሜዳ ወጥቷል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 20.07.2026
ፈረንሣይ፥ ስፔን፥ አርጀንቲናና እንግሊዝ በግማሽ ፍጻሜ፣ አጋጣሚ ወይንስ? 14.07.2026

ለግማሽ ፍጻሜው ካለፉት አራት አገራት መካከል ዛሬ ማታ የሚጫወቱት ፈረንሣይ እና ጠንካራ ተፎካካሪ ኾና ብቅ ያለችው ስፔን ናቸው ።ፈረንሣይ ከስፔን፤ እንግሊዝ ከአርጀንቲና ለግማሽ ፍጻሜ መገናኘታቸው ብዙዎች የአጋጣሚ አይደለም የፊፋ ረጅም እጅ አለበት ይላሉ፦ ቃለ መጠይቁን በማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።

የሐምሌ 6 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 13.07.2026

የዓለም ዋንጫ፦ ከአሜሪካ እስከ ሶማሊያ፤ ከግብጽ እስከ አርጀንቲና፤ ከሞሮኮ እስከ ፈረንሣይ፥ መላ ዓለምን ሲያስደምም፣ ሲያስቦርቅና እንባ ሲያራጭ ቆይቶ ወደ ፍጻሜው እየተጠጋ ነው ። የኢትዮጵያ አዳጊ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በመጨረሻዎቹ ሰዓቶች ለዓለም ዋንጫ የነበረው ዕድል ለምን መከነ? ቃለ-መጠይቁንና ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ማገናኛው ያድምጡ።

ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት 06.07.2026
ሴኔጋል እና ኮንጎ ባለቀ ሰዓት ምን አፍረከረካቸው? 02.07.2026

ለዓለም ዋንጫ አፍሪቃን ከወከሉ 10 አገራት ስምንቱ ወደ ጥሎ ማለፍ መሻገር ተሳክቶላቸው ነበር ። ትናንት በነበረው ግጥሚያ ግን ሴኔጋል እና የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክየአውሮጳ ኃያላን ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያስጨንቁ ቆይተው በስተመጨረሻ ሁለቱም እጅ ሰጥተዋል ። በዋነኛነት ችግሩ ምን ነበር? ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ 29.06.2026
የሰኔ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 29.06.2026

በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ የበርካታ አፍሪቃውያንን ድጋፍ የተነፈገችው ደቡብ አፍሪቃ ምንም እንኳን ጠንካራ ተፎካካሪ መኾኗን ብታስመሰክርም በካናዳ ከውድድሩ ተሰናብታለች ። የብዙዎች ዐይን ያረፈው ስምንቱ የአፍሪቃ ቡድኖች ላይ ነው ። ለዓለም ዋንጫ ከአፍሪቃ እነማን ይጠበቃሉ? ዝርዝር ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።

የሰኔ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 22.06.2026

ከአዲስ አበባ ስታዲየም ሜዳ ያቋረ ውኃን በመወልወያ እና ባልዲ ለማስወገድ የተጣረበትን አስደማሚ ክስተትም በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በዋናነት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ዳሰሳ እንአደርጋለን ። ተጨማሪ የስፖርት መሰናዶ አካተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።

Escucha el podcast ስፖርት | Deutsche Welle en Replaio

Radio y podcasts en una sola app - gratis y sin registro. Instálala hoy y no te pierdas el estreno

Descárgala en Google Play

Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos