DW
ስፖርት | Deutsche Welle
ት እንቅስቃሴ የሚታይበት ዝግጅት ነው።
Author
DW
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 6, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ሴኔጋል እና ኮንጎ ባለቀ ሰዓት ምን አፍረከረካቸው? 02.07.2026 4:48
ለዓለም ዋንጫ አፍሪቃን ከወከሉ 10 አገራት ስምንቱ ወደ ጥሎ ማለፍ መሻገር ተሳክቶላቸው ነበር ። ትናንት በነበረው ግጥሚያ ግን ሴኔጋል እና የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክየአውሮጳ ኃያላን ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያስጨንቁ ቆይተው በስተመጨረሻ ሁለቱም እጅ ሰጥተዋል ። በዋነኛነት ችግሩ ምን ነበር? ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።
የሰኔ 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 29.06.2026 9:40
በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ የበርካታ አፍሪቃውያንን ድጋፍ የተነፈገችው ደቡብ አፍሪቃ ምንም እንኳን ጠንካራ ተፎካካሪ መኾኗን ብታስመሰክርም በካናዳ ከውድድሩ ተሰናብታለች ። የብዙዎች ዐይን ያረፈው ስምንቱ የአፍሪቃ ቡድኖች ላይ ነው ። ለዓለም ዋንጫ ከአፍሪቃ እነማን ይጠበቃሉ? ዝርዝር ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።
የሰኔ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 22.06.2026 9:59
ከአዲስ አበባ ስታዲየም ሜዳ ያቋረ ውኃን በመወልወያ እና ባልዲ ለማስወገድ የተጣረበትን አስደማሚ ክስተትም በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በዋናነት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ዳሰሳ እንአደርጋለን ። ተጨማሪ የስፖርት መሰናዶ አካተናል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ እና በጽሑፍ በማገኛው በኩል መከታተል ይቻላል ።
የሰኔ 8 ቀን፣ 2016 ዓም የስፖርት ዘገባ 15.06.2026 11:36
ተጠባቂው የዓለም ዋንጫ በድምቀት ተጀምሯል ። የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እስካሁን ከተደረጉ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ በአንድ ጨዋታ በርካታ ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ቀዳሚ ብሔራዊ ቡድን ኾኗል ። አትሌቲክስ እና ሌሎች ዘገባዎችንም አካትተናል ።
የሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 08.06.2026 8:37
ያሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ የበራበትና የአትሌቶቻችን የበላይነት የታየበት ሆኖ አልፏል። በሩሲያ እና በኢጣሊያ በተደረጉ ታላላቅ ውድድሮች ላይ አትሌቶቻችን ድንቅ ስኬት አስመዝግበዋል።በሌላ በኩል እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር 2026 የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ሀሙስ ይጀምራል።
የግንቦት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 25.05.2026 9:51
ኢትዮጵያውያን እና የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ደምቀው የዋሉበት የተለያዪ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል። የአፍሪካ ኬፕ ታውን ማራቶን የኢትዮጵያውያን ድርብ ድል የተሰራበት ነበር። በሌላ በኩል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትላንት ምሽት የአርሰናል ዘውድ መጫን፣ የዌስትሃም መውረድ እና የስንብት እንባዎች አስተናግዶ ተጠናቅዋል።
የግንቦት 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 18.05.2026 9:40
ጋና አክራ ውስጥ በተከናወነው የአፍሪቃ አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት በ3ኛ ደረጃ አጠናቅቃለች ። ኤርትራ በ1 ብቸኛ ግን ደግሞ በወርቅ ሜዳሊያ 16ኛ ደረጃ አግኝታ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት የተሳናት አስተናጋጇ ጋናን በልጣለች ። በፕሬሚየር ሊጉ ዛሬ ማታ መሪው አርሰናል እንዲሁም ነገ ተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ ወሳኝ ጨዋታ አላቸው ።
የግንቦት 3 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 11.05.2026 10:01
ሞሮኮ ውስጥ ትናንት በተከናወነው የራባት ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም መድረኩን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው በአስደናቂ ውጤት ለድል በቅተዋል ። አርሰናል የማታ ማታ ከጉድ ወጥቷል ። በቡንደስሊጋው ወራጅ ቀጠና ቡድኖች ግብግቡ ቀጥሏል ። ሌሎችንም ጨምሮ ሙሉ ዘገባውን በድምፅና ጽሑፍ ከማገኛኛው ይከታተሉ።
የሚያዝያ 26 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 04.05.2026 10:29
በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ እግር ኳስ በነገው ምሽት አርሰናል እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይፋለማሉ ። የአትሌቲኮ ማድሪዱ አንቷን ግሪዝማን በሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ያላጠናቀቀውን የቤት ሥራ ነገ ማታ አርሰናል ላይ ለመፈጸም ዝቷል ። የዕድሜ ጉዳይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ እጅግ አነጋጋሪ ኹኗል ። ሙሉውን ዘገባ በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።
ማን ለዋንጫ ያልፍ ይሆን? ባዬርን ሙይንሽን ወይንስ ፓሪ ሳንጃርሞ? 28.04.2026 4:12
ዛሬ ማታ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ለአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ፓሪስ ከተማ ውስጥ የጀርመኑ ኃያል ባዬርን ሙይንሽን እና ፓሪ ሳንጃርሞ ይገናኛሉ ። ማን ያሸንፍ ይሆን? የጀርመኑ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተሰላፊ ቶኒ ክሮስ ባዬርን፤ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ ፓሪ ሳንጃርሞ ብለዋል ። ሙሉ ቃለ መጠይቁን በማገናኛው ማድድመጥ ይቻላል ።
የሚያዝያ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 27.04.2026 10:05
አዲስ አበባ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተከናወነው አወዛጋቢ የድብልቅ ማርሻል አርት ፍልሚያ ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በለንደን ማራቶን የወንዶች ፉክክር ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተመዝግቧል ። የአትሌቲክስ፤ የእግር ኳስ እና ተጨማሪ የስፖርት ዘገባዎችንም አካተናል ። ሙሉ ዘገባውን ማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።
የሚያዝያ 12 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 20.04.2026 10:49
በዛሬው የስፖርት መሰናዶ፦ አዲስ አበባ ውስጥ ስለተደረገው የመጀመሪያው ግራንድ ፕሪ ፉክክር ዘገባ ይኖረናል ። ባዬር ሙይንሽን ከወዲሁ ዋንጫውን ማንሳቱን ስላረጋገጠበት የጀርመን ቡንደስሊጋም ዳሰሳ ይኖረናል ። ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን ድል አድርጎ በነጥብ ተጠግቶታል ።
የሚያዝያ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 13.04.2026 10:01
አዲስ አበባ የመጀመሪያውን «የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ» ፉክክር ልታሰናዳ ነው ። ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። እድሜያቸው ከ17ና ከ18 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል ። ሦስት የዓለማችን ምርጥ ቡድኖች ከሻምፒዮንስ ሊግ ሊሰጫፍ ላይ ደርሰዋል ። ሙሉ ዘገባውን በጽሑፍና ድምጽ በማገናኛው ማግኘት ይቻላል ።
የመጋቢት 28 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 06.04.2026 10:40
ባለፈው ቅዳሜ በፈንሳዊቷ ሊል ከተማ በተካሄደው የአምስት ኪሊሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵዉያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።በሌላ በኩል አርሰናል እና ሊቨርፑል በኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግደዋል።
የመጋቢት 21 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 30.03.2026 9:56
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ቡድን ጋር ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የቅድመ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በነገው ዕለት በድሬዳዋ ስታዲየም ያከናውናል ። የጀርመን እግር ኳስ ቡድን በወዳጅነት ግጥሚያ ድንቅ ጨዋታ ዐሳይቶ የስዊትዘርላንድ አቻውን 4 ለ3 አሸንፏል ። ይህን ጨምሮ ሙሉ ዘገባው በድምፅና በጽሑፍ ከማገናኛው ይገኛል ።
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.