Eden Teshome

Continental Drift

News EN ↓ 46 episodios

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, market...

No dejes de visitar la web del podcast y apoyar a su creador: continental-drift.mave.digital

Autor

Eden Teshome

Categoría

News

Último episodio

30 de sep. de 2026

¿Dónde escuchar?

Podcasts en la app Replaio Radio Muy pronto

Los podcasts llegarán muy pronto a la app. Instálala ahora y sé el primero en descubrir una forma totalmente nueva de vivir los podcasts

Descárgala en Google Play Instálala gratis Android casi 10 M de descargas · valoración de 4,8 iOS muy pronto

Episodios

ንግድ፣ ውሃ እና የራስን እድል በራስ መወሰን፡ አፍሪካ የዘላቂ ልማት መሠረቶችን መገንባት ትችላለች? 30.09.2026

የአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና አፍሪካን አንድ የንግድ ገበያ ለማድረግ ያለመ ቢሆንም፣ ስምምነቶች ብቻ ንግድን አያሳድጉም። ንግድ እንዲያድግ የገንዘብ አቅም፣ ተስማሚ የሕግና የቁጥጥር ሥርዓት እና በአፍሪካ ገበያዎች መካከል የሚፈጠሩ የንግድ ትስስሮች ያስፈልጋሉ። “የውሃ ሉዓላዊነት ማለት መሠረተ ልማቱ፣ የገንዘብ አቅሙ እና የውሃ ሀብትን በራስ አቅም ለማስተዳደር የሚያስችል አቅም ግንባታ መኖር ማለት ነው። ማን ያቅዳል፣ ማን ይከፍላል እና ማን ይጠግናል የሚሉት ጉዳዮችም በአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል እና ለህዝብ ተጠያቂ በሆነ መንገድ መረጋገጥ አለባቸው።” ሲሉ ከፍተኛ የውሃ ሀብት አማካሪው ወ...

ሩሲያ-ቻይና ግንኙነት እና የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር 30.09.2026

የሩሲያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢነርጂ፣ በንግድ፣ በፋይናንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱ፣ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ወደ ባለብዙ ማዕከል ሥርዓት እንዲሸጋገር እያበረከተ ይገኛል። ይህ እድገት የአፍሪካ ሀገራት ከተለያዩ አጋሮች ጋር በነፃነት እንዲሠሩ እና የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ አዳዲስ አማራጮችን ይከፍታል። “... እንደ ቻይና፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን እና ሌሎች ታዳጊ መካከለኛና ዓለም አቀፍ ኃይሎች በአፍሪካ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም የአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ካሏቸው አማራጮች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪ...

የቡና ንግድ እና የዕሴት መጨመር አብዮት፡ የአፍሪካ ሀብት በማን እጅ ይገባል? 30.09.2026

የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶች በጥሬ ዕቃነት ከአህጉሪቱ ወጥተው፣ በሌሎች አገራት የተለያዩ ሂደቶች ተከናውነውባቸውና የተጨመረ ዕሴት ተጨምሮባቸው ለገበያ ይቀርባሉ። ይህ አካሄድ አፍሪካ ከሀብቷ ሙሉ ጥቅም እንዳታገኝ ካደረጉ ተግዳሮቶች አንዱ ነው። የዕሴት ጭማሪ አብዮት ግን አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ባሻገር ወደ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ብራንድ ግንባታና ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ወሳኝ አቅጣጫ ነው። "ቡናው በአብዛኛው በጥሬ ዕቃነት ይላካል፤ የዕሴት ጭማሪው ሥራ ግን ቡናው ከሚመረትበት ቦታ በጣም ርቆ በሌላ ስፍራ ይከናወናል። አብዛኛው ትርፍም የሚገኘው በዚያው ነው። በዚያም ይቀራል፤ ቡናው ወደሚመረትባቸው አገራት አ...

የአፍሪካ ቀጣይ ትውልድ፡- ወጣቶችን ወደ ኢኮኖሚ ኃይል መቀየር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች 30.09.2026

የአፍሪካ ወጣት ሕዝብ ብዛት ለአህጉሪቱ ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድል ቢሆንም፣ ይህ ዕድል በራሱ የሚገኝ አይደለም። በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ ዕድገት እና በምርት ዘርፎች ኢንቨስትመንት ሊገነባ ይገባል። "የአፍሪካ የጋራ ደኅንነት በተናጠል ጥረት ሊረጋገጥ አይችልም። ሁለተኛ፣ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ደኅንነት በውጭ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተመርኩዞ ሊሳካ አይችልም። ሦስተኛ፣ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ደኅንነት ጠንካራ የማንነት ቀውስ ባለበት ሁኔታ ሊረጋገጥ አይችልም። ስለዚህ የአፍሪካን የደኅንነት ችግሮች መፍታት የሚቻለው እነዚህን መሠረታዊ ጉዳዮች በመፍታት ነው።" ሲሉ የአፍሪካ ሪበርዝ መሥራችና ፕሬዝዳንት ኢኖክ ቱምዊን...

ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂ፡ የምግብ ምርታማነት እና የገበሬዎች መብት 29.09.2026

"የቁጥጥር ሥርዓቱ የገበሬዎች ማኅበረሰቦችና ልዩነቶቻቸው በምርታማነት ማሳደግ ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ማረጋገጥ አለበት። ስለዚህ ስለ ብዝኃ ሕይወት፣ ስለ መፈናቀል ወይም ስለ ገበሬዎች ዘርን ያለ ማንኛውም እንቅፋት የመሸጥ፣ የማስቀመጥ፣ የመለዋወጥ እና የመጠቀም መብት መጣስ ወይም መጥፋት ማውራት አለብን።" ሲሉ የኢትዮጵያ ዘላቂ ስርዓተ-ምግብና ስነ-ምህዳራዊ ግብርና ሕብረት ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡   በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂና ባዮሴፍቲ ላይ ያተኮረውን ውይይት በማስተናገድ፣ ፈጠራን ከምግብ ሉዓላዊነት ጋር ማመጣ...

ከAI ጋር መስራት፡ ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ባሻገር አዲስ የመስተጋብር ችሎታ 29.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ AI በሥራና በፈጠራ ዓለም እያመጣ ያለውን ለውጥ፣ ሰዎች ከማሽኖች ጋር የሚኖራቸው አዲስ የመስተጋብር መንገድ እና ቴክኖሎጂውን ከመጠቀም ባሻገር እንዴት በብቃት ከAI ጋር መስራት እንደሚቻል እንቃኛለን።

የአፍሪካ ቀጣዩ የኢኮኖሚ ሞተር፡ ሥራ ፈጣሪነት የኢትዮጵያን ወጣቶች ወደ አምራች የሥራ ኃይል ሊቀይራቸው ይችላል? 28.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን ወጣቶች አቅም ወደ አምራች የሥራ ኃይል በመቀየር ረገድ የሥራ ፈጣሪነትን ሚና፣ የስታርትአፕ ፋይናንስ ተደራሽነት ተግዳሮቶችን እና በሥራ ፈጣሪነት ሥነ-ምህዳሩ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን እንቃኛለን።

ብሪክስ እና አዳዲስ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶች፡ የኢትዮጵያ ሚና ምንድን ነው? 27.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የብሪክስ እና የአፍሪካ ነጠላ ገበያ መስተጋብርን፣ አዳዲስ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እና ኢትዮጵያ በዚህ ተለዋዋጭ የንግድ አውታር ውስጥ ያላትን ሚና እንቃኛለን።

በኢትዮጵያ የሥራ ኃይል ውስጥ ያለው የተደበቀ ቀውስ፡ የሥራ መዳከም (Burnout) እና የምርታማነት ፈተና 27.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የሥራ መዳከም (Burnout) በኢትዮጵያ የሥራ ኃይል ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ፣ ድርጅቶች የሚገጥሟቸውን የሰው ኃይል አስተዳደር ተግዳሮቶችና ጤናማ የሥራ ከባቢ አየር መፍጠር የሚቻልባቸውን መንገዶች እንቃኛለን።

የአፍሪካ ነጠላ ገበያ ፈተናዎች፡ ከምዕራባውያን ምንዛሬ ጥገኝነት መላቀቅ እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እውነታዎች 27.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት»ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን ነጠላ ገበያ እውን ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶችን፣ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እውነታዎችን እና በውጭ ምንዛሬዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ሊወሰዱ ስለሚችሉ አቅጣጫዎች እንቃኛለን።

የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ዲኮሎናይዜሽን፡ አፍሪካ ለራሷ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ዓይነት ትምህርት ያስፈልጋታል? 27.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ከቅኝ ግዛት ቅርስ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ የተወላጅ ዕውቀት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ያለውን ሚና፣ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በትምህርት ማጠናከር የሚያስከትለውን ዕድል እና ትምህርት ከአፍሪካ የልማት ፍላጎቶች ጋር ማገናኘት ስለሚቻልበት መንገድ እንመለከታለን።በተጨማሪም፣ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ዕውቀትና ሳይንስን ሳትከለክል የራሷን ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና የአካባቢ ዕውቀት እንዴት በትምህርት ሥርዓቷ ውስጥ ማዕከላዊ ቦታ ማስያዝ እንደምትችል እንዳለ እንወያያለን።

የዌልነስ ኢኮኖሚ፡ ከግል ጤና እስከ የኢኮኖሚ ዕድል 23.09.2026

በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የዌልነስ ኢኮኖሚ፣ የሴቶችን ጤና እና የአካል ብቃት፣ የሀገር ውስጥ የዌልነስ ንግዶችን እና ዘርፉ ለሰው ሀብትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖረው የሚችለውን ሚና እንቃኛለን። የዌልነስ ንግዶች ከጂም እና ከአካል ብቃት ክፍሎች ባሻገር ሥራ መፍጠር፣ የስፖርት ልብስና መሣሪያ አቅራቢዎችን መደገፍ እና የአካባቢ የንግድ ሰንሰለትን ማሳደግ ይችላሉ። ታዲያ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ዝና ወደ የሀገር ውስጥ የስፖርት፣ የአካል ብቃት እና የዌልነስ ብራንዶች ሊቀየር ይችላል? እነዚህስ ከኢትዮጵያ አልፈው ወደ ሌሎች የአፍሪካ ገበያዎች ሊስፋፉ ይችላሉ?ለዚህም የአፍሮሂት ፋትነስ  መሥራች እና ማኔጂ...

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድገት፡ የመንግስት ቁርጠኝነት እና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች 16.09.2026

በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዘርፍ ፈጣን ዕድገት፣ የመንግስትን ቁርጠኝነት እና የኢኮኖሚ ምሰሶነቱን እንዲሁም እንደ እንቁጣጣሽ ያሉ ባህላዊ በዓላትን ወደ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ምርት መቀየር የሚቻልበትን ሁኔታ እንቃኛለን። ለዚህም የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ገበያ ማህበር ፕሬዚዳንት ጌታሁን አለሙ ጋር አድርገነውን ቆይታ እናቀርባለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ።

አፍሪካ የፈጠራ ባለጸግነቷን እንዴት ትቆጣጠራለች? 08.09.2026

አፍሪካዊ ሙዚቃ እና የባህል ኢንዱስትሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደጉ ቢመጡም፣ እውነተኛ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራሳችንን ድምፅ እና የፈጠራ ሥራዎች ያለ የውጭ ማሻሻያ በራሳችን መንገድ መቅረጽና መቆጣጠር ወሳኝ ነው። “መጀመሪያውና ትልቁ ነገር አፍሪካውያን የራሳቸውን ድምፅ በመፍጠር ሂደት ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖራቸው ይገባል፤ ምክንያቱም አፍሪካዊው የራሱን ታሪክ ያለምንም የውጭ ማሻሻያ በራሱ መንገድ መናገር ይችላልና። ሙዚቃው በሌላ አካል ሲዘጋጅ ግን፣ እንደምናውቀው፣ አንዳንድ የራሱ ክፍሎችን ሊያጣ እና ለሌሎች ፍላጎት ብቻ የተመቻቸ ሊሆን ይችላል።” — ኪሩቤል አሰፋ ከበደ ፣ ኢትዮጵያዊ ባለብዙ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫ...

ዓለም ወደ ደቡባዊ ዓለምና ምሥራቅ እያዘነበለች ነው ፦ ለአፍሪካ ይዞት የሚመጣዉ ዕድል ምንድን ነው ? 03.09.2026

የዓለም ኢኮኖሚ እየተለወጠ ነው። የኢኮኖሚ እና የንግድ ኃይል ከባህላዊ ማዕከላት በመውጣት ወደ እስያና ወደ ተለያዩ የዓለም ክልሎች እየተስፋፋ ነው። ሩሲያ የሩቅ ምሥራቅ ክልሏን ከእስያ-ፓሲፊክ ጋር ለማገናኘት እየሰራች ሲሆን፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ እና ሌሎች የእስያ ኢኮኖሚዎችም በአዲሱ የዓለም ኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ የበለጠ ሚና እየወሰዱ ነው። ይህም እ.ኤ.አ ከመስከረም 1 እስከ 4 2026 በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ - የምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም በሰፊው እየተነሳ ነው፡፡  “በብዙ ማዕከላዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን፣ አገራት ራሳቸውን ወደ ዓለም ኢኮኖሚ ማዕከል ማምጣት አለባቸው፤ ይህም በመከፋፈል ሳይሆን በትብብር፣ በመቀና...

ከብሉዝ እስከ ኢትዮ-ጃዝ፡ የሙዚቃ ታሪክና የአፍሪካ ድምፅ 02.09.2026

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ ዓለም አቀፍ የብሉዝ ሙዚቃ ቀንን አስመልክተን፣ ከብሉዝ እስከ ኢትዮ-ጃዝ ያለውን የሙዚቃ ትስስር፣ ታሪክ እና ባህላዊ ተፅዕኖ ከታዋቂው ፒያኖ ተጫዋችና አቀናባሪ ሳሙኤል ይርጋ ጋር እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ በአዲስ አበባ የተካሄደውን "የዓለም ሕዝቦች ጉባኤ፡ አፍሪካ" በመመልከት፣ አፍሪካ የራሷን እጣ ፈንታ፣ የሀብት ሉዓላዊነት እና የጋራ የወደፊት ዕድል እንዴት መቅረጽ እንደምትችል ከምሁራን ጋር እንወያያለን። ሙሉውን መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡

ከሆርሙዝ እስከ ብሪክስ፡ የኢራን ውጥረት የዓለምን የኃይል የበላይነት እንዴት እየቀየረው ነው? 20.08.2026

«አሜሪካ በኢራን ላይ በርካታ ሙከራዎችን አድርጋለች፣ ነገር ግን የኢራንን ኃይል መቆጣጠር አልቻለችም... ጦርነቱ እየሰፋ ከሄደ እና ኢኮኖሚው ጥያቄ ውስጥ ከገባ፣ አሜሪካ አሁን እውነተኛ ተፅዕኖ ላላቸው ብሪክስን ጨምሮ ለተቀናጁ ሀገራት እጇን ለመስጠት ልትገደድ ትችላለች።» ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር መሐመድ ኢሳ ሹራላ (ዶ/ር) ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በሆርሙዝ ሰርጥ ያለው የጂኦፖለቲካ ውጥረት በአፍሪካ የኢነርጂ ደህንነትና ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚፈጥረውን ዕድ...

የኮንፈረንስ ቱሪዝም፡ አፍሪካ ከ3.1 ትሪሊዮን ዶላር ዘርፍ እንዴት ትጠቀም? 10.08.2026

"የዝግጅቶች የጉባኤ ወይም MICE ቱሪዝም በመባል የሚታወቀው ዘርፍ በ180 ሀገራት ውስጥ በተደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች ወደ 1.6 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አዘዋውሯል፤ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ገቢም አስገኝቷል። ስለዚህ በቢሊዮኖች ሳይሆን በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ይህም በቀጥታ ሽያጭ ብቻ የሚገኝ ነው። ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ሲጨምር ወደ 3.1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ይደርሳል። ይህም በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ሲሰላ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። በእርግጥ ይህ ኢንዱስትሪ ራሱ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ስለዚህ ከአንድ ሀገር ኢኮኖሚ አንፃር...

የኢንሹራንስ ዘርፍ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ጽናት ያለው ወሳኝ ፋይዳ 05.08.2026

በአብዛኛው የኢንሹራንስ አገልግሎት ከጉዳት በኋላ የሚደረግ ማካካሻ ተደርጎ ይታሰባል። ነገር ግን የኢንሹራንስ ዘርፍ ከዚህም በላይ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ምሰሶ በመሆን ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት እና አገሮች ከድንገተኛ አደጋዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና አለው። "በአፍሪካ ያለው የኢንሹራንስ ዘርፍ አሁን ካለበት የካሳ ክፍያ ብቻ ላይ የሚያተኩር አቀራረብ ወደ የጽናትና የመቋቋም አቅም ኢንቨስትመንት የሚያተኩር ሥርዓት መሸጋገር ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የአስተሳሰብ ለውጥ በጣም ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ተቋማት ይህንን የጥበቃ ክፍተት ለመሙላት አዳዲስ የንግድ...

ዘላቂና ፍትሐዊ የልማት መመዘኛዎች ፦ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ዕድገቷን እንዴት ታረጋግጥ ? 05.08.2026

በዓለም አቀፍ ደረጃ 'ኢኤስጂ' (አካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና አመራራዊ) ዘላቂ የመልካም ስራ መመዘኛዎች ከተለመደው የማህበራዊ ኃላፊነት ባለፈ የኢንቨስትመንት ፍሰትን፣ የብድር አቅርቦትንና የንግድ ተወዳዳሪነትን የሚወስኑ ወሳኝ መስፈርቶች እየሆኑ መጥተዋል። አፍሪካ የአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠናን እውን ለማድረግና የኢንዱስትሪ ልማቷን ለማፋጠን በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህ መስፈርቶች ተጨማሪ የፋይናንስና የአቅም ጫና የሚፈጥሩ እንዳይሆኑ ስጋት አለ። "አፍሪካውያን የአካባቢ የበካይ ጋዝ ልቀት ምንጮች ባንሆንም፣ የ'ኢኤስጂ' መመዘኛዎችን ከእኛ አህጉራዊ እና ማህበራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር አጣጥመን መጠቀም ይኖርብናል። ለአውሮፓ የ...

ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለት፡ አፍሪካ ሀብቷን ውስጣዊ አቅም እንዴት ማቆየት ትችላለች? 30.07.2026

አፍሪካ ለዓለም ገበያ በርካታ ጥሬ ዕቃዎችን የምታቀርብ ቢሆንም፣ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶችም ጥገኛ ናት። አሁን ላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሲመሠረት፣ ትኩረቱ ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለቶች ግንባታ እና የሎጂስቲክስ አውታሮችን በማጠናከር ሀብቱ በአህጉሪቱ እንዲቆይ ማድረግ ላይ እየተሸጋገረ ይገኛል። " አብዛኛዎቹ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከአፍሪካ አይደሉም፤ ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው የገቢና የወጪ ንግድ ጭነት የሚከናወነው በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ ኩባንያዎች ነው። ይህ በወጪያችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በቁጥር ላሳያችሁ፤ ከቻይና ሻንጋይ እስከ ኢትዮጵያ ለአንድ የዕቃ መጫኛ ኮንቴነር የምንከፍለውን ክፍያ እንመል...

የሳህል ወጣቶች፣ ፋይናንስ እና ቱሪዝም፡- የአፍሪካ ዕድገት በሂደት ላይ 25.07.2026

አፍሪካ ትልቅ ወጣት ህዝብን ይዛለች፤ ነገር ግን ይህ የዴሞግራፊ ዕድል ወደ እውነተኛ የኢኮኖሚ ውጤት እንዲቀየር የፋይናንስ ተደራሽነት እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች ወሳኝ ናቸው።  "የውስጥ ሀብታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ይረዳናል። ማናቸውም ሀገር ያለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ብቻውን ኢኮኖሚውን ማሳደግ ይችላል ማለቴ አይደለም፤ ድጋፋቸው ያስፈልገናል። ነገር ግን ማድረግ ያለብን ጥገኝነታችንን መቀነስ ነው። የውጭ ተቋማትን አስተዋጽኦ ለመቀነስ ማዕድናችንን ማቀነባበር አለብን። ለምሳሌ በማሊ ከወርቅ ብቻ ብዙ ወጣቶችን ስራ ማስያዝ እና ዓላማዎቻችንን ማሳካት እንችላለን።...

የክህሎት ሉዓላዊነት፡ አፍሪካ በወጣቶቿ ችሎታ የምትገነባው መጻኢ ዕድል 18.07.2026

አፍሪካ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የአህጉሪቱ ህዝብ ከ25 ዓመት በታች ነው። ይህ ግዙፍ የሰው ኃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንዲቀየር፣ ትምህርት እና ሥልጠና ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር መጣጣም አለባቸው።  "ኢትዮጵያ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ከ70 በመቶ በላይ የሆነው ህዝባችን ከ30 ዓመት በታች ነው። መንግስት ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ኢላማ በማስቀመጥ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ይህንን ለማሳካትም በ2020 መጀመሪያ ላይ የተቋቋመውና በአሁኑ ወቅት ወጣት ከሚባሉ ተቋማት አንዱ የሆነው 'የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር' ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።" ሲሉ በኢትዮጵያ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ብሔራዊ አስተባባሪ እና የ ‘አሶሴሽን...

የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት 22.06.2026

የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ "ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል።...

ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ 08.06.2026

ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ ሥርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት አቅም እና ቁጥጥር የሚፈትን ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ለውጥ ግልጽነትን፣ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝን እና ተወዳዳሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮችን መኖር የግድ ይላል። "ገበያው በተለያዩ መንገዶች ዝግጁ መሆን እንዳለበት እናውቃለን። አንደኛው ነገር ግልጽነት እና ተገቢ የሆነ የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ነው። በዚህ ረገድ እንደ IFRS ያሉ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከ...

Escucha el podcast Continental Drift en Replaio

Radio y podcasts en una sola app - gratis y sin registro. Instálala hoy y no te pierdas el estreno

Descárgala en Google Play

Replaio no es editor de podcasts; los nombres de los programas, las portadas y el audio pertenecen a sus autores y se distribuyen a través de canales RSS públicos