Eden Teshome

Continental Drift

News EN ↓ 23 episodes

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, market...

Author

Eden Teshome

Category

News

Latest episode

Jun 22, 2026

Where to listen?

Podcasts in the app Replaio Radio Coming soon

Podcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts

Get it on Google Play Install for free Android 5M+ downloads · 4.8 rating iOS soon

Episodes

የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት 22.06.2026

የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ "ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል።...

ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ 08.06.2026

ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ ሥርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት አቅም እና ቁጥጥር የሚፈትን ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ለውጥ ግልጽነትን፣ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝን እና ተወዳዳሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮችን መኖር የግድ ይላል። "ገበያው በተለያዩ መንገዶች ዝግጁ መሆን እንዳለበት እናውቃለን። አንደኛው ነገር ግልጽነት እና ተገቢ የሆነ የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ነው። በዚህ ረገድ እንደ IFRS ያሉ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከ...

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል? 20.05.2026

"የቭላድሚር ፑቲን የቻይና ጉብኝት የዓለም ሥርዓት ከአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ-ዋልታ እየተቀየረ መሆኑን ካሳዩ ግልጽ ማረጋገጫዎች አንዱ ነው። ይህ ጉብኝት የምዕራባውያን አገራት በዓለም መድረክ ላይ የነበራቸው የበላይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው" ሲሉ ሙሉዓለም ኃይለማርያም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን ሁለት አበይት ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ፤ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቤጂንግ ጉብኝት እና ለአፍሪካ የሉዓላዊነት ጉዞ የሚኖረው ስትራቴጂካዊ ትርጉም ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ም...

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል 18.05.2026

የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጥያቄ ከማዕድን እና ከንግድ ኮሪደሮች ባለፈ፣ አህጉሪቱን የሚያስተዳድሩ መሪዎች በሚቀረጹበት የዕውቀት ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የተራራ ብስክሌት ውድድር በማስተናገድ፣ ከተማን እንደ ዲፕሎማሲ እና የ'ሶፍት ፓወርን' መድረክነት እየተጠቀመችበት ትገኛለች። "አፍሪካውያን የራሳቸውን ሥርዓተ-ትምህርት ማዘጋጀት አለባቸው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር በመካከላችን ጠንካራ አህጉራዊ ግንኙነት የለንም። ስለዚህ ይህንን ግንኙነት መገንባት አለብን። ይህ ጉባኤ የአፍሪካ ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ችግሮች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ...

"ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ 06.04.2026

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው አለመረጋጋት—ከአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ እስከ ቀይ ባሕር የጸጥታ ስጋት በአፍሪካውያን ማዕድ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። እንዴት ? "እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ በዕርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው። [...] ይህ ለእኛ ሌላ የዝግጅት ጊዜ ሊሰጠን ይገባ ነበር። እውነቱን ለመናገር፣ የዓለም ሥርዓት ወዴት እየሄደ እንደሆነ በጥንቃቄ ብንከታተል ኖሮ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችል ነበር።" — ሲሉ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረ...

የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች 26.03.2026

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዓለምን የኢነርጂ ፍሰት እና ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፍ እየቀየረ ነው ። በተለይም በሆርሙዝ የባህር በር ላይ የሚፈጠር አለመረጋጋት በአፍሪካ የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው ። "አፍሪካ አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር ተጋላጭነቷን እና ጥገኝነቷን ለመቀነስ መሞከር ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ምሳሌ ናት። ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአንድ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮቿን በማባዛት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታለች።" ሲሉ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተ...

የባህረ ሰላጤው የኢነርጂ ቀውስ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት 16.03.2026

በመካከለኛው ምስራቅ የሚከሰት ግጭት እንዴት በአፍሪካውያን የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ በትራንስፖርት እና በምግብ ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥራል? የዓለም የነዳጅ ገበያ መናጋት አፍሪካ የራሷን የኢነርጂ መሠረተ ልማት እንድትገነባ እና በውጭ ገበያ ላይ ያላትን ጥገኝነት እንድትቀንስ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል? "በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ የሚታየው ከፍተኛ መዋዠቅ፣ በተለይም እንደ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ባሉ ማዕቀፎች ውስጥ ጠንካራ የአህጉር አቀፍ የኢነርጂ ትብብር እንዲኖር እንደ ማነቃቂያ ሊያገለግል ይችላል። እዚህ ላይ አንድ ዋና ነጥብ መጥቀስ እንችላለን፤ ምክንያቱም ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መ...

መካከለኛው ምስራቅ ፦ የዓለም አቀፍ የሕግና ሥርዓት ዕጣ ፈንታ ነጋሪ 06.03.2026

በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለው ቀውስ የአንድ ቀጠና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት ታላቅ ፈተና ነው። በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን እና የሉዓላዊነት መርሆዎችን አደጋ ላይ ጥሏቸዋል። "ሩሲያና ቻይና ሁነቶቹን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውና ከትዕይንቱ በስተጀርባ የራሳቸውን ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው በጣም ግልጽ ነው። ከሚታየው ነገር ባሻገር ጠልቀን ማየት አለብን። በአንድ በኩል በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኢራን መካከል በመካከለኛው ምስራቅ እየተከሰተ ባለው የፖለቲካ ቀውስ ቻይና እና ሩሲያ በዝምታ...

የዓድዋ ድልና የዘመኑ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት፦ ያልተቋረጠው የሉዓላዊነት ትግል 03.03.2026

የዓድዋ ድል ከጦር ሜዳ ስኬት በላይ፤ አፍሪካውያን የሉዓላዊነት ድርድር የማይደረግበት መሆኑን ለዓለም ያወጁበት የታሪክ ምዕራፍ ነው። ዛሬስ ሉዓላዊነት ሲባል ግዛትን ከመጠበቅ ባለፈ የኢኮኖሚ ፣ ባህል ጥንካሬን እና በሌሎችም ሉዓላዊ ነን ? ወይስ አሁንም በ"ስልጣኔ" ስም በሚቀርቡልን የዲፕሎማሲ ወጥመዶች ውስጥ ተይዘናል? "ጤነኛ አእምሮ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚያ የአውሮፓውያን ዲፕሎማሲ ውስጥ እንዳይዘፈቅ። እንዳትዘፈቁ! ምክንያቱም አባቶቻችን በምኒልክ ዘመን ያለ ጫማ፣ ያለ ሱፍ ልብስ፣ ያለ ከረባት የአውሮፓውያንን፣ የምዕራብ አውሮፓውያንን ተንኮል ማየት ይችሉ ነበር። እኛ ግን በዚህ ሁሉ ዲግሪ፣ በዚህ ሁሉ ሱፍ እና ዘመናዊ መኪ...

ዓድዋ:- የሉዓላዊነት መሠረትና የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አቀጣጣይ 02.03.2026

የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የተመዘገበው የዓድዋ ድል ጣሊያንን በጦር ሜዳ የማሸነፍ ጉዳይ ብቻ አይደለም።አፍሪካውያን በራሳቸው መደራጀት እና ማሸነፍ እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት የታሪክ ምዕራፍ ጭምር እንጂ። ዛሬም ግን የሉዓላዊነት ጥያቈ መልኩ ብዙ ሆኖ እያየነው ነው። "አፍሪካ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳትጠይቅ በጠንካራ አቋም ወደ ድርድር ጠረጴዛው መምጣት አለባት። እነዚህን ሐሳቦች ስላስተዋወቅን ብቻ ‘ባህላዊ’ ጉዳዮች ሊባሉ አይገባም፤ ምክንያቱም ይህ ማንነታችን በመሆኑ ወሳኝ ነው።[...]‘ጭራው ውሻውን እንዲያወዛውዝ’ መፍቀድ የለብንም።" ሲሉ ፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ለስፑቲክ አፍሪካ ተናግረዋል...

አዲሱ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ንቅናቄ፡ የሳህል ቀጠና፣ ሩሲያ እና የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ፍጻሜ 04.02.2026

ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በምዕራባውያን ላይ ያነሱት የሉዓላዊነት ጥያቄ የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካ ቀይሮታል። ለዘመናት "ፀረ-ሽብር" በሚል ሽፋን የተካሄደው የሀብት ዘረፋ እና ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ፣ ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ሞስኮ አዙረዋል። ለመሆኑ ይህ የሽግግር ወቅት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት እና ለባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓት ምን ትርጉም አለው? " የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የሚወሰነው በሩሲያና በአፍሪካ መሪዎች ነው። እና ይህ መሰረታዊ ነገር ነው። የሁለቱ ማለትም ሩሲያ እንደ አንድ ሀገር፣ አፍሪካ እንደ ብዙ ሀገር—የሚሰጡት፣ መሪዎቻቸው የሚወስኑት ነገር ወደፊት የሁለቱን ግንኙነት... የሚወስን ይመስለኛል።" — ፕሮፌሰ...

የገንዘብ ህትመት በሀገር ውስጥ፡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አዲሱ ምዕራፍ 28.01.2026

ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ ኖት በሀገር ውስጥ የደረሰችው ውሳኔ፣ ከውጭ ኩባንያዎች ጥገኝነት የመላቀቅ እና የገንዘብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ውሳኔ ከዶላር ጥገኝነት ለመውጣት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በሌላ በኩል Make Africa Borderless Now ''አሁን አፍሪካን ንብር የለሽ እናድርጋት ንቅናቄ'' አህጉሪቱን ትስስር ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው። "የራስን ገንዘብ ማተም ካልተቻለ ፣ በራስ ገንዘብ መበደር ፣ መገበያየት እና መቆጠብ ካልተቻለ ፤ ሉዓላዊነት እንደ ሀገር አደጋ ላይ ይወድቃል።[...] የራስን ገንዘብ ማተም የራስን ሀገር በራስ አቅም ከማስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ቁር...

የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ነፃ ንግድ ቀጣና ፡- ኢትዮጵያ የአፍሪካ እድገትና ሉዓላዊነት ማዕከል የመሆን ውጥን 22.01.2026

ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ለማንቀሳቀስ ስታቅድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ የአፍሪካን የአቪዬሽን ታሪክ የሚቀይር ግዙፍ የኤርፖርት ፕሮጀክት ጀምሯል። እነዚህ የአየር እና የየብስ መሰረተ ልማቶች ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና ለአፍሪካ ትስስር ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ነው፣የኢኮኖሚ ዞኖችም ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ። "ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከላዊ ሚና መጫወት አለባት። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ይረዱናል።[...] የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን በመጠቀም ያለንን አቅም ወደ...

የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ እንቅስቃሴ በአፍሪካ፡- 'ኢትዮ ፔይ' ከዶላር ጥገኝነት ነጻ ለመሆንና ለፋይናንስ ሉዓላዊነት 15.01.2026

የ'ኢትዮ-ፔይ' መጀመር ኢትዮጵያ በዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥናል። በሌላ በኩል፣ ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ብርሃን ባልታደሉበት አፍሪካ፣ የኢነርጂ አቅርቦትንና ብቃትን ማሳደግ ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል። "በዶላር ላይ ጥገኝነት አይኖርም... ቴክኖሎጂው ክፍያዎች በቀላሉ እንዲተላለፉ ያስችላል። ነገር ግን ወደ ተግባራዊ ትግበራው ስንመጣ፣ የሕግ ማዕቀፍ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል። በህግ በኩል፣ ሁለቱ ሀገራት ክፍያው እንዴት እንደሚፈጸምና የገንዘብ ምንዛሪው እንዴት እንደሚሆን መስማማት አለባቸው።" ሲሉ የኢት-ስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡...

ፋይዳ በለውጥ መንገድ፡ ዲጂታል ማንነት፣ የመረጃ ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ 13.01.2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ "ፋይዳ" ከሙከራ ደረጃ አልፎ አሁን ላይ መላውን ሀገራዊ ሥርዓት እያስተሳሰረ ይገኛል። ባንኮችና የክፍያ ሥርዓቶች ከፋይዳ ጋር መገናኘታቸው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ የዜጎች የግል መረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ስልቶች እየተተገበሩበት ነው ። "የግል መረጃችሁ በትላልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች እጅ ሆኖ በየትኛው የሕግ ሥልጣን ሥር እንደሚገኝ እንኳን ማወቅ[አይቻልም]፤ ምክንያቱም ይህ የኩባንያዎች ምስጢር ነው። ፋይዳን በሚመለከት ግን አንድ ያደረግነው መልካም ነገር የመረጃ ቅነሳ ወይም 'ዳታ ሚኒማይዜሽን' የተሰኘውን መርህ መከተል ነው ፤ ስለዚህ ስለ አንድ...

ኃይል፣ ወደብ እና ቅርስ፡- የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ እና የሉዓላዊነት ትግል 02.01.2026

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ናቸው። እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችው ዕውቅና፣ የሁቲ አማጽያን ዛቻ እና ከእስራኤል ጋር የገብበት ፍጥጫ ቀጥሏል፡፡ በሌላ በኩል፣ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ከብሪታኒያ ሙዚየም "በብድር" ሳይሆን በክብር የመመለስ ትግል የአፍሪካዊያን ሌላ ሜዳ ሆኗል። "እስራኤል ለሶማሌላንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ እና አስፈላጊነት ትኩረት እየሰጠች ነው፤ ምክንያቱም ሁቲዎች በእስራኤል ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው። ስለዚህ ይህ አንዱ ጉዳይ ነው።" ሲሉ  የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ...

የአፍሪካ የሉዓላዊነት ትግል፡ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የአስተሳሰብ ነጻነት 30.12.2025

አፍሪካ በአሁኑ ወቅት የዓለም የኃይል ሚዛን በሚቀያየርበት ባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ የራሷን ድምፅ ለማሰማት እና የፖለቲካ ተጽዕኖዋን ለማሳደግ እየጣረች ትገኛለች። "እንደሚታየው አፍሪካ እና እስያ በተለይም ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ነው። በትምህርት ረገድም ሰፊ ግንኙነት አለን። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አፍሪካ ውስጥ ከሩሲያ ትምህርትን እና ሌሎች ድጋፎችን ለማግኘት የሚያስችሉ የዳታ ማኔጅመንት ዕቅዶች አሉን።" ሲሉ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ይመር አሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያላትን ስል...

የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ምርት አዲስ መልክ 18.12.2025

የኢትዮጵያ የቅመማ ቅመም ዘርፍ ባለው ከፍተኛ እምቅ አቅም ልክ ተገቢውን ዋጋ አላገኘም። በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስፈን በደቡብ-ደቡብ ትብብር እና በሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ላይ እየሰራች ነው። የጓሮ እርሻዎች ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቅድስት አምዴ "እኛ ጋር ወደ 23 የሚደርሱ የምግብ ቅመሞች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ አንዳንዶቹን አናውቃቸውም። ወደ 800 የሚጠጉ የመድኃኒት ዕፅዋትም አሉን። ይህ በጣም ሰፊ የልዩ ልዩ ዝርያዎች ሀብት ነው። በየቦታው አይገኝም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ዕድል አለ ብዬ አስባለሁ።" ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች፡፡ በዛሬው የ...

ኃይል፣ ትብብር እና ምርት፡ የአፍሪካ አዲሱ የሉዓላዊነት መንገድ 15.12.2025

"[...] የብሪክስ ቁልፍ መርህ የሉዓላዊነትን ማስከበር፣ የሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ነባራዊ እውነታዎችን ማክበር ነው። በኢነርጂ ዘርፉም ቢሆን የምናደርገው ትብብር ይህንን ያገናዘበ ነው።" ሲሉ የሩሲያ የኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ሶስት የተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮችን እንመለከታለን በቀዳሚነ የብሪክስ የኢነርጂ ትብብር ለኢትዮጵያ ምን ይዞ መጥቷል ፣ ለአፍሪካ የኢነርጂ ሉዓላዊነትስ ምን ማለት ነው ስንል የሩሲያ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካይ አናስታሲያ ሺሮኮግራድ አነጋግረናቸዋል፡፡ በሁለተኛው ክፍል ከታህሳስ 2 እስከ 3 በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአ...

ከፖሊሲ አውጪነት ወደ ፖሊሲ ተቀባይነት :- በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የተደቀኑ ፈተናዎች በአፍሪካ 19.11.2025

አፍሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለእዳ ክፍያ በማውጣት፣ ከጤናና ትምህርት በለጠ የፋይናንስ ጫና ውስጥ ወድቃለች ። " አለምዓቀፉን የገንዘብ ተቋም በተቀበልክ ጊዜ፣ የማክሮ ፖሊሲህን በሙሉ አሳልፈህ ትሰጣለህ። እኔ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነኝ፤ ሁሉንም ፖሊሲዎች አውቃለሁ። ከአይ.ኤም.ኤፍ. ጋር ስምምነት ስትፈጽም፣ የማክሮ ፖሊሲ የመወሰን አቅምህን በጠቅላላ ታጣለህ። የፊስካል ፖሊሲ ታጣለህ፤ የገንዘብ ፖሊሲ ታጣለህ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ታጣለህ። በመሠረቱ ራስን በራስ የማስተዳደር አቅምህን ታጣለህ።" ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተ...

ፍትህ በችሎት ላይ : የአፍሪካ ድምፆች ከአለምዓቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባሻገር 14.11.2025

ፍትህ የውጭ ተጽዕኖን ሲከናነብ ፣ ማን ይዳኛል ? ማንስ ደግሞ በነጻ ይለቀቃል? '' የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምስረታን ስንመለከት፣ አብዛኞቹ ለክስ የሚቀርቡ ጉዳዮች የአፍሪካ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ለጦርነቶች አስተዋጽኦ የሚያደርጉት አብዛኞቹ ሀገራት ግን የአፍሪካ ሀገራት አይደሉም። ስለዚህ እንደ አፍሪካውያን የዉስጥ ጉዳዮቻችንን የምናይበት የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምናቋቁምበት ጊዜ አሁን እንደሆነ አምናለሁ። ራሳቸውን ከአይሲሲ ቻርተር ያገለሉትን የአፍሪካ ሀገራትንም ማድነቅ ወይም ማመስገን እወዳለሁ '' ስትል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐ...

የባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የዉዝዋዜዎች ኃይል - ማንነትን ለመግለጥና ለምጣኔ ኃብታዊ እድገት 14.11.2025

ኢትዮጵያ የብዝሃ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ተፈጥሮ ካደላት መገለጫዎቿ እኩሌታ ብዙኃ ቋንቋና ባህል ያላት መሆኑ የልዩ መልካነቷ ማሳያ ነው፡፡ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎቿም ትናንቷን የሚዘክሩ ፣ የነገን መልክ ዛሬ ላይ ለመቅረጽ በብዙ የሚጥሩ ናቸው፡፡ እንዴት ? “ አንደኛ የስራ እድል ምንጭ ይሆናል። የሚጫወቱ ሰዎች ቢበዙ የስራ እድል ነው ብዙ ሙዚቀኛ በዚህ ሙያ ላይ ያሉ ሙዚቀኞች እንደመኖሪያቸው ይሆናል። ሁለተኛ ደግሞ የሀገር ሀብት ነው። እንደ ሀገርም መሸጥ ይቻላል ሙዚቃን መሸጥ ይቻላል ፣ በነገራችን ላይ ያው [ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር] በተለያየ መንገድ ገቢ ማግኘት አለብን ብዬ አስባለሁ። እና አንደኛው ሙዚቃ ነው...

መጭውን ጊዜ መቅረጽ፡ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ፈጠራ ኢኮኖሚ 28.10.2025

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ170 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውጪ ለምታስገባው የእንጨት ዉጤቶች ወጪን ታወጣለች ።  [...]መንግሥት የእንጨት ሥራ ውጤቶች ከውጭ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ቢያንስ ለመቀነስ ዉሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በውስጡ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ምክንያት ይህ ውሳኔ ተሰርዟል፣ የእንጨት ውጤቶች እንደገና ለማስገባት ተፈቅዷል። ነገር ግን ክልከላው በተጣለበት አስር ወራት ጊዜ ውስጥ እንኳን በሀገር ውስጥ ገበያው ፍላጎት ምክንያት ብዙ ሀገር በቀል የእንጨት ሥራ ውጤት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየአቅጣጫው መጥተው አይተናቸዋል።” ሲሉ የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕ...

Listen to the Continental Drift podcast in Replaio

Radio and podcasts in one app - free, with no sign-up. Install today and do not miss the launch

Get it on Google Play

Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.