DW

በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle

News AM ↓ 50 Folgen

ሳይንሳዊ እና ስነ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እና ለህብረተሰቡ ያላቸቸውን ጠቀሜታ ይመለከታል።

Autor

DW

Kategorie

News

Neueste Folge

8. Jul 2026

Wo hören?

Podcasts in der App Replaio Radio Bald verfügbar

Podcasts kommen bald in die App. Installiere sie jetzt und erlebe als Erster einen ganz neuen Blick auf Podcasts

Bei Google Play herunterladen Kostenlos installieren Android 5 Mio.+ Downloads · Bewertung 4,8 iOS bald

Folgen

እየተባባሰ የመጣው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ጥቃት 04.03.2026

በኢትዮጵያ ዲጂታል ክኖሎጂ አጠቃቀም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እያደገ መጥቷል። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሳትፎ ደግሞ 17.7% ደርሷል። በዚያው ልክም ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ጨምሮ በበይነመረብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚያሳድሩ ጎጅ ባህሪያትንም እንዲስፋፋ እና በስፋት ሊሰራጩ የሚችሉባቸውን ምቹ ሁኔታም ፈጥሯል።

እየተባባሰ የመጣው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ጥቃት 04.03.2026
ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያስችሉ መተግበሪያዎች 25.02.2026

እነዚህ መተግበሪያዎች ኢንተርኔት ፈፅሞ በሌለባቸው ወይም ደካማ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ባላቸው አካባቢዎችም ያለ ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያግዙ ናቸው። መተግበሪያዎቹ በተፈጥሮ አደጋዎች የኃይል መቆራረጥ ሲኖር፣ ኢንተርት ሆን ተብሎ በሚዘጋበት ወይም ተደራሽነት በሌለበት ቦታ የሰዎች መስተጋብር ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋሉ።

አሳሳቢው የልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም 18.02.2026

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘትን ለረጅም ጊዜ መመልከት፤ ባህሪን እና የአእምሮ ጤናን በዘላቂነት ሊጎዳ ይችላል።ጉዳቱ በተለይም እድገቱ ባልተጠናቀቀ የልጆች አእምሮ ላይ በመሆኑ ደግሞ የሚመጣው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።ይህ ያሳሰባቸው ሀገራት ልጆጆን ከዲጅታል መድረኮቹ የሚያግዱ ህጎችን እያወጡ ነው።

አሳሳቢው የልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም 18.02.2026
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለምን ይሰበስባሉ? 11.02.2026
ብራይት ኬን፡ ዓይነስውራንን በድምፅ የሚመራው ቴክኖሎጂ 04.02.2026
ብራይት ኬን፤ዓይነስውራንን በድምፅ የሚመራው ቴክኖሎጂ 04.02.2026

ብራይት ኬን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የፈጠራ ስራ ባልተስተካከሉ መንገዶች እና በተጨናነቁ ጎዳናዎች ላይ እንቅፋቶችን እና አደጋዎችን ቀድሞ ለማስጠንቀቅ ያግዛል።ይህ መሳሪያ የ«አልትራሶኒክ ሴንሰሮች»ን በመጠቀም የተገነዘበውን አደጋ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በድምጽ ያሳውቃል።በዚህም አይነስውራንን ከአደጋ ያስጠነቅቃል አቅጣጫም ይመራል።

የዲጅታል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተከታዮቻቸው ላይ ያላቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ 21.01.2026

የቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም እና የፌስቡክ ዘመን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከተዋናዮች፣ ስፖርተኞች ወይም ከፖለቲካ መሪዎች - በተለይም በወጣቶች ዘንድ የበለጠ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የሚያቀርቧቸው ይዘቶች ጠቃሚ እና በሳል ዕይታ እና አስተሳሰብ የታከለበት ካልሆነ፣ተፅዕኗቸው በሚከተሏቸው ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

የኦንላይን ግብይት ስጋቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች 14.01.2026

ማሽን ሰዎችን ተክቶ እንዲሰራ የሚያደርገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዲጅታል መንገድ ግብይቶችን ለመፈፀም አገልግሎት ላይ ይውላል። ቴክኖሎጂው የኦንላይን ግብይቶችን ምቹ እና በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ አቅርቦቶችን ለማግኘት የሚያግዝ ቢሆንም፤ የግል መረጃ ደህንነት፣ ማጭበርበር ፣ የቁጥጥር ወይም የግልጽነት ችግር ስጋቶች ናቸው።

በማንጎ ተክል በሽታ ላይ የተደረገው ምርምር 17.12.2025

በአሶሳ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘውን የማንጎ በሽታን ለማከም የተደረገው ጥናት ለውጥ ማስገኘቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና ሌሎች አጋሮች ጋር ለሁለት ዓመታት በተደረገው ጥናት በአሶሳ በሁለት ቦታዎች ላይ በሽታውን በማከም ተጨባጭ ለውጥ መታየቱን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኒዎሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር አብዱልሙሲን ሀሰን አመልክተዋል፡፡ ጥናቱ አብዛኛውን የገቢ ምንጫቸው በማንጎ ምርት ላይ ያደረጉት አርሶ አደሮችን ችግር እንደሚፈታም አክለዋል፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለምን አሳሳቢ ሆነ? 26.11.2025

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፎልከር ቱርክ ሰሞኑን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።ኮሚሽነሩ እንዳሉት በተለይም ጀነሬቲቭ ኤአይ ቁጥጥር ካልተደረገበት «ራንከንስታይን ሞንስተር» እየተባለ የሚጠራውን እኩይ ወይም በተለምዶ «ጭራቅ» የምንለው አይነት ገፀባህሪ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዕድል እና ፈተና በአፍሪቃ 19.11.2025

ሰውሰራሽ አስተውሎት በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው።ቴክኖሎጂው ትምህርትን ግላዊነት በማላበስ፣ በቂ አገልግሎት ለሌላቸው ተማሪዎች ተደራሽነትን በማሻሻል በአፍሪካ በትምህርት ላይ በጎ ተጽእኖ እያሳደረ ነው።ያም ሆኖ ቴክኖሎጂውፈተናዎችም አሉት።ባለሙያዎች ፈተናዎቹን ለመሻገር ቴክኖሎጂው የሚገዛበት ፖሊሲዎች ማውጣትን ይመክራሉ።

የዓይን ብርሃንን ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ቴክኖሎጂ 12.11.2025

የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተመራማሪዎች፤ የእስፒል ራስ መጠን ያላት በጣም ትንሽ ቁስ (ቺፕ) ሬቲና በሚባለው የዓይን ክፍል ውስጥ በመቅበር የዓይን ብርሃንን ለመመለስ ያስችላል የተባለ ህክምና ላይ ሙከራ አድርገዋል። በአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ፣ ኔዘርላንድ እና ጣሊያን በተደረገ ሙከራ ተስፋ ሰጪ ውጤት መገኘቱንም ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።

የዓይን ብርሃንን ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ቴክኖሎጂ 12.11.2025
የኤሎን ማስክ ግሮክፒዲያ ምን የተለዬ ነገር ይዞ መጣ? 05.11.2025

ቱጃሩ ኤሎን ማስክ፤ በቅርቡ ግሮክፔዲያ ተብሎ የሚጠራ በሰውሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረተ አዲስ የበይነመረብ ኢንሳይክሎፔዲያ ይፋ አድርጓል። ግሮክፔዲያ በጎርጎሪያኑ ባለፈው ጥቅምት 27 ቀን 2025 ይፋ የተደገ ሲሆን፤በአሁኑ ጊዜ 900,000 የሚጠጉ መጣጥፎችን በውስጡ ይዟል።ለመሆኑ አዲሱ ዲጅታል መድረክ ከዊኪፒዲያ በምን ይለያል?

የኤሎን ማስክ ግሮክፒዲያ ምን የተለዬ ነገር ይዞ መጣ? 05.11.2025
በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሰተኛ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት እንለይ? 29.10.2025

በሰውሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሚፈጠሩ ሀሰተኛ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው።በተለይ ዲፕፌክ የሚባለው ዘዴ ሰዎች ያልተናገሩትን አስመስለው የሚናገሩ፣ያላደረጉትን ድርጊት የሚፈጽሙ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፍጠር ይውላል። ለመሆኑ እነዚህ ይዘቶች ከእውነተኛዎቹ እንዴት መለየት ይቻላል?

የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች 22.10.2025

ከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።በምትኩ በሳተላይት እና እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች ስርጭቱን ይቀጥላል።ያም ሆኖ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔው የሚጎዳ ነው ተብሏል።

የ2025 የኬሚስትሪ እና የፊዚክስ የኖቬል አሸናፊ ግኝቶች 15.10.2025
የ2025 የኬሚስትሪ እና የፊዚክስ የኖቬል አሸናፊ ግኝቶች 15.10.2025

የዘንድሮው የኖቬል ሽልማት በኬሚስትሪ ዘርፍ ተፈጥሯዊ የብረት ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ምርምር ላደረጉት ሶስት ሳይንቲስቶች ተሰጥቷል።ይህ ግኝት ብክለትን ለመቀነስ፤በረሃማ በሆኑ አካባቢዎች እርጥበታማ አየርን በመጭመቅ ዝናብ እንዲኖር ለማድረግ፣ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።በፊዚክስ ዘርፍ ደግሞ የኳንተም ሜካኒካል መተላፊያ አሸናፊ ግኝት ሆኗል።

ኢትዮጵያ የኒዩክሌር ኃይል ማመንጫ ያስፈልጋታልን? 09.10.2025

የኑክሌር ኃይል ለአዳጊ ሀገራት ዕድሎችን እና ጉልህ ተግዳሮቶችን አካቶ የያዘ ነው።የኑክሌር ሃይል ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመደገፍ እና ከካርቦን ነፃ የሆነ አስተማማኝ ኃይል ለማግኘት ይረዳል ። ነገር ግን ማብላያውን ለመገንባት ከፍተኛ ወጭ ይጠይቃል። የሕግ ማዕቀፎችን ፣ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲሁም ትልቅ እና የተረጋጋ የኤሌክትሪክ መረቦችን ይፈልጋል።

ኢትዮጵያ የኑክሌር ሃኃል ማመንጫ ያስፈልጋታልን? 08.10.2025
የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን? 01.10.2025

ስለ ጠፈር ቴክኖሎጂ ሲነሳ ብዙ ጊዜ የሚታሰበው ስለጨረቃ እና ማርስ ጉዞ ነው። ከዚህ አኳያ ቴክኖሎጂው በድህነት እና በኋላ ቀርነት ስማቸው ተደጋግሞ ለሚነሳው የአፍሪቃ ሀገራት ቅንጦት ተደርጎ ይታያል።እውን የጠፈር ቴክኖሎጂ ለአፍሪቃ ቅንጦት ነውን?

የአውሮፓ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ከስራ ያስተጓጎለው የሰሞኑ የሳይበር ጥቃት 24.09.2025

ካለፈው አርብ ምሽት ጀምሮ በአውሮፓ ታላላቅ አውሮፕላን ማረፊያዎች የመንገደኞችን የመግቢያ ፍተሻ የሚከውኑ የዲጅታል ስርዓቶች ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል።በሂትሮው፣በርሊን እና ብራስልስ አየር ማረፊያዎች የደረሰው ይህ የሳይበር ጥቃት በመያዣነት ወይም በ«ራሰምዌር» የተከሰተ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቋል።

Höre den Podcast በሳይንስ እና ቴክኒክ ላይ ያተኩራል። | Deutsche Welle in Replaio

Radio und Podcasts in einer App - kostenlos und ohne Anmeldung. Installiere sie noch heute und verpasse den Start nicht

Bei Google Play herunterladen

Replaio ist kein Herausgeber von Podcasts; die Namen der Sendungen, Cover und Audioinhalte gehören ihren Autoren und werden über öffentliche RSS-Feeds verbreitet