DW

የዓለም ዜና

News AM ↓ 226 episoder

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

Husk at besøge podcastens hjemmeside og støtte skaberen: www.dw.com

Forfatter

DW

Kategori

News

Podcastens hjemmeside

www.dw.com

Seneste episode

12. nov. 2026

Hvor kan du lytte?

Podcasts i appen Replaio Radio Kommer snart

Podcasts kommer snart til appen. Installer nu, og vær den første til at se en helt ny tilgang til podcasts

Hent den på Google Play Installer gratis Android næsten 10 mio. downloads · 4,7+ i bedømmelse iOS snart

Episoder

የመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 23.09.2026

የኢትዮጵያ የፈደራል መንግሥትና ትግራይን የሚገዛዉ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይላት አዲስ ዉጊያ ገጥመዋል።የደቡብ ሱዳን ፕረዝደንት ሳልቫኺር የሐገሪቱን የሽግግር መንግስት አፈረሱ። ኢራን በአሜሪካና እስራኤል ጥቃቶች የወደመውን የነዳጅ ማምረቻ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ 50 በመቶ ማጠናቀቋን አስታወቀች።

News AMH_am Dienstag den 22.09.2026 - MP3-Stereo 22.09.2026

የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። በሃገሪቱ ውጥረቶችን ለመቀነስ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በአፍሪቃ ኅብረት የሚመራውን ጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደገፉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ኒዮርክ ላይ በይፋ ጀመረ።

የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 21.09.2026

አርዕስተ ዜና -የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከስርጭት መታገዱን አስታወቀ። -የየመን ሁቲዎች ስልታዊ የተባሉ የየመን ከፍተኛ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ ናቸው - የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ ሜክለንቡርግ ፎር ፖመርን ግዛት ፓርላማ መግባት ሳይችል ቀረ

የመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 20.09.2026

ሰባት ታጣቂ ቡድኖች የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና የተባለ ጥምረት መመሥረታቸውን አወጁ ። አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ከፈጸመች በመካከለኛ ምስራቅ ውስጥ የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿንና ጥቅሞቿ ላይ ጽኑ ሕመን የሚያስከትል ጥቃት እንደምትፈጽም ኢራን አስጠነቀቀች።

የመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 19.09.2026

• በደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ከተማ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን የክልሉን የመገናኛ ብዙኃን ጠቀሶ የትግራይ ቴሌቭዥን በፌስ ቡክ ገጹ ዘገበ። • በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ተገደሉ ። ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ። • ሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ ውስጥ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱ ተዘገበ ።

የመስከረም 8፣ 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 18.09.2026

• የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት 300 ያህል የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች አባላት እጃቸውን መስጠታቸውን አስታወቀ። • የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” የተመሠረዉ “ፅምዶ” ተባለ ህብረት ውስጥ ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታወቀ፡፡

የዓለም ዜና፤ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም 17.09.2026

አርስተ ዜና፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ከጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አደረሱት በተባለው ጥቃት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ።-የስምረት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ን እርምጃ አወደሰ። ሜሪካ ለደቡብ አፍሪቃውያን አዲስ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ ማዉጣትዋን አስታወቀች።

የመስከረም 6 ቀን 2019 የዓለም ዜና 16.09.2026

-ሊቢያ ዉስጥ በየእስር ቤቱ የሚገኙ የኤርትራ ሥደተኞች ከፍተኛ ሥቃይ እንደሚደርስባቸዉ አስታወቁ።ሥደተኞቹ እንደሚሉት የየእስር ቤቱ ተቆጣጣሪዎችና ጠባቂዎች።ይደበድቧቸዋል።ሴቶቹን ይደፍሯቸዋል።---የየመን አንሳር አላሕ ተዋጊዎች የሙስሊሞቹን ቅድስት ከተማ መካን ለማጥቃት ሞከራዋል የሚለዉን የሪያድ ገዢዎችን ክስ አስተባበሉ።

የመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 15.09.2026

• በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትናንት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአስራ ሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡ • የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመደቡ ተማሪዎችን ማመልከቻዎች መቀበል መጀመሩን አስታወቀ።

የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 14.09.2026

የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ታጣቂዎቸ አደረሱት በተባለው ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ፤ 4 ደግሞ ቆሰሉ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥቢያ በሱዳኑ የብሉ ናይል ግዛት በአል-ዳማዚን ከተማ የድሮን ጥቃት ፈፀመ ። የሁቲ አማጽያን ዛሬ የሀኒሽ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ ።

የመስከረም 03 ቀን 2019 የዓለም ዜና 13.09.2026

በየመን በሑቲዎችና የመንግሥት ኃይሎች ውጊያ 86,000 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,000 በላይ ጅቡቲ ገቡ። “በዓለም ዙሪያ የግጭቶችና ውጥረቶች ቁጥር እየጨመረ” በመሔዱ በሕዝቦች ሕይወት ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስጠነቀቁ። ሩሲያ ከዋርሶ ወደ ኪየቭ በተዘረጋ ባቡር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ፖላንድ አስታወቀች።

የመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና 12.09.2026

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች። ለብሪክስ ጉባኤ ሕንድ ኒውደልሂ ከተማ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢራን ፕረዚደንትን ጨምሮ ከተለያዩ ሐገራት መሪዎች መወያየታቸውን ገለፁ።ኢራቅ ከኢራን ጋር የሚያዋሱኗት ሦስት ድንበሮች ዛሬ መዝጋቷን አስታወቀች።

የመስከረም አንድ ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና 11.09.2026

በአሜሪካን በኒውዮርክ፣ በፔንታገንና በፔንሲልቬንያ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት 25 ተኛ ዓመት ዛሬ በአሜሪካን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየታሰበ ነው። ነገ ህንድ ውስጥ በሚጀመረው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራት መሪዎች ኒውዴልሂ እየገቡ ነው። የሁቲ አማጻያን ዛሬ ስልታዊ የሚባለውን ፔሪም ደሴትንና የዱባብ ከተማንም ይዘዋል

የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና 10.09.2026

አ.አ፥ ከ600 እስረኞች በላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ዐሳወቀ፤ ጊምቢ፥ አልጄሪያ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋረጠች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን በቀይ ባሕር ቁልፍ የወደብ ከተማን ተቆጣጠሩ፤ ዋሽንግቶን፥ ዶናልድ ትራምፕ ፓርቲያቸው በአማካይ ዘመን ምርጫ ካሸነፈ ለእያንዳንዱ አዋቂ 5ሺህ ዶላር ሊሰጡ ቃል ገቡ

የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና 09.09.2026

-- የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸዉ የኢሕአፓ መሪዎችና ጠበቃ በዋስ እንዲፈቱ የተላለፈላቸዉ ዉሳኔ ታገደ።-ብሪታንያ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኝ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን እንድትዘጋ እስራኤል ማሳሰቧን ብሪታንያ የሚጠበቅ፣ግን አሳዛኝና ግንኙነትን የሚያበላሽ በማለት ነቀፈችዉ።-የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።

የዓለም ዜና፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ 08.09.2026

አርስተ ዜና፤ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች ሞቱ። -በትግራይ ክልል የሚገኙ አማፅያን የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ሌላ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል አሉ።-በሌላ በኩል በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የወጣቶችና የታዳጊ ልጆች አፈሳ ይቁም ሲሉ በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ እናቶች ለተቃዉሞ ወጡ።

የጳጉሜ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና 07.09.2026

የትግራይ ክልል ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ገለልተኛ አይደሉም” በማለት ወነጀለ። በኢትዮጵያ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጥሪ አቀረቡ። መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ያስመዘገው የምርጫ ድል ፓርቲያቸውን ከመሠረቱ እንደነቀነቀ ተናገሩ

የጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 06.09.2026

በየመን መንግስት ኃይሎችና «በኢራን ይደገፋሉ» የሚባሉት የሑቲ ደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ትላንት አገርሽቶ እስከ ዛሬ በተካሄደ ውግያ ከሁለቱም ወገን ከ140 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ተሰማ። በምሥራቅ ጀርመን በምትገኘው የዛክሰን አንሃልት ግዛት የአካባቢ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 05.09.2026

• በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ምስራቅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 20 ሰዎች ተገደሉ ። አስራ ስድስቱ የመንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ናቸው ። • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።

የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 04.09.2026

በኢትዮጵያ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም ወደ 38,000 ኮምፒውተሮች እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።

የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 03.09.2026

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሾመው የሱዳን ጉዳይ የምርመራ ቡድን፤ የውጭ ሐገራት ታጣቂዎች በሐገሪቱ ያለውን ግጭት እያባባሱት ነው ሲል ከሰሰ። የእስራኤል ጦር አባላት በምዕራባዊ ዮርዳኖስ የባሕር ዳርቻ 2 ፍልስጤማውያን ወጣቶችን ተኩሰው መግደላቸውን

የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና 02.09.2026

-የጀርመንና የሩሲያ ተዘዋዋሪ ግጭት ወደ ቀጥታ ዉዝግብ፣ የጥቃት ሙከራ፣ ቅጣትና የአፀፋ ቅጣት ዛቻ ንሯል።---የቻይና መሪ ሺ ጂፒንግ የዉጪ መንግሥታት በመካከለኛዉ ምሥራቅ የዉስጥ ጉዳይ ጠልቃ እንዲገቡ የአካባቢዉ መንግሥታት መፍቀድ የለባቸዉም አሉ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን አንዳቸዉ የሌላቸዉን ተቋማትና ጥቅሞች መደብደባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና 01.09.2026

አርዕስተ ዜና የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማቸውን ማቋረጣቸው ተገለፀ ። የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ ። የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ ለያዘችው አቋም ፑቲንን አመሰገኑ። ፑቲንም ፔሽኬቭያንን ለተጋድሎአቸው አወደሱ

DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 የዓለም ዜና 31.08.2026

በአንድ ሣምንት 2,463 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት ከ6,000 በላይ ሰዎች በኢቦላ መያዛቸውን አረጋገጠ። በሱዳን የታቀደው ብሔራዊ ውይይት “የመጨረሻ ግብ በሕጋዊ ሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር” ያላት “የተባበረች፣ ሉዓላዊ እና ሰላማዊ” አገር መፍጠር ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መከረ። ሕንድ ከፓኪስታን ጋር የተፈራረመችውን የውኃ መጋራት ሥምምነት እንድታከብር በፍርድ ቤት የተላለፈባትን ውሳኔ ውድቅ አደረገች። የአሜሪካና ኢራን ጦርነት ዳግም ሲያገረሽ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ።

የነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና 30.08.2026

የዛምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሐገር ክህደት ወንጀል እንደተከሰሱ የሐገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በወታደሮች ተቀስቅሶ የነበረው ዓመጽ በኒጀር መንግስት ታማኝ ወታደሮችና በሐገሪቱ ያሉ የሩስያ የአፍሪካ ጓድ ጦር አባላት ድጋፍ መክሸፉን ተከትሎ ከተማዋ በዛሬው ዕለት አንጻራዊ ሰላም ማግኘቷን ተነገረ። እስራኤል በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 2 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። ቱርክ፣ ሳውዲ ዓረቢያና ፓኪስታን በጋራ የመከላከያ ስምምነት ላይ ለመምከር ነገ በኢስታምቡል እንደሚገናኙ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Lyt til podcasten የዓለም ዜና i Replaio

Radio og podcasts i én app - gratis og uden tilmelding. Installer i dag, og gå ikke glip af lanceringen

Hent den på Google Play

Replaio er ikke podcastudgiver; programmernes navne, coverbilleder og lyd tilhører deres ophavsmænd og distribueres via offentlige RSS-feeds.