DW
ዜና መጽሔት
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መፅሔት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ያዳምጡ።
Husk at besøge podcastens hjemmeside og støtte skaberen: www.dw.com
Hvor kan du lytte?
Podcasts i appen Replaio Radio Kommer snartPodcasts kommer snart til appen. Installer nu, og vær den første til at se en helt ny tilgang til podcasts
Episoder
የኅዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.11.2026 24:09
የዜና መጽሔት የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራና ሱዳን ላይ ብርቱ ክስ ማቅረቡ ፣ የጸጥታ ስጋት በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ ወረዳዎች ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ሁለት ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ነዋሪዎች ለረሃብና ስደት ተዳረጉ ግብፅና አጋሮቿ በቀይ ባሕር ጉዳይ የያዙት ከኢትዮጵያ የተለየ አቋም እንዲሁም የደንጊ በሽታ ወረርሽኝና የመከላከሉ ሂደት ይቃኛል
የሕዳር 2 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 11.11.2026 22:50
ጅማ ላይ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላን የተቃወሙ ዜጎችና የፀጥታ አካል ግጭት፣ አርሲ ዞን በተደጋጋሚ ጥቃቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች የርዳታ ጥሪ፣ አማራ ክልል ለድርቅ የተጋለጡ ወገኖች ሁኔታ፣
የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 1 ቀን 2019 ዓም ማክሰኞ 10.11.2026 19:33
ዜና መጽሔት፤ ሱዳንና ግብፅ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ያደ,ርስብናል ያሉትን ጉዳት ለመርመር መስማማታቸዉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።የሞያሌ ዉጊያ መቀጠሉ፣ የደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋዜጠኞች ጣቢያዉን ለማዳን የሚያደርጉት ዘመቻና አምቦ ዩኒቨርስቲ አንዲት ተማሪ መሞቷ ያስከተለዉ ድጋጤና ጥርጣሬ የተሰኙ ርዕሶች ይተነተናሉ።
የዜና መጽሔት ፦ የጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 09.11.2026 15:31
በዜና መጽሔት ባለፈዉ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን በአርሲ ሮቤ ዲዳዓ እንደቶ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 40 መድረሱ ፣ በድርቅ እና በጦርነት ምክንያት በዋግ ኸምራ ዞን በተከሰተዉ ከፍተኛ ረሃብ ሰዎች መሞታቸዉ እንዲሁም ዲፕሎማቶችን የማባረር እርምጃ በመንግሥታት ግንኙነት ያለው ትርጉም እንቃኛለን
የጥቅምት 27 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 06.11.2026 28:18
ከዓለም ዜና ቀጥሎ በሚቀርበዉ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን፤-- የአርሲ ዳግም የተከሰተዉ ጥቃት እና ያሳደረዉ ስጋት-- የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ የገታዉ እያወደመዉ ያለዉ ጦርነት በአማራ ክልል-- ዲፕሎማቶች ከህወሓት የተማረኩ የተባሉ የጦር መሣሪያዎችን ዛሬ መጎብኘታቸዉ
የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ሐሙስ 05.11.2026 27:25
በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ሁለት ወረዳዎች የደረሰው ጥቃት-በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ ድጋፍ አለማግኘታቸው-በአማራና ትግራይ ክልሎች ደረሱ የተባሉ የድሮን ጥቃቶች ያስከተሉት ሥጋት-የአፍሪካ ኀብረት የኢትዮጵያና ኤርትራን ውጥረት ለማርገብ እየጣርኩ ነው ማለቱ እንዲሁም አድማ እና ተቃውሞ በፈረንሳይ የተሰኙ ዘገባዎች ቀርበዉበታል።
መጽሔተ ዜና የዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2019 ዓ.ም 04.11.2026 24:29
አርሲ ዉስጥ ሰሞኑን ሥለተፈ,ፀመዉ ጉድያ የሐገር ዉስጥና የዉጪ ድርጅቶችና ተቋማት የሰጧቸዉ መግለጫዎች በሁለት ዘገቦች ያሰማናል።የጉራጌ ዞኖችን የፀጥታ ችግርና ሁከትን ለማቃለል የሐገር ሽማግሌዎች የጀመሩት ጥረት፣ የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ዉጤትና ሥለዉጤቱ የአዉሮጶች አስተያየት ርዕሶች በቃለ መጠይቅና በዘገባ ይተነተናሉ።
የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 03.11.2026 20:08
ኢሰመኮ 60 ሰዎች የተገደሉበትን የአርሲውን ጥቃት የምርመራ ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ ያደርጋል፤ በሰሜናዊ ኬንያ የጸጥታ ስጋት የደቀነው የሞያሌው ግጭት፤ የሪፓርተር ጋዜጣ መታገድ እና የዘርፉ ባለሞያዎች ሥጋቶች፤ የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የተሰኙ ዘገባዎች ተጠናክረዋል።
የጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄት 02.11.2026 20:57
በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅት፤ዓለም አቀፍ ዉግዘት ያስከተለዉ የአሩሲ ዞን የሽርካዉ ጭፍጨፋ፣ተጠናክሮ የቀጠለዉ የሞያሌ ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውስ፣ ትብብር ለሕልውና የጀመረውን ትግል እንደሚያጠናክር መግለፁ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ ነገ የሚካሄደዉ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአጋማሽ የስልጣን ዘመን ምርጫ የተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል።
የጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 30.10.2026 28:25
በደቡብ ወሎ ዞን ፤«ቱርክ» የተፈናቃዮች መጠለያ በደረሰ ድሮን ጥቃት 16 ሰዎች መገደላቸዉ በአርሲ ሺርካ ጥቃት ለተገደሉ ለቅሶ የደረሱ ቀብር ያስፈፀሙ መታሰራቸው በአሩሲዉ ጥቃት የመንግሥትና የመገናኛ ዐውታሮች ዝምታ ምን ትርጉም ይኖረዉ ይሆን? በሞያሌዉ የተነሳዉን ግጭት መወገዙ ዜና መጽሔት ከሚያስቃኘን ጉዳዮች መካከል ናቸው።
የጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔት 29.10.2026 46:35
በዛሬው የዜና መፅሔት-የኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ጄቶች ግዢ አንድምታ፤-በሳዮ ኖሌ ወረዳ ከ20 በላይ ሰዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 2 ወራት ማስቀጠራቸው፤ የቀጠለው የሞያሌ ግጭትና ሰብዓዊ ቀውሱ፤ትብብር ለሕልውና በመንግሥት ላይ ያቀረበው ክስ፤-የአፍሪካ ኀብረት ከዲፕሎማቶች መባረር ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውዝግብ እንዴት የሚሉ ርዕሶችን አካቷል።
የጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 28.10.2026 22:46
በዜና መጽሔት በሞያሌው ግጭት ወደ ኬንያ የተሻገሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር የአርሲው ተደጋጋሚ የንጹሃን ግድያ የፈጠረው ቁጣ በአማራ ክልል የባንክ አገልግሎቶች መስተጓጎል ተቃውሞ የህወሓት"ካድሬዎች" በፖሊስ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ በመጠየቁ፣ በአፍሪካ ቀንድ ግጭቶች መጨመር በዓለምአቀፍ ትኩረት ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ የሚሉ ዘገቦች ይቀርባሉ።
የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ማክሰኞ 27.10.2026 19:32
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የተፈጸመው ግድያ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ጉዳዩ የሰጡትን አስተያየት፤ በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው በሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዕገታዎች የገጠማቸውን ሥጋት የተመለከቱ ዘገባዎች ዜና መጽሔት የያዛቸዉ ናቸዉ።
News magazine 261026 - MP3-Stereo 26.10.2026 21:23
በዜና መጽሔት፤ የቀጠለው የአርሲ- ሺርካው የጅምላ ግድያ፣የሞያሌ ግጭትና ሰብዓዊ ቀውሱ፣ የሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ በሞያሌ ግጭት የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቁ ፣ በአፋርና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ሰዎች ተገደሉ፣ እንዲሁም - ስለ ትግራይ ክልል ኹኔታ መንግሥትና ሌሎች የሚሰጡት መረጃዎች የተሰኙ ዘገቦች ይደመጡበታል
የስራ ዘመኑን ያጠናቀቀው አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና ውጤቱ 24.10.2026 4:09
ከአራት አመት በላይ በስራ ላይ የቆየው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ በህግ የተሰጠውን የስራ ዘመኑን አጠናቋል፡፡የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 8 ዋና ዋና አገራዊ አጀንዳዎች እና የውሳኔ ምክረ ሐሳቦችንም አስቀድሞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት አስረክቧል፡፡ ለመሆኑ የኮሚሽኑ ስራና ውጤቱ እንዴት ይገመገማል?
የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች 24.10.2026 4:14
የቀይ ባሕር ደህንነት ጉዳይ ለጥቂት ሀገራት ብቻ የሚተው አይደለም ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች።የአፍሪካ የደህንነት ጉባኤ የኾነው ጣና ፎረም ባዘጋጀው መድረክ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ኢትዮጵያ የደህንነት ሰጋቶችን የማስወገድና የንግድ መርከቦቿን የመጠበቅ አስፈላጊ ኃላፊነት አለባት ብለዋል።
የጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 22.10.2026 31:33
በአፍሪካ ቀንድ "እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋት መነሻ ኢትዮጵያን ናት"ስትል - ኤርትራ መክሰስዋ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ቀዉስና ሰብዓዊ አቅርቦቱ በአማራና በትግራይ ክልሎች ያለዉ ወቅታዊ ሁኔታ፤ ሞያሌ ከተማ በሰንደቅ ዓላማ ውዝግብ ሕይወት መጥፋቱ፤ በጋምቤላ ግጭት በመሳተፍ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ፤ የአሜሪካ አጋማሽ ምርጫና አንደምታዉ
የጥቅምት 11 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 21.10.2026 19:56
የዜና መጽሔት፤ በኦሮሚያ አርሲ ዞን ሲቪሎች ላይ ጥቃት እና ግድያ መቀጠሉ ፤ በትግራይ ለተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የተመድ መግለፁ፤ የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታ በፓለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዕይታና በቀይ ባሕር ያለው የፀጥታ ችግር መቀጠል የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት የመነሳት እድል ይቀንሳል? ሲል የሚጠይቅ ዘገባዎችን አካቷል።
የጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 20.10.2026 19:27
የዜና መፅሔት ጥንቅር፤የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ኤርትራን መዉቀስና ማስጠንቀቃቸዉን የሚዳስሰዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፤ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ተሥፋና ሥጋት፣ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ፊንጫኣ ሥኳር ፋብሪካ ላይ የከፈቱት ጥቃትና ያደረሱት ጥፋት፣የኢቦላ ተሕዋሲ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የሚደረገዉ ጥንቃቄን አካቷል
DW Amharic የጥቅምት 09 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 19.10.2026 15:54
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስተያየትና ትብብር ለሕልውና የሰጠው ምላሽ፤ ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ የፀጥታ ኹኔታ የፓርቲዎች እና የሲቪክ ድርጅት አስተያየት፤ የህብረት ለምርጫ የ7ኛው ምርጫ ትዝብት እና ዘገባ
የጥቅምት 6 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 16.10.2026 31:30
-በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር መቋቋሙእና የህዝቡ አስተያት-ቆቦ የሚገኙ የራያ አካባቢ ተፈናቃዮች ተሳታፊነታቸውን ያገለለ የምርጫ ሂደት እንዲቆም መጠየቃቸዉ -በኦሮሚያ ክልል የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና የፀጥታው ችግር-የሚዲያ ነፃነትን የሚጋፉ "በርካታ" አሳሳቢ ጉዳዮች ተለይተዋል ያለዉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
DW Amharic የጥቅምት 05 ቀን 2019 ዜና መፅሔት 15.10.2026 25:50
በዶቸ ቬለ የዜና መጽሔት አሜሪካን ጨምሮ ብዙዎች እንዲናገሩ እያደረገ ያለው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት፤ በትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንዲቆም መጠየቁ፤በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት፤ በሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ፤ በጦርነት በምትታመሰው የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማጽኖ የሚል ርዕስ የተሰጣቸው ዘገባዎች ይቀርባሉ።
የጥቅምት 4 ቀን 2019 የዜና መጽሔት 14.10.2026 25:57
የዕለቱ ዜና መጽሔታችን አምስት ጉዳዮችን ያስደምጣል። የቀጠለው የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ውጊያ ፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ መድረሳቸው ፣ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ማለቱ፣
የዜና፤ መጽሔት፤ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ማክሰኞ 13.10.2026 21:35
በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለው ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊ እና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ አስቀድሞ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ አገራት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አሳሰበ፡፡
የጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔት 12.10.2026 19:07
የዜና መጽሔት፤ በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት እና የኑሮ ዉድነት በትግራይ ክልል የፌዴራል አመራሮች አቀባበል እና አሁንም ያሉ ስጋቶች ስለ ትግራይ ክልል ቀጣይ ኹኔታ በባለሥልጣናት የተሰጡ አስተያየቶችን የሚያስደምጡ ዘገባዎችን አካቷል
Lignende podcasts
Replaio er ikke podcastudgiver; programmernes navne, coverbilleder og lyd tilhører deres ophavsmænd og distribueres via offentlige RSS-feeds.