SBS
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Určitě navštivte web podcastu a podpořte jeho tvůrce: www.sbs.com.au
Kde poslouchat?
Podcasty v aplikaci Replaio Radio Už brzyPodcasty míří do aplikace už brzy. Nainstaluj si ji teď a jako první uvidíš úplně nový pohled na podcasty
Epizody
"የኢትዮጵያ አየር መንገድን 'ከአፍሪካ የወጣ አፍሪካዊ አየር መንገድ' ነበር የምንለው፤ አሁን 'ከአፍሪካ የወጣ የዓለም አየር መንገድ' ነው የምንለው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ 25.11.2025 30:50
"አውስትራሊያ ጥሩ ሀገር ናት፣ ብንመጣም የምናተርፍባት እንጂ የምታከስረን ሀገር አይደለችም፤ ሕዝቧም ተቀባይ የሆነ ሀገር ስለሆነች ወደ አውስትራሊያ መብረር የማይፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የለም። እርግጠኛ ነኝ፤ አውሮፕላን እንደተገኘ የድርጅቴ ቀዳሚ ጉዳይ የሚሆነው ወደ አውስትራሊያ መብረር ነው" ያሉት ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ፤ ተሰናባች የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላናድ ቀጣና ሥራ አስኪያጅ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የቀጣና ተግዳሮቶችንና ስኬታማ ክንውኖችን አንስተው ይናገራሉ።
የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበራትን በባሕር ማዶ የማቋቋም ፋይዳ፣ ሳቢና ገፊ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? 25.11.2025 15:56
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት እና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፤ የማኅበረሰብ ማኅበራትን የአገልግሎት ፋይዳዎች ያስረዳሉ።
በአዲስ አበባ በፆታዊ ጥቃት የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሔዱት መካከል ከ70-80 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች መሆናቸው ተገለጠ 25.11.2025 13:01
ከ44 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የላቸውም ተባለ
ለሥራ አጥነትና የወጣት ጥፋተኞች እሥራት ቁጥር መናር አስባቦች ምንድን ናቸው? 19.11.2025 30:04
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ስለ ወጣት አፍሪካውያን ሥራ አጥነት ቁጥርና ማኅበራዊ ተግዳሮት አስባቦች ይናገራሉ።
"ኢትዮጵያውያንም ማንኛውም ጥቁር የሚደርስበት ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ጥቁር አይደለሁም የሚል አስተሳሰብ ካለ ይህ የንቃት ጉድለት ነው፤ ያሳስባል" ዶ/ር ተበጀ ሞላ 19.11.2025 20:10
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አክሎ በፍልሰተኞች ዘንድ ያሉ የማንነት አተያዮችን ያጋራሉ።
"ዘረኝነት ቴክኖሎጂ እያገዘው እየሰፋ የሔደበት ጊዜ ላይ ስለምንገኝ በተለይ ኢትዮጵያውያንን ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው" ዶ/ር ይርጋ ገላው 19.11.2025 15:36
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ዳይሬክተርና ዶ/ር ተበጀ ሞላ፤በዲከን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፖሊሲና የማኅበራዊ ፍትሕ ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ አውስትራሊያ ውስጥ በተለይም ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ከማንነት ጉዳዮችን ጋር ተያይዘው ገጥመዋቸው ስላሉ ማኅበራዊ እንከኖች አንስተው ያስረዳሉ።
የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ከሕግ ውጪ የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ ምጣኔ ሃብታዊ ውድቀትና የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ በአስቸኳይ እንዲገታ ጥሪ አቀረበ 19.11.2025 6:49
የተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊ ድጋፋቸውን ለነፈጓቸው የምክር ቤት አባል ምፀታዊ ውዳሴ አቀረቡ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በቦታው ሆኖ መመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪ ወደ አካባቢው መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ 19.11.2025 9:26
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 'የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሙስሊሙ መሪ ተቋም ጋር ሳይወያይ የሙስሊም ተማሪዎች በግዳጅ የግዕዝ ቋንቋ እንዲማሩ ውሳኔ ማሳለፉ ተቀባይነት የለውም' አለ
ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያላቸው የሕክምና ቁሳቁሶች ከአውስትራሊያ ወደ ድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል እያመሩ ነው 18.11.2025 8:40
በሜልበርን አውስትራሊያ የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጃማ ፋራህ፤ የድሬዳዋን መርጃና መደጎሚያ ማኅበር በአውስትራሊያ ተጠሪዎች፤ አቶ ሳምሶን ከበደና አቶ ዳዊት ከበደ ስለምን ለድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁሶችን ለመላክ እንደተነሳሱ ይናገራሉ።
የጤና ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ ከተማ ተከሰተ የተባለው አዲሱ በሽታ ከኢቦላ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ማርበርግ ቫይረስ እንደሆነ አስታወቀ 17.11.2025 12:53
'ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግሥት በሉዓሏዊነቷና የግዛት አንድነቷ ላይ በሚፈፅማቸው ጥሰቶች ላይ ስትከተል የቆየችው እርምጃ ከመውሰድ የመታቀብ አካሔድ ሁሌም የሚቀጥልና ገደብ የለሽ ተደርጎ መወሰድ የለበትም' አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ
#99 Saying ‘No’ to alcohol - #99 አልኮልን ‘እምቢኝ’ ማለት 13.11.2025 8:06
Learn polite ways to refuse a drink in English. Discover useful expressions for taking it slow, sitting one out or explaining you're on a permanent dry spell. - ትህትና በተመላው መልኩ በእንግሊዝኛ መጠጥን እምቢ ማለትን ይማሩ። እያዘገምኩ፣ እቆያለሁ ወይም አልኮል ዳር ሳልደርስ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል ዓይነት ጠቃሚ አባባሎችን ይግለጡ።
በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ፍጆታዎች ዋጋ መናሩን ነዋሪዎች ተናገሩ 12.11.2025 10:22
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ በ2027 አዲስ አበባ ላይ ለማስተናገድ ይሁንታን አገኘች
ተስፋ የራዲዮ ድራማ፤ ሕይወትና ሞት - ነፃነትና ፅልመት 11.11.2025 17:54
ተስፋ የራዲዮ ድራማ፤ ድርሰት በሱራፌል ወንድሙ - ተዋናዮች ተስፋዬ ገብረሃና፣ ጌታሁን ሰለሞን እና ዐቢይ አየለ - ድምፅ ቀረፃና ቅንብር SBS
ቲክቶክ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ 2017 ከ2.1 ሚሊዮን በላይ በኢትዮጵያውያን የተለቀቁ ቪዲዮዎችን 'በአደገኛነት' ፈርጆ ለዕይታ እንዳይበቁ ማድረጉን አስታወቀ 09.11.2025 11:35
የአፍሪካ ሕብረት፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ 'የናይጄሪያ መንግሥት በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ግድያ እጁ አለበት' በማለት በሀገሪቱ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ መዛታቸው ያሳሰበው መሆኑን አስታወቀ።
የቀድሞው የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሣና ቤተሰቦቻቸው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ 04.11.2025 11:52
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሩብ ዓመት ክንውኑ በትግራይና አማራ ክልሎች ከ20 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማስቻሉን አስታወቀ
"ትልቁ ነገር ባለ ትልቅ ቤት መሆኑ ሳይሆን፤ ከልጆቻችን ጋር ያለን ትልቅ ግንኙነት ነው፤ በተለይ አባቶች። ለእናቶች ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ" ዶ/ር ብርሃን አሕመድ 04.11.2025 18:28
ዶ/ር ብርሃን አሕመድ፤ የAfricause ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ አፍሪካውያን አውስትራሊያውያን ልጆቻቸውን ለመታደግና እየናረ ላለው ፍቺ ብልሃት ለማበጀት ማለፊያ ቤተሰባዊ ትስስሮሽ ስለሚኖረው ሚና ይናገራሉ።
"እኛ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ሶማሌ እንላለን፤ ልጆቻችን የሚኖሩት እንደ አፍሪካዊ ነው። በእነሱ ጭንቅላት ማሰብ ግድ ይሆናል" ዶ/ር ብርሃን አሕመድ 04.11.2025 15:04
ዶ/ር ብርሃን አሕመድ፤ የAfriCause ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ የድርጅታቸውን ተልዕኮና ሚና፣ አፍሪካውያን - አውስትራሊያውን አውስትራሊያ ውስጥ ገጥሟቸው ስላሉ አንኳር ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን ነቅሰው ያመላክታሉ።
ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ የሚሰጥበት ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ጥሪ ቀረበ 02.11.2025 14:29
በሶማሌ ክልል ማረሚያ ቤቶችና በፖሊስ ጣቢያዎች፤ በታሳሪዎችና ተጠርጣሪዎች ላይ ይፈፀሙ የነበሩ ድብደባዎችና የማሰቃየት ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እንዳስየ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጠ
"ይቅርታ ይደረግልኝና የኢትዮጵያ ፊልም ከአዳራሽና ሬስቶራንት በባሕል ማዕከል ወይም ሲኒማ ቤት ቢታይ ሲኒማችን ክብር ይኖረዋል" ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ 30.10.2025 21:10
ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ፤ ለ10ኛ ዓመት የበቃው የHabeshaview ተባባሪ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ስለ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ዕድገትና ሂደት አተያያቸውን ያጋራሉ።
"ከኔትፊሊክስ ጋር ያለን ችግር 'የኢትዮጵያን ፊልም ከፍሎ የሚያየው ማነው?'ነው፤ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ፊልም አክብረን፤እየከፈልን ማየት ይኖርብናል"ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ 30.10.2025 16:25
ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ፤ ለ10ኛ ዓመት የበቃው የHabeshaview ተባባሪ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ድርጅታቸው እያበረከተ ያለውን ሚናና ዋነኛ ተልዕኮውን ነቅሰው ያስረዳሉ።
#98 Splitting the bill (Med) - #98 Splitting the bill (Med) 29.10.2025 9:42
Learn how to split the bill in English. Discover useful expressions for sharing costs, shouting rounds, and transferring your share easily. - Learn how to split the bill in English. Discover useful expressions for sharing costs, shouting rounds, and transferring your share easily.
"ግጥም በጃዝን በየሶስት ወራቱ ወደ ተለያዩ የአውስትራሊያ ዋና ዋና ከተሞች እየተዘዋወርን እናሳያለን" ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን 29.10.2025 16:03
ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን፣ እሑድ ጥቅምት 30 / ኖቬምበር 9 በKindred Studio, 3 Harris St, Yarraville በሜልበርን ለተመልካቾች ስለሚቀርበው "ግጥም በጃዝ" ልዩ ዝግጅት ፕሮግራም ይገልጣል።
ግጥም በጃዝ በሜልበርን አውስትራሊያ ዳግም መድረክ ላይ ሊያዋዛ ነው 28.10.2025 21:32
ተዋናይና ገጣሚ ጌታሁን ሰለሞን፣ ጥቅምት 30 / ኖቬምበር 9 ተቋርጦ ከርሞ ዳግም በሜልበርን ከተማ ለመድረክ ስለሚበቃው "ግጥምን በጃዝ" ልዩ ዝግጅት አስመልክቶ ይናገራል።
"ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ድርሰትን ለድርሰት ብለው ነው የጀመሩት፤ የኢትዮጵያ ደራሲያን ግን ድርሰትን ለሀገር የችግር መፍቻ ብለው ስለሆነ ልዩ ያደርጋቸዋል"ደራሲ ጌታቸው በለጠ 28.10.2025 13:54
ምልሰታዊ ምልከታ፤ ደራሲ ጌታቸው በለጠ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር (ኢደማ) ፕሬዚደንት፤ ስለ ኢደማ ምሥረታ፣ ተልዕኮና ሚና ይናገራሉ።
ምልሰታዊ ምልከታ "የወታደር ክፉ የለውም፤ የመሪ ክፉ ነው ያለው" ሻለቃ ቦጋለ ንጋቱ 27.10.2025 25:36
ደራሲ ሻለቃ ቦጋለ ንጋቱ፤ ስለ "ትውልድ ያናወጠ ጦርነት" መፅሐፋቸው ተልዕኮና ታሪካዊ ፋይዳ አንስተው ይናገራሉ።
Podobné podcasty
Replaio není vydavatelem podcastů; názvy pořadů, obálky a audio patří jejich autorům a šíří se přes veřejné RSS kanály