SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episódios

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Não deixe de visitar o site do podcast e apoiar quem o produz: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categoria

News

Site do podcast

www.sbs.com.au

Último episódio

8 de jul de 2026

Onde ouvir?

Podcasts no app Replaio Radio Em breve

Os podcasts estão chegando ao app. Instale agora e seja o primeiro a descobrir um jeito totalmente novo de curtir podcasts

Baixe no Google Play Instale grátis Android 5 mi+ downloads · nota 4,8 iOS em breve

Episódios

"ጥምቀት ከፍተኛ የሆነ ምስጢር ያለው፣ የስላሴ ሶስትነት፣ አንድነት የተገለፀበት፤ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የተወለደበት ሙሉ የሆነበት ነው" ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሉ 22.01.2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊው በዓለ ጥምቀት በሀገረ አውስትራሊያ - ብሪስበን ከተማ በ Oxley Creek Common ከጃኑዋሪ 24 - 25 / ጥር 16 - 17 ተከብሮ ይውላል። ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ እንዲሁም አቶ ወርቅነህ ባየህ፤ በብሪስበን የደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስለ በዓሉ መሰናዶ፣ መርሃግብርና የበዓለ ጥምቀትን ተምሳሌነትና ፋይዳዎች ያስረዳሉ።

የፀረ ጥላቻ ንግግርና የጠብመንጃ ባለቤትነት ሕጎች በፓርላማ ይሁንታ ተቸራቸው 21.01.2026

ኩዊንስላንድ ውስጥ ሕይወቷ አልፎ የተገኘችው ካናዳዊት ቱሪስት ምናልባትም በዲንጎ ተጠቅታ ይሆናል የሚል ስጋት አሳድሯል

ግብፅ ኢትዮጵያ ካሣ ትክፈለኝ አለች 21.01.2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ገንዘብ ሚኒስቴር 'ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አራተኛውን ዙር የኢትዮጵያ የብድር ግምገማ ሰሞኑን ማፅደቁ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ቀደም ሲል ከተጠበቀው በላይ ጠንካራ መሆኑን ያረጋግጣል' አሉ

"ግጥምን በጃዝ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ዒላማ 'ለሰዎች የመዝናኛ መድረክ መክፈት፤ ባሕልን፣ የሀገር ፍቅርንና ዕሴትን ማስተዋወቅ ነው" ተዋናይ ጌታሁን ሰለሞን 20.01.2026

መታሰቢያነቱ ለሰዓሊ ታምራት ገብረማሪያም የተቸረውና ለሁለተኛ ጊዜ የተከወነው 'ግጥምን በጃዝ' የአንድ ሰው ተውኔትን አጣምሮ በዕለተ እሑድ ጃኑዋሪ 18 / ጥር 10 ለሕዝብ ቀርቧል። የመድረክ መሪዎች፣ ገጣሚዎችና የሙዚቃ መሳሪያ ባለሙያዎች አተያያቸውን አጋርተዋል። ለቀጣዩ ዝግጅት ኢትዮጵያውያን በነቂስ እንታደሙ የግብዣ ጥሪያቸውን በጥበብ አንደበት አቅርበዋል።

"የጥምቀትን የተለያዩ የሃይማኖት ሥርዓቶችንና የሕዝቡን ደስታ ስመለከት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያለሁ ነው የመሰለኝ" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ 20.01.2026

የከተራና ጥምቀት በዓል በሀገረ አውስትራሊያ የሜልበርንና ፐርዝ ከተሞች ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ደምቆና ገንኖ ተከብሮ ውሏል። በዓለ ጥምቀቱን በጋራ የአንድነት መንፈስ ያከበሩት ቤተክርስቲያናት፣ ምዕመናንና ምዕመናት የእምነትና ሀገራዊ አንድነትን አንፀባርቀዋል። የሃይማኖት አባቶችና ታዳሚዎች አተያያቸውን አጋርተውናል።

ኢትዮጵያ በአሜሪካ የፍልሰት ቪዛ ከማያገኙት 75 ሀገራት መካከል አንዷ ሆነች 19.01.2026

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ጉባኤ ላይ ከአራት ሺህ በላይ ተወካዮች ይሳተፋሉ ተባለ

"በጥራት ስለምንጨርስ ከደንበኞች ጋር ጥሩ ወዳጅነት አለን፤ እምነት ይጥሉብናል" ዳይሬክተር ጀማል አይዲን 15.01.2026

አቶ ጀማል አይዲን፤ የGo Cabinets & Home Renovation ዳይሬክተር፤ እንደምን ወደ ግንባታና ዕድሳት ሙያ እንደተሠማሩና ለሜልበርን የምሥራቅ አፍሪካና የሕንድ ማኅበረሰብ አባላት ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር እየሰጡ ስላሉት ሙያዊ አገልግሎታቸው ይናገራሉ።

ጀማል አይዲን፤ የቤት ግንባታና የቤት ውስጥ ዕድሳት 15.01.2026

አቶ ጀማል አይዲን፤ የGo Cabinets & Home Renovation ዳይሬክተር፤ እንደምን ወደ ግንባታና ዕድሳት ሙያ እንደተሠማሩና ለሜልበርን የምሥራቅ አፍሪካና የሕንድ ማኅበረሰብ አባላት ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር እየሰጡ ስላሉት ሙያዊ አገልግሎታቸው ይናገራሉ።

ኢራን በአንድ ተቃዋሚ ሠልፈኛ ላይ ይሙት በቃ ፈረደች 14.01.2026

በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረሱ ዛቻዎች በ63 ፐርሰንት ማሻቀቡ ተመለከተ

በአዲስ አበባ ቅሬታ ካሰሙ ግብር ከፋዮች መካከል የ58 በመቶዎቹ ቅሬታ ትክክል ሆኖ እንዳገኘው የከተማይቱ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ 14.01.2026

'በአማራ ክልል አዲሱ የገጠር መሬትና አስተዳደር አጠቃቀም አዋጅ በተበታተነ መንገድ የሚኖሩ የክልሉን አርሶ አደሮች በፈቃደኝነት በአንድ አካባቢ ለማስፈር ያለመ ነው' ሲል የክልሉ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ገለጠ

"የSBS አማርኛ የፎቶግራፍ ባለሙያ ሆኜ መሥራቴ በጣም ነው የሚያስደስተኝ" ፎቶ አንሺ ስንታየሁ በቀለ 13.01.2026

የፎቶግራፍ ባለሙያ ስንታየሁ በቀለ፤ ስለ ፕሮፌሽናል የፎቶ ባለሙያነትና ከሞባይል ይልቅ የግል የፎቶ ካሜራን የመጠቀምን ተመራጭነት አንስቶ ምክረ ሃሳቡን ይቸራል።

"በሕይወት ያሉትንና የሌሉትን አስታዋሽና ጊዜን ገላጭ ሆኖ የሚቀረው ፎቶግራፍ ነው" ፎቶ አንሺ ስንታየሁ በቀለ 13.01.2026

የፎቶግራፍ ባለሙያ ስንታየሁ በቀለ፤ እንደምን ከግራፊክ ዲዛይን ወደ ፎቶ ማንሳት እንደተሸጋገረ ይናገራል።

"ምግብ አቅርቤ ባዶ ሳህን ሲመለስልኝ ደስ ይለኛል" ወ/ሮ ገነት ሐብተወልድ 12.01.2026

የሐረር መሶብ ምግብ ቤት ባለቤቶች፤ ወ/ሮ ገነት ሐብተወልድና አቶ አንተነህ ሐረገወይን፤ ስለ ምግብ ቤታቸው ከፈታና የደንበኞች መስተንግዶ አንስተው ይናገራሉ።

የቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል መያዝ ከሚችለው የተጠርጣሪዎች ቁጥር በላይ እየያዘ በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ መፈጠሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አመለከተ 12.01.2026

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧ ተነገረ

በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችና መራጮች በስድስት ቋንቋዎች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ ድረገፅ ይፋ ሆነ 07.01.2026

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልታቋቁም ነው

#101 Having a laugh (Med) - #101 መሳሳቅ 07.01.2026

Learn how to talk about things that make you laugh. Practise phrases that help you share stories, react to jokes, and enjoy conversations more. - ስለ ሚያስቅዎት ነገሮች በእንግሊዝኛ እንደምን መናገር እንዳለብዎት ይወቁ። ወጎችን ለማጋራት፣ ለቀልዶች ምላሾችን ለመስጠትና በሃሳብ ልውውጦች ይበልጥ ተደሳች ለመሆን እንዲያግዝዎ ቃለ ሐረጎችን ይካኑ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች መያዝ የሚገባቸውን ወርሃዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ ምጣኔ በሁለት መደበ 04.01.2026

በሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ብዙኅን መገናኛና ጋዜጠኞች በአግባቡ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ተባለ

"እንኳን ለዘላለማዊ ተስፋ ላገኘንበት ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ" መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ 04.01.2026

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አሕጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓለ ልደት አከባበርን አስመልክተው ያስረዳሉ። መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።

"የልደት በዓል ታሪክ አይደለም፤ እውነት ነው። እግዚአብሔር መልካም በዓል ይስጣችሁ" ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 04.01.2026

ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ፤ በዘጸዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር የ2006 በዓለ ልደት መልዕክታቸውን ለእምነቱ ተከታዮች ያስተላልፋሉ፤መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።

የሁለት ክፍለ ሀገራት የማኅበረሰብ አባላትን ለፍቅር አብቅቶ ወደ አንድ ጣራ ስር ኑሮ የመራው ዓመታዊው የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ 29.12.2025

ሰቲት ሁመራ ከግዕዝ ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጎ በ5 ለ 4 የፍፁም ቅጣት ምት ውጤት ለሁለተኛ ጊዜ የድል ዋንጫ ባለቤት ሆነ

በኢትዮጵያ ከ35 ሚዮን በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከቀላል እስከ ከባድ የአዕምሮ ሕመም እንዳለበት የባለ ሙያዎች ጥናት አመለከተ 28.12.2025

በወርኅ ጥቅምት በቀን 1456 ያህል ሰዎች ድንበር እንዳቋረጡ ተገለጠ

"የዓመታዊ ስፖርቱ መንፈስ በየሳምንቱ እንዲሆን የምንመኘው ዓይነት ኢትዮጵያዊነትን ያንፀባረቀ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 26.12.2025

ረቡዕ ዲሴምበር 24 / ታህሳስ 15 የተጀመረው ዓመታዊው 29ኛው የኢትዮጵያውያን የእግርኳስ ውድድር ዓርብ ታህሳስ 27 ሶስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። የሶስቱ ቀናት የግጥሚያ ውጤቶችና ሌሎች ክንውኖች ተጠናቅረው ተካትተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የሚውል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ልታደርግ ነው 24.12.2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር ፈቀደ

"የኢትዮጵያ ቀን ትልቁ የቶርናመንቱ ቀን ነው። ከኢትዮጵያ ብንወጣም፤ ኢትዮጵያ ከውስጣችን አልወጣችም። እየሠራን ያለነው ትንሽቷን ኢትዮጵያ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 22.12.2025

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ዲሴምበር 27 / ታህሳስ 18 በሜልበር ከተማ በልዩ ድምቀት ስለሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ትሩፋቶች ያስረዳሉ። ዓመታዊው በዓል ተከብሮ የሚውለው Arndell Parke Reserve, 49 Federation Blvd, Truganina ነው።

"ይህ ቶርናመንት በዋነኛነት የሚያደርገው፣ ኢትዮጵያዊነታችንን ማጉላት፤ ልጆቻችን ደህና ቦታ እንዲውሉና የተጠፋፉ ሰዎች እንዲገናኙ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 22.12.2025

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ከዲሴምበር 24 - 28 / ታህሳስ 15 - 19 በሜልበር ከተማ ስለሚከበረው ዓመታዊው 29ኛ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ሂደትና ተልዕኮ ይናገራሉ። አ ምስት ቀናት የሚፈጀው ዓመታዊው የስፖርት በዓል የሚከናወነው Arndell Parke Reserve, 49 Federation Blvd, Truganina ነው።

Ouça o podcast SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ no Replaio

Rádio e podcasts em um só app - grátis e sem cadastro. Instale hoje e não perca o lançamento

Baixe no Google Play

O Replaio não é o publicador dos podcasts; os nomes dos programas, as capas e o áudio pertencem aos seus autores e são distribuídos por feeds RSS públicos