SBS

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

News AM ↓ 912 episódios

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Não deixe de visitar o site do podcast e apoiar quem o produz: www.sbs.com.au

Autor

SBS

Categoria

News

Site do podcast

www.sbs.com.au

Último episódio

8 de jul de 2026

Onde ouvir?

Podcasts no app Replaio Radio Em breve

Os podcasts estão chegando ao app. Instale agora e seja o primeiro a descobrir um jeito totalmente novo de curtir podcasts

Baixe no Google Play Instale grátis Android 5 mi+ downloads · nota 4,8 iOS em breve

Episódios

ሁለት ዋነኛ የኑሮ ውድነት መቋቋያሚያ ዘዴዎች ምንድናቸው? 20.05.2024

ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ፤ የዘንድሮውን 2024/25 የአውስትራሊያ በጀት የትኩረት አጀንዳዎችና ፋይዳዎች አንስተው ያስረዳሉ። የኑሮ ውድነትንም አስመልክተው ሙያዊ ምክረ ሃሳቦችን ያጋራሉ።

በኒው ሳውዝ ዌልስ የቤት ውስጥ እና የቤተሰብ ጥቃትን በፈጸሙ ሰዎች ላይ በተደርገ የአራት ቀን ዘመቻ ፖሊስ በ550 ሰዎች ላይ ክስ መሠረተ 20.05.2024

የኢራኑ ፕሬዝደንት ለሞት የዳረገው የሂሊኮፕተር አደጋ መንሥኤ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ክልል ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ ሲል አስታወቀ 19.05.2024

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለሕክምና የሚሔዱት ወደ ውጭ ሃገራት መሆኑ ቀርቶ ወደ ቢሾፍቱ እንደሚሆን ተመለከተ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ለመንግሥትና ለታጣቂዎች ጥሪና ማሳሰቢያ አቀረቡ 16.05.2024

ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የዓለም መሪዎች በስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አወገዙ

ድጋፍና ትችት ያጀቡት የአውስትራሊያ በጀት 2024 ዋነኛ ትኩረት የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት መሆኑ ተመለከተ 15.05.2024

የአውስትራሊያ 2024 በጀት የ9 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ተረፈ ፈሰስ አስመዘገበ

የሜዳል፣ ኒሻንና ሽልማት አዋጅ ፀደቀ 14.05.2024

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች አመራረጥ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው

መለስ ሳህሌ፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያ 14.05.2024

የቀድሞው የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና አዘጋጅ መለስ ሳህሌ፤ ስለ ድሬዳዋ ትውልድና ዕድገቱ፣ የጂቡቲ ስደት ፈተናዎቹና የአውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።

የአውስትራሊያ መንግሥት የፍልሰተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ላይ ገደብ ሊጥል ነው 13.05.2024

እስከ ዓመቱ መጨረሻ የዋጋ ግሽበት እንደሚቀንስና የወለድ መጠን ሊጨምር እንደማይችል ተተነበየ

የእናቶች ቀን 2024፤ ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እናቶችና ልጆች በአውስትራሊያ 13.05.2024

ሐዌሪ ድንቄሳ (ከሲድኒ)፣ ፀሐይ በየነ (ከሜልበርን) እና ኤስሮት ሐብታሙ (ከብሪስበን)፤ የእናቶች ቀን አከባበርን፣ ለእናቶቻቸው ያላቸውን ፍቅርና ዕለተ በዓሉን እንደምን እንዳሳለፉ ይናገራሉ። ለመላ እናቶች መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

የአዲስ አበባ አየር ብክለት ከፍ ማለቱ ተገለጠ 13.05.2024

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ማረጋገጫ መርሃ ግብር ሊጀመር ነው

የእናቶች ቀን በሀገረ አውስትራሊያ 12.05.2024

በሜልበርን የተከበረውን የእናቶች ቀን አስመልክቶ ወ/ሮ ነጁም አብደላ ፤ ወጣት ባህጃ አብደይ ፤ ወ/ሮ መሊካ መሐመድ ፤ አርቲስት ሰብለ ግርማ ፤ ወ/ሮ ፍርዱስ ዪሱፍ እና ወ/ሮ ተወድዳ ዩሱፍ ዕለቱ ለእናቶችና ለማኅበረሰብ ስላለው ፋይዳዎች ይናገራሉ። የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውንም ያስተላልፋሉ።

"የመብት ረገጣ ሊቆም ይገባል፤ የሕዝባችን ሰቆቃ ካልቆመ ጥያቄያችን ይቀጥላል" አቶ ዓለማየሁ ቁቤ 12.05.2024

በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት የአቶ በቴ ኡርጌሳና ሌሎች ፖለቲከኞችን ግድያ በመቃወም በቪክቶሪያ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሠልፍ አከናውነዋል።

#61 Tackling a DIY project (Med) 10.05.2024

Learn how to talk about doing do-it-yourself (DIY) projects.

Navigating the implicit right to protest in Australia - አውስትራሊያ ውስጥ ስውር የተቃውሞ መብትን ማሰስ 09.05.2024

Every week, impassioned Australians take to the streets, raising their voices in protest on important issues. Protesting is not an offence, but protesters sometimes test the limits of the law with extreme and antisocial behaviour. The chance of running into trouble depends on where you’re protesting and how you behave. - በየሳምንቱ ስሜታቸው የገነፈለ አውስትራሊያውያን ጎዳናዎች ላይ ወጥተው ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንስተው ድምፆቻቸውን ያሰማሉ።...

የአስትራዜኒካ ኮቪድ-19 ክትባት ከዓለም ገበያዎች እየተሰበሰበ ነው 08.05.2024

የዘንድሮው የአውስትራሊያ በጀት የዋጋ ግሽበትን በማያባብስ መልኩ የተበጀተ መሆኑ ተመለከተ

የበዓለ ትንሣኤ አከባበር በአገረ አውስትራሊያ 08.05.2024

ወ/ሮ ሰላማዊት ታደሰ (ከፐርዝ)፣ ዘውዴ ተስፋማሪያም (ከብሪስበን) እና አቶ ወንድወሰን ሽቱ (ከሜልበርን) እንደምን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳሳለፉ ይናገራሉ። ለመላ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

"የባና ርዕይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለዓለም ገበያ ማቅረብና የኢትዮጵያን ባሕል በሉላዊ መድረክ ላይ እንዲያንፀባርቅ ማስቻል ነው" ድምፃዊትና ሥራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን 08.05.2024

የባና ሙዚቃ አሳታሚ መሥራች፣ ድምፃዊትና ዋና ሥራ አስፈፃሚት ብሌን መኮንን፤ ስለ ባና አመሠራረትና ሚና ታስረዳለች፣ ድምፃዊ ዕብነ ሐኪም እንደምን ወደ ሙዚቃ ዓለም እንደዘለቀና ስለመጪ የሙዚቃ አልበሙ "ብራና" ይናገራል።

ኢትዮጵያ በሕዋ የአምስት ዓመት የቆይታ ዕድሜ የሚኖራት ሳተላይት ለማምጠቅ ጨረታ አጠናቀቀች 07.05.2024

40 በመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል አስፈላጊ ሰነድ የሌላቸው መሆኑ ተገለጠ

የእሥራኤል ጦር የጋዛ ራፋህ መተላለፊያን ተቆጣጠረ 07.05.2024

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሱዳን ፈጣን ኃይል ሕወሓት ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር አብሮ እየወጋን ነው የሚለው ክስ መሠረተ ቢስ ነው ሲል አስተባበለ

"የአድዋ ጀግኖች ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉት ለእንጀራና ቡና አይደለም፤ የተለያየ ዘርና ሃይማኖት ላለው ሕዝብ ነፃነት ነው" ድምፃዊት ቤቲ ጂ 07.05.2024

"ሽልማት ማለት ሥራችሁን ጨርሳችኋል፤ አቁሙ ማለት አይደለም። ለኒሻን ሲሆን ደግሞ ለሀገር ገና ብዙ ትሠራላችሁ የሚል አደራም ጭምር ነው" የምትለዋ ድምፃዊት፣ የሰብዓዊ ረድዔትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ማንነት አጉሊ ድምፅ ብሩክታይት ጌታሁን "Betty G"፤ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ስለተበረከተላት የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ኒሻንና ሀገራዊ አንድነት ፋይዳዎች ትናገራለች።

የፐርዝ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት በእስልምና ስም የሚካሔዱ የአመፅ ድርጊቶችን አወገዙ 06.05.2024

የሃማስና እሥራኤል ድርድር በተስፋና ጥርጣሬ መካከል ነው

ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በ1.5 ቢሊየን ዶላር ተጨማሪ የኔትዎርክ ማስፋፊያ ሊያደርግ ነው 05.05.2024

ኢትዮጵያ ውስጥ የጉበት በሽታ እየጨመረ ነው

“ የክርስቶስ ትንሳኤ ሞት የተሸነፈበት ታላቅ የምስራች የተሰበከበት ቀን ነው ። ” - መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ 05.05.2024

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አሕጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ እንዲሁም የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የፋሲካ በዓል መልዕክት፡፡

"እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ትንሣኤ የክርስቲያኖች ተስፋ የተረጋገጠበት ነው” ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ 05.05.2024

ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋሉ።

"ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ 04.05.2024

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።

Ouça o podcast SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ no Replaio

Rádio e podcasts em um só app - grátis e sem cadastro. Instale hoje e não perca o lançamento

Baixe no Google Play

O Replaio não é o publicador dos podcasts; os nomes dos programas, as capas e o áudio pertencem aos seus autores e são distribuídos por feeds RSS públicos