ECFC in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.

Não deixe de visitar o site do podcast e apoiar quem o produz: ecfc-finland.org

Autor

ECFC in Finland

Categoria

Religion

Site do podcast

ecfc-finland.org

Último episódio

5 de jul de 2026

Onde ouvir?

Podcasts no app Replaio Radio Em breve

Os podcasts estão chegando ao app. Instale agora e seja o primeiro a descobrir um jeito totalmente novo de curtir podcasts

Baixe no Google Play Instale grátis Android 5 mi+ downloads · nota 4,8 iOS em breve

Episódios

022_የአካል መታነጽና መክበር 11.11.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የአካል መታነጽና መክበር" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ አማካይነት ቅዱሳንን ያንጻል የሚል ነው::

021_ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል 04.11.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ የአካል ብልቶች ሁሉ ለአካላቸው ህልውና መቀጠል ተግባብተውና ተሳስበው እንደሚሠሩ፣ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አማኞችም የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ህያው ሆና ተግባሯን በሚገባ መፈጸም እንድትችል በመተሳሰብ አብረው ለአንድ ዓላማ ሊቆሙ ይገባል የሚል ነው::

020_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 3 21.10.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ባልንጀራችንን እንደራሳችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? ባልንጀራችንስ ማን ነው? ባልንጀራችንስ እንደራስ መውደድ ይቻላል ወይ? ባልንጀራችንን እንደራስ መውደድ የሚገለጽባቸው መንገዶችስ ምን ምን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::

019_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 2 14.10.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔርን በሁለንተናችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? የሰው ሁለንተናስ ምንድን ነው? እግዚአብሔርንስ በሁለንተናችን መውደድ የምንችለው እንዴት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::

018_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 1 07.10.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ለህዝቡ የሰጣቸውን ህጎች መዳሰስ ነው:: እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራ በተሻሩና ባልተሻሩ የእግዚአብሔር ህጎች መካከል መለየት ነው::

017_በመንፈሱ መታጠቅ! 30.09.2018

በዮሐንስ ወንጌል 21:15-19 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ በሥጋ ማንነቱ የሚፈራውን በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ እንደማይፈራና ለእግዚአብሔር ክብር እስከ ሞት ድረስ እደሚጨክን ያስረዳል:: በመንፈስ ቅዱስ መታጠቅ ፈሪን ደፋር ያደርጋል:: ለዚህም የጴጥሮስን ህይወት ልብ ይሏል::

016_ይቅርታ 23.09.2018

"ይቅርታ" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:32-43 እና ማቴ 6:14-15 ባለው ክፍል ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

015_ዘመኑን ማወቅ 16.09.2018

"ዘመኑን ማወቅ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና በዘመናት መካከል ህዝቡን አገሮችን እና ቤተሰቦችን በማስተዋልና በጥበብ ለመምራት እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚያስነሳ የሚያገነዝብ ነው:: በዘመናችንም ምልልሳችን በጥበብና በማስተዋል መሆን እንደሚገባና ጥበብንም ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠየቅ እንደሚቻል ይመክራል::

014_በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል 09.09.2018

"በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና አሳብ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በአማኝ ህይወት ውስጥ የሚያደርጋቸውን ለውጦች የሚያስረዳ ነው::

013_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 3 02.09.2018

"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻ ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ምዕመናን መሪዎችን በመምረጥ ጉዳይ ልዩ ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማስገንዘብና ትክክለኛ መሪዎችን መለየት የሚችሉባቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመዘኛዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::

012_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 2 19.08.2018

"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ለሰው የተሰጡ አራት የሥልጣን ደረጃዎችን መተንተንና ከሰው ሥልጣን ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን መጠቆም ነው::

011_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 1 12.08.2018

"የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ከሰው በላይ የሆኑና የእግዚአብሔር ብቻ ስለሆኑ የሥልጣን ደረጃዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::

010_ቤተ ክርስቲያን ክፍል 6 05.08.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት የተቀበልነውን የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ መለየት የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ይሰጣል::

009_ቤተ ክርስቲያን ክፍል 5 29.07.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ የጸጋ ሥጦታዎችን ማወቅና መለየት ነው::

008_ቤተ ክርስቲያን ክፍል 4 22.07.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::

007_ቤተ ክርስቲያን ክፍል 3 15.07.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::

006_ቤተ ክርስቲያን ክፍል 2 08.07.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይ ክፍል:: ይህ ቤተ ክርስቲያን በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::

005_እምነት 01.07.2018

"እምነት" በሚል ርዕስ በዮሐ. 14:1 እና በዕብ. 11:23-27 ባለው ክፍል ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

004_ቤተ ክርስቲያን 24.06.2018

"ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በቆላ. 1:15-23 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

003_መንፈሱ ይሠራል ነገሩም ይሠምራል! 17.06.2018

ይህ መል ዕክት በዘፍ. 1:1-5 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተና በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱም ማዕከላዊ ጭብጥ ምንም እንኳን ነገሮች ቅርጽ አልባ ዋጋ ቢስና ተስፋ ቢስ ቢሆኑ ሠራተኛው መንፈስ ቅዱስ ስላለ ከእግዚአብሔር ቃል ሲወጣ ሁሉም ለበጎ ይለወጣል የሚል ነው:: በጨለመው ነገራችን ላይ ሁሉንም የሚለውጠው እግዚአብሔር ብርሃንን ያዛል:: ብርሃን ሲሆን ደግሞ ልዩነት ይሆናል:: ብርሃን የሌሎች መልካም ነገሮች ሁሉ መነሻ ነው::

002_ለእግዚአብሔር መቀደስ 14.06.2018

ይህ መልዕክት በዘፍ. 12:1-3 ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ጭብጥ "የእግዚአብሔር ጥሪ ወይም ድምጽ ሲመጣ መለየትን ያመጣል" የሚል ነው::

001_እግዚአብሔር አዋቂ ነው! 03.06.2018

ይህ መልዕክት የተመሠረተው በ1ኛ ሳሙ. 2:3 ላይ ሲሆን በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ነው:: የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍና ግራ ብንጋባ በፍጻሜው ይህ ሁሉ ለምን እንደሆነብን እግዚአብሔር ሊገልጽልን ይችላል:: ስለዚህ በጽናት መቆምና ማለፍ ይኖርብናል:: በህይወታችን ከሚሆኑ ከእያንዳንዱ ክስተቶች ጀርባ የእግዚአብሔር ልዑአላዊ አሳብና ፈቃድ እንዳለ መገንዘብ እንደሚኖርብን ለማስገንዘብ የቀረበ መልዕክት ነው::

Ouça o podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland no Replaio

Rádio e podcasts em um só app - grátis e sem cadastro. Instale hoje e não perca o lançamento

Baixe no Google Play

O Replaio não é o publicador dos podcasts; os nomes dos programas, as capas e o áudio pertencem aos seus autores e são distribuídos por feeds RSS públicos