ECFC in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

This is a podcast from the Ethiopian Christian Fellowship in Finland, where you can listen to biblical teachings, messages, and sermons. May God bless all our listeners.

Não deixe de visitar o site do podcast e apoiar quem o produz: ecfc-finland.org

Autor

ECFC in Finland

Categoria

Religion

Site do podcast

ecfc-finland.org

Último episódio

5 de jul de 2026

Onde ouvir?

Podcasts no app Replaio Radio Em breve

Os podcasts estão chegando ao app. Instale agora e seja o primeiro a descobrir um jeito totalmente novo de curtir podcasts

Baixe no Google Play Instale grátis Android 5 mi+ downloads · nota 4,8 iOS em breve

Episódios

047_የእግዚአብሔር ምህረት ክፍል 2 14.04.2019

ይህ "የእግዚአብሔር ምህረት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል ቀጣይ ክፍል ነው::

046_የእግዚአብሔር ምህረት ክፍል 1 07.04.2019

 የእግዚአብሔር ምህረት በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

045_የጌታን ራት የሚካፈል ማን ነው? 31.03.2019

"የጌታን ራት የሚካፈል ማን ነው?" በሚል ርዕስ በ1ቆሮ. 11:26-32 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

044_እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር 24.03.2019

"እግዚአብሔርን የማወቅ ምስጢር ታላቅነት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

043_የጌታ ራት 17.03.2019

  "የጌታ ራት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው::

042_የልብ ንጽህና ክፍል 3 10.03.2019

 ይህ "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት የልብ ንጽህና ፋይዳዎች የሚል ሲሆን ሁለት መሠረታዊ አሳቦች ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል:: 1) የልብ ንጽህና እግዚአብሔርን እንድናይ ይረዳናል:: 2) የልብ ንጽህና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዳንስት ይረዳናል:: 

41_እግዚአብሔር በቤታችን እንዴት ነው? 03.03.2019

"እግዚአብሔር በቤታችን እንዴት ነው?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

040_የልብ ንጽህና ክፍል 2 24.02.2019

  ይህ ትምህርት "የልብ ንጽህና" በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የሚቀበው ተከታታይ መልዕክት ሁለተኛው ክፍል ሲሆን ልብን እንዴት ንጹህ ማድረግ ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ክፍል ነው:: 

039_የልብ ንጽህና ክፍል 1 17.02.2019

  የልብ ንጽህና በሚል ርዕስ በማቴ. 5:8 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል ነው::  ይህ ክፍለ ጊዜ "የልብ ንጽህና ምንድን ነው?" እና "ስለልብ ንጽህና ማሰብና መማር አስፈላጊ ነውን?" የሚሉ ጥያቄዎችን ይመልሳል:: 

038_ኢየሱስን መውደድ 10.02.2019

ኢየሱስን መውደድ በሚል ርዕስ በሉቃ. 7:36-50 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!

037_አንተም እንዲሁ አድርግ 03.02.2019

  "አንተም እንዲሁ አድርግ" በሚል ርዕስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አሥር ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

036_የእምነት ተግዳሮቶች 27.01.2019

  የእምነት ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

035_እምነት 20.01.2019

  "እምነት" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: 

034_እግዚአብሔርን ማመስገን! 13.01.2019

  "እግዚአብሔርን ማመስገን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት!

33_የዕይታ ለውጥና የግል ህይወት ተሃድሶ 06.01.2019

  ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት በመዝሙር ምዕራፍ 73 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ዕይታችን በዙሪያችን ባሉ ሰዎችና ሁኔታዎች ላይ ስናደርግ ሳናውቀው ከመንፈሳዊ ከፍታችን እንንሸራተታለን ነገር ግን በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ስንሆንና እንደ እግዚአብሔር ዕይታ ነገሮችን ማየት ስንጀምር የነገሮች ሁሉ ፍጻሜ ግልጽ ይሆንልናል የሚል ነው::

032_እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው! 31.12.2018

 "እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው!" በሚል ርዕስ በዘጸ.17:8-16 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: 

031_ጀግና አይታዘንለትም! 30.12.2018

  "ጀግና አይታዘንለትም!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:26-29 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ኢየሱስ ስለሰው ልጆች መከራን የተቀበለው እንዲናዝንለት ሳይሆን እንድናምንበት ነው:: ሊታዘንላቸው የተገባቸው የተደረገላቸውን ያልተረዱና ክርስቶስን ያልተቀበሉት ናቸው:: 

30_ንጉሥ ለሚወደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል! 29.12.2018

  "ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይደረግለታል!" በሚል ርዕስ በአስቴር ምዕራፍ 6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ንጉሥ ሲወድ በንጉሥ አቅም ልክ መሆኑን ለማስገንዘብና እኛም በእግዚአብሔር የተወደድነው ለመረዳት ከአቅም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ማስገንዘብ ነው::  

29_የእግዚአብሔር ክብር 29.12.2018

  "የእግዚአብሔር ክብር" በሚል ርዕስ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው በ2ኛ ዜና 7:1-10 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን በመልዕክቱም የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የሚሆኑ 4 መሠረታዊ ነገሮች ተዳስሰዋል::

28_ምርኮው ይመለሳል! 23.12.2018

  ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ምርኮው ይመለሳል"  በሚል ርዕስ በ1ሳሙኤል ምዕራፍ 30 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ "ነገራችን በጠላት ሲወሰድብንና የሚናደርገው ግራ ሲገባን 1) ልባችንን በእግዚአብሔር ማበርታት አለብን 2) ማድረግ የሚገባንን እንዲያሳውቀን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ አለብን 3) ምርኮአችንን ለመመለስ እግዚአብሔር አድርጉ የሚለንን ማድረግ አለብን" የሚል ነው:: 

027_ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል! 16.12.2018

ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" በሚል ርዕስ የገና በዓልን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ማዕከላዊ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋና ዋና ዓላማዎች መተንተን ነው::

026_ምንጭ 09.12.2018

ይህ የእግዚአብሔር መልዕክት "ምንጭ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የካሌብ ሴት ልጅ በነበረችው በአክሳ ህይወት ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው:: የመልዕክት ዋና መልዕክት ስለምንጭ አስፈላጊነት ነው [ኢያ. 15.16-19ና መሳ. 1:11-15]:: ምንጭ ለአንድ የእርሻ መሬት ፍሬያማነት አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ላለ የእግዚአብሔር ጸጋ ፍሬያማነት እጅግ አስፍላጊ ነው::

025_ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል? 02.12.2018

ይህ መልዕክት "ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ ሲሆን የመልክቱ ማዕከል እግዚአብሔር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወስጥ ባልተጠበቁ ሰዎች ሌሎችን መርዳት እንደምችል የሚያስረግጥ መልዕክት ነው:: ለምሳሌ: 1) አንድ ህጻን ልጅ በያዘው ዳቦና ዓሣ አምስት ሺህ ህዝብ መመገቡ 2) በሰታፕታ መንደር እፍኝ ዱቀት ብቻ በነበራት ባልተት ኤልያስን መመገቡና 3) ባዶ የሚመስል የዘይት ማድጋን ተጠቅሞ የነቢይ ሚስት የነበረችን ባልቴት ባለዕዳ ልጆቿን እንዳይወስድባት መርዳቱ::

24_እግዚአብሔርን መከተል 25.11.2018

ይህ "እግዚአብሔርን መከተል" በሚል ርዕስ በወ/ዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: መልዕክቱ በኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ 13 ላይ የተመሠረተ ሲሆን ማዕከላዊ አሳቡም እግዚአብሔርን በመከተል ሂዴት ውስጥ ትኩረታችን መሆን ያለበት ዙሪያችን ላይ በሚታየው ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰጠን የተስፋ ቃል ላይ ነው የሚል ነው::

023_የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች 18.11.2018

"የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የመልዕክቱ ጭብጥ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሥራ ለመሥራት የሚረዱ ቁልፎች 1) የእግዚአብሔር ቃል 2) የኢየሱስ ስም 3) ጸሎትና 4) መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ማስገንዘብ ነው::

Ouça o podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland no Replaio

Rádio e podcasts em um só app - grátis e sem cadastro. Instale hoje e não perca o lançamento

Baixe no Google Play

O Replaio não é o publicador dos podcasts; os nomes dos programas, as capas e o áudio pertencem aos seus autores e são distribuídos por feeds RSS públicos