ወሰንሰገድ አሰፋ
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።
Author
ወሰንሰገድ አሰፋ
Category
Podcast website
Latest episode
Jul 11, 2026
Where to listen?
Podcasts in the app Replaio Radio Coming soonPodcasts are coming to the app soon. Install now and be the first to see a whole new take on podcasts
Episodes
ከቅድመ አያቶች ጥበብ እስከ ጤና ሉዓላዊነት፡ አፍሪካ ለፍትሕ የምታደርገው ትግል 10.11.2025 1:00:00
“የቅኝ ገዥዎች ልጆቻችንን ማሠልጠን ጀመሩ። እኛ እንደ ሕዝብ በአእምሮአችን ውስጥ ልጆቻችንን የሚያሠለጥኑልን ለእኛ መስሎን ነበር። ግን የሚያሠለጥኗቸው ለራሳቸው ነበር። እና ልጆቹን ለራሳቸው እያሠለጠኑ መሆናቸውን የተረዳንበት ጊዜ፣ በጣም ዘግይቶ ነበር። አሁን በእኛና በልጆቻችን መካከል ክፍተት መጣ።” ሲሉ የአፍሪካ ቴስት ድርጅት ተባባሪ መስራች ተንጎል ክፕለማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ በቅኝ ግዛት የተናጋውን የአፍሪካን ባህላዊ ማንነት እና የሞራል መሰረቶችን /የቅድመ አያቶች ጥበብ/ እንዴት መልሶ ማቋቋም እንደሚቻል የኮንጎ እና የዛምቢያ የብዊሌ ህዝቦች ንጉስ...
የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ አጀማመር በኢትዮጵያ ፡ አዲሱ የፋይናንስ ምዕራፍ ጅማሮ 05.11.2025 1:00:00
“የሚሰራ የካፒታል ገበያ ካለህ፤ ገበያው በራሱ የረዥም ጊዜ ብድሮችንና ለዚያ የሚሆኑ ነገሮችን ያቀርባል፡፡ ባንኮች ደግሞ ለአጭር ጊዜ የሚሆኑ ዐይነት ብድሮችን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ገበያ በምንፈልገው ደረጃ አለመኖሩን ተከትሎ የሆነ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በተለመዱት ባንኮች በኩል እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ አንዳንድ ክፍተቶችም አሉ ፤ ሆኖም ክፍተቶቹ በካፒታል ገበያው የሚፈቱ ይሆናል፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ አማካሪ አቶ ሲራክ ሰለሞን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባ ለስልጣን ከፍተኛ አማካሪ ከሆኑት አቶ ሲራክ...
ዩኒቨርሲቲ መግባት ብቸኛ አማራጭ ነውን? ሀገር ያፈራቻቸው ሌሎች ዕድሎችን እንዴት እንጠቀም? 04.11.2025 1:00:02
“ቴክኒክ እና ሙያ መግባት ማለት ከዩኒቨርሲቲ ያነሰ ተደርጎ ነው ትርጉም የተወሰደው። ምክንያቱም ይሄ እንደ ዲፕሎማ ነው የሚቆጠረው። ያኛው እንደ ዲግሪ ስለሚቆጠር እና ማሻሻል ይፈልጋል። ይሄ የዩኒቨርሲቲ ባህሪ ኖሮት ሌላ ደረጃዎች ተቀምጦለት ታርጌቱም ተቀይሮ ነው መምጣት ያለበት።” ሲሉ የስነ-አዕምሮ ባለሙያ እና አማካሪ አቶ እድሜአለም ግዛ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የስነ-አዕምሮ ባለሙያ እና አማካሪ ከሆኑት አቶ እድሜአለም ግዛ ጋር በመሆን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ጋር ተያይዞ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የተቆረጠውን ውጤት የማያስመዝገቡ ተማሪዎች ቁጥር እየላቀ መምጣቱን ተከትሎ እነኚህ ተ...
የሀገር-በቀል እውቀት፡ የማንነት እና የስነ-ልኬታችን መሣሪያ 03.11.2025 59:59
“የሀገር-በቀል እውቀት የስነ-ልኬታችን መሳሪያ ነው [……..] የአንድ ሰው፣ የአንድ ህዝብ፣ የአንድ ሃገር የጥሩ እና የመጥፎ ነገር መለኪያ ማለት ነው፡፡ ይሄ መጥፎ ነው፣ ይሄ ጥሩ ነው፣ ይሄ ይሻላል፣ ይሄ አይሻልም፣ ይሄ ይበልጣል ይሄ አይበልጥም ብሎ ህዝብ የሚበይንበት፣ የሚለካበት፣ ያሉትን እሴቶች የሚለካበት ነው፡፡ እሱ የለህም ማለት መለኪያህን ተነጠቅህ ማለት ነው፡፡ መለኪያህ ካንተ ወጣ ማለት በሌሎች መለኪያ ውስጥ ትገባለህ፡፡” ሲሉ በሀገር-በቀል እውቀት ጥናት እና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብዱልፈታህ አብደላህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሀ...
የአፍሪካ ጉዞ ከትግል እስከ መታደስ ፡ ታሪክን መመለስና የወደፊቱን መወሰን 31.10.2025 1:00:00
"አፍሪካ ነጻ አይደለችም። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በወታደራዊ ወይንም በሌላ በማንኛውም ነገር ቢሆን፤ የአፍሪካ ነፃነት መጀመር ያለበት ከእውቀት [ጥገኝነት] ነፃነት ነው ።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 🎧በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ ከአፍሪካ የተረሱ ያለፉ ምዕራፎች ተነስተን ወደፊት ወደ ሚዘራው ዘር እንጓዛለን። በክፍል አንድ፣ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር የአፍሪካን የትግል ጀግኖች በምዕራባዉያኑ ቦታ የማይሰጣቸውና የተረሱት ለምንድን ነው ስንል እንጥይቃለን ፤ በክፍል ሁለት ደግሞ በአዲስ አበባ በተካሄደው የቻይና–አፍሪካ ግብ...
የለውጥ ዋጋ: ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምና ኢትዮጵያ 24.10.2025 59:56
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የአለምዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍን) እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ እድገት ዋሰትና ይሆን ወይስ የዕዳ ወጥመድ የሚለውን እንመረምራለን። ለዚህም ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና እና በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል፡፡ '' እንደ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት (FDI) እና የወጪ ንግዳችን መጠን መጨመር ያሉ ትክክለኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች እስካልተፈጠሩ ድረስ፣ የውጭ ምንዛሪ ችግር ተፈቷል ልንል አንችልም ፣" ሲሉ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የለውጥ ዉጥኗን...
ነገን ማልማት፡ የግብርና ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ 21.10.2025 1:00:00
“ግብርና ላይ የተመሰረተ የወጣቶች የስራ እድል እየፈጠርን ነው፡፡ በትንሽ ገንዘብ በጣም ብዙ ወጣት ነው ስራ የምናስይዘው፡፡ ወደ 611 ሺ ወጣት ነው ስራ ልናስይዝ በ 5 ዓመት ውስጥ ፈንድ የወሰድነው፡፡ አንዱን ዓመት አጠናቀናል፡፡ ከዚህ ውስጥ 80 በመቶው ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ጋር ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ እና የፖሊሲ ለውጥ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች እርሻዎ...
የማይታይ ሞተር : የአፍሪካ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ 10.10.2025 1:00:00
“እነዚህ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የምንላቸው ዋነኛ ቀጣሪ ሴክተር ናቸው፤ መተዳደሪያም ነው፤ ኢኮኖሚው የተረጋጋ እነዲሆን ያደርጋል፡፡ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ደረጃ የተለያዩ ነገሮች ለዝቅተኛ ማህበረሰብ በማቅረብ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው፡፡“ ሲሉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚው ያለውን አስተዋጽዎ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ በተጭማሪም ስለ ኢትዮጵያ የ...
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ፡ ለአፍሪካ ንግድ አዲስ ምዕራፍ 08.10.2025 59:59
“የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መመስረት [...]ለአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ ለመነገድ ዕድል ይሰጣል። እስከ አሁን ድረስ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ንግድ 15 በመቶ ብቻ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ያለ ቀረጥ እንዲነግዱም ዕድል ይሰጣል።” ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዝግጅትን ተከትሎ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል። በዚሁ ዝግጅታችን ፣ ትናንት ሁለተኛ ዓመቱ የደፈነውን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት መነሻ...
የኢትዮጵያ ወደ ባህር የመመለስ ጥያቄ 06.10.2025 1:00:00
“የወደብ አጠቃቀም ሶስት አይነት ናቸው፡፡ አንደኛ አብሮ በማልማት፣ ሁለተኛ በሊዝ ኪራይ፣ ሶስተኛ ደግሞ ይዞታ በመለዋወጥ ነው፡፡ እና ይሄንን ማድረግ የምንችልበት መደራደር፣ መነጋገር፣ መወያየት እና መቀራረብ ነው፡፡ ስለዚህ ያነሳነው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እኛ ብቻ እንጠቀም አላልንም፡፡ እነሱም ይጠቀሙ ነው፡፡” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰላምና የዉጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር መውጫ ለማግኘት ያቀረበቸውን ጥያቄ እና የምታደርገውን ጥረት በጥልቀት እንመረምራለን። በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት...
ካሪኮም (CARICOM)፣ ብሪክስ (BRICS)፣ እና ለፍትሐዊ ዓለምአቀፍ ሥርዓት የሚደረግ ጥረት 30.09.2025 1:00:00
“የምንጠይቀው ገንዘብ እንዲሰጠን ብቻ አይደለም። ከፍተኛ የሆነ የዕዳ ሸክም የመጣው ከረጅም ጊዜ የባርነት ታሪክ ጋር በተያያዘ መሆኑን እውቅና እንዲሰጥ እንጠይቃለን። ስለዚህ፣ ዛሬ ያለውን ሁኔታ የካሳ ፍትሕ ለማምጣት ሲባል ዕዳው የሚተውበት ጊዜ ደርሶ ሊሆን ይችላል። የምንጠይቀው ይህን ነው።” ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በአፍሪካ እና በካሪቢያን መካከል ለፍትህ የሚደረገው ትግል ምን ያገናኛቸዋል? የሚለውን ለመዳሰስ ከሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ ጋር ተወያይተናል። እንዲሁም...
ሰላምን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነጻ ማውጣት፡ በአፍሪካ ላይ ትርክቶችን መቀየር 24.09.2025 1:00:11
“አፍሪካ የተባረከች አህጉር ናት፡፡ [...] በጣም ለምና ድንግል መሬት፣ የውሃ ሀብትና የተፈጥሮ ሀብት ሁሉም ነገር አላት። በዘመናዊ መንገድ የተማሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ሌሎች ቦታዎች የሌላቸውን ባህላዊ እውቀት ያላቸው ሰዎችም አሉን። ስለዚህ ጊዜው ሳይረፍድ፣ የራሳችንን ትርክቶች መስራት አለብን። [የተሳሳቱ ትርክቶችን] ማፍረስ እና እንደገና መገንባት በጣም አስፈላጊ ነው።” ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ዓለም አቀፍ የሰላም ቀንን በማስመልከት የሰላም አማካሪ ከሆኑት ዶ/ር ገለታ ሲመሶ ጋር ውይይት አድርገናል። ለአፍሪካ ሰላም የጦር መሳሪያ ዝምታ ብቻ ሊሆን እንደማይገባና ሰላምን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነ...
የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር፣ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ያገኙት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች 22.09.2025 58:58
“ይሄ ምርት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በአፋር ክልል ተሸጦ በቆላና መስኖ አካባቢ ሚኒስቴር ገዢነት ወደ ሁለቱ ክልል ቴክኖሎጂው እንዲተገበር ተደርጎ ሁለቱም ክልል ላይ ቴክኖሎጂውን ሰርተን አምርተን ገጥመንላቸው እየተጠቀሙ ነው።” በግብርና ዘርፍ በሰራው ስራ የወርቅ ተሸላሚው ዘላለም እንዳለው በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቅርቡ ከብሪክስ አባል ሀገራት በተውጣጡ 300 ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች መካከል በቻይና በተካሄደው የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች በመሳተፍ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ከተሸለሙት ሶስት ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያ ወጣቶች ከዘላለም እንዳለው፣ አቤኔ...
የታንዛኒያ የባህር በር አቅርቦት፡ በምስራቅ አፍሪካ ያለው የቀጣናዊ ትብብር መጠናከር 18.09.2025 30:00
“ቅን ልቦና ምርጡ መፍትሄ ነው። እንደ ወንድማማቾች፣ እንደ አፍሪካውያን፣ በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ፣ እነዚያ በአፍሪካ የባህር ዳርቻ ያላቸው አገሮች የባህር በር ለሌላቸው አገሮች የባህር ላይ መዳረሻን ሊያቀርቡ ይገባል።” የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የቀድሞ ከፍተኛ ዲፕሎማት ፕሮፌሰር ብሩክ ሃይሉ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በምስራቅ አፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ አንድ ወሳኝ ለውጥን እንቃኛለን—ታንዛኒያ የባህር በር ለሌላቸው አገሮች ያልተቋረጠ የባህር ላይ መዳረሻ ለመስጠት የገባችውን ቃል። ይህ እንደ ኢትዮጵያ ላሉት ሀገራት ምን ትርጉም አለው? የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቀድሞ ከፍተኛ ዲፕሎማት ፕሮፌሰር ብሩክ ሃይሉ...
ፓን አፍሪካኒዝም እና የኢትዮጵያ አበርክቶት፡ የአንድነት እና የጋራ ትግል ራዕይ 15.09.2025 30:00
“ፓን አፍሪካኒዝም በአፍሪካውያን እና በአፍሪካን ዲያስፖራ ቅንጀት የሚመራ አለም አቀፍ የሆነ እንቅስቃሴ ነው፤ ይሄ የምሁራን፣ የፖለቲከኞች እና ደግሞ ባህላዊ የሆነው ማህበረሰብ የጋራ የሆነ እንቅስቃሴ ነው፤ ዋናው ግቡ አንድነትን እና መተባበርን ማምጣት ነው፡፡” ጋዜጠኛ እና ተመራማሪ ሂወት አዳነ ይህ የራይዚንግ ሳውዝ ክፍል የፓን አፍሪካኒዝምን ታሪክ እና ትግል ያስቃኛል—ይህም በአህጉሪቱ እና በዳያስፖራው የትግል፣ የአንድነት እና የጋራ ምኞቶች ላይ የተመሠረተ ርዕዮተ ዓለም ነው። የአድዋ ጦርነት የተካሄደባት እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ እንደመሆኗ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጽናት እና ሉዓላዊነት ምልክት ሆና በፓን አፍሪካኒዝ...
''የዘመኑ አድዋ'' ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የአፍሪካ ሚናና ቦታ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ 11.09.2025 1:00:00
“የህዳሴው ግድብ፣ እንደ አድዋ ድል ሁሉ፣ አፍሪካውያን "እኛ ማድረግ አንችልም" ወይም "ያለ ድጋፍ መቆም አንችልም" ከሚለው አስተሳሰብ ወጥተው የኢኮኖሚና የፖሊሲ ነፃነታቸውን የሚያረጋግጡበት ትልቅ ክስተት ነው።” ክቡር አቶ መላኩ አለበል በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ልዩ ዝግጅት፣ የአፍሪካ የፈጠራ፣ የመቋቋም አቅም እና የትጋት ምልክት የሆነውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃን በስፍራው ከተገኙ እንግዶች ጋር በጉባ ተገኝተን ታሪካዊ ክስተቱን እንቃኛለን። ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ቀድሞ የዉሃ እና ኢነርጂ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖ ግድቡ በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ፣ በዲፕ...
አፍሪካ እና ካሪቢያን፡ ለፍትህ እና ለለውጥ የተደረገ ትብብር 10.09.2025 30:00
“በካሪቢያን የሚገኙት እነዚህ ወንድሞቻችን ላለፉት 400 ዓመታት ከእናታቸው አህጉር ተነጥለው ቆይተዋል። አሁን አብረን ተገናኝተን ወደፊት ማቀዳችን፣ ስለ ካሳ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካንና የካሪቢያንን ህዝቦች፣ በተለይም ከአፍሪካ አህጉር ውጭ የሚኖሩ የአፍሪካ ተወላጆችን ህይወት ለማሻሻል ለወደፊት የጋራ እርምጃ ማቀድም ጭምር ተገቢ ነው።” አምባሳደር ነብያት ጌታቸው “በመሰረትንው ግንኙነት ወሳኙ ነገር መተባበር ነው። እኛ አንድ ህዝቦች ነን። በካሪቢያን ክልል የምንገኝ እና በአፍሪካ አህጉር የምንገኝ ሁላችንም አንድ መሆን እንዳለብን እንገነዘባለን።” ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የ2ኛው የአፍሪካ-ካሪኮም...
የሩሲያ ስነ-ጽሑፍ፡ ፍልስፍናዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ መሰረት 07.09.2025 1:00:00
“በምንም አይነት ቋንቋ ቢጻፍ፣ በሩሲያንኛ የተጻፉ መጻህፍትና ደራሲያን ብዛት የአለም ሁሉ ደራሲያን ቢደመሩ ሩሲያ ውስጥ ያሉትን ደራሲያኖች የሚበልጡአቸው አይመስለኝም፤ ይሄ ትልቅ ሀብት ነው፡፡” አለማየሁ አሊ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ከጸሐፊ አለማየሁ አሊና ደራሲና ተርጓሚ ታደለ ገድሌ (ዶ/ር) ጋር በሩሲያ ሥነ ጽሑፍ እና በኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ መካከል ያለውን አስገራሚ የአስተሳሰብ ዝምድና እንመረምራለን። "የሩሲያ ደራሲያን ሥራዎች ፣ ለራሳቸዉ ለግላቸው ክብርና ዝና የቆሙ ሳይሆኑ ለደሃው ህዝብ ማህበራዊ ህይወት ለውጥ የቆሙ በመሆናቸው በዚህ ረገድ በጣም ተወዳጅ ናቸው፡፡ ለስነ-ጽሑፍም ፣ ለኢኮኖሚም፣ ለፖለቲካውም፣ ለ...
"ኮሬክት ዘ ማፕ" ፣ አፍሪካን በዓለም ካርታ ላይ በትክክለኛ የስፋት መጠኗ ለማስፈር የሚደረግ ዘመቻ 02.09.2025 1:00:00
“የአፍሪካን ትክክለኛ መጠንና ስፋት በጣም በሚቀንስ መልኩ ያንን ምስላዊ ውክልና ያለማቋረጥ ማየቱ፣ በእርግጥ በጂኦፖለቲካ፣ በባለሀብቶች፣ አፍሪካን በሚመለከቱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።" የአፍሪካ ኖ ፊልተር የአድቮኬሲ እና የእንቅስቃሴ መሪ ሎራቶ ሞጎአት በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በአፍሪካ ' ኖ ፊልተር እና ስፒክ አፕ አፍሪካ' የሚመራውን "ኮሬክት ዘ ማፕ" ዘመቻን እና አፍሪካ በዓለም ካርታ ላይ እና በዓለም አቀፍ ትርክት ውስጥ ትክክለኛ ቦታዋን እንድታገኝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንቃኛለን።
አፍሪካዊ ሚዲያ ለአፍሪካ 29.08.2025 58:05
“ታሪኮቻችንን በመጻፍ፣ ታሪኮቻችንን እንደገና በመጻፍ እና የራሳችንን ትርክት በአጀንዳ ላይ በማስቀመጥ፣ እነዚህን ትርክቶች በራሳችን ባህላዊ እና ማህበራዊ አመለካከቶች በመቅረጽ የአፍሪካ ሚዲያ እና የመገናኛ ብዙሃን ምሁራን በቅኝ ግዛት ቅርስ ስር የሰደዱትን የምዕራባውያን የጋዜጠኝነት ሞዴሎችን የበላይነት መሞገት ይገባቸዋል።” ፕሮፌሰር ማርጋሬት ጁኮ፣ የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር (EACA) ፕሬዝዳንት “ከአፍሪካ የመጡ ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ላይ ያለውን አድልኦ፣ የተሳሳተ መረጃን እና የውሸት ዘገባን ለመመከት ተባብረው መስራት አለባቸው።” ዮሐንስ ሽፈራው (ፒኤችዲ)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙ...
የኢትዮጵያ የመጨረሻውን ንጉሠ ነገሥት የአጼ ኃይለ ሥላሴ 50ኛ ሙት ዓመት ሲታወስ 27.08.2025 1:00:00
“እንግሊዞች ኢትዮጵያን በፋሺዝም ወረራ ወቅት አገዝን ብለው እንደገና እኮ በእንግሊዝ ስር ለማድረግ ነበረ ትልቁ ጥረታቸው። ከዛ መንጋጋ ውስጥ ነው እኮዛ አውጥተው ነጻ ሀገር የሰጡን፡፡ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው እሱ ራሱ፡፡” ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ በዚህኛው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን፣ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት ዘላቂ የሆነውን የተወሳሰበ ታሪካቸውን እንመረምራለን። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ንጉስ የነበሩት አጼ ኃይለ ሥላሴ ለአለም አቀፍ አመራራቸው፣ ለዘመናዊነት ያደረጉትን ተጋድሎ እንዲሁም በአፍሪካ አንድነት ው...
የኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት መነቃቃት እና ለቀጣናዊ ውህደት ያለው ሚና 25.08.2025 30:00
“በጭነት መኪናዎች ከአራት እስከ ሰባት ቀናት ይወስዳል። በኤሌክትሪክ ኃይል በሚሠራ ባቡር ግን ከ12 እስከ 18 ሰዓታት ብቻ ይወስዳል፤ ከአንድ ቀን ያነሰ ጊዜ። የጭነት ወጪዎችን ይቀንሳል፣ ከመኪና ትራንስፖርት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ ቅናሽ ያደርጋል።” በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ኢትዮጵያ የባቡር መሠረተ ልማቷን ለማዘመን ያደረገችውን እና በማድረግ ላይ ያለችውን እንቅስቃሴ እንቃኛለን — ይህም የአገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር እና የቀጣናዊ ትስስር ርዕይ ወሳኝ ምሰሶ ነው። የኢትዮጵያ የባቡር ምህንድስና ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር መኮንን ጌታቸው በዘርፉ የታየውን ለውጥ እና የባቡር ትራንስፖርት ለሀገር ልማት ያለውን ስትራቴጂካዊ...
የሰላም ተስፋ፦ የአላስካው ስብሰባ አንድምታዎች 19.08.2025 30:00
ሳለፍነው ሳምንት በአላስካ የተካሄደው ጉባኤ በታሪክ ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ ገለፃ የአውሮፓውያን እና የዩክሬንን እንቅፋቶችን ተሻግሮ የተከናወነ ነው። ውይይቱ ግን ለዓለም አቀፍ ስጋቶችም መፍትሄ የመሆን ተስፋን የሰጠ ነው። በሩሲያ እና በአሜሪካ የሚደረግ ስምምነት ሌሎች ዓለም አቀፍ ስጋቶችን ለመፍታት እንደ ማዕቀፍ ሊያገለግል ይችላል -ፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያ በፍቃዱ ዳባ በዚህኛው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን የፕሬዝደንት ፑቲን እና የፕሬዝደንት ትራምፕን የአላስካ ስብሰባ በጥልቀት እንዳስሳለን። የመሪዎቹን ዉይይት ቀጣይ ተፅዕኖዎችንም በተመለከተ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አየለ በክ...
የአህያ ክሊኒክ፦ በአህዮች እና በባለቤቶቻቸው ህይወት ላይ ያመጣው ለውጥ 12.08.2025 30:00
“የአህዮች ዕድሜ ተሻሽሏል። ቀደም ሲል አንድ አህያ እስከ 10 ዓመት ይኖር ነበር፣ ነገር ግን አሁን እስከ 20 ዓመት ሊኖር ይችላል [...] በተጨማሪም የአህያ ባለቤቶችን በአጠቃላይ [የአህዮች] ደህንነታቸው፣ አመጋገባቸው፣ ማለትም የአመጋገብ ስርዓታቸው፣ የመኖሪያ ቤታቸው ሁኔታ ላይ እናስተምራለን።” ዶ/ር ደረጀ ፀጋዬ፣ የእንስሳት ሐኪም በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚያስተዳድራቸው የእንስሳት ህክምና ክሊኒኮች፣ የአህዮችን ደህንነት በማሻሻል እና በእነሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች እንዴት እንደሚደግፉ እንቃኛለን። የፕሮጀክቱ መሪ አቶ አለ...
አፍሪካን መመገብ፦ የምግብ ጥገኝነት ሰንሰለትን በመስበር 08.08.2025 30:00
"ቅኝ ገዢዎች ጥለውት የሄዱት ውርሶች አሁንም እንዳሉ አምናለሁ። አሁን ለንግድ እና ለምግብነት የሚውሉ ሰብሎችን ሚዛን ለማስጠበቅ እየሞከርን ነው።" አቡበከር ኪያሪ፣ የናይጄሪያ የግብርና እና ምግብ ዋስትና ሚኒስትር ለዚህ አይነቱ ለውጥ ሀገር በቀል እውቀቶችን መጠቀምም የግድ ይላል። "ወደ ሀገር በቀል እውቀት መመለስ አለብን፣ ምክንያቱም የአየር ንብረት ለውጥን እንድንቋቋም፣ የምግብ ዋስትናን እንድናጠናክር እና ለሚመጣው ትውልድ እውቀትን ለማስተላለፍ የሚረዳ ብዙ እውቀት እየጠፋ ነው።" ዊሊስ ኦቺንግ፣ የኬንያ የገጠር ማጠናከሪያና የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለዘላቂነት ማዕከል (ክሪየትስ ኢንተርናሽናል) ዋና ዳይሬክተር ይህ የራይ...
Similar podcasts
Replaio is not a podcast publisher; show names, artwork and audio belong to their authors and are distributed through public RSS feeds.